Forwarded from SOA
እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት ስማርት ስልኮችን ከተጠቀሙ የአዕምሮ ጤናቸው ይጎዳል - ጥናት
*******
በዓለም አቀፍ ደረጃ በ163 ሀገራት በተደረገ ጥናት፤ ስማርት ስልኮችን መጠቀም እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችን አዕምሮ ሊጎዳ እንደሚችል ጥናት አመላክቷል።
መቀመጫውን በአሜሪካ ቨርጂኒያ ያደረገውና በዶ/ር ታራ ታጋራጃን የሚመራው ይኸው የተመራማሪዎች ቡድን፤ የጥናቱን ውጤት ይፋ አድርጓል።
2 ሚሊዮን በሚሆኑ እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች በሆኑ ታዳጊ ወጣቶች ላይ በተደረገው በዚህ ጥናት መሰረት፤ በዚህ እድሜ ስማርት ስልኮችን መጠቀም በተለይም በሴት ታዳጊዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሥነ-አዕምሮ ችግር ሊዳርግ እንደሚችል በጥናቱ ተገልጿል።
በተመራማሪዎቹ የጥናት ውጤት መሰረትም በዚህ እድሜ ስልክ የሚጠቀሙ ታዳጊዎች፤ በኢንተርኔት ለሚቃጣ ጾታዊ ትንኮሳ፣ ስሜታዊ የመሆን፣ በቂ እንቅልፍ አለማግኘት፣ ራስን ዝቅ አድርጎ የማየት፣ ከወላጆች ጋር አለመግባባት፣ ብሎም ራስን ለማጥፋት እስከማሰብ ለሚደርስ አደገኛ የስነ አዕምሮ ችግር ሊያጋልጣቸው ይችላል ተብሏል።
የተመራማሪዎች ቡድኑ አባላት የጥናቱን ውጤት ይፋ ባደረጉበት ወቅት አፅንኦት ሰጥተው እንዳሳሰቡት፤ እየተባባሰ የመጣውን ይህንን ችግር ለመፍታት በዓለም አቀፍ ደረጃ እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ስማርት ስልኮችንና ማህበራዊ ሚዲያዎችን እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ሕግ እንዲወጣ መጠየቃቸውንም ሲኤንኤን ዘግቧል።
ዶ/ር ታራ ታጋራጃን ወላጆች ሊወስዱት የሚገባው ትልቅ እርምጃ፤ በተቻለ አቅም ልጆች ከስማርት ስልኮች እንዲርቁ እና በሌሎች እንቅስቃሴዎች ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ ማድረግ መሆኑንም ገልጸዋል።
©️እጅግ አስተማሪ ታሪኮች