SIRARA
9.55K subscribers
3.67K photos
40 videos
2 files
732 links
ይህ ቻናል ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና የተረጋገጡ እና አዝናኝ የሆኑ መረጃዎች የሚቀርቡበት ነው!
ለማስታወቂያ እና ጥቆማ በዚህ ያናግሩን 👉 https://t.me/mo_anbesa
Download Telegram
መረቅ ያለው ዱባ ብጠጣስ ? 😂

1 ስኒ ማኪያቶ - 125 ብር 😎 ኧረ ቶሞካ ወዴት እየሄደ ነው🤔


እዝናናለሁ ብዬ ሄጄ ቀልቤ ግፍፍ ብሎልሃል። ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ሀገር አይደለችምን ?

መቀመጫ እንኳን ለሌለው ቤት በሃገራችን የተመረተ ቡና ይሄ ፌዬር ነው በዱባ ሞት😊
ምነው መረቅ ያለው ዱባ ብጠጣስ ?

Via ጉርሻ
መንገድ ለሚዘጉ የሠርግ አጃቢ አሽከርካሪዎች ማስጠንቀቂያ ተላለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ በዓላትና ሰርግን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ የሚፈጽሙ መንገድ የሚዘጉ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ።

ሕብረተሰቡ የጸጥታ አካላት የሚያስተላልፉትን የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶች በአግባቡ እየተገበረ መሆኑን ተከትሎ በከተማዋ የወንጀል ድርጊቶች እየቀነሱ መምጣታቸውንም ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንዳሉት፣ በከተማዋ የትንሳኤ በዓል በሰላማዊ ሁኔታ ተከብሯል።

ቀላል ከሚባሉ የስርቆትና የማጭበርበር ድርጊቶች ውጪ በዓሉን ተከትሎ ውስብስብና ከባድ የወንጀል ድርጊቶች አለመፈጸማቸውንም አመልክተዋል።

ለዚህ ደግሞ ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በአግባቡ በመተግበሩ መሆኑን በመጥቀስ።

መጪውን የሰርግ ወራት ተከትሎ በከተማዋ የትራፊክ ፍሰት ላይ ያልተገባ የመንገድ መጨናነቅ የሚፈጽሙ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

ከተማዋን በማይመጥን መልኩ መንገድ በሚዘጉና የትራፊክ ፍሰቱን በሚያስተጓጉሉ አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢው የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድም መናገራቸውን ተዘግቧል።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ እና ኬንያ ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት ሰረዙ


የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ ማይክ ሩቢዮ በናይሮቢ እና በአዲስ አበባ ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት መሰረዛቸው ተሰምቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት የሰረዙት፤ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ለአምስት ቀናት በቻይና ጉብኝት ለማድረግ ወደ ቤጂንግ ካቀኑ ከሰዓታት በኋላ መሆኑ ነው የተገለጸው።

እንደ አፍሪካ ኢንተለጀንስ ዘገባ ከሆነ የሩቢዮ የመጀመሪያው የአፍሪካ ጉብኝት 'በደህንነት እና የንግድ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደርጋል' ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም፤ ጉብኝቱ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።
ቦይንግ የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ መክፈቱ መልካም ዜና ነው

የዚህ ክስተት ዋናው መንስኤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተከታታይ ስኬት እና ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ከምስረታው ጀምሮ የነበረው ታሪካዊ ትስስር ነው።

አሁንም ይህ ትብብር በሌሎች ሀገራት እንደሚታየው ወደ አውሮፕላን ቁሶች ማምረት እና በሀገር ውስጥ ያለውን የ Maintenance፣ Repair እና Overhau (MRO) አገልግሎቶችን ወደማሳደግ እና ማዘመን እንዲያድግ ምኞታችን ነው። (EliasMeseret)

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
" የትግራይ ህዝብ ከሰጠኝ እውቅናና ክብር በላይ የምመኘው የክብርና የምስጋና መድረክ የለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በአዲሱ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) የቀረበላቸው የክብርና የምስጋና የሽኝት መድረክ ውድቅ አደረጉ።

አቶ ጌታቸው ረዳ ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚድያ ቃለ-መጠይቅ ሰጥተዋል።

ሚንስትሩ UMD ለተባለ ሚድያ በትግርኛ ቋንቋ በሰጡት ቃለመጠይቅ " በትግራይ የተደረገው የስልጣን ሽግግር የትግራይ ህዝብን ደህንነትና ህልውና የሚያስጠብቅ አይደለም " ብለውታል። 


"እኔን በክብር መሸኘት ቅድሚያ የሚሰጠው አይደለም ፤ ቅድሚያ የሚሰጠው በትግራይ የሰፈነው ህግ አልባ አካሄድ እንዲስተካከል መስራት ነው" ያሉት አቶ ጌታቸው አክለውም "የትግራይ ህዝብ የሰጠኝ ክብርና እውቅና  ከፍተኛ ነው ፤ ከዚህ ክብርና እውቅና በላይ የምመኘው የምስጋና መድረክ የለም " ሲሉ የገለፁ ሲሆን በአዲሱ ፕሬዜዳንት የቀረበላቸው የምስጋናና የክብር የሸኝት መድረክ እንደማይቀበሉት አሳውቀዋል።

በክልሉ ያሉ ሌቦችና ህገ-ወጦች አደብ ለማስገዛት ለሚደረገው ጥረት እንደሚያግዙ ህዝቡ ለማገለገል እንደ ትናንት ዛሬም ዝግጁ እንደሆኑም ገልጸዋል።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
የኤርትራን ሕዝብ የጨቆነ የምስራቅ አፍሪካ የሰላም ፀር ሊገረሰስ ይገባል:-ኢብራሂም ሀሩን

አቶ ኢብራሂም ሃሩን የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (RSADO) ዋና ሊቀመንበር የሰጡትን ሀሳብ ትናንት Al Jazeera English አሰራጭቶታል።

“ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በወታደራዊ መንግስት ጭቆና ውስጥ ህልቆ መሳፍርት የሌለው ሰቆ'ቃ ለሚንከላወሱ ኤርትራውያን ሊደርስላቸው ጊዜው አሁን ነው...”ሲል ፅፏዋል።

ጦርነትን እንጂ ሰላምን የማይወድ ክፋትን እንጂ መልካምነትን የማያውቅ ጭቆነን እንጂ ነፃነትን የማይፈልግ እድሜ ልኩን ምስራቅ አፍሪካን ብሎም የኤርትራ ዜጎችን እያሰቃየ ያለ አምባገነን ሊገረሰስ ይገባል ብሎል።

ዓለም ሁሉ ለኤርትራ ሕዝብ ነፃነት የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ እንቅስቃሴ ማድረግ አለበት ብሏል።
via Zenaethiopia

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
የወጣቱ ስደት‼️

ያለፈው መጋቢት ወር ብቻ  9000 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ የመን ገብተዋል ከመስከረም ወር ጀምሮ ደግሞ ከ 37,000 በላይ ስደተኞች በባህር ወደ የመን ገብተዋል።

ይህ በየቀኑ የዓሳ ነባሪ እራት ሆኖ ከሚቀረው ውጭ ነው ። ባህር ላይ የሚቀረው ቤት ይቁጠረው በዚህ ሁለት ወር ውስጥ ብቻ ወደ 365 ሰዎች አካባቢ ባህር ላይ ቀርተዋል።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
ሌላኛው ትራኦሬ‼️

የ41 አመቱ የቻድ ፕሬዝዳንት ማሃማት ዴቢ የሚገኙትን የፈረንሳይ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዙ‼️

ፈረንሳይ በሰላም ማስከበር ሰበብ ወርቅን ጨምሮ በርካታ ማዕድናትን ወስዳለች ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ማሃማት ዴቢ የፈረንሳይ ወታደሮች ቻድን ለቀው እንዲወጡ ያዘዙ ሲሆን፣ ይህም ለ70 አመታት የቆየውን ወታደራዊ ቆይታ እንዲያበቃ የሚያደርግ ውሳኔ መሆኑ ተነግሯል።

ይህ ውሳኔ በሉዓላዊነት እና በፀረ-ፈረንሳይኛ እንቅስቃሴን ከሚያራምዱት ከማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪናፋሶ ሀገራት ጋር ይመሳሰላል(አዩዘሀበሻ)።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
ተዋናይት ናርዶስ አዳነ የላይፍታይም ፕሮፐርቲስ ብራንድ አምባሳደር ሆነች።

ላይፍ ታይም ፕሮፐርቲስ ተዋናይት ናርዶስ አዳነ የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር በማድረግ በዛሬው እለት በስካይ ላይት ሆቴል ስምምነት አድርጓል።

ላይፍ ታይም ፕሮፐርቲስ የሪል ስቴት ስራዎች ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን በ4 ኪሎ አካባቢ አፓርታማ ሰርቶ ያስረከበ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በቦሌ መድኃኒአለም አካባቢ ባለ 21 ፎቅ አፓርታማ እያስገነባ ይገኛል።

በዚህም ተዋናይቷ ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደምታገኝ ተገልጿል።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
አስቸኳይ ስብሰባ በአቡነ ገብርኤል አስተምህሮ ምክንያት ተጠራ

የሸዋ ሀገረ ስብከት አቡነ ገብርኤል "አትደናገጡ ማሪያም ቤዛ አይደለችም!” ማለታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ለአርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ጠራ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር መርህ ግብር ላይ ያስተላለፉት "ሱሁት" (የተሳሳተ) የነገረ ማርያም እና የነገረ ድኅነት አስተምህሮ ለማረም ለመወያየት ስብሰባው እንደተጠራ ገልጿል።

በተለይም አቡነ ገብርኤል "ማሪያም ቤዛ አይደለችም!" በማለታቸው የተነሳው ውዝግብ ቤተ ክርስቲያኒቱን እያነጋገረ ሲሆን፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ በዚህ ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ለማሳለፍ እንደሚችል ይጠበቃል።

ይህ አስቸኳይ ስብሰባ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት ያገኘ ሲሆን፣ ምእመናንና የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት የሲኖዶሱን ውሳኔ በጉጉት እየተጠባበቁ ናቸው። ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላ ቤተ ክርስቲያኒቱ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መግለጫ እንደምትሰጥ ይጠበቃል።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
‼️መሬት መንቀጥቀጥ‼️

በኢስታንቡል በሬክተር ስኬል 6.2 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መደረሱ ተሰምቷል

በዛሬው እለት በቱርክ 6.2 በሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የሀገሪቱ የአደጋ እና የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር ባለስልጣን (AFAD) አስታወቋል።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
የአሜሪካ ኢንባሲ ማስጠንቀቂያ ለኢትዮጵያውያን።

በቪዛዎ ከተፈቀደሎት ጊዜ በላይ ከቆዩ ወደፊት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመጓዝ ቋሚ እገዳ ሊጣልቦትና በህግ ሊያስጠይቅ ይችላል።

የቆንስላ ኦፊሰሮች የኢሚግሬሽን ሙሉ ታሪክዎን ማግኘት ይችላሉ።  በተጨማሪም ከዚህ በፊት የተላለፉት የኢሚግሬሽን ሕግ ጥሰቶች ካሉም የቆንስላ ኦፊሰሮች ያውቃሉ። ቪዛዎን በትክክል መጠቀም የእርስዎ ኃላፊነት ነው"ብሏል።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
ራሺያ ለቡርኪናፋሶ ደረሰች‼️

የቡርኪናፋሶ መሪ በሆነው ኢብራሂም ትራኣሬ ላይ ከቀናት በፊት ለ20ኛ ጊዜ የተቀነባበረ የግድያ ሙከራ መደረጉን ተከትሎ የራሺያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስቸኳይ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ወደ ቡርኪናፋሶ ለመላክ ቁርጠኛ መወሰናቸውን የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።


#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
በትራፊክ አደጋ የ16 ሰዎች ሕይዎት አለፈ

በምዕራብ አርሲ ዞን ኔጌሌ አርሲ ወረዳ ራፉ ሃርጊሳ ቀበሌ በደረሳ የትራፊክ አደጋ የ16 ሰዎች ሕይዎት ሲያልፍ በ22 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል አካል ጉዳት ደርሷል፡፡

አደጋው የደረሰው፤ ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዝ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ባለ ተሳቢ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጋር በማጋጨቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አደጋውን ተከትሎም ከሟቾች በተጫመሪ በ16 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ6 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የኔጌሌ አርሲ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
ሀማስ ሁሉንም ታጋቾች መልቀቅ አለበት - ሙሀመድ አባስ

የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አባስ፣ ሀማስ ሁሉንም የእስራኤል ታጋቾች በፍጥነት መፍታ አለበት ማለታቸው ተገለጸ፡፡

በጋዛ ያለውን ቀውስ ያባባሳው እና እስራኤል የተጠናከረ ጥቃት እያደረሰች ያለው ሀማስ አግቶ በያዛቸው ሰዎች ምክንያት ስለሆነ፤ አሁኑኑ ታጋቾችን መልቀቅ እንዳለበት ሙሀመድ አባስ ጥሪያቸውን አሰምተዋል፡፡

አባስ በራማላህ በነበራቸው ስብሰባ "እኔም ህዝቤም ዋጋ እየከፈልን መቀጠል የለብንም" ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

አክለውም በየቀኑ ሞት ማስተናገድ ሰልችቶናል፤ በጋዛ ያለውን ህዝብ ሰላም ለመጠበቅ ሀማስ ቀሪ ታጋቾችን መልቀቅ አለበት ብለዋል፡፡

እንናተ ማትረቡ ከጋዛ ህዝብ ላይ እጃችሁን አንሱ በማለት ሀማስን መዝለፋቸውም ታውቋል፡፡

የሀማስ ከፍተኛ መሪ ባሲም ናኢም በበኩሉ፤ የአባስ ዘለፋን በማውገዝ ተቀባይነት የሌለው ሲል አጣጥሎታል፡፡

ቢቢሲ

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
በስቅላት ተቀጣ‼️

በኢራን አምስት ህፃናትን ደፍሮ መድፈሩ ሳያንስ ቪዲዮ ቀርፆ በኦንላይን የለቀቀው ግለሰብ በቴህራን አደባባይ በስቅላት ተቀጥቷል።

ይህ ግለሰብ በኢራን ፍርድቤት ሞት ከተፈረደበት በሗላ ማስተማሪያ እንዲሆን ህዝብ በተሰበሰበበት በአደባባይ እንዲሰቀል መደረጉን ሚድል ኢስት አስነብቧል።

ኢራን ከ 1979 በሗላ የሼሪአ ህግ መተዳደሪያየ ነው ብላ ያወጀች ሲሆን አስገድዶ መድፈር በኢራን በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
#Factcheck‼️
ይሄ መንገድ የተቆፈረው በአማራ ክልል ውስጥ  ሳይሆን Umzinyathi በሚባል በደቡብ አፍሪካ አንዲት ከተማ ውስጥ ሲሆን እነዚህ ሰዎች መንገድ ለመቆፈር የተገደዱት ውሃ እና መብራት አልገባልንም በሚል ነበር። ምስሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነሳነው ከአምስት አመት በፊት November 24 2020 ላይ ነው።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
‼️ ሰበር ኢየሩሳሌም እየነደደች ነው

በእስራኤል ከተሞች ከፍተኛ የሰደድ እሳት ተነሳ‼️


የሰደድ እሳቱ የተነሳው በእየሩሳሌም እና በዋና ከተማዋ ቴልአቪቭ አቅራቢያ ሲሆን እሳቱን ለመቆጣጠር የእስራኤል ባለስልጣናት ኤሊኮፍተሮችን እና የእሳት አደጋ መኪኖችን ወደ ስፍራው በመላክ እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢኒያሚን ኔታንያሁ በሀገሪቱ የተነሳውን እሳት ለመቆጣጠር ከባድ መሆኑን ገልጸው የሰደድ እሳቱ የሚባባስ ከሆነ እስራኤል የጎረቤት ሀገራት እርዳታን ትጠይቃለች ሲሉ ገልጸዋል።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
‼️ ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ታገደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚሰሩ ኦርቶዶክሳውያን የሚዲያ ተቋማት በአንድ ማዕከል  እንዲያገለግሉ፣ የመረጃ ፍሰቱ ወጥነት ያለውና ተቋማዊ መሆን ይችል ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቶ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብረው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ ማከናወን የሚችሉበት ፈቃድ ከመምሪያው መሰጠቱ ይታወሳል።

ከእነዚህ የሚዲያ ተቋማት መካከልም የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን አንዱ ሆኖ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት "ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም።" በሚል ርእስ  የተላለፈው ትምህርትን ውዝግብ በማሰነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያችን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው የታገደ መሆኑን እንገልጻለን።
                ሚያዚያ ፲፭ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
                     አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
          የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
                      ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