SIRARA
9.54K subscribers
3.68K photos
40 videos
2 files
732 links
ይህ ቻናል ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና የተረጋገጡ እና አዝናኝ የሆኑ መረጃዎች የሚቀርቡበት ነው!
ለማስታወቂያ እና ጥቆማ በዚህ ያናግሩን 👉 https://t.me/mo_anbesa
Download Telegram
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቅቡልነት አሽቆልቁሎ 42 በመቶ ደረሷል ተባለ።

ዘ ኢኮኖሚስት እና ዩጎቭ ያካሄዱት የሕዝብ አስተያየት ጥናት 52 በመቶ ምላሽ ሰጪዎች ለትራምፕ የእስካሁን አፈጻጸም አሉታዊ አመለካከት እንዳላቸው አሳይቷል።

በተመሳሳይ በሕዝብ አስተያየቱ መሠረት በጥናቱ የተሳተፉ 35 በመቶ ሴቶች ትራምፕን ሲቃወሙ፤ 49 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች ፕሬዝዳንቱን ይደግፋሉ።

ከሚያዚያ 5 እስከ 7 በተደረገው ጥናት 1 ሺህ 512 ሰዎች ተሳትፈዋል።

ዎል ስትሪት ጆርናል በቅርቡ አካሂዶት በነበረው የሕዝብ አስተያየት መስጫ የትራምፕ ቅቡልነት 46 በመቶ እንደነበር ገልጿል።
Via adissneger
ይህ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአይሁድ ካህናት የሴራ ምክር ሞት እንዲሰቀል ሲደረግ የተከነቸረበት ሚስማር ሲሆን በጣሊያን ሮም ሙዚየም ውስጥ በዚህ መልኩ ተቀምጦ ይገኛል።
እለተ ቅዳሜ የተሻረች ሰንበት
ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሰ ምድር አርፎ የዋለባት ሰዓት
የትንሳኤ ..ዋዜማ*
ፕሬዚዳንት ፑቲን የፋሲካ በዓልን አስመልክተው የተኩስ አቁም አወጁ!

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ከዩክሬን ጋር ባለው ጦርነት መጪውን የትንሣኤ በዓል አስመልክተው ተኩስ አቁም አወጁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ቅዳሜ ከሌሊቱ 6 ሰዓት ላይ የሚጀምረውን እና እስከ እሁድ እኩለ ሌሊት የሚዘልቅ የተናጠል ተኩስ አቁም ማወጃቸውን ነው የክሬምሊን ምንጮች የገለጹት።

ሩሲያ ባወጀችው የተኩስ አቁም የትንሳኤ በዓል እስኪያልፍ ሁሉንም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እንደምታቆም ተነግሯል፡፡
ቴዲ አፍሮ የፋሲካን በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

ተወዳጁ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የ2017 ዓ.ም የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በጽሑፍ መልዕክቱን አስተላልፏል። ቴዲ አፍሮ በመልዕክቱ "በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ" ብሏል።

"ፍቅር ያሸንፋል!" የሚለውን ታዋቂ መሪ ቃሉን በመልዕክቱ ያካተተው አርቲስቱ፣ በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ምኞቱን ገልጿል። "መልካም በዓል! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!" ሲልም መልዕክቱን አጋርቷል።

#ቴዲአፍሮ  #ፍቅርያሸንፋል
🤩🤩 ሲራራ ሚዲያ 🤩🤩

🎉እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ🎉
      🙏መልካም በዓል ይሁንላችሁ🙏
አስገራሚ ዜና

ይህ ዜና የሚለው ኔዘርላንድ ወስጥ በ1987 የባዮሎጂ የመውጫ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎች በድጋሜ እንዲፈተኑ ሊጠሩ ነው ነው። የተሰጠው ምክንያት ደግሞ የባዮሎጂ ፈተና መሰረቁ ተረጋግጧል  የሚል ነው።  ይህ እንግዲህ የተረጋገጠው ከ38 ዓመት በኋላ ነው።  የያኔዎቹ ተማሪዎች ዛሬ እድሜያቸው 55 ደርሷል ።

ባለስልጣኑ ለሁሉም ጥሪ እንደሚደረግና ፈተናውን በድጋሜ እንደሚወስዱ ገልፀው ፣ ካልወሰዱ ግን ዲፕሎማቸው ሙሉ እንደማይሆን አስጠንቀቀዋል ።

ከ38 ዓመት በኋላ በድጋሜ ተፈተኑ ብትባሉ ምን ትላላችሁ?
ፋሲል
ቢቀርስ?? ይሄ ሁሉ ሰው በዚች ስጦታ ላይ ክሬዲት ለመውሰድ መረባረብ . . . ወይ ሀገሬ?
አርቲስት ገነት ንጋቱ እና አርቲስት ሙሉጌታ ጀዋሬ ድጋሚ ተጋብተዋል

ከአስራ አራት ዓመት መለያየት በኋላ አርቲስት ገነት ንጋቱና አርቲስት ሙሉጌታ ጀዋሬ በትንሳኤው በዓል ቀን ድጋሚ ተጋብተዋል። ሰርጉ በልጆቻቸው፣ በጓደኞቻቸው እና በዘመድ አዝማዶቻቸው ፊት ተከናውኗል።

