ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
803 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ራስህን_ፈልገህ_አግኝ

"በማንኛውም ግለሰብ ሕይወት ውስጥ ታላቁ ቀን የሚባለው ሰው ራሱን ለመጀመርያ ሰዓት መረዳት የጀመረበት ጊዜ ነው። ሰው ራሱን ፈልጎ ካላገኘ በራስ የመተማመን መንፈስን አያገኝም፤ በእንቅስቃሴውም እርካታ የለውም። ለዚህም ነው ራስን እንደማግኘት በደስታ ሊያጥለቀልቅ የሚችል ሌላ ምንም ነገር አይኖርም የሚባለው። ሰለሆነም ከራሱ ጋር ለተገናኘ ሰው ሕይወት ዛሬ ትጀምራለች።
የራስን ማንነት ለማግኘት ምን እናድርግ? ለራሳችን ሕይወት ትልቅ ግምት እንስጥ። እግዚአብሔር ሲፈጥረን እጅግ ግሩም አድርጎ ሠራን እንጂ ማናችንንም የሰው ጎዶሎ አድርጎ አልፈጠረንም። "ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ።" መዝ. ፻፴፰፥፲፬፣ "እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም።" መዝ. ፻፲፰፥፸፫ በተሸናፊና በአሸናፊ መካከል፣ በደሀውና በሀብታሙ መካከል፣ በወንድና ሴት መካከል እግዚአብሔር ያስቀመጠው አድልዎ የለም፤ ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ብሏል "እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያዳላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ።"ሐዋ. ፲፥፴፬-፴፭፣ ፩ጴጥ. ፩፥፲፯ ሰው በእንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ ካላመነ ራስን ፈልጎ ማግኘት ያቅተዋል። "ትልቅ ሰው ትልቅ ሆኖ አይወለድም ነገር ግን ትልቅ ለመሆን ራሱን ያሳድጋል።"
የፈጠረን አምላክ ለእኛ ሊያደርግልን የሚገባውን ስለሚያውቅ የሚያጎልብን ነገር ስለሌለ በጎዶሎ ቀን ተፈጥሬ እያልን በእርሱ ማመካኘት አይገባንም። "እግዚአብሔር ሰዎችን ቅኖች አድርጎ እንደ ሠራቸው እነሆ ይህን ብቻ አገኘሁ።" መክ. ፯፥፳፱፣ "በእኔና በወይኑ መካከል እስኪ ፍረዱ ለወይኔ ያላደረኩለት ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድር ነው?" ኢሳ. ፭፥፫-፯፣ መክ. ፮፥፪ መኖር በራሱ ቀላል ነገር አይደለም በራሳችን ችሎታ ሕይወትን አግኝተን አልመጣንም የሕይወትን እስትንፋስ እግዚአብሔር ሰጠን እንጂ ኢሳ. ፵፬፥፳፬ ከእግዚአብሔር ለተቀበልነው ሕይወት ትልቅ ግምት ካልሰጠን የማይረባ ቦታ ላይ ራሳችንን እናገኘዋለን። ለራስ ሕይወት ትልቅ ግምት ካለመስጠት የተነሣ እየኖሩ የሞቱ፣ መንቃት ሲገባቸው ያንቀላፉ አሳዛኝ ሰዎች አሉ። ብዙዎቻችን የተስፋ መቊረጥ ስሜት የሚጠናወተን እኛው ለራሳችን ከምንሰጠው ግምት ይልቅ ሰዎች ስለ እኛ ስለሚያወሩት ነገር አበክረን ስለምናስብ ነው። ከራስህ በበለጠ ሁኔታ ሰዎች ሙሉ በሙሉ ስለአንተ አያውቁም ሰለዚህ ለሰዎች ብለን በማስመሰል መኖር የለብንም። "በውጭ ለሰው እንደ ጻድቃን ትታያለችሁ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ዓመፀኛነት ሞልቶባችኋል።" እንዳለ ጌታ በወንጌል ማቴ. ፳፫፥፳፰ አንድ ጊዜ ለተሰጠንና አንድ ጊዜ ለምንኖርበት ሕይወት ትልቅ ግምት መስጠት አለብን። "ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና።" ኤፌ ፭፥፴ ማንም ሰው ሕይወት የተሰጠው ኑሮውን ትርጉም ባለው መንገድ ሙሉ በሙሉ እንዲኖረው ነው። አንዳንዴ ለራሳችን ከምንሰጠው አነስተኛ ግምት የተነሣ ተስጥዖአችንን የሆነውን ነገር ብናገኝም እንኳን ምላሽ መስጠት ስለምንፈራ ከራሳችን ጋር ሳንገናኝ እንቀራለን። የሕይወትን ጦርነት ማሸነፍ የምንችለው መጀመሪያ የራሳችንን ማንነት አግኝተን መራመድ ስንችል ነው።

🙏መልካም ቀን🙏 ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
ለመንፈሳዊ ልምምድ ጠቃሚ ምክሮች
++++++++++++++++++++++

በመጀመሪያ ምን ያህል አዋቂዎች ብንሆን ማወቃችን ብቻ ሊያስደስትን እና ሊያረካን አይገባም፡፡ ትልቅ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ያወቅነውን በስራ ለምንተረጉምበትና ትእዛዛትን መፈፀም ለምንችልበት ሕይወት ነው፡፡
ጌታችን የተራራው ስብከቱን ሲያጠቃልል የተናገረው ቃል ይህን ነው፡፡ ‹‹ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በአለት ላይ የሰራ ልባምን ሰው ይመስላል፣ ይህንንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሰራ ሰነፍን ሰው ይመስላል፡፡›› (ማቴ 7÷24-6) ስለዚህ እንደሰማን ለመስራት ለምግባራችን ትልቅ ትኩረት ልንሰጥ ይገባል፡፡ ይህንንም ሲያረጋግጥልን ‹‹በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡›› ብሏል ካህኑም በፀሎተ ቅዳሴ (ቅድመ ወንጌል) ወንጌልን ለመስማት፣ እንደሰማንም ለመስራት በቅዱሳን ፀሎት የበቃን አድርገን›› እያለ የሚጸልየው ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ እኛም እንደ ትእዛዙ ለመኖር እና ቃለ ወንጌሉን ለመፈፀም ራሳችንን እናለማምድ፡፡
መንፈሳዊ ልምምድ አንድ ሰው ለነፍሱ ድኅነት ያለውን ተስፋ ያመለክታል፡፡ ስሕተቶቹን፣ ድክመቶቹን ሁሉ ለይቶ አውቆ ለማስወገድ እየጣረ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ አንተም ወንድሜ ስህተቶችህን ሌሎች
አይተው እስከሚነግሩህ ድረስ መጠበቅ ሳይኖርብህ በራስህ ለይተህ እወቃቸው፡፡ምክንያቱም ያለብህን ችግር ሳታውቀው ለመንፈሳዊ ልምምድ መነሳት ስለማትችል ነው፡፡ ‹‹በሽታውን የደበቀ መድሃኒት አይገኝለትም›› ይባል የለ፡፡ ‹‹ህምምተኞች እንጂ ባለጤናዎች ባለመድሃኒት አያስፈልጋቸውም›› (ማቴ 9÷12)

ባንተ ያለውን ችግር ሌሎች ማወቃቸውም ቢሆን አያበሳጭህ፡፡ ይልቁንም በየትኛው መንፈሳዊ
መስክ ልምምድ ማድረግ እንደሚገባህ አድርገህ ተቀበለው፡፡
በእግዚአብሔር ህግ ብርሃንነት ራስህን እየመረመርክ ድክመቶችህን ፈልግ፡፡ ትንንሽ ድክመቶች እንኳ ቢሆኑ አትናቃቸው፤ምክንያቱም
ያድጋሉና፡፡ ‹‹ወይናችን አብቧል ኑ የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮዎች፣ ጥቃቅን ቀበሮዎች አጥምዳችሁ ያዙ፡፡››(መኃ 2÷15)

#ራስህን ከማፅደቅ ተቆጠብ ለስህተቶችህም ማስተባበያ አትፈልግ ራሱን የሚያፀድቅ ሰው ዘወትር ባለበት መሔድ እንጂ የሚያሻሽለው አንድም ነገር የለምና፡፡ ምክንያቱም በዓይኑ ፊት ከእርሱ በላይ ሰው የለም ለራሱ እንከን የለሽ ነው፡፡ለችግሮች መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ይህን ያደረኩት በዚህ ምክንያት ነው እያለ ሲያስተባብል ወድቆ ይቀራል፡፡ለራሱ ትክክለኛ ግምት ያለው የማይመፃደቅ ሰው ግን ድክመቱን መናዘዝ ብሎም ማስወገጃውን መንገድ መለማመድ ይችላል፡፡ ችግሮችህ ስር ሰደው ሰዎች ሊገልጡብህ የሚችሉበት ደረጃ ሲደርሱ የሚሰማህ መሸማቀቅ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር ግን ቀደም ብለህ እራስህ ገልጠሀቸው ለመፍትሔው ልምምድ ብታደርግ ይህ ሁሉ ነገር ባንተ ላይ አይከሰትም፡፡

#ሁሌም ራስህን ሁነህ ተገኝ፡፡በሕይወትህ ቅንነት የሚነበብብህ ሰው ሁን፡፡ መጽሃፍትን ስታነብም ሆነ ስብከት ስታዳምጥ ጉድለቶችህን እየፈለክ ይሁን፡፡ ሰምተህ ለማድረግም ተነሳሳ፡፡

#የኃጢያት ስሩ አንድ ነው፡፡ ብዙ መንገዶች ቢኖሩትም እርስ በራሳቸው የተያያዙ መሆናቸውንም እርግጠኛ ሁን፡፡ አንድ የተወሰነ የሀጢያት አይነትን ለመቅረፍ ስትነሳ ሳታውቀው
ሌሎችንም እየበጣጠስክ መሆኑን እወቅ፡፡እንዲሁም አንድ በጎ ሥነ ምግባርን ለማዳበር ስትለማመድም ቢሆን ሌሎች ብዙ ሥነ ምግባራትን እያተረፍክ መሆኑን ልብ በል፡፡ ሥነ ምግባራቱም በአንድ ሠንሰለት የተያያዙ ናቸው፡፡

@zekidanemeheret
ለመንፈሳዊ ልምምድ ጠቃሚ ምክሮች
++++++++++++++++++++++

በመጀመሪያ ምን ያህል አዋቂዎች ብንሆን ማወቃችን ብቻ ሊያስደስትን እና ሊያረካን አይገባም፡፡ ትልቅ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ያወቅነውን በስራ ለምንተረጉምበትና ትእዛዛትን መፈፀም ለምንችልበት ሕይወት ነው፡፡
ጌታችን የተራራው ስብከቱን ሲያጠቃልል የተናገረው ቃል ይህን ነው፡፡ ‹‹ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በአለት ላይ የሰራ ልባም ሰው ይመስላል፣ ይህንንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሰራ ሰነፍን ሰው ይመስላል፡፡›› (ማቴ 7፣24-26) ስለዚህ እንደሰማን ለመስራት ለምግባራችን ትልቅ ትኩረት ልንሰጥ ይገባል፡፡ ይህንንም ሲያረጋግጥልን ‹‹በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡›› ብሏል ካህኑም በጸሎተ ቅዳሴ (ቅድመ ወንጌል) ወንጌልን ለመስማት፣ እንደሰማንም ለመስራት በቅዱሳን ጸሎት የበቃን አድርገን›› እያለ የሚጸልየው ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ እኛም እንደ ትእዛዙ ለመኖር እና ቃለ ወንጌሉን ለመፈፀም ራሳችንን እናለማምድ፡፡
መንፈሳዊ ልምምድ አንድ ሰው ለነፍሱ ድኅነት ያለውን ተስፋ ያመለክታል፡፡ ስሕተቶቹን፣ ድክመቶቹን ሁሉ ለይቶ አውቆ ለማስወገድ እየጣረ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ አንተም ወንድሜ ስህተቶችህን ሌሎች
አይተው እስከሚነግሩህ ድረስ መጠበቅ ሳይኖርብህ በራስህ ለይተህ እወቃቸው፡፡ምክንያቱም ያለብህን ችግር ሳታውቀው ለመንፈሳዊ ልምምድ መነሳት ስለማትችል ነው፡፡ ‹‹በሽታውን የደበቀ መድሃኒት አይገኝለትም›› ይባል የለ፡፡ ‹‹ህምምተኞች እንጂ ባለጤናዎች ባለመድሃኒት አያስፈልጋቸውም›› (ማቴ 9፤12)

ባንተ ያለውን ችግር ሌሎች ማወቃቸውም ቢሆን አያበሳጭህ፡፡ ይልቁንም በየትኛው መንፈሳዊ
መስክ ልምምድ ማድረግ እንደሚገባህ አድርገህ ተቀበለው፡፡
በእግዚአብሔር ሕግ ብርሃንነት ራስህን እየመረመርክ ድክመቶችህን ፈልግ፡፡ ትንንሽ ድክመቶች እንኳ ቢሆኑ አትናቃቸው፤ምክንያቱም
ያድጋሉና፡፡ ‹‹ወይናችን አብቧል ኑ የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮዎች፣ ጥቃቅን ቀበሮዎች አጥምዳችሁ ያዙ፡፡››(መኃ 2፣15)

#ራስህን ከማፅደቅ ተቆጠብ ለስህተቶችህም ማስተባበያ አትፈልግ ራሱን የሚያፀድቅ ሰው ዘወትር ባለበት መሔድ እንጂ የሚያሻሽለው አንድም ነገር የለምና፡፡ ምክንያቱም በዓይኑ ፊት ከእርሱ በላይ ሰው የለም ለራሱ እንከን የለሽ ነው፡፡ለችግሮች መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ይህን ያደረኩት በዚህ ምክንያት ነው እያለ ሲያስተባብል ወድቆ ይቀራል፡፡ለራሱ ትክክለኛ ግምት ያለው የማይመፃደቅ ሰው ግን ድክመቱን መናዘዝ ብሎም ማስወገጃውን መንገድ መለማመድ ይችላል፡፡ ችግሮችህ ስር ሰደው ሰዎች ሊገልጡብህ የሚችሉበት ደረጃ ሲደርሱ የሚሰማህ መሸማቀቅ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር