😢ባለፉት 9 ወራት 538 የሳይበር ጥቃቶች መድረሳቸዉን ኤጀንሲዉ ገለጸ።በኢትዮጵያ በ2012 በጀት ዓመት 9 ወራት ውስጥ 538 #የሳይበር ጥቃቶች መድረሳቸዉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ገልጿል፡፡ኤጀንሲው ከተፈጸሙት #የሳይበር ጥቃቶች 263ቱ በአጥፊ ሶፍትዌሮች (ማልዌር) የተፈጸሙ ጥቃቶች ሲሆኑ፣ 106 ወዳልተፈቀደ ሲስተም ሰርጎ መግባት ፣ 105 የድረ-ገፅ ጥቃቶች፣ 54 የመሰረተ-ልማት ቅኝት ፣ 9 የሳይበር መሠረተ ልማቶችን ሥራ ማቋረጥ እንዲሁም 1 በሳይበር ማጭበርበር መሆኑን ገልጿል፡፡
በሃገሪቱ ባለፉት 9 ወራት ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ #የሳይበር ጥቃት 48.9 በመቶዉ ወይም 263 የሚሆኑት አጥፊ ሶፍትዌሮችን (ማልዌር) በመጠቀም የተፈጸሙ መሆኑን የኤጀንሲው የሳይበር ጥቃት አደጋ ዝግጁነት እና ምላሽ መስጫ ዲቪዥን /ኢትዮ-ሰርት/ አስታውቋል፡፡ቁጥራቸው 106 የሚሆኑት ጥቃቶች ደግሞ ወዳልተፈቀደ ሲስተም ስርጎ በመግባት የተፈጸሙ ሲሆን ይህም ከአጠቃላይ ጥቃቶች 19.7 ከመቶ መሆኑን የገለጸዉ ኢትዮ-ሰርት በድረ-ገጽ ላይ የተከሰተው ጥቃት ደግሞ 105 ወይም 19.5 ከመቶ በመያዝ ከማልዌር ጥቃት በመቀጠል ከፍተኛዉን ድርሻ ይዘዋል፡፡በተለየ ሁኔታ ባለፈው 9 ወራት ውስጥ በከፍተኛ መጠን የተከሰተው የሳይበር ጥቃት በማልዌሮች የተፈጸሙ ጥቃቶች መሆናቸዉን የጠቆመዉ ኢትዮ-ሰርት እነዚህ የማልዌር ጥቃቶች በተለያዩ መንገዶች የሚፈጸሙ መሆናቸዉን አውስቷል፡፡ከማልዌር ጥቃቶች ዉስጥም በ (አጋች ማልዌር) አማካኝነት የሚፈጸሙ ሲሆኑ የመረጃ መንታፊዎች የተለያዩ ፋይሎችን በመቆጣጠር መረጃዉን ካገቱበት አካል ጋር ፍላጎታቸውን ለድርድር በማቅረብ ገንዘብ የሚጠይቁበት የሳይበር ጥቃት አይነት ነዉ፡፡ሌላዉ የማልዌር ጥቃት ውስጥ (ክሪፒቶ ከረንሲ ማይነር) የሚል ስያሜ የተሰጠውና ከጀርባ ሆኖ ባለቤቱ ሳያውቅ የሲስተሙን ሪሶርስ በህገ-ወጥ መንገድየሚመዘብርበት ነዉ፡፡ከዚህ ባለፈ የመረጃ መዝባሪዎች ጥቃት ለማድረስ Bot malware (ቦት ማልዌር) የሚባለዉን እና የሳይበር አጥቂዎች ተጠቃሚው የሚሰራበትን አንድ ኮምፒውተር በመቆጣጠር በበይነ-መረብ የተገናኙትን ሌሎች ኮምፒውተሮችን ለማጥቃት የሚጠቀሙበት ዘዴ ነዉ፡ከቀደሙት ሁለት ሩብ ዓመት አንጸር በሶስተኛዉ ሩብ ዓመት የሳይበር ጥቃቱ ጭማሪ ማሳየቱን የኤጀንሲው የሳይበር ጥቃት አደጋ ዝግጁነት እና ምላሽ መስጫ ዲቪዥን /ኢትዮ-ሰርት/ አስታውቋል፡፡በዚህም በ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያዉ ሩብ ዓመት የደረሰዉ የሳይበር ጥቃት 113 ሲሆን በሁለተኛዉ ሩብ ዓመት ደግሞ 172 እንዲሁም በሶስተኛዉ ሩብ ዓመት ቁጥሩ 253 መድረሱን ዲቪዥኑ ገልጿል፡፡
በያዝነዉ 2012 በጀት ዓመት ከሁለተኛዉ ሩብ ዓመት አንጻር በ3ኛዉ ሩብ ዓመት የጥቃት መጠኑ 68 በመቶ ከፍ ማለቱን ኢትዮ ሰርት ጠቁሟል፡፡
ህብረተሰቡም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመጣዉ እና በግለሰብም ሆነ በተቋም ደረጃ ሊከሰቱ ከሚችል የሳይበር ጥቃት ተጋላጭ እንዳይሆን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አሳስቧል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሃገሪቱን የኢንፎርሜሽን እና የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ልማቶችን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችል አቅም በመገንባት ብሄራዊ ጥቅሞችን በማስጠበቅ ተልዕኮውን እየተወጣ ያለ ተቋም መሆኑ ተገልጿል፡፡
