ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
802 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

👉ደስታችሁን መርምሩ👈

ዛሬ ይህን ቃል ይዘን የቅዱሳን አበውን መጽሐፍት ለእኔና ለእናንተ የራሳችንን ደስታ እንድንመረምር በሚረዳን መልኩ እንቃኛለን።
ውድ ቤተሰቦቻችን በያላችሁበት እናንተም በቃሉ #ደስታችሁን መርምሩ!!!
@zekidanemeheret

መጀመሪያው እግዚአብሔር እኛን የፈጠረው በደስታ እንድንኖር ነው። ይህም ይታወቅ ዘንድ አባታችንን አዳምን በኤደን ገነት በአትክልት ሥፍራ ምቾት ያላቸውን ሀብቶች ሁሉ አቀረበለት። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም አጉልቶ ሲያመለክተን በ1ኛ ቆሮ 2፥9 " ዓይን ያላየውን ጆሮም ያልሰማውን በሰውም ልብ ያልታሰበውን #ደስታ አዘጋጀለት። ከዚህም በላይ ደግሞ ሰውን በሞቱ ከወዳጆቹ ከመላእክት እና ጻድቃን ነፍሳት ጋር ደስታን ወደ ሚያጣጥምበት ወደ ገነት አሸጋግሮታል።
🙏 ደስታና እርካታን እንለይ!!!!!
#እርካታ በአብዛኛው ለሥጋና ለስሜቶች የተገባ ነው። ይህም ይታወቅ ዘንድ ሰው በመብላት እና በመጠጣት ወይም ውብ የሆኑ ትዕይንት በማየት ወይም በመስማት እርካታ ሊሰማው ይችላል። #እውነተኛ ደስታ ግን ለመንፈስ የተገባ ነው።
👉 ፥- #ሐሰተኛ ደስታ(በራስ ላይ የሚሰራ ኃጥያት)
በጠላት ውድቀት ወይም በእርሱ ላይ በደረሰበት ማንኛውም ክፉ ነገር መደሰት የውሸት ደስታ ምሳሌ ነው። ይህ በራስ ላይ የሚሰራ ኃጥያት ነው። ምሳሌ 24፥17 ላይ "ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ" ዳግመኛም ለኃጢአት መጋበዝን የሚያመለክት በኃጢአት የተሞላ ደስታ ነው። ይህም #የፍቅር ተቃራኒ ነው።
@zekidanemeheret
👉፥- #ትዕቢት እና ራስን ማዕከል ያደረገ ደስታ በሉቃ 10፥17- 20 ላይ ሰባውም ደቀ መዛሙርት በደስታ ተመልሰው "#ጌታ ሆይ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል" አሉት። ጌታም በዚህ ደስ አይበላችሁ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ።
👉 ፥- ሰዎች በኃጥያት ይደሰታሉ
ሀዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው በፊል 3፥19 ላይ ክብራቸው በነውራቸው ነው አሳባቸው ምድራዊ ነው። አብዛኞቹም በቁሳዊ ነገሮች ይደሰታሉ። የጠፋው ልጅ በተመለሰ ጊዜ ያልተደሰተው ታላቁ ወንድሙ የእነዚህ ሰዎች ምሳሌ ነው።
#ጠቢቡ ሰሎሞን ሲናገረን የደስታ ፍጻሜ ለቅሶ ነው #ልብ ለሌለው ሰው ስንፍና ደስታ ናት። የጠቢባን ልብ በልቅሶ ቤት ነው። ምሳ 14፥13 15፥21 መክ 7፥4 በዚህም የውሸት ደስታ እና ስሕተት የሆነ የሥሜቶች እና የሥጋ ጊዜያዊ ልቅሶ ወይም መንፈሳዊ ያልሆነ ደስታን ማለቱ ነው።
👉 ፥- #መንፈሳዊ ደስታ

መንፈሳዊ ደስታ በጌታ በእርሱ ሕልውና እና ጥበቃ ውስጥ በመሆን እና ከእርሱም ጋር በመገናኘት መደሰት ነው። ይህም ይታወቅ ዘንድ "ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው።ክርስቶስም #እንደገና አያችኃለሁ ልባችሁም ደስ ይለዋል ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም ብሏቸዋል። ዮሐ 16፥22 ፣ዮሐ 20፥20
🙏ዘወትር ደስታችንን እንመርምር ውድ ቤተሰቦቻችን🙏
መንፈሳዊ ደስታዎች፥-
#በጌታ ያለ መንፈሳዊ ደስታ
ሉቃ 1፥47 ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች በማለት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጌታ ያለ መንፈሳዊ ደስታን ገልጻዋለች።
#በንሥሓና ኃጢአትን በማስወገድ የሚገኝ ደስታ ነው።
የአንድ ሰው ተደጋጋሚ ከሆኑ ኃጢአቶች ወይም ተገዢ ከሆነበት መጥፎ ልማድ ነፃ የመውጣት እና በንሥሓና ድል የመንሳት ይቅርታንም የማግኘት ደስታ ነው። ይህም የተመለሰው ልጅ ደስታ ነው።ሉቃ 15
#በኃጢአተኛ መመለስ የሚገኝ ደስታም አለ።
ይህ ደስታ በመጽሐፍ ቅዱስ "ንስሓ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል በማለት በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይ የሚደረግ ደስታ ነው።
#መልካም ነገርን በማድረግ የሚገኝ ደስታ
መልካም ሥራ በምድርና እና በሰማይ ደስታን ያመጣል። የተሰበረ ልብን ደስተኛ በማድረግህ ወይም ለተጨነቀ ሰው ፍትህን በመስጠትህ ውስጣዊ ደስታ ይሰማሃል ለእንስሳት እንኳን መልካም ስታደርግ ደስታ ይሰማሃል።
@zekidanemeheret
አንድ ጸሐፊ ሰው ሲናገር "ዛፌን ውሃ አጠጣታለሁ ነገር ግን የምሥጋና ቃል ለእኔ አትሰጠኝም። ይሁንና ዛፏ ሕይወት ስትዘራ ሳያት እኔም ሕይወት እዘራለሁ። በማለት ደስታ ምናገኘው ለሰው ስናደርግ ብቻ እንዳልሆነ ይገልጽልናል።
🙏 በመጨረሻም በተስፋ መደሰት/ሮሜ 12፥12/ እንመለከታለን ሁላችንም ወደ ፊት ሊፈጸም በሚችል ነገር ውስጥ ያለ ተስፋ እግዚአብሔር ጣልቃ ከሚገባበት እና ከሚሠራበት እምነት ይመጣል። ይህም ይታወቀን ዘንድ መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት በመዝ 5፥11 "በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ደስ ይላቸዋል።
#ሁላችንም በሙሽራው ጽምድ ደስ ይበለን!!!!!!!! ዮሐ 3፥29

🙏ከጻድቁ አባታችን #ከአቡነ #ተክለሃይማኖት ምልጃና በረከት ይክፈለን።🙏
🙏🙏 ቸር ያቆየን🙏🙏
#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_2
#እውነተኛ_ፍቅር
"ወደ እውነተኛ ፍቅር ስንደርስ ወደ እግዚአብሔር መድረሳችንና የጉዞአችንም መጨረሻ ነው ። በእውነተኛ ፍቅር ተንሳፈን ከዓለም ባሻገር አብ ወልድና መንፈስቅዱስ ወዳሉበት ደሴት እንደርሳለን " (ቅዱስ ይስሐቅ/ሶርያዊ/ የእውነተኛ ፍቅር ምንጭ #እግዚአብሔር ነው ። እግዚአብሔር ደግሞ ለሁለት የፍቅር ተጓዳኞች ቃላት ሊገልፀው የማይችለው የመዋደድን ጸጋ ይሰጣቸዋል ። #ከልብ የሆነ ፍቅር በወርቅ ፣ በብር ፣ በዕንቁ ፣ በአልማዝና በፔትሮሊየም የማይለውጡት ፣ዝገት የማይበላው ፣ ቀናትና ዘመናት ሊሽሩት አቅም የማያገኙለት የእውነተኛ ስሜት ነጸብራቅ ነው ። #ፍቅር ጥልቅ ነገር ነው ። ለባልና ለሚስትም ትልቁ ሐብት ውበትና እርካታቸው #ፍቅራቸው ነው ።ባል ለሚስቱ ሚስትም ለባሏ የምትመግበው ፍቅር ትዳሩን በመልካም ውበት እንዲያሸበርቅ የሚያደርገው የሕይወት ፈርጥ ነው ።ራሳቸውን ለይተው /በገዳም ህይወት/ ለመኖር ከተሰጣቸው በስተቀር ሰው ያለ ፍቅር ብቻውን መኖር አይችልም። ለዚህ ነው እግዚአብሔርም አለ "ረዳት እንፍጠርለት"ያለው ። #ፍቅር በሀገር ርቀት ተገድቦ የሚወሰን አይደለም ። ፍቅርን ሀገር አይወስነውም ። ድንበርም አይከለክለውም ። ክልል ጥሶ የመጓዝ አቅሙም አስተማማኝ ነው ። ፍቅርን ሐብትና ድህነት ፣ በዜግነት መለያየትም አያግደውም ። ቅዱስ ጳውሎስ "አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም ባሪያ ወይም ጨዋ የለም " እንዳለው ሁሉም ሰው ለፍቅር እኩል ነው ። /ገላ 3÷28/ ። #ፍቅር ከባድ ኃይል ያለው ሕይወት ነው ። "ሰው እናትና አባቱን ይተዋል " እንደተባለው እናትና አባት ያህል ነገር እስከማስተው ድረስ ብርቱ አቅም አለው ። #ፍቅር ለማንም አይሸነፍም ። በማንም ልብ ውስጥ ገብቶ የሰውን ማንነት የሚያንበረክክ ጀግና ነው ። #እውነተኛ ፍቅር ማስመሰልን አያውቅም ። ከሽንገላም የጸዳ ነው ። ፍቅር በአንደበት ብቻ የሚገለፅ ሳይሆን በሥራና በእውነት የተደገፈም ነው ።"በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ /1ኛ ዮሐ3÷18/ ። #እውነተኛ_ፍቅር በጥቅም የማይለካ ፣ በመከራ ቀን የማይበገር ፣ የማይሞት ፣ ሁሌም የሚያብብና የማይደርቅ ፣ ጎርፍ የማይንደው ጠንካራና ጽኑ ነው ። "ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና... ብዙ ውሃ ፍቅርን ያጠፋት ዘንድ አይችልም ፡ ፈሳሾችም አያሰጥሟትም "ተብሎ /መኃ 8÷6/ የተመዘገበው ለዚህ ነው ። በአጠቃላይ ከእውነተኛ ፍቅር የሚታጨደው #ደስታ ነው ። ለዚህም ይመስላል ምሁራን "ሕይወት አበባ ሲሆን ፍቅር ደግሞ ከዚህ የሚቀሰም ማር ነው " ያሉት ። ፍቅር የሚጓጓለት ድንቅ የሕይወት አንዱ ክፍል ነው ። እውነተኛ ፍቅር የሕይወት ግሩም ቅመም ናትና ።በቀጣይ ክፍላችን ደሞ #12ቱን የፍቅር አይነቶች እናያለን ። ይቆየን

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#እውነተኛ_ወዳጅ፥ ወዳጅ መኾኑ የሚታወቀው ጓደኛውን መገሠጽ ሲችል ነው፡፡ ኹላችንም በየጊዜው ኃጢአት እንሠራለን፡፡ አብዛኞቻችን ደግሞ ኃጢአታችንን እንዳላየነው ኾነን ለማለፍ እንጥራለን፡፡ ለራሳችን ይቅርታ እንቸራለን፡፡ ወይም ምንም እንዳላጠፋ ሰው ለመምሰል እንሞክራለን፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሰዓት እውነታውን በትክክል እናይ ዘንድ ዓይናችንን የሚከፍት እውነተኛ ወዳጅ ያስፈልገናል፡፡

አንተ ሆይ! እስኪ ራስህን መርምር፡፡ ጓደኛህ እውነታውን እንዲያይ ታደርጋለህ? ጓደኛህ ኃጢአት ሠርቶ ሲያበቃ ለራሱ ይቅርታ ሲያደርግ ይቅርታው ያደረገው ይቅርታ ትክክለኛ እንዳልኾነ እንዲያውቅ ታደርጓለህን? እንዲህ እውነታውን ስትነግረው ምናልባት ጓደኛህ አለአግባብ ሊቈጣህ ይችላል፡፡ ታዲያ ሲቈጣህ ለመታገሥ ዝግጁ ነህን? ወይስ ከዚህ በተቃራኒ የጓደኛህን ኃጢአት አይተህ እንዳላየህ ነው የምትኾነው?

ጓደኛ ስንመርጥ ከእኛ ጋር እውነተኛ ወዳጅ ሊኾን የሚገባውን መኾን አለበት፤ ስንቈጣው እንኳን ቁጣችንን ታግሦ ስናጠፋ የሚያርመን ሊኾን ይገባል፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ጓደኝነት ጥልቀት አይኖረውምና፤ ጓደኞች ነን መባባላችን ጥቅም የለውምና፡፡

ልናውቀው የሚገባን ነገር ግን አለ፡፡ ጓደኛችን በሚያጠፋበት ሰዓት ተግሣጽ አስመስለን እንዲሁ ክብሩን በሚነካ መልኩ ልንናገረው አይገባንም፡፡ ተግሣጻችን ኹልጊዜ እውነቱን ብቻ እንጂ የተጋነነና ሌላውን መልካምነቱን የሚክድ መኾን የለበትም፡፡ ጥፋቱን ስንነግረው ኹልጊዜ በቀና ልብ እንደምንነግረው እርግጠኛ እንዲኾን ማድረግ አለብን፡፡ ይህን የምናደርገው ከፍቅራችን የተነሣ እንጂ ከቅናት ወይም ከንቀት እንዳልኾነ እንዲያውቅ ማድረግ አለብን፡፡ እውነተኛ ወዳጅነት ማለት ይህ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