SIRARA
9.54K subscribers
3.68K photos
40 videos
2 files
732 links
ይህ ቻናል ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና የተረጋገጡ እና አዝናኝ የሆኑ መረጃዎች የሚቀርቡበት ነው!
ለማስታወቂያ እና ጥቆማ በዚህ ያናግሩን 👉 https://t.me/mo_anbesa
Download Telegram
የወጣቱ ስደት‼️

ያለፈው መጋቢት ወር ብቻ  9000 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ የመን ገብተዋል ከመስከረም ወር ጀምሮ ደግሞ ከ 37,000 በላይ ስደተኞች በባህር ወደ የመን ገብተዋል።

ይህ በየቀኑ የዓሳ ነባሪ እራት ሆኖ ከሚቀረው ውጭ ነው ። ባህር ላይ የሚቀረው ቤት ይቁጠረው በዚህ ሁለት ወር ውስጥ ብቻ ወደ 365 ሰዎች አካባቢ ባህር ላይ ቀርተዋል።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
ሌላኛው ትራኦሬ‼️

የ41 አመቱ የቻድ ፕሬዝዳንት ማሃማት ዴቢ የሚገኙትን የፈረንሳይ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዙ‼️

ፈረንሳይ በሰላም ማስከበር ሰበብ ወርቅን ጨምሮ በርካታ ማዕድናትን ወስዳለች ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ማሃማት ዴቢ የፈረንሳይ ወታደሮች ቻድን ለቀው እንዲወጡ ያዘዙ ሲሆን፣ ይህም ለ70 አመታት የቆየውን ወታደራዊ ቆይታ እንዲያበቃ የሚያደርግ ውሳኔ መሆኑ ተነግሯል።

ይህ ውሳኔ በሉዓላዊነት እና በፀረ-ፈረንሳይኛ እንቅስቃሴን ከሚያራምዱት ከማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪናፋሶ ሀገራት ጋር ይመሳሰላል(አዩዘሀበሻ)።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
ተዋናይት ናርዶስ አዳነ የላይፍታይም ፕሮፐርቲስ ብራንድ አምባሳደር ሆነች።

ላይፍ ታይም ፕሮፐርቲስ ተዋናይት ናርዶስ አዳነ የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር በማድረግ በዛሬው እለት በስካይ ላይት ሆቴል ስምምነት አድርጓል።

ላይፍ ታይም ፕሮፐርቲስ የሪል ስቴት ስራዎች ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን በ4 ኪሎ አካባቢ አፓርታማ ሰርቶ ያስረከበ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በቦሌ መድኃኒአለም አካባቢ ባለ 21 ፎቅ አፓርታማ እያስገነባ ይገኛል።

በዚህም ተዋናይቷ ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደምታገኝ ተገልጿል።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
አስቸኳይ ስብሰባ በአቡነ ገብርኤል አስተምህሮ ምክንያት ተጠራ

የሸዋ ሀገረ ስብከት አቡነ ገብርኤል "አትደናገጡ ማሪያም ቤዛ አይደለችም!” ማለታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ለአርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ጠራ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር መርህ ግብር ላይ ያስተላለፉት "ሱሁት" (የተሳሳተ) የነገረ ማርያም እና የነገረ ድኅነት አስተምህሮ ለማረም ለመወያየት ስብሰባው እንደተጠራ ገልጿል።

በተለይም አቡነ ገብርኤል "ማሪያም ቤዛ አይደለችም!" በማለታቸው የተነሳው ውዝግብ ቤተ ክርስቲያኒቱን እያነጋገረ ሲሆን፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ በዚህ ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ለማሳለፍ እንደሚችል ይጠበቃል።

ይህ አስቸኳይ ስብሰባ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት ያገኘ ሲሆን፣ ምእመናንና የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት የሲኖዶሱን ውሳኔ በጉጉት እየተጠባበቁ ናቸው። ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላ ቤተ ክርስቲያኒቱ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መግለጫ እንደምትሰጥ ይጠበቃል።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
‼️መሬት መንቀጥቀጥ‼️

በኢስታንቡል በሬክተር ስኬል 6.2 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መደረሱ ተሰምቷል

በዛሬው እለት በቱርክ 6.2 በሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የሀገሪቱ የአደጋ እና የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር ባለስልጣን (AFAD) አስታወቋል።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
የአሜሪካ ኢንባሲ ማስጠንቀቂያ ለኢትዮጵያውያን።

በቪዛዎ ከተፈቀደሎት ጊዜ በላይ ከቆዩ ወደፊት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመጓዝ ቋሚ እገዳ ሊጣልቦትና በህግ ሊያስጠይቅ ይችላል።

የቆንስላ ኦፊሰሮች የኢሚግሬሽን ሙሉ ታሪክዎን ማግኘት ይችላሉ።  በተጨማሪም ከዚህ በፊት የተላለፉት የኢሚግሬሽን ሕግ ጥሰቶች ካሉም የቆንስላ ኦፊሰሮች ያውቃሉ። ቪዛዎን በትክክል መጠቀም የእርስዎ ኃላፊነት ነው"ብሏል።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
ራሺያ ለቡርኪናፋሶ ደረሰች‼️

የቡርኪናፋሶ መሪ በሆነው ኢብራሂም ትራኣሬ ላይ ከቀናት በፊት ለ20ኛ ጊዜ የተቀነባበረ የግድያ ሙከራ መደረጉን ተከትሎ የራሺያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስቸኳይ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ወደ ቡርኪናፋሶ ለመላክ ቁርጠኛ መወሰናቸውን የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።


#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
በትራፊክ አደጋ የ16 ሰዎች ሕይዎት አለፈ

በምዕራብ አርሲ ዞን ኔጌሌ አርሲ ወረዳ ራፉ ሃርጊሳ ቀበሌ በደረሳ የትራፊክ አደጋ የ16 ሰዎች ሕይዎት ሲያልፍ በ22 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል አካል ጉዳት ደርሷል፡፡

አደጋው የደረሰው፤ ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዝ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ባለ ተሳቢ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጋር በማጋጨቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አደጋውን ተከትሎም ከሟቾች በተጫመሪ በ16 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ6 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የኔጌሌ አርሲ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
ሀማስ ሁሉንም ታጋቾች መልቀቅ አለበት - ሙሀመድ አባስ

የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አባስ፣ ሀማስ ሁሉንም የእስራኤል ታጋቾች በፍጥነት መፍታ አለበት ማለታቸው ተገለጸ፡፡

በጋዛ ያለውን ቀውስ ያባባሳው እና እስራኤል የተጠናከረ ጥቃት እያደረሰች ያለው ሀማስ አግቶ በያዛቸው ሰዎች ምክንያት ስለሆነ፤ አሁኑኑ ታጋቾችን መልቀቅ እንዳለበት ሙሀመድ አባስ ጥሪያቸውን አሰምተዋል፡፡

አባስ በራማላህ በነበራቸው ስብሰባ "እኔም ህዝቤም ዋጋ እየከፈልን መቀጠል የለብንም" ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

አክለውም በየቀኑ ሞት ማስተናገድ ሰልችቶናል፤ በጋዛ ያለውን ህዝብ ሰላም ለመጠበቅ ሀማስ ቀሪ ታጋቾችን መልቀቅ አለበት ብለዋል፡፡

እንናተ ማትረቡ ከጋዛ ህዝብ ላይ እጃችሁን አንሱ በማለት ሀማስን መዝለፋቸውም ታውቋል፡፡

የሀማስ ከፍተኛ መሪ ባሲም ናኢም በበኩሉ፤ የአባስ ዘለፋን በማውገዝ ተቀባይነት የሌለው ሲል አጣጥሎታል፡፡

ቢቢሲ

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
በስቅላት ተቀጣ‼️

በኢራን አምስት ህፃናትን ደፍሮ መድፈሩ ሳያንስ ቪዲዮ ቀርፆ በኦንላይን የለቀቀው ግለሰብ በቴህራን አደባባይ በስቅላት ተቀጥቷል።

ይህ ግለሰብ በኢራን ፍርድቤት ሞት ከተፈረደበት በሗላ ማስተማሪያ እንዲሆን ህዝብ በተሰበሰበበት በአደባባይ እንዲሰቀል መደረጉን ሚድል ኢስት አስነብቧል።

ኢራን ከ 1979 በሗላ የሼሪአ ህግ መተዳደሪያየ ነው ብላ ያወጀች ሲሆን አስገድዶ መድፈር በኢራን በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
#Factcheck‼️
ይሄ መንገድ የተቆፈረው በአማራ ክልል ውስጥ  ሳይሆን Umzinyathi በሚባል በደቡብ አፍሪካ አንዲት ከተማ ውስጥ ሲሆን እነዚህ ሰዎች መንገድ ለመቆፈር የተገደዱት ውሃ እና መብራት አልገባልንም በሚል ነበር። ምስሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነሳነው ከአምስት አመት በፊት November 24 2020 ላይ ነው።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
‼️ ሰበር ኢየሩሳሌም እየነደደች ነው

በእስራኤል ከተሞች ከፍተኛ የሰደድ እሳት ተነሳ‼️


የሰደድ እሳቱ የተነሳው በእየሩሳሌም እና በዋና ከተማዋ ቴልአቪቭ አቅራቢያ ሲሆን እሳቱን ለመቆጣጠር የእስራኤል ባለስልጣናት ኤሊኮፍተሮችን እና የእሳት አደጋ መኪኖችን ወደ ስፍራው በመላክ እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢኒያሚን ኔታንያሁ በሀገሪቱ የተነሳውን እሳት ለመቆጣጠር ከባድ መሆኑን ገልጸው የሰደድ እሳቱ የሚባባስ ከሆነ እስራኤል የጎረቤት ሀገራት እርዳታን ትጠይቃለች ሲሉ ገልጸዋል።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
‼️ ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ታገደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚሰሩ ኦርቶዶክሳውያን የሚዲያ ተቋማት በአንድ ማዕከል  እንዲያገለግሉ፣ የመረጃ ፍሰቱ ወጥነት ያለውና ተቋማዊ መሆን ይችል ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቶ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብረው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ ማከናወን የሚችሉበት ፈቃድ ከመምሪያው መሰጠቱ ይታወሳል።

ከእነዚህ የሚዲያ ተቋማት መካከልም የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን አንዱ ሆኖ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት "ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም።" በሚል ርእስ  የተላለፈው ትምህርትን ውዝግብ በማሰነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያችን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው የታገደ መሆኑን እንገልጻለን።
                ሚያዚያ ፲፭ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
                     አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
          የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
                      ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ዘገባውን ሚዛናዊ ለማድረግ የሄደው ጋዜጠኛ ታሰረ!

የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ ጋዜጠኛ አበበ ፍቅር ታሰረ፡፡ጋዜጠኛ አበበ የታሰረው ትናንት ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት አካባቢ ነው፡፡

ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገው ከልደታ ክፍለ ከተማ ኃላፊዎች መረጃ በማሰባሰብ ላይ እያለ ሲሆን፣ የታሰረበት ምክንያት እስካሁን ግልጽ አልሆነም፡፡

ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገው እየሠራው ለነበረው ዘገባ ሚዛኑን ለመጠበቅ፣ የክፍለ ከተማውን ኃላፊዎች ለማነጋገር በሥፍራው በተገኘበት ወቅት ነበር፡፡


#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
‼️ይቅርታ ጠየቁ

ከሰሞኑ ትክቅ መነጋገሪያ ሆነው የሰነበቱት አቡነ ገብርኤል ቤተ ክርሰቲያኒቱን እና ህዝቡን ይቅርታ ጠይቀዋል።

==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የፍልስጤም አስተዳደር ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ከፍልስጤም ነፃነት ድርጅት (PLO) ማዕከላዊ ምክር ቤት ስብሰባ በፊት ለሐማስ ባስተላለፈው መልዕክት:-

“እናንተ የውሻ ልጆች ሆይ፣ [የእስራኤላውያን ምርኮኞችን ፍቱ፣ ሕዝባችንንም አድኑ፣ እስራኤልም ከእንግዲህ ወዲህ ሰበብ እንዳታገኝ አድርጉ" ለሐማስ ድርጊት ዋጋ እየከፈለ ያለው ህዝቡ ነው ዋጋ እየከፈልኩ ያለሁት እኔ ነኝ እስኪ የሞተውን ህዝብ አስቡት" ሲል ተናግሯል።
ነገሩ እንዴት ነው??

ሃገር በፕሮፖጋንዳ እና በአክቲቪስት ጩኸት ሊመራ፣ እውነትም በሃሰት ድግግሞሽ ሊጠፋ አይችልም። ለአንድ ሃገር ደግሞ ክብርና ተገቢ ክፍያ የሚገባው የሰውን ነፍስ ለሚያድን ሃኪም፣ ድንበር ለሚጠብቅ ሰራዊት፣ ትውልድ ለሚቀርጹ መምህራን እንጂ ህዝብ ሲያጋጭ የሚውል፣ ጸብ ጠማቂ ወሬኛ አይደለም

==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
አስገራሚው የኔቶ በጀት🤫

🔻አንድም ጦረንት ላይ ሳይሳተፍ በአንድ አመት ብቻ 486 ቢሊዮን ዶላር ወጭ አድርጓል‼️

የሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረት (ኔቶ) ባለፈው በፈረንጆቹ 2024 ለመከላከያ በሚል 19 ነጥብ 4 በመቶ ወይም 486 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን ወጭ ማውጣቱ ተገለጸ።

በ2024 ህብረቱ ለወታደራዊ አገልግሎት 486 ቢሊዮን ዶላር በመመደብ ከ2023 የተሻለ እንደነበርም የኔቶ ዋና ጸሀፊ ማርክ ሩቴ መረጃውን አጋርተዋል፡፡

የቃል ኪዳን ጦሩ በዩክረን ሩሲያ ጦርነት ከዩክሬን በኩል ወግኖ ሊዋጋ ይችላል በሚል ስጋቶች ሲነሱ ቢቆዩም ሶስተኛውን የአለም ጦርነት በይፋ ማወጅ ይሆናል በሚል እቅዱ የእሰረ ሲሆን፣ ጦሩ ባለፈው 2024 ብቻ አንድም ጦርነት ላይ ሳይሳተፍ 486 ቢሊዮን ዶላር ወጭ አድርጓል መባሉ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው‼️

==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
ትራምፕ ከፑቲን ጋር ለመገናኘት ማቀዳቸወን ገልጸዋል!!

ትራምፕ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጉብኝታቸው በኋላ ከፑቲን ጋር ለመገናኘት አቅደዋል ተባለ። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከግንቦት 5 እስከ 8 ወደ ኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ይጓዛሉ።

"ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ከፑቲን ጋር እንገናኛለን ብዬ አስባለሁ" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ የክሬምሊን ቃል አቀባይ የሩሲያ እና የአሜሪካ መሪዎች ግንኙነት ፍሬያማ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ እና ዝግጅቶች ከውዲሁ እየተደረጉ እንደሆነ ረቡዕ ዕለት አስታውቀዋል፡፡

==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews