SIRARA
9.16K subscribers
3.99K photos
51 videos
2 files
666 links
ይህ ቻናል ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና የተረጋገጡ እና አዝናኝ የሆኑ መረጃዎች የሚቀርቡበት ነው!
ለማስታወቂያ እና ጥቆማ በዚህ ያናግሩን 👉 https://t.me/mo_anbesa
Download Telegram
ሀራ የወንድማአምችነት መዲና 💚💚

የአፋር እና የወሎ ወንድማማች ህዝቦች የእርቅ እና የአንድነት መድረክ በሰሜን ወሎ ሀራ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ ድንበር አካባቢ ከእንስሳት ግጦሽ ጋር ተያይዞ ያጋጠሙ አለመግባባቶችን በእርቅ ለመቋጨት ያለመ ነው ተብሏል።

ከ1 ወር በፊት በጭፍራ ከተማሌላ ተመሳሳይ መድረክ መካሄዱ ይታወሳል።
በአሜሪካ የሀማስ ተቃውሞ ሰልፍ ላይ ጥቃት ተሰነዘረ

በአሜሪካ ኮሎራዶ በሚገኝ የገበያ ማዕከል አንድ ግለሰብ በሰዎች ላይ በፈፀመው እሳት የመልቀቅ ጥቃት ስድስት ሰዎች አካላዊ ጉዳት ገጠማቸው ተባለ፡፡

ግለሰቡ በገበያ ስፍራው በነበሩ ሰዎች ላይ ሞሎቶቭ ኮክቴል የተሰኘውን ጓዳ ሰራሽ ተቀጣጣይ ቁስ በመወርወር በስድስቱ ላይ አካላዊ ጉዳት ማድረሱን ቢቢሲ ፅፏል፡፡

ስፍራው በሐማስ ተይዘው የሚገኙ ታጋቾች እንዲለቀቁ የሚጠይቁ ሰዎች መሰባሰቢያ ነበር ተብሏል፡፡

ግለሰቡ ተቀጣጣይ ቁሱን በሚወረውርበት ወቅት ነፃነት ለፍልስጤም ብሎ ይጮህ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

የአሜሪካ ፌዴራል የምርመራ ቢሮ ሹሞች የግለሰቡ ድርጊት የሽብር ጥቃት እንደሆነ እንጠረጥራለን ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

የእስራኤሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኮሎራዶውን ጥቃቱ የፀረ ሴማዊነት ውጤት ነው ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡
በድጋሚ ታሰሩ‼️

አቶ ታዬ ደንደአ በድጋሚ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት  አቶ ታዬ ደንደአ በዋስ የተለቀቀው ሁለቱ ክሶች በከፍተኛ ፍርድ ቤት ነፃ ሰለተባለ ስለነበረ አሁን ግን የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ የተሻረ በመሆኑ የዋስ መብቱ ቀሪ ሆኖ በዛሬው ቀን በቁጥጥር ስር ውሏል፡
ዜና ዕረፍት‼️

ዘማሪት የምስራች ጨጓራዋ አከባቢ ከነበረው 4ኛ ደረጃ ካንሰር ተፈውሳ ነበር፣ ከጊዜያት በኋላ ቼካፕ ስታደርግ ጀርባዋ አከባቢ ሶስተኛው አጥንት ላይ እና ሳንባዋ ላይ ካንሰር ተገኝቶባት ከባድ ሳል ታክሎበት ፅኑ ሕሙማን ክፍል እንድትገባ ተደርጎ ነበር ዛሬ የተሰማው ዘማሪት የምስራች ህይወቷ ማለፉ ነው።

ለመላው ቤተሰቦቿ ወዳጆቿ መጽናናትን እንመኛለን።
ቢል ጌትስ ካለው 200 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ውስጥ አብዛኛውን ለአፍሪካ ሊሰጥ መሆኑን ተናገረ

የማይክሮሶፍት መስራች ቢልጌትስ፤ በቀጣዮቹ 20 ዓመታት ካለው ሀብት ውስጥ አብዛኛውን በአፍሪካ የጤና እና ትምህርት አገልግሎቶችን ለማሻሻል እንደሚያውል ተናገረ።

የ69 ዓመቱ ባለጸጋ፤"በጤና እና ትምህርት የሰው ልጅን በማውጣት፤ አፍሪካ ውስጥ እያንዳንዱ ሀገር በብልጽግና ጎዳና ላይ መሆን አለበት" ብሏል።
የትራፊክ ፖሊሱ፡- "አምጣ ባክህ!"

ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ ያለው የትራፊክ ፖሊስ በቀን መብራት አይሰራም በሚል ምክንያት ከአሽከርካሪ ገንዘብ ሲቀበል የሚያሳይ ቪዲዮ ብዙዎችን አስቆጥቷል።

ይህ ክስተት "ትራፊኮች በቀን ከደሞዛቸው በላይ ያገኛሉ" የሚለውን የተለመደ ወሬ ዳግም እንድናነሳ አድርጎናል።
የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ሐሚቲ ኢትዮጵያ ገብቷል

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) መሪ መሀመድ ሃምዳን ዳግሎ ለሰራዊቱ ሽንፈት ኤርትራን ተጠያቂ አደረገ። በአረብ ኢምሬትስ የሚደገፈው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) መሪ የሆኑት መሀመድ ሃምዳን ዳግሎ ኤርትራ ለሰራዊቱ ሽንፈት ምክንያት እንደሆነች አስታወቀ። ሄሜቲ ከሱዳን በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ ባንጊ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ታውቋል።
ነገረ ፌስታል‼️
ከሱቅ እቃ ገዝቶ በፌስታል ይዞ መምታት ሊቀር ነው፣ ማዳበሪያ አዘጋጁ ተብሏል . . . አይ ፌስታሌን ካላችሁ 5 ሺህ ብር ኪሳችሁ ውስጥ መያዛችሁን አረጋግጡ።

