አስገራሚ ዜና
ይህ ዜና የሚለው ኔዘርላንድ ወስጥ በ1987 የባዮሎጂ የመውጫ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎች በድጋሜ እንዲፈተኑ ሊጠሩ ነው ነው። የተሰጠው ምክንያት ደግሞ የባዮሎጂ ፈተና መሰረቁ ተረጋግጧል የሚል ነው። ይህ እንግዲህ የተረጋገጠው ከ38 ዓመት በኋላ ነው። የያኔዎቹ ተማሪዎች ዛሬ እድሜያቸው 55 ደርሷል ።
ባለስልጣኑ ለሁሉም ጥሪ እንደሚደረግና ፈተናውን በድጋሜ እንደሚወስዱ ገልፀው ፣ ካልወሰዱ ግን ዲፕሎማቸው ሙሉ እንደማይሆን አስጠንቀቀዋል ።
ከ38 ዓመት በኋላ በድጋሜ ተፈተኑ ብትባሉ ምን ትላላችሁ?
ፋሲል

አርቲስት ገነት ንጋቱ እና አርቲስት ሙሉጌታ ጀዋሬ ድጋሚ ተጋብተዋል❤
ከአስራ አራት ዓመት መለያየት በኋላ አርቲስት ገነት ንጋቱና አርቲስት ሙሉጌታ ጀዋሬ በትንሳኤው በዓል ቀን ድጋሚ ተጋብተዋል። ሰርጉ በልጆቻቸው፣ በጓደኞቻቸው እና በዘመድ አዝማዶቻቸው ፊት ተከናውኗል።
ሁለቱም ጥንዶች በሀሴት ስሜት እንባቸውን እያፈሰሱ ደስታቸውን ገልጸዋል። "ሁሉን ነገር ለፈጣሪ አሳልፈን ስጥተን ጋብቻችንን ድጋሚ ለመጀመር ወስነናል" በማለት መልካም ምኞትን እንድናደርግላቸው ጠይቀዋል። ብዙ ኢትዮጵያውያን ይህን አንድነት ለረጅም ጊዜ ሲናፍቁ የነበረ ሲሆን አሁን ይህ ፍላጎታቸው እውን ሆኗል።
❤ መልካም ጋብቻ ይሁንላቸው፣ የተባረከ የትዳር ዘመን ይኑራቸው ❤

#ፍርፍሪና በባድመ ተዘፈነ‼️
እውቋና በበዙ ኢትዮጵያውያን ጭምር ተወዳጅነት ያተረፈችው ኤርትራዊቷ ድምፃዊት #ሄለን_መለስ በባድመ ለሚገኙ የኤርትራ ሠራዊት አባላት የሙዚቃ ሥራዎቿን ማቅረቧ ተሰማ።
#sirara #SHARE #JOIN
==/ ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews

ከሸፈ‼️
በ#ቡርኪናፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ላይ ያነጣጠር ግድያ/Assassination/ ከሸፈ‼️
የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው በርካታ ወታደራዊ አባላትን ያሳተፈ እንደነበር የሀገሪቱ የደህንነት ሚኒስትር ማሃማዱ ሳና አስታውቀዋል።
የሀገሪቱ የደህንነት አገልግሎት ተቋማት የሴራው አካል በሆኑ የቡርኪናቢ ወታደሮች እና የታጣቂ ቡድን መሪዎች መካከል የነበረውን ግንኙነት በመጥለፍ የሚገኙበትን ቦታ እና የወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ዝርዝር ሁኔታ እንዳገኙ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ላይ የተሴረው መፈንቅለ መንግሥት በመጀመሪያ ሚያዝያ 8 ቀን ለማካሄድ ታቅዶ እንደነበር ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የውጪ ዜጎችን ጨምሮ ዘጠዥ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከዚህ ጀርባ የፈረንሳይ እጅ እንዳለበት ተዘግቧል። (Ethio FM)

ትራምፕ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ እንዲል ትዕዛዝ ሰጡ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ክብር የፌደራል እና የግዛቶች ሰንደቅ ዓላማዎች ዝቅ ብለው እንዲውለበለቡ መመሪያ ሰጥተዋል።
እስካሁን የተያዘ ዕቅድ ባይኖርም፤ ትራምፕ በቀድሞው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ሥርዓተ ቀብር ላይ ለመታደም ወደ ሮም ሊያቀኑ እንደሚችሉም ነው ዋይት ሀውስ ያመላከተው።

ሞቃዲሾ‼️
ወደ ሶማሊያ መዲና #ሞቓዲሾ በፍጥነት እየገሰገሰ የሚገኘውን የአልሸባብ እንቅስቃሴ ለመግታት ቱርክ 500 ልዩ ኮማንዶ ሰራዊቷን ወደ ሶማሊያ የላከች ሲሆን፣ የኮማንዲ አባላቱን የያዙ 2 የጦር አውሮፕላኖች ሶማሊያ ሞቃዲሾ አርፈዋል። በዚህም በመጀመሪያ 500 የቱርክ ኮማንዶ ከስፍራው መድረሳቸው ተሰምቷል።

SIRARA
ከሸፈ‼️ በ#ቡርኪናፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ላይ ያነጣጠር ግድያ/Assassination/ ከሸፈ‼️ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው በርካታ ወታደራዊ አባላትን ያሳተፈ እንደነበር የሀገሪቱ የደህንነት ሚኒስትር ማሃማዱ ሳና አስታውቀዋል። የሀገሪቱ የደህንነት አገልግሎት ተቋማት የሴራው አካል በሆኑ የቡርኪናቢ ወታደሮች እና የታጣቂ ቡድን መሪዎች መካከል የነበረውን ግንኙነት በመጥለፍ የሚገኙበትን ቦታ እና የወታደራዊ…
20ኛ የግድያ ሙከራ‼️
የዛሬው የግድያ ሙከራ በሁለት አመት ብቻ በዚህ ቆፍጣና መሪ ላይ ለ20ኛ ጊዜ የተደረገ የግድያ ሙከራ ነው።

🇪🇹 ኢትዮጵያ አዲሱን የልማት ባንክ ለመቀላቀል የብሪክስ አባላትን ድጋፍ ማግኘቷን አስታወቀች
ባንኩን ለመቀላቀል ጥያቄ ማቅረቧን እና በቅርቡም ሂደቶቹን አልፋ እንደምተቀላቀል ያላቸውን ተስፋ ያሳወቁት በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልኡልሰገድ ታደሰ ናቸው።
አምባሳደሩ አክለውም ኢትዮጵያ ባንኩን ከተላቀለች የትኩረት አቅጣጫዎቿ ባንኩ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ዘርፎች መካከል ግብርና፣ ኢነርጂ፣ ማኑፋክቸሪንግ ይሆናሉ ብለዋል።
አምባሳደሩ ከቲቪ ብሪክስ ጋር በነበራቸው ቃለ-መጠየቅ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ያላትን አቅም የዘረዘሩ ሲሆን ብሪክስ የተቀላቀለችበት አንዱ አላማ የኢኮኖሚ ትስስሯን ለማጠናከር መሆኑን እና ለዚህም የቱሪዝም ኢንደስትሪው አንዱ መንገድ መሆኑን ገልፀዋል።
#sirara #SHARE #JOIN
==/ ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
ባንኩን ለመቀላቀል ጥያቄ ማቅረቧን እና በቅርቡም ሂደቶቹን አልፋ እንደምተቀላቀል ያላቸውን ተስፋ ያሳወቁት በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልኡልሰገድ ታደሰ ናቸው።
አምባሳደሩ አክለውም ኢትዮጵያ ባንኩን ከተላቀለች የትኩረት አቅጣጫዎቿ ባንኩ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ዘርፎች መካከል ግብርና፣ ኢነርጂ፣ ማኑፋክቸሪንግ ይሆናሉ ብለዋል።
አምባሳደሩ ከቲቪ ብሪክስ ጋር በነበራቸው ቃለ-መጠየቅ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ያላትን አቅም የዘረዘሩ ሲሆን ብሪክስ የተቀላቀለችበት አንዱ አላማ የኢኮኖሚ ትስስሯን ለማጠናከር መሆኑን እና ለዚህም የቱሪዝም ኢንደስትሪው አንዱ መንገድ መሆኑን ገልፀዋል።
#sirara #SHARE #JOIN
==/ ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ አቶ አማኑኤል አሰፋን ምክትላቸው አድርገው ሾሙ
የትግራይ ክልል አዲሱ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የደብረጽዮን ገብረሚካኤልን ቡድን ምክትል ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል አሰፋን ምክትላቸው አድርገው ሾመዋል።
ይህ እርምጃ የጌታቸው ረዳ ቡድን በክልሉ ተቃዋሚ እየሆነ ባለበት ወቅት የተወሰደ ነው። ፕሬዝዳንት ሆነው ከተሾሙ አስራ አንድ ቀናት በኋላ ነው ጄ/ል ታደሰ ወረደ የካቢኔ አባሎቻቸውን ይፋ ያደረጉት።
#sirara #SHARE #JOIN
==/ ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
የትግራይ ክልል አዲሱ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የደብረጽዮን ገብረሚካኤልን ቡድን ምክትል ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል አሰፋን ምክትላቸው አድርገው ሾመዋል።
ይህ እርምጃ የጌታቸው ረዳ ቡድን በክልሉ ተቃዋሚ እየሆነ ባለበት ወቅት የተወሰደ ነው። ፕሬዝዳንት ሆነው ከተሾሙ አስራ አንድ ቀናት በኋላ ነው ጄ/ል ታደሰ ወረደ የካቢኔ አባሎቻቸውን ይፋ ያደረጉት።
#sirara #SHARE #JOIN
==/ ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
ይህም አለ!
ለ10 ዓመታት ቆጥቦ የገዛው አዲስ ‘ፌራሪ’ መኪና በ1 ሰዓት ውስጥ ነደደበት😮😥
ወጣቱ ጃፓናዊ የሙዚቃ ፕሮዲዩሰር ሆንኮን ለ10 ዓመታት ቆጥቦ ሕልሙ የነበረውን ‘ፌራሪ 458 ስፓይደር’ መኪና ከገዛ በኋላ ያሽከረክረው በጀመረ በ1 ሰዓት ውስጥ መኪናው ሲነድ ቁጭ ብሎ ተመልክቷል።
ሕልሙ የነበረውን እና የሚወደውን ፌራሪ መኪና በገዛበት በመጀመሪያው ቀን መንደዱ ብዙዎችን አሳዝኗል፤ ጉዳዩም መነጋገሪያም ሆኗል።
የ33 ዓመቱ ወጣት መኪናውን በገዛበት ዕለት በጃፓን፣ ቶኪዮ ውስጥ በሚገኝ በሹቶ ፈጣን መንገድ ላይ እየተደሰተ የነዳው ቢሆንም ደስታው አብሮት የቆየው ለደቂቃዎች ብቻ ነበር።
ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ዕለት ነበር ሆንኮን መኪናውን የተረከበው፤ መኪናውን እንደተረከበም ለሙከራ መንዳት ይጀምራል፤ በዚህ መሃል በውጭ በኩል ከጎኑ ጭስ ይመለከታል፤ ከሌላ መኪና የሚወጣ ይመስለውና ችላ ይለዋል።
አጠገቡ የነበረው መኪና ርቆ ቢሄድም ጭሱ ከጎኑ አልተወገደም፤ ይሄኔ እየጨሰ ያለው የራሱ አዲስ ፌራሪ መኪና መሆኑን ይጠረጥርና ዳር ይይዛል፤ እየነደደ ያለው በእርግጥም የእርሱ መኪና ነበር።
ስልክ አውጥቶ ለእሳት አደጋ ይደውላል፤ እሳት አደጋ እስኪደርስለት ከ20 ደቂቃ ያላነሰ ጊዜ ፈጅቷል፤ ይህ ሲሆን ምንም ማድረግ ያልቻለው ሆንኮን የገዛው አዲስ ፌራሪ መኪና ሙሉ በሙሉ ሲነድ ቁጭ ብሎ ለመመልከት ተገዷል።
ሆንኮን ከክስተቱ በኋላ በX ገጹ ላይ ባጋራው ጽሑፍ፥ "በጃፓን ውስጥ እንዲህ ዓይነት አስቀያሚ ክስተት የገጠመኝ እኔ ብቻ እንደሆንኩ ይሰማኛል፤ 306 ሺህ ዶላር አውጥቼ ሳልመው የኖርኩትን አዲስ ፌራሪ መኪና ብገዛም ከ1 ሰዓት በኋላ ለማስተዛዘኛ የተረፈኝ ይህ ፎቶ ብቻ ነው" ሲል ከተቃጠለ መኪናው ፎቶ ምስል ጋር አያይዞ አስነብቧል። (EBC መዝናኛ)
@siraranews

መንገድ ለሚዘጉ የሠርግ አጃቢ አሽከርካሪዎች ማስጠንቀቂያ ተላለፈ
በአዲስ አበባ ከተማ በዓላትና ሰርግን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ የሚፈጽሙ መንገድ የሚዘጉ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ።
ሕብረተሰቡ የጸጥታ አካላት የሚያስተላልፉትን የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶች በአግባቡ እየተገበረ መሆኑን ተከትሎ በከተማዋ የወንጀል ድርጊቶች እየቀነሱ መምጣታቸውንም ገልጿል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንዳሉት፣ በከተማዋ የትንሳኤ በዓል በሰላማዊ ሁኔታ ተከብሯል።
ቀላል ከሚባሉ የስርቆትና የማጭበርበር ድርጊቶች ውጪ በዓሉን ተከትሎ ውስብስብና ከባድ የወንጀል ድርጊቶች አለመፈጸማቸውንም አመልክተዋል።
ለዚህ ደግሞ ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በአግባቡ በመተግበሩ መሆኑን በመጥቀስ።
መጪውን የሰርግ ወራት ተከትሎ በከተማዋ የትራፊክ ፍሰት ላይ ያልተገባ የመንገድ መጨናነቅ የሚፈጽሙ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
ከተማዋን በማይመጥን መልኩ መንገድ በሚዘጉና የትራፊክ ፍሰቱን በሚያስተጓጉሉ አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢው የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድም መናገራቸውን ተዘግቧል።