✝ ገድለ ቅድስት ማርያም ግብጻዊት
[ ምዕራፍ ፭]
......ቅዱስ መስቀሉን ካየሁ በኋላ ወዲያውኑ ዓለምንና ደስታዋን በሙሉ እንደምክድና እርሱ ወደሚመራኝ ለመሄድ ቃል ገባሁ ። ከጸለይኩ በኋላ የመተማመን መንፈስ ተሰማኝ ። ከቆምኩበትና ከጸለይኩበት ቦታ ተነሥቼ ከሚሄደው ተሳላሚ ጋር ተቀላቀልኩ ። ከዚያም በፊት አልደርስበት ካልኩበት ቦታ መድረስ ቻልኩ ። ያለ ችግር ገብቼ ከተቀደሰው ቦታ ደረስኩ ፤ መሬት ላይ ወድቄ ቅዱስ መስቀሉን በመንቀጥቀጥ በዕንባ ሳምኩት ። የእግዚአብሔርን ምሥጢርና ንስሐን እንዴት እንደምቀበል አየሁ ። የቆምኩበት መሬትንም ሳምኩት ። እስከ እኩለ ቀን ድረስ ራሴን ረሳሁ ።
ከዚያም ከቤተ ክርስቲያኑ ወጥቼ ቃል ከገባሁት ከዚያች #የእመቤታችን_ሥዕል_ሥር_ሆኜ " #የኃጥአንን_ንስሐ_በአንቺ_አማላጅነት_የሚቀበል_እግዚአብሔር_የተመሰገነ_ይሁን ። የከበርሽ እመቤቴ ሆይ ኃጥእት እኔ ሌላ ምን ማለት እችላለሁ ? አሁን የገባሁትን ቃል እፈጽም ዘንድ ጊዜው ነው ፤ እጄን ይዘሽ በንስሐ መንገድ ምሪኝ " አልኩ ። ያን ጊዜ " #ዮርዳኖስን_ብትሻገሪ_ታላቅ_ዕረፍት_ታገኛለሽ " የሚል ድምጽ ሰማሁ ። ይህን ሰምቼ እመቤቴ ሆይ አትተይኝ ብዬ አለቀስኩ ። ከዚያ በኋላ ቶሎ ቶሎ እያልኩ ተጓዝኩ ። ከቤተ ክርስቲያን ስወጣ ከተጓዦች አንዱ " እህቴ ሆይ እነዚህን እንኪ " ብሎ ሦስት ሳንቲሞች ሰጠኝ ። ከነዚያ ሳንቲሞችም ትንሽ ዳቦ ለመንገዴ ገዛሁ ። እያለቀስኩ የከተማውን በር አለፍኩ ። በማታም ከዮሐንስ መጥምቅ ቤተ ክርስቲያን ደርሼ ሌሊቱን ሁሉ በዚያ እያለቀስኩ አደርኩ ። በጠዋት ካስቀደስኩ በኋላ ትንሽ ጀልባ አገኘሁና በእርሱ ዮርዳኖስን ተሻገርኩ ። ወደ ፈቀደችው ትመራኝ ዘንድ እንደገና ወደ #እመቤታችን_ጸለይኩ ። ከዚያም ወደዚህ በረሃ ደረስኩ ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከሰው ሆነ ከማንኛውም ነገር ሁሉ ተለይቼ #ወደ_እርሱ_የሚመለሱትን_ከሚቀበል_ከፈጣሪዬ_ጋር_እኖራለሁ ።
ቅዱስ ዞሲማስም " እመቤቴ ሆይ በዚህ በረሃ መኖር ከጀመርሽ ስንት ዓመት ሆነሽ ? " አላት ። እርሷም " ከኢየሩሳሌም ወጥቼ ወደዚህ በረሃ ከመጣሁ #ዐርባ_ሰባት_ ዓመት የሆነኝ ይመስለኛል " አለችው ። ከዚያም " በሕይወትሽ ከሆነው ለውጥ የተነሣ ይህን ሁሉ ዓመት ያለ መከራ ኖረሻልን ? " አላት ። " አባት ዞሲማስ ሆይ ልናገረው ስለምፈራው ነገር ጠየቅኸኝ በፈጣሪዬ ቸርነት ያለፍኩትን ፈተናና መከራ ባስታውሰው እንደገና የሚመጣብኝና የሚያሸንፈኝ እየመሰለኝ እፈራለሁና አለችው ።
እርሱም የተቀደሽ እመቤቴ ሆይ ምንም አትደብቂኝ አላት " አባት ዞሲማስ ሆይ ዐሥራ ሰባት ዓመት በዚህ በረሃ ከአራዊት ፤ ከክፉ ምኞትና ከክፉ ኅሊና ጋር ስታገል ኖርኩ ። በመጀመርያ በዚህ በረሃ ሕይወት በጣም ከባድ ነበር ። ያለፈ ሕይወቴንና ያሳለፍኩትን ደስታ በማሰብ እፈተን ነበር ። በዚህ በምድረ በዳ በረሃ ውስጥ የሚጠጣ የውኃ ጠብታ እንኳን ለማግኝት አስቸጋሪ ነበር ። ከረሃብና ከውሃ ጥም እንዲሁም ከፀሐይ ሐሩር የተነሣ በጣም ተሰቃይቻለሁ ። ብዙ ጊዜ እታመምና ለሞት የተቃረብኩ እሆን ነበር ። ያለፈ ሕይወቴ ትዝታ ደጋግሞ ባሰቃየኝ ጊዜ ደረቴን እየደቃሁ ወደ በረሃው ስገባ የገባሁትን ቃል ለራሴ አስታውሰው ነበር ። ጌታዬም እንዲረዳኝ እለምነው ነበር ። #ኅሊናዬንም መጀመርያ ወደ ተቀበለችኝ የእመቤታችን ሥዕል በማቅናት ትረዳኝ ዘንድ ወደ እርሷ አለቅስ ነበር ።
ነፍሴን የሚያንገላቷትን ክፉ አሳቦች እንድታስወግድልኝ እማጸናት ነበር ። ብዙ ካለቀስኩና ደረቴን ከደቃሁ በኋላ ከሁሉም አቅጣጫ በእኔ ላይ የሚያበራ የሚመስል ብርሃን እመለከት ነበር ። ከአስጨናቂው ማዕበል በኋላ ዘላቂ የሆነ ሰላም ይሰፍን ነበር ።
እያስጨነቁኝ የነበሩትን ነገሮች እንዴት ልገልጽልህ እችላለሁ ? ይፈትነኝ ስለነበረው የዝሙት አሳብስ እንዴት አድርጌ ላስረዳህ እችላለሁ ? እንዲህ ፈተናው አብዝቶ ሲያስጨንቀኝ በሠራሁት ኃጢአቴ ምሥክር ሆኖ እንደሚያስፈርድብኝና ስለ ወንጀሌ ቅጣትን የሚያስፈራራኝ ሆኖ በፊቴ እንዳየሁ ሆኜ ፤ መሬት ላይ ወድቄ እያለቀስኩ በዕንባ እታጠብ ነበር ። የሚያረጋጋና ደስ የሚል ብርሃን መጥቶ እስኪያበረታታኝና የሚያስጨንቁኝን አሳቦች ሁሉ እስኪያባርራቸው ድረስ ከመሬት አልነሳም ነበር ። አንዳንዴም አንድ ቀንና አንድ ሌሊት ሙሉ መሬት ላይ እንደ ወደቅሁ እቆያለሁ ። ሁል ጊዜ የኀሊናዬን አይኖች ወደምትጠብቀኝ ወደ #እመቤታችን በመመለስ በበረሃው ሞገድ ውስጥ እየተጨነቀች ላለችው ፍጥረት እጇን ትዘረጋ ዘንድ እለምናት ነበር ። እርሷም ሁል ጊዜ ትረዳኝና ትቀበለኝ ነበር ።
#ለአስራ_ሰባት_ዓመታት ያህል እንዲህ ባለ ቋሚ በሆነ መከራና ፈተና ውስጥ ኖርኩ ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዛሬም ድረስ #ወላዲተ_አምላክ በሁሉም ነገር ትረዳኛለች ፤ ልክ እጁን ይዞ እንደሚመራት ትመራኛለች .........።
ይቆየን
በረከቷ ይደርብን በጸሎቷ ይማረን
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት
👉 ኢዮአታም
ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን
❖ ነሐሴ ፲፮ ❖
➫ እንኩዋን ለእመቤታችን
#ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ የትንሳኤና የዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
➫ #ዕርገተ_ድንግል_ማርያም
➫ ይሕች ዕለት እጅጉን ታላቅና ክብርት ናት:: ምክንያቱም
የድንግል ማርያም ሥጋዋ ተነስቶ ዐርጐባታልና:: ድንግል
እመቤታችን ተነሳች: ዐረገች ስንል እንደ እንግዳ ደርሶ:
እንደ ውሃ ፈሶ: ወይም በአጋጣሚ የተደረገ አይደለም::
ጥንቱን በአምላክ ልቡና ታስቦ: ሁዋላም ትንቢት
ተነግሮለት ነው::
➫ ታሪኩ: ነገሩ: ምሥጢሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም
በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር:: ከነገር ሁሉ በፊት
#እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር::
➫ ዓለም ተፈጥሮ: አዳምና ሔዋን ስተው: መርገመ ሥጋና
መርገመ ነፍስ አግኝቷቸው: በኃዘን ንስሃ ቢገቡ
"እትወለድ እም ወለተ ወለትከ - ከ5 ቀን ተኩል (5500
ዘመናት) በሁዋላ ካንተ ባሕርይ ከምትገኝ #ንጽሕት_ዘር
ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ተስፋ ድኅነት ሰጠው::
¤ከአዳም አንስቶ ለ5500 ዓመታት አበው: ነቢያትና
ካህናት ስለ ድንግል ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን
ተናገሩ:: መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት:: ምሳሌም
መሰሉላት:: ከሩቅ ዘመን ሁነውም ሊያገኟት እየተመኙ
እጅ ነሷት::
"እምርሑቅሰ ርእይዋ: ወተአምኅዋ" እንዲል::
➫ የድንግል ማርያም ሐረገ ትውልድ
○ ከአዳም በሴት
○ ከያሬድ በሔኖክ
○ ከኖኅ በሴም
○ከአብርሃም በይስሐቅ
○ ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ
○ ከይሁዳ በእሴይ: በዳዊት: በሰሎሞንና በሕዝቅያስ ወርዳ ከኢያቄም ትደርሳለች::
➫ ከሌዊ ደግሞ #በአሮን: #አልዓዛር: #ፊንሐስ:
#ቴክታና_በጥሪቃ አድርጋ ከሐና ትደርሳለች::
➫ አባታችን #አዳም ከገነት በወጣ በ5,485 ዓመት
#ወላዲተ_አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት
ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ
#ኢያቄም_ወሐና ትወለዳለች:: (ኢሳ. 1:9, መኃ. 4:7)
"ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ::
(#ቅዱስ_ቴዎዶጦስ_ዘዕንቆራ)
➫ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለ3 ዓመታት ቆይታ ወደ
#ቤተ_መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለ12
ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና
እያገለገለች: እርሷን ደግሞ #መላእክተ_ብርሃን
እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ: ጽዋዕ ሰማያዊ
እየመገቧት ኑራለች:: 15 ዓመት በሞላት ጊዜ ጻድቅ
#አረጋዊ_ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት::
➫ በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና
ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማሕጸንዋ ጸነሰችው::
ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር:
ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ::
(#ሊቁ_ቅዱስ_ኤፍሬም #ለብሐዊ)
➫ ወልደ እግዚአብሔርን ለ9 ወራት ከ5 ቀናት ጸንሳ:
እንበለ ተፈትሆ (በድንግልና) ወለደችው:: (ኢሳ. 7:14)
"#ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በናዝሬት ገሊላ ለ2
ዓመታት ቆዩ::
➫ አርዌ ሔሮድስ "እገድላለሁ" ብሎ በተሳበት ወቅትም
ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም: በላበትና በድካም:
በዕንባና በኃዘን ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ከገሊላ እስከ
#ኢትዮዽያ ተሰዳለች:: ልጇ ጌታችን 5 ዓመት ከ6 ወር
ሲሆነው: ለርሷ ለድንግል ደግሞ 21 ዓመት ከ3 ወር
ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ::
➫ በናዝሬትም ለ24 ዓመታት ከ6 ወራት ልጇን ክርስቶስን
እያሳደገች: ነዳያንን እያሰበች ኑራለች::
እርሷ 45 ዓመት: ልጇ 30 ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን
ተጠምቆ በጉባኤ ትምሕርት: ተአምራት ጀመረ:: ለ3
ዓመታት ከ3 ወራትም ከዋለበት እየዋለች: ካደረበትም
እያደረች ትምሕርቱን ሰማች::
➫ የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም
የመጨረሻውን ፍጹም ሐዘን አስተናገደች:: አንጀቷ በኃዘን
ተቃጠለ:: በነፍሷም ሰይፍ አለፈ:: (ሉቃ. 2:35) ጌታ
በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሳኤውን አየች::
ለ40 ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች::
➫ ከልጇ #ዕርገት በሁዋላ #በጽርሐ_ጽዮን ሐዋርያትን
ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች:: በጽርሐ ጽዮን
ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ15 ዓመታት ኖረች::
በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ:
ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል: ሐዋርያትን ስታጽናና:
ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች::
➫ ዕድሜዋ 64 በደረሰ ጊዜ ጥር 21 ቀን #መድኃኒታችን
አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ:: ኢየሩሳሌምን
ጨነቃት:: አካባቢውም በፈውስ ተሞላ:: በዓለም ላይም
በጐ መዓዛ ወረደ:: እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት
ባልተደረገ: ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ:
ክብርና ተአምራት ዐረፈች:: ሞቷ ብዙዎችን አስደንቁአል::
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ:
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ" እንዲል::
➫ ከዚህ በሁዋላ መላእክት እየዘመሩ: ሐዋርያቱም
እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ: በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው
ወሰዱ:: ይሕንን ሊቃውንት:-
"ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ:
እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ:
ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ" ሲሉ ይገልጡታል::
➫ በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ
#ቅዱስ_ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው) እነርሱን ቀጥቶ
እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር
አኑሯታል::
በዚያም #መላእክት እያመሰገኗት ለ205 ቀናት
ቆይታለች::
➫ ቅዱስ_ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን
ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ 1 ሱባኤ
ጀመሩ:: 2ኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል
ማርያምን ➫ንጹሕ_ሥጋ ሰጣቸው:: እየዘመሩም
➫በጌሴማኒ ቀብረዋታል::
¤በ3ኛው ቀን (ነሐሴ 16) እንደ ልጇ ባለ ➫ትንሳኤ
ተነስታ ዐርጋለች:: ትንሳኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ
➫ቅዱስ_ቶማስ አይቶ: መግነዟን ተቀብሏል:: ሐዋርያቱም
መግነዟን ለበረከት ተካፍለው: እንደ ገና በዓመቱ ነሐሴ
1 ቀን ሱባኤ ገቡ::
➫ ለ2 ሳምንታት ቆይተው: በዚህች ቀንም ሁሉንም ወደ
ሰማይ አወጣቸው:: በፍጡር አንደበት ተከናውኖ
የማይነገር ተድላ: ደስታና ምሥጢርንም አዩ:: ጌታ ራሱ
ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የበዓሉን ቃል ኪዳን
ሰምተው: ከድንግል ተባርከው ወደ ➫ደብረ_ዘይት
ተመልሰዋል::
➫ ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን:
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን:
ለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::
➫ ቅዱስ_ጊጋር_ሶርያዊ
➫ ይሕ ቅዱስ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን የሶርያ
መስፍን የነበረ ሲሆን #ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ
ሰምቷል:: እመ ብርሃን ለስደት ስትወጣ በመጀመሪያ
የሔደችው ወደ ➫ ሊባኖስ ተራሮች ነው::
#መስፍኑ_ጊጋር ነበርና እርሱም የአምላክ እናትነቷን
አምኖ አክብሮ አስተናግዷታል::
+ሔሮድስም ይሕንን ሲሰማ ጦር አስከትቶ ወደ ጊጋር
ሔደ:: መስፍኑ ጊጋር ሔሮድስን እንደማይችለው ሲረዳ
ድንግል ማርያምን ወደ #ግብጽ ሸሽጐ አሸሻት::
ሔሮድስንም ፊት ለፊት ተገናኘው:: ከአቅሙ በላይ
ስለነበረም በወታደሮች ተማርኮ ወደ ሔሮድስ ቀረበ::
+እመቤታችንንና ልጇን "አምጣ" ቢለው "አልናገርም"
አለው:: በዚህ ምክንያት አካሉን ከብዙ ቆራርጦ ገድሎታል::
በቤተ ክርስቲያን ታሪክም #ስለ_እመ_አምላክ_ፍቅር
የተሰዋ የመጀመሪያው ሰው ተብሎ ይታወቃል:: ጌታም
ስለ ሃይማኖቱ: ፍቅሩና ሰማዕትነቱ 3 አክሊላትን
ሰጥቶታል::

✝✝††† እንኳን ለዓምደ ሃይማኖት ቅዱስ ቄርሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† ✝✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✝✝†††
††† ✝✝ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ✝✝ †††
††† ቅዱስ ቄርሎስን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን " #ዓምደ_ሃይማኖት- የሃይማኖት ምሰሶ" ይሉታል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ሊቁ የተወለደው በእስክንድርያ (ግብጽ) በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: እናቱ የወቅቱ ፓትርያርክ #ቅዱስ_ቴዎፍሎስ እህቱ ነበረችና አጎቱ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ወስዶ አሳድጐታል:: ገና በልጅነቱ ወደ #አባ_ሰራብዮን ገዳም ገብቶ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል:: በጾም: በጸሎትና በትሕትና የታሸ ነውና ሲማር አንድ ጊዜ ካነበበው በሕሊናው ተስሎ ይቀር ነበር::
ቅዱስ ቴዎፍሎስ "ምዕመናንን አስተምርልኝ" ብሎ ወደ ከተማ አመጣው:: #መንፈስ_ቅዱስ አድሮበታልና ሲያስተምር ወይ ደግሞ መጻሕፍትን ሲያነብ ከምዕመናን ወገን ስንኩዋን የሚያወራና የሚንቀሳቀስ ቀርቶ የሚቀመጥም አልነበረም:: ጣዕመ ስብከቱም ብዙዎችን ለወጠ::
ከዚያም በ412 ዓ/ም አጎቱ የነበረው ፓትርያርክ አባ ቴዎፍሎስ ሲያርፍ ዻዻሳትና ሊቃውንት በአንድነት ቅዱስ ቄርሎስን መረጡ:: የእስክንድርያም 24ኛ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ #ቤተ_ክርስቲያን አበራች:: በቅድስናው: በሊቅነቱ: በስብከቱ: በድርሰቶቹና በትጋቱ በፍጹም አገለገላት::
በወቅቱ ስመ ክፉ መናፍቅ ንስጥሮስ ተነስቶ የእስያ አብያተ ክርስቲያናትን አወካቸው:: ትምሕርቱ ክርስቶስን "2 አካል: ባሕርይ ነው" (ሎቱ ስብሐት!) የሚል ነበር:: በእውነት እንየው ከተባለ ግን ጠቡና ጥላቻው ከድንግል ማርያም ጋር ነበር:: ምክንያቱም ጌታችንን ወደ 2 የከፈለው #እመቤታችንንየአምላክ እናት አይደለሽም ለማለት ነው:: (ላቲ ስብሐት!)
ነገሩን #ቅዱስ_ቄርሎስ በሰማ ጊዜ ወዳለበት ሒዶ ቢመክረውም ንስጥሮስ ሊሰማ አልፈለገም:: በዚህ ምክንያት በትንሹ ቴዎዶስዮስ (የቁስጥንጥንያ ንጉሥ) ትዕዛዝ በኤፌሶን ታላቅ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሆነ:: ይህ ጉባዔ በቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻው የተቀደሰ ጉባዔ ነው:: በ431 ዓ/ም #በኤፌሶን ከተማ የመናፍቃኑን ጥርቅም ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና 200 #ቅዱሳን_ሊቃውንት ተገኙ::
የሚገባው ጸሎትና ሱባዔ ከተፈጸመ በሁዋላ ጉባዔው ተጀመረ:: አፈ ጉባዔው ሊቀ ማሕበር ማር (ቅዱስ) ቄርሎስ ነበርና በጉባዔ ፊት ንስጥሮስን ተከራክሮ ረታው:: ምላሽም አሳጣው:: ከቅዱሳት መጻሕፍት #ክርስቶስ አንድ ባሕርይ መሆኑን: #ድንግል_ማርያምም #ወላዲተ_አምላክ መሆኗን እየጠቀሰ: በምሳሌም እያሳየ አስረዳ::
የሰይጣን ማደሪያ ንስጥሮስ ግን እንቢ: አላምንም በማለቱ ተወግዞ ተለየ:: ቅዱሳን ሊቃውንቱም በቅዱስ ቄርሎስ አርቃቂነት 12 አንቀጾችን አዘጋጅተው ወደ ዓለም ሁሉ ላኩ:: እሊህ አንቀጾች ዛሬም በሊቃውንቱ እጅ አሉ:: ይነበባሉ: ይተረጎማሉ::
††† ከእነዚህም አንዱ ድንግል ማርያም " #ታኦዶኮስ(የእግዚአብሔር እናቱ) ናት" የሚል ነው:: እመቤታችንን:-
¤የአምላክ እናት:
¤ዘላለማዊት ድንግል:
¤ፍጽምት:
¤ንጽሕትና አማላጅ ብሎ ማመን ለሰማያዊ ርስት የሚያበቃ በጐ ሃይማኖት ነውና::
ጉባዔው ከተጠናቀቀ በሁዋላ ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን ጠርቶ "በድንግል ማርያም እመን:: እርሷ ከልጇ ታስታርቅሃለች" ቢለው በድጋሚ "እንቢ" አለው:: ያን ጊዜ ሊቁ "ለአምላክ እናት ያልታዘዘ ምላስህ ላንተም አይታዘዝህ" ብሎ ረገመው:: ወዲያው ምላሱ ተጐልጉሎ ወጥቶ ደረቱ ላይ ወደቀ::
እንደ ውሻ እየተዝረከረከ ሒዶ ከወዳጆቹ ጋር ቁሞ ሳለ መሬት ተከፍታ ውጣዋለች::
ቅዱስ ቄርሎስ ግን ለ32 ዘመናት በመንበሩ ላይ አገልግሎ: ፍሬ ትሩፋት አፍርቶ: ብዙ ድርሰቶችንም ደርሶ በ444 ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፏል:: ከድርሰቶቹም ቅዳሴው: ድርሳነ ቄርሎስና ተረፈ ቄርሎስ ይጠቀሳሉ::
††† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቶቻችን ጸሎት ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን:: ከሊቁም በረከቱን ይክፈለን::
††† ሐምሌ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት)
2.ቅዱስ ክልስቲያኖስ ዘሮሜ (ታላቅ ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት)
3.አባ ሉቅያስ ኤዺስ ቆዾስ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
††† "የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ:: የኑሯቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው:: ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ: እስከ ዘለዓለምም ያው ነው:: ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምሕርት አትወሰዱ:: ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም:: በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና::" †††
(ዕብ. 13:7)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
'
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

✞✞✞ 🌷በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞🌷
❖ ነሐሴ ፲፮ ❖
✞✞✞ እንኩዋን ለእመቤታችን
#ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ የትንሳኤና የዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+"+ #🌷ዕርገተ_ድንግል_ማርያም🌷 +"+
=>ይሕች ዕለት እጅጉን ታላቅና ክብርት ናት:: ምክንያቱም
የድንግል ማርያም ሥጋዋ ተነስቶ ዐርጐባታልና:: ድንግል
እመቤታችን ተነሳች: ዐረገች ስንል እንደ እንግዳ ደርሶ:
እንደ ውሃ ፈሶ: ወይም በአጋጣሚ የተደረገ አይደለም::
ጥንቱን በአምላክ ልቡና ታስቦ: ሁዋላም ትንቢት
ተነግሮለት ነው::
¤ታሪኩ: ነገሩ: ምሥጢሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም
በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር:: ከነገር ሁሉ በፊት
#እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር::
¤ዓለም ተፈጥሮ: አዳምና ሔዋን ስተው: መርገመ ሥጋና
መርገመ ነፍስ አግኝቷቸው: በኃዘን ንስሃ ቢገቡ
"እትወለድ እም ወለተ ወለትከ - ከ5 ቀን ተኩል (5500
ዘመናት) በሁዋላ ካንተ ባሕርይ ከምትገኝ #ንጽሕት_ዘር
ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ተስፋ ድኅነት ሰጠው::
¤ከአዳም አንስቶ ለ5500 ዓመታት አበው: ነቢያትና
ካህናት ስለ ድንግል ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን
ተናገሩ:: መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት:: ምሳሌም
መሰሉላት:: ከሩቅ ዘመን ሁነውም ሊያገኟት እየተመኙ
እጅ ነሷት::
"እምርሑቅሰ ርእይዋ: ወተአምኅዋ" እንዲል::
+"+ የድንግል ማርያም ሐረገ ትውልድ +"+
*ከአዳም በሴት
*ከያሬድ በሔኖክ
*ከኖኅ በሴም
*ከአብርሃም በይስሐቅ
*ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ
*ከይሁዳ በእሴይ: በዳዊት: በሰሎሞንና በሕዝቅያስ
ወርዳ ከኢያቄም ትደርሳለች::
¤ከሌዊ ደግሞ #በአሮን: #አልዓዛር: #ፊንሐስ:
#ቴክታና_በጥሪቃ አድርጋ ከሐና ትደርሳለች::
¤አባታችን #አዳም ከገነት በወጣ በ5,485 ዓመት
#ወላዲተ_አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት
ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ
#ኢያቄም_ወሐና ትወለዳለች:: (ኢሳ. 1:9, መኃ. 4:7)
"ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ::
(#ቅዱስ_ቴዎዶጦስ_ዘዕንቆራ)
¤ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለ3 ዓመታት ቆይታ ወደ
#ቤተ_መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለ12
ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና
እያገለገለች: እርሷን ደግሞ #መላእክተ_ብርሃን
እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ: ጽዋዕ ሰማያዊ
እየመገቧት ኑራለች:: 15 ዓመት በሞላት ጊዜ ጻድቅ
#አረጋዊ_ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት::
¤በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና
ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማሕጸንዋ ጸነሰችው::
ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር:
ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ::
(#ሊቁ_ቅዱስ_ኤፍሬም #ለብሐዊ)
¤ወልደ እግዚአብሔርን ለ9 ወራት ከ5 ቀናት ጸንሳ:
እንበለ ተፈትሆ (በድንግልና) ወለደችው:: (ኢሳ. 7:14)
"#ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በናዝሬት ገሊላ ለ2
ዓመታት ቆዩ::
¤አርዌ ሔሮድስ "እገድላለሁ" ብሎ በተሳበት ወቅትም
ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም: በላበትና በድካም:
በዕንባና በኃዘን ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ከገሊላ እስከ
#ኢትዮዽያ ተሰዳለች:: ልጇ ጌታችን 5 ዓመት ከ6 ወር
ሲሆነው: ለርሷ ለድንግል ደግሞ 21 ዓመት ከ3 ወር
ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ::
¤በናዝሬትም ለ24 ዓመታት ከ6 ወራት ልጇን ክርስቶስን
እያሳደገች: ነዳያንን እያሰበች ኑራለች::
እርሷ 45 ዓመት: ልጇ 30 ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን
ተጠምቆ በጉባኤ ትምሕርት: ተአምራት ጀመረ:: ለ3
ዓመታት ከ3 ወራትም ከዋለበት እየዋለች: ካደረበትም
እያደረች ትምሕርቱን ሰማች::
¤የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም
የመጨረሻውን ፍጹም ሐዘን አስተናገደች:: አንጀቷ በኃዘን
ተቃጠለ:: በነፍሷም ሰይፍ አለፈ:: (ሉቃ. 2:35) ጌታ
በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሳኤውን አየች::
ለ40 ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች::
¤ከልጇ #ዕርገት በሁዋላ #በጽርሐ_ጽዮን ሐዋርያትን
ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች:: በጽርሐ ጽዮን
ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ15 ዓመታት ኖረች::
በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ:
ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል: ሐዋርያትን ስታጽናና:
ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች::
¤ዕድሜዋ 64 በደረሰ ጊዜ ጥር 21 ቀን #መድኃኒታችን
አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ:: ኢየሩሳሌምን
ጨነቃት:: አካባቢውም በፈውስ ተሞላ:: በዓለም ላይም
በጐ መዓዛ ወረደ:: እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት
ባልተደረገ: ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ:
ክብርና ተአምራት ዐረፈች:: ሞቷ ብዙዎችን አስደንቁአል::
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ:
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ" እንዲል::
¤ከዚህ በሁዋላ መላእክት እየዘመሩ: ሐዋርያቱም
እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ: በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው
ወሰዱ:: ይሕንን ሊቃውንት:-
"ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ:
እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ:
ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ" ሲሉ ይገልጡታል::
¤በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ
#ቅዱስ_ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው) እነርሱን ቀጥቶ
እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር
አኑሯታል::
በዚያም #መላእክት እያመሰገኗት ለ205 ቀናት
ቆይታለች::
¤#ቅዱስ_ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን
ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ 1 ሱባኤ
ጀመሩ:: 2ኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል
ማርያምን #ንጹሕ_ሥጋ ሰጣቸው:: እየዘመሩም
#በጌሴማኒ ቀብረዋታል::
¤በ3ኛው ቀን (ነሐሴ 16) እንደ ልጇ ባለ #ትንሳኤ
ተነስታ ዐርጋለች:: ትንሳኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ
#ቅዱስ_ቶማስ አይቶ: መግነዟን ተቀብሏል:: ሐዋርያቱም
መግነዟን ለበረከት ተካፍለው: እንደ ገና በዓመቱ ነሐሴ
1 ቀን ሱባኤ ገቡ::
¤ለ2 ሳምንታት ቆይተው: በዚህች ቀንም ሁሉንም ወደ
ሰማይ አወጣቸው:: በፍጡር አንደበት ተከናውኖ
የማይነገር ተድላ: ደስታና ምሥጢርንም አዩ:: ጌታ ራሱ
ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የበዓሉን ቃል ኪዳን
ሰምተው: ከድንግል ተባርከው ወደ #ደብረ_ዘይት
ተመልሰዋል::
=>ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና #እመቤታችን:
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን:
ለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::
+"+ #🌷ቅዱስ_ጊጋር_ሶርያዊ🌷 +"+
=>ይሕ ቅዱስ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን የሶርያ
መስፍን የነበረ ሲሆን #ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ
ሰምቷል:: እመ ብርሃን ለስደት ስትወጣ በመጀመሪያ
የሔደችው ወደ #ሊባኖስ ተራሮች ነው::

በወቅቱ ስመ ክፉ መናፍቅ ንስጥሮስ ተነስቶ የእስያ አብያተ ክርስቲያናትን አወካቸው:: ትምሕርቱ ክርስቶስን "2 አካል: ባሕርይ ነው" (ሎቱ ስብሐት!) የሚል ነበር:: በእውነት እንየው ከተባለ ግን ጠቡና ጥላቻው ከድንግል ማርያም ጋር ነበር:: ምክንያቱም ጌታችንን ወደ 2 የከፈለው #እመቤታችንን የአምላክ እናት አይደለሽም ለማለት ነው:: (ላቲ ስብሐት!)

#ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ የትንሣኤና የዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+"+ #🌷ዕርገተ_ድንግል_ማርያም🌷 +"+
=>ይሕች ዕለት እጅጉን ታላቅና ክብርት ናት:: ምክንያቱም
የድንግል ማርያም ሥጋዋ ተነስቶ ዐርጐባታልና:: ድንግል
እመቤታችን ተነሳች: ዐረገች ስንል እንደ እንግዳ ደርሶ:
እንደ ውሃ ፈሶ: ወይም በአጋጣሚ የተደረገ አይደለም::
ጥንቱን በአምላክ ልቡና ታስቦ: ሁዋላም ትንቢት
ተነግሮለት ነው::
¤ታሪኩ: ነገሩ: ምሥጢሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም
በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር:: ከነገር ሁሉ በፊት
#እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር::
¤ዓለም ተፈጥሮ: አዳምና ሔዋን ስተው: መርገመ ሥጋና
መርገመ ነፍስ አግኝቷቸው: በኃዘን ንስሃ ቢገቡ
"እትወለድ እም ወለተ ወለትከ - ከ5 ቀን ተኩል (5500
ዘመናት) በሁዋላ ካንተ ባሕርይ ከምትገኝ #ንጽሕት_ዘር
ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ተስፋ ድኅነት ሰጠው::
¤ከአዳም አንስቶ ለ5500 ዓመታት አበው: ነቢያትና
ካህናት ስለ ድንግል ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን
ተናገሩ:: መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት:: ምሳሌም
መሰሉላት:: ከሩቅ ዘመን ሁነውም ሊያገኟት እየተመኙ
እጅ ነሷት::
"እምርሑቅሰ ርእይዋ: ወተአምኅዋ" እንዲል::
+"+ የድንግል ማርያም ሐረገ ትውልድ +"+
*ከአዳም በሴት
*ከያሬድ በሔኖክ
*ከኖኅ በሴም
*ከአብርሃም በይስሐቅ
*ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ
*ከይሁዳ በእሴይ: በዳዊት: በሰሎሞንና በሕዝቅያስ
ወርዳ ከኢያቄም ትደርሳለች::
¤ከሌዊ ደግሞ #በአሮን: #አልዓዛር: #ፊንሐስ:
#ቴክታና_በጥሪቃ አድርጋ ከሐና ትደርሳለች::
¤አባታችን #አዳም ከገነት በወጣ በ5,485 ዓመት
#ወላዲተ_አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት
ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ
#ኢያቄም_ወሐና ትወለዳለች:: (ኢሳ. 1:9, መኃ. 4:7)
"ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ::
(#ቅዱስ_ቴዎዶጦስ_ዘዕንቆራ)
¤ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለ3 ዓመታት ቆይታ ወደ
#ቤተ_መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለ12
ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና
እያገለገለች: እርሷን ደግሞ #መላእክተ_ብርሃን
እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ: ጽዋዕ ሰማያዊ
እየመገቧት ኑራለች:: 15 ዓመት በሞላት ጊዜ ጻድቅ
#አረጋዊ_ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት::
¤በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና
ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማሕጸንዋ ጸነሰችው::
ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር:
ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ::
(#ሊቁ_ቅዱስ_ኤፍሬም #ለብሐዊ)
¤ወልደ እግዚአብሔርን ለ9 ወራት ከ5 ቀናት ጸንሳ:
እንበለ ተፈትሆ (በድንግልና) ወለደችው:: (ኢሳ. 7:14)
"#ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በናዝሬት ገሊላ ለ2
ዓመታት ቆዩ::
¤አርዌ ሔሮድስ "እገድላለሁ" ብሎ በተነሳበት ወቅትም
ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም: በላበትና በድካም:
በዕንባና በኃዘን ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ከገሊላ እስከ
#ኢትዮዽያ ተሰዳለች:: ልጇ ጌታችን 5 ዓመት ከ6 ወር
ሲሆነው: ለርሷ ለድንግል ደግሞ 21 ዓመት ከ3 ወር
ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ::
¤በናዝሬትም ለ24 ዓመታት ከ6 ወራት ልጇን ክርስቶስን
እያሳደገች: ነዳያንን እያሰበች ኑራለች::
እርሷ 45 ዓመት: ልጇ 30 ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን
ተጠምቆ በጉባኤ ትምህርት: ተአምራት ጀመረ:: ለ3 ዓመታት ከ3 ወራትም ከዋለበት እየዋለች: ካደረበትም
እያደረች ትምህርቱን ሰማች::
¤የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም
የመጨረሻውን ፍጹም ሐዘን አስተናገደች:: አንጀቷ በኃዘን
ተቃጠለ:: በነፍሷም ሰይፍ አለፈ:: (ሉቃ. 2:35) ጌታ በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሣኤውን አየች::
ለ40 ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች::
¤ከልጇ #ዕርገት በሁዋላ #በጽርሐ_ጽዮን ሐዋርያትን
ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች:: በጽርሐ ጽዮን
ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ15 ዓመታት ኖረች::
በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ:
ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል: ሐዋርያትን ስታጽናና:
ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች::
¤ዕድሜዋ 64 በደረሰ ጊዜ ጥር 21 ቀን #መድኃኒታችን
አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ:: ኢየሩሳሌምን
ጨነቃት:: አካባቢውም በፈውስ ተሞላ:: በዓለም ላይም
በጐ መዓዛ ወረደ:: እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት
ባልተደረገ: ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ:
ክብርና ተአምራት ዐረፈች:: ሞቷ ብዙዎችን አስደንቁአል::
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ:
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ" እንዲል::
¤ከዚህ በሁዋላ መላእክት እየዘመሩ: ሐዋርያቱም
እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ: በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው
ወሰዱ:: ይሕንን ሊቃውንት:-
"ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ:
እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ:
ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ" ሲሉ ይገልጡታል::
¤በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ
#ቅዱስ_ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው) እነርሱን ቀጥቶ
እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር
አኑሯታል::
በዚያም #መላእክት እያመሰገኗት ለ205 ቀናት
ቆይታለች::
¤#ቅዱስ_ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን
ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ 1 ሱባኤ
ጀመሩ:: 2ኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል
ማርያምን #ንጹሕ_ሥጋ ሰጣቸው:: እየዘመሩም
#በጌሴማኒ ቀብረዋታል::
¤በ3ኛው ቀን (ነሐሴ 16) እንደ ልጇ ባለ #ትንሣኤ
ተነስታ ዐርጋለች:: ትንሣኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