ᔑᏆᖇᗩᒍ ቴክ
693 subscribers
412 photos
435 videos
353 files
520 links
ቴክኖሎጂ በፈረው አለምን ለማወቅ ወደኛ እንደ መጡ እርግጠኛ ነን።

እኛን ይቀላቀሉ እና ስለ ቴክኖሎጂ አዳዲስ ዘዴዎችን እና ምክሮችን ይማሩ።
ከሁሉም የቴክኖሎጂ ዜናዎች በዓለም ዙሪያ ያግኙ ፡፡ በቴሌግራም

http://t.me/share/url?url=t.me/daily_tech2
🔶 @yourtech_bot
🔶 @techgroup9
Via siraj
Download Telegram
💥pc_software_websites

💥ምርጥ 10 የኮምፒዉተር #ሶፍትዌር ማዉረጃ ሳይቶች

#1. Download.com

የኮምፒዉተር ሶፍትዌሮችን ከማዉረጃ ሳይቶች ቀደምት ሲሆን ከዛሬ 14 ዓመት በፊት የተመሰረተ ነዉ፡፡ የዚህ ሳይት ባለቤት በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ ገናና ስም ያለዉ CNet ነዉ፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን እንዲሁም የሞባይል አፕሊኬሽኖችን እዚህ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከ 100,000 በላይ ፕሮዳከቶችን አካቷል፡፡ ሶፍትዌሮቹ በ ኤዲተሮች ተገምግመዉ እና ደረጃ ተሰጥቷቸዉ ተቀምጠዋል፡፡ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ግምገማዎችን መፃፍ እና ለ ሶፍትዌሮቹ ደረጃ መስጠት ይችላሉ፡፡


#2.FileHippo.com

ይህ ሳይት በብዙ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈ ነዉ፡፡ FileHippo Update Checker የሚል ፕሮግራም ያካተተ ሲሆን ይህም በኮምፒዉተራችን ላይ የጫንናቸዉን ሶፍትዌሮች scan በማድረግ አዲስ የተሻሻለ ምርት ካላቸዉ ይጠቁመናል፡፡ ይህም ኮምፒዉተርን ከሚያጠቁ ቫይረሶች ለመከላከል እጅጉን ይጠቅመናል፡፡

#3. ZDNet Download.com

ይህ ሳይትም እንደሌሎቹ ብዙ የ ሶፍትዌር አማራጮችን የያዘ እና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈ ሳይት ነዉ፡፡

#4. Softpedia.com

Softpedia የሮማኒያ ዌብሳይት ሲሆን ሶፍትዌሮችን ዳዉንሎድ ማድረግ እና ስለ ሶፍትዌሮቹ ማብራሪያ መረጃዎችን ማግኘት ያስችለናል፡፡ ከ ሶፍትዌሮቹም በተጨማሪ የ ቴክኖሎጂ፣ ጤና፣ ሳይንስ እና መዝናኛ ዜናዎችን ያገኙበታል፡፡ ሶፍትዌሮችን በ ካታጎሪ ተቀምጠዉ ማግኘት ስለምንችል ስራችንን ያቀልልናል፡፡ ተጠቃሚዎችም በሚፈልጉት መስፈርት መፈለግ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በተሻሻሉበት ቀን፣ በተጠቃሚ ብዛት፣ ሬቲንግ እና በመሳሰሉት፡፡

#5. Tucows.com

ስሙ ምህጻረ ቃል ሲሆን ይህም The Ultimate Collection Of Winsock Software ማለት ነዉ፡፡ ለ Windows, Linux እንዲሁም ለድሮዎቹ የ Windows ቨርዢኖች የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡


#6. FreewareFiles.com

ነፃ የሆኑ ሶፍትዌሮችን በብዛት የምናገኝበት ሳይት ሲሆን ከ 15,800 በላይ ነፃ ሶፍትዌሮችን አካቷል፡፡ እነዚህን ሶፍትዌሮችንም በ ካታጎሪ ስለተቀመጡ በቀላሉ ማግኘት እንችላለን፡፡

#7. MajorGeeks.com

ይህ ሳይት በፊት TweakFiles በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ አብዛኞቹ ፋይሎች አሪፍ ኢንተርፌስ ያላቸዉ እና ለተጠቃሚዎች በቀላሉ የተገለፁ ናቸዉ፡፡ ፋይሎቹ ዌብሳይቱ ላይ ከመለጠፉ በፊት ጥራታቸዉ ይረጋገጣል ይህም ብዙዎችን ከሚያሰለቸዉ የዉሸት ሶፍትዎሮች እንዲሁም ቫይረሶች ይጠብቅዎታል፡፡ በተጨማሪም አሪፍ ዩሰር ኮሚዩኒቲ ያለዉ ሲሆን ስለ ኮምፒዉተር ያሉንን ጥያቄዎች ይመልሱልናል፡፡

#8. FileCluster.com

FileCluster አሁን ላይ ከተመሰረቱ አዳዲስ ዌብሳይቶች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡ ተጠቃሚዎቹም አዲስ እና የተሻሻሉ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡ የ WordPress Themes፣ ዜናዎችን እና ሶፍትዌር ካምፓኒዎችንም ማግኘት ይችላሉ፡፡


#9. Soft32.com

በ 2003 የተመሰረተ ሲሆን የ ሶፍትዌር ዳይሬክተሪዉን ቶሎ ቶሎ update በማድረግ ይታወቃል፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux እንዲሁም ለ ሞባይል የሚሆኑ ሶፍትዌሮች ሲኖሩት ለ iPhone ተጠቃሚዎች ብቻ ራሱን የቻለ ክፍል አዘጋጅቷል፡፡ ከ 85,000 በላይ ሶፍትዌሮች ሲይዝ ጥያቄዎቻችንን መጠየቅ የምንችልበት ፎረምም አለዉ፡፡

#10. FileHorse.com

እንደ ሌሎቹ ሳይቶች በቁጥር ብዙ ሶፍትዌሮችን ያካተተ ባይሆንም በጣም ታወቂ እና ጥራት ያላቸዉን ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡ የምናወርዳቸዉ ፋይሎችም ቫይረስ እንደሌለዉ የሚያረጋግጥ ሲስተም አካቷል፡፡ ነጻ ሶፍትዌሮችን ስለያዘ በክፍያ የሚገኙ ሶፍትዌሮችንም አማራጭ ነጻ ሶፍትዌር ልናገኝበት እንችላለን፡፡