ሁለቱም ጥንዶች በሀሴት ስሜት እንባቸውን እያፈሰሱ ደስታቸውን ገልጸዋል። "ሁሉን ነገር ለፈጣሪ አሳልፈን ስጥተን ጋብቻችንን ድጋሚ ለመጀመር ወስነናል" በማለት መልካም ምኞትን እንድናደርግላቸው ጠይቀዋል። ብዙ ኢትዮጵያውያን ይህን አንድነት ለረጅም ጊዜ ሲናፍቁ የነበረ ሲሆን አሁን ይህ ፍላጎታቸው እውን ሆኗል።

መልካም ጋብቻ ይሁንላቸው፣ የተባረከ የትዳር ዘመን ይኑራቸው
እኛኮ አኗኗሪ ከሆንን ቆይተናል፣ ማመን ነው እንጂ ያቃተን🙈🙉🙊

👉 600,000 ብር ደመውዝተኛዋ ስራ አስፈፃሚ😎😎

የውሎ አበል፣ የወንበር፣ የትራንስፖርት፣ የቤት ኪራይ ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን ሳይጨምር የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ወርሃዊ ደመውዝ 600,000 ብር መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን??

🔻ማስተርስ ዲግሪ ያላችሁ ወርሃዊ ደሚዛችሁ ስንት ነው?
🔻 የዶክትሬት ዲግሪ ባለቤት ሆናችሁ እድሜያችሁን በምርምርና ጥናት የገፋችሁትስ??
ድንገተኛ ሞት

ሁሉም ዜሮ ዜሮ በሚለው ዘፈኑ የሚታወቀው አርቲስት ሰለሞን በዛሬው እለት ህይወቱ ማለፉን የመረጃ ምንጮቼ ተወደ አሜሪካ ገልፀውልኛል። ኑሮውን በሃገረ አሜሪካ  በአትላንታ ከተማ አድርጐ የነበረው ሰለሞን የፋሲካ በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር ካሳለፈ በኋላ አመሻሽ ላይ ትንሸ ህመም ተሰማችኝ ብሎ ወደ ሆስፒታል እንደሄደና በዛው ህይወቱ እንዳለፈ ምንጮቼ ገልፀውልኛል። ለአድናቂዎቹና ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን።(ayuzehabesha)
የቡርኪናፋሶ ሽግግር ፕሬዝዳንት ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ በሀገራቸው የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ እና ሌሎች የግብረ-ሰዶማዊነት ድርጊቶችን በይፋ አግደዋል። "ከአሁን በኋላ፣ በሀገራችን ይህንን ማድረግ ከባድ ቅጣት ያስከትላል" ብለዋል።

ፕሬዝደንቱ ጨምረው እንደተናገሩት "የግብረ-ሰዶማዊነት ድርጊቶች የአፍሪካን ባህል ይቃረናሉ እናም መታገስ አንችልም" ሲሉ ተሰምተዋል።
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት #ፖፕ_ፍራንሲስ በ88 ዓመታቸው ህይታቸው ማለፉ ተሰምቷል።
ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ተገድለው መገኘታቸው ተሰማ‼️

ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት በታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው መገደላቸው ነው የተነገረው።

አቶ ፋራህ አሂጃማ የተባሉት በፑንት ላንድ የኢትዮጵያ ኢንባሲ የስራባልደረባ እና ዲፕሎማት ሲሆኑ፣ ቅዳሜ ሚያዝያ 11/2017 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ተወስደው ተገድለው አስፖልት ላይ ተጥለው ተገኝተልዋል ተብሏል። እስካሁን በኤምባሲው በኩል የተሰጠ መረጃ የለም።
#ፍርፍሪና በባድመ ተዘፈነ‼️

እውቋና በበዙ ኢትዮጵያውያን ጭምር ተወዳጅነት ያተረፈችው ኤርትራዊቷ ድምፃዊት #ሄለን_መለስ በባድመ ለሚገኙ የኤርትራ ሠራዊት አባላት የሙዚቃ ሥራዎቿን ማቅረቧ ተሰማ።

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews
ከሸፈ‼️
በ#ቡርኪናፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ላይ ያነጣጠር ግድያ/Assassination/ ከሸፈ‼️

የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው በርካታ ወታደራዊ አባላትን ያሳተፈ እንደነበር የሀገሪቱ የደህንነት ሚኒስትር ማሃማዱ ሳና አስታውቀዋል።

የሀገሪቱ የደህንነት አገልግሎት ተቋማት የሴራው አካል በሆኑ የቡርኪናቢ ወታደሮች እና የታጣቂ ቡድን መሪዎች መካከል የነበረውን ግንኙነት በመጥለፍ የሚገኙበትን ቦታ እና የወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ዝርዝር ሁኔታ እንዳገኙ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ላይ የተሴረው መፈንቅለ መንግሥት በመጀመሪያ ሚያዝያ 8 ቀን ለማካሄድ ታቅዶ እንደነበር ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የውጪ ዜጎችን ጨምሮ ዘጠዥ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከዚህ ጀርባ የፈረንሳይ እጅ እንዳለበት ተዘግቧል። (Ethio FM)

#sirara  #SHARE  #JOIN
==/  ቤተሰባችን ይቀላቀሉ \==
https://t.me/siraranews
https://t.me/siraranews