ወይ ጊዜ??
አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ ለ14 ዓመታት ሲጠራበት የነበረውን ስያሜ ወደ አዲስ ባንክ መቀየሩን አስታውቋል። በተጨማሪም የባንኩን አርማም መለወጡን ገልጿል።
ዛሬ በዚህ ሰዓት እና በዚህ ቀን አርበኛ ዘመነ ካሴ ከእስር የተፈታበት ቀን እንደሆነ ፌስቡክ "2 Years Memories" ብሎ ለጉርሻ ፔጅ አስታውሷል።

አርበኛ ዘመነ ካሴን በተመለከተ፡-

* ኢትዮጵያን በፍቅር ከሚወዱት ውስጥ ይመደባሉ።

* ሚሊዮኖች ጀግናና የጀግና ዘር እንደሆኑ ይመሰክሩለታል።

* እጅግ ብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በፍቅር ይወዱታል።

* ላመኑበት ነገር ሟች ነው ይሉታል።

* ከሁለት ዓመት በፊት በዚህ ሰዓት ከብዙ ወራት እስር በኋላ ሲፈታ፣ መላው ሕዝብ በፍቅርና በክብር አጅቦ፣ እንዲሁም ደማቅ አቀባበልም አድርጎለታል ለቤቱ አብቅቶታል::

ስለ አርበኛ ዘመነ ካሴ ስታስቡ ግን ምን ይሰማችኋል? ሀሳባችሁን አካፍሉን።

🙏🙏🙏

ጉርሻ
💚💚 እንደምን አደራችሁ ቤተሰቦች🤩🤩
ቀናችሁ ያማረ ድካማችሁ ፍሬ የሚያፈራ ይሁንላችሁ 🙏🙏🙏🙏🙏
ኤርትራ በአሜሪካ ከታገዱ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተካተተች

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከ12 ሀገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን ጉዞ የሚከለክል አዋጅ መፈራረማቸውን ዋይት ሀውስ አስታወቀ።

ክልከላ የተደረገባቸው ሀገራት አፍጋኒስታን፣ ምያንማር፣ ቻድ፣ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኤርትራ፣ ሄይቲ፣ ኢራን፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና የመን ናቸው።

አዋጁ ከቀጣዩ  ሰኔ 9 ጀምሩ ተግባራዊ ይሆናል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እገዳውን ተችተውታል፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል  እገዳውን "አድሎአዊ፣ ዘረኛ እና  ጨካኝ" ሲል ገልፆታል።
ድምፃዊው መብሬ መንግስቴ ታሰረ!

ድምፃዊ መብሬ መንግስቴ በአዲስ አበባ የካ ሾላ ገበያ አካባቢ ከሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ታስሯል።

ድምፃዊው ከሚኖርበት አዲስአበባ ለገጣፎ ቤቱ ሲፈርስበት ወደ ደብረብርሃን በመሄድ የምሽት ክለብ ከፍቶ ቅዳሜ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ነበር። ዛሬ መታሰሩ ታውቋል።(gion)
ተሰረዘ‼️

መንግስት እና የግል ሰራተኞች ከደመወዛቸው ላይ ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ እንዲያዋጡ የሚያስገድድ ድንጋጌ ተሰረዘ


ወደፊት ለሚቋቋመው “የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ”፤ ከመንግስት እና ከግል ተቋማት ሰራተኞች ደመወዝ መዋጮ እንዲሰበሰብ የሚያስገድደው የአዋጅ ድንጋጌ ተሰረዘ።

ባለፈው መጋቢት ወር መጀመሪያ ለተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ይኸው አዋጅ፤ የመንግስት እና የግል ተቋማት ከሚሰጧቸው 15 አይነት አገልግሎቶች “ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” ገቢ እንዲሰበሰቡ የሚያስገድድ ድንጋጌ በውስጡ ይዞ ነበር።

ድንጋጌው በዛሬው ዕለት በፓርላማ ከጸደቀው “የአደጋ ስጋት ስራ አመራር አዋጅ” ውስጥ እንዲወጣ የተደረገው፤ በሰራተኞች ላይ “ተደራራቢ ጫና እንዳያስከትል” ታስቦ መሆኑ ተገልጿል።
በዓለም የቁንጅና ውድድር 2ኛ የወጣችው ሀሴት ደረጄ ደማቅ አቀባበል ተደረገላት

በሕንድ ሃይድራባድ በተዘጋጀው የ'ሚስ ወርልድ' ዓለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር ላይ ተሳትፋ 2ኛ የወጣችው ሞዴል ሀሴት ደረጄ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል፡፡

የባህል እና ስፓርት ሚኒስትር ዴኤታ ረ/ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፣ የባህል እና ስፓርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማሀዲ፣ የአዳስ አበባ ባህል እና ኪነ-ጥበብ ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳ (ዶ/ር) በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡
ክርስትና 🥰❤️

አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን ውስጥ አንዳንድ ነገሮች ሲመጡ በፀጋ መቀበል ያለብን ይመስላል

ምክንያቱም እነዛ አስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ የተደበቀ በረከት ሊኖሩ ይችላሉና::

እድግ ይበልልሽ…..

🙏🙏🙏❤️❤️

Via:Gursha