የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ የመንግሥት ኮሙኒከሸን ዳይሬክቶረት
173 subscribers
1.31K photos
3 videos
7 files
76 links
Download Telegram
በደቡብ ኢትዮጵያ እና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዋሳኝ አካባቢዎች የሚስተዋለውን ወቅታዊ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በሚያስችል ቅንጅታዊ አሠራሮችና በሠላም እሴት ግንባታ ዙሪያ የምክክር መድረክ በኮሬ ዞን ኬሌ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
ወላይታ ሶዶ፦ መጋቢት 18/2017 ዓ/ም የደቡብ ኢትዮጵያ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኮሬ ዞን፣ በቡርጂ ዞን እና በምዕራብ ጉጂ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች የሚስተዋለዉን የሰላም እጦት በዘላቂነት ለመፍታት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካል መስተጋብሮችን በማስፈን በቀጠናዉ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ዓላማ ያደረገ የዉይይት መድረክ እንደሆነ ተገልጿል።

በመድረኩ በሁለቱ አጎራባች ክልሎች ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ለሠላም መደፍረስ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉትን ጉዳዮች በዝርዝር ቀርቦ ዉይይት ተካሂዶ የቀጣይ አቅጣጫዎችም ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ፣ የደቡብ ክልል ሚሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊ፣ የ37ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮለኔል ካስዬ፣ የኮሬ፣ ቡርጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞን አስተዳዳሪዎችና አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ የጎርካ፣ ሳርማሌ፣ የሶያማ ዙሪያ ወረዳ፣ ገላና አባያና ሱሮ ባርጉዳ ወረዳዎች እንዲሁም የኬሌ ከተማና የሶያማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች እና የየመዋቅሮቹ የፀጥታ አመራር አካላት መድረኩን እየተሳተፉ እንደሚገኙ ከኮሬ ዞን መንግስት ኮሙኒከሸን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።
የስቅለትና የፋስካ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር በቂ የቅደመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቁን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የዘንድሮ የስቅለትና የፋስካ በዓል የፀጥታ ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ በዓሉ ከወትሮ በተሻለ ሁኔታ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር የቅደመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ገልፀዋል።

ማህበረሰቡ ያለምንም የፀጥታ ችግር በዓሉን እንዲያከብር ዕቅድ ተዘጋጅቶ በክልሉ በሁሉም መዋቅሮች ወደ ተግባር መገባቱንም ጠቁመዋል።

በበዓሉ ጤናማ፣ የተረጋጋና የህግ የበላይነት የሰፈነበት የግብይት ስርዓት እንዲረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

የገንዘብ ተቋማት አካባቢ ከፍተኛ የገንዘብ ልውውጥ ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ ከኪስ አውላቂና ሌቦች እራሱን እንዲጠብቅ በማሳሰብ፣ ህብረተሰቡ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የጥበቃ ስራዎች እንዲጠናከሩ የማድረግ ስራ እየተሰራ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።

ህዝቡ እንደተለመደው በዓልን አስታኮ ከሚመጡ ሌቦች እራሱን እንዲጠብቅና አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲኖሩ ፈጥኖ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ ማድረግ እንደሚገባውም አመላክተዋል።

በመጨረሻም ለመላው ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለስቅለትና የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሚያዝያ 9/2017 ዓ.ም