INSA
⚠️ባለፉት 9 ወራት 538 የሳይበር ጥቃቶች መድረሳቸዉን ኤጀንሲዉ ገለጸ።
በኢትዮጵያ በ2012 በጀት ዓመት 9 ወራት ውስጥ 538 #የሳይበር ጥቃቶች መድረሳቸዉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ገልጿል፡፡
➡️ኤጀንሲው ከተፈጸሙት #የሳይበር ጥቃቶች 263ቱ በአጥፊ ሶፍትዌሮች (ማልዌር) የተፈጸሙ ጥቃቶች ሲሆኑ፣ 106 ወዳልተፈቀደ ሲስተም ሰርጎ መግባት ፣ 105 የድረ-ገፅ ጥቃቶች፣ 54 የመሰረተ-ልማት ቅኝት ፣ 9 የሳይበር መሠረተ ልማቶችን ሥራ ማቋረጥ እንዲሁም 1 በሳይበር ማጭበርበር መሆኑን ገልጿል፡፡
➡️በሃገሪቱ ባለፉት 9 ወራት ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ #የሳይበር ጥቃት 48.9 በመቶዉ ወይም 263 የሚሆኑት አጥፊ ሶፍትዌሮችን (ማልዌር) በመጠቀም የተፈጸሙ መሆኑን የኤጀንሲው የሳይበር ጥቃት አደጋ ዝግጁነት እና ምላሽ መስጫ ዲቪዥን /ኢትዮ-ሰርት/ አስታውቋል፡፡
ቁጥራቸው 106 የሚሆኑት ጥቃቶች ደግሞ ወዳልተፈቀደ ሲስተም ስርጎ በመግባት የተፈጸሙ ሲሆን ይህም ከአጠቃላይ ጥቃቶች 19.7 ከመቶ መሆኑን የገለጸዉ ኢትዮ-ሰርት በድረ-ገጽ ላይ የተከሰተው ጥቃት ደግሞ 105 ወይም 19.5 ከመቶ በመያዝ ከማልዌር ጥቃት በመቀጠል ከፍተኛዉን ድርሻ ይዘዋል፡፡
በተለየ ሁኔታ ባለፈው 9 ወራት ውስጥ በከፍተኛ መጠን የተከሰተው የሳይበር ጥቃት በማልዌሮች የተፈጸሙ ጥቃቶች መሆናቸዉን የጠቆመዉ ኢትዮ-ሰርት እነዚህ የማልዌር ጥቃቶች በተለያዩ መንገዶች የሚፈጸሙ መሆናቸዉን አውስቷል፡፡
➡️ከማልዌር ጥቃቶች ዉስጥም በ #Ransomeware (አጋች ማልዌር) አማካኝነት የሚፈጸሙ ሲሆኑ የመረጃ መንታፊዎች የተለያዩ ፋይሎችን በመቆጣጠር መረጃዉን ካገቱበት አካል ጋር ፍላጎታቸውን ለድርድር በማቅረብ ገንዘብ የሚጠይቁበት የሳይበር ጥቃት አይነት ነዉ፡፡
ሌላዉ የማልዌር ጥቃት ውስጥ #cryptocurrency_miner (ክሪፒቶ ከረንሲ ማይነር) የሚል ስያሜ የተሰጠውና ከጀርባ ሆኖ ባለቤቱ ሳያውቅ የሲስተሙን ሪሶርስ በህገ-ወጥ መንገድ የሚመዘብርበት ነዉ፡፡
ከዚህ ባለፈ የመረጃ መዝባሪዎች ጥቃት ለማድረስ Bot malware (ቦት ማልዌር) የሚባለዉን እና የሳይበር አጥቂዎች ተጠቃሚው የሚሰራበትን አንድ ኮምፒውተር በመቆጣጠር በበይነ-መረብ የተገናኙትን ሌሎች ኮምፒውተሮችን💻 ለማጥቃት የሚጠቀሙበት ዘዴ ነዉ፡፡
ከቀደሙት ሁለት ሩብ ዓመት አንጸር በሶስተኛዉ ሩብ ዓመት የሳይበር ጥቃቱ ጭማሪ ማሳየቱን የኤጀንሲው የሳይበር ጥቃት አደጋ ዝግጁነት እና ምላሽ መስጫ ዲቪዥን /ኢትዮ-ሰርት/ አስታውቋል፡፡
➡️በዚህም በ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያዉ ሩብ ዓመት የደረሰዉ የሳይበር ጥቃት 113 ሲሆን በሁለተኛዉ ሩብ ዓመት ደግሞ 172 እንዲሁም በሶስተኛዉ ሩብ ዓመት ቁጥሩ 253 መድረሱን ዲቪዥኑ ገልጿል፡፡

➡️የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሃገሪቱን የኢንፎርሜሽን እና የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ልማቶችን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችል አቅም በመገንባት ብሄራዊ ጥቅሞችን በማስጠበቅ ተልዕኮውን እየተወጣ ያለ ተቋም መሆኑ ተገልጿል፡፡
#INSA
@daily_tech2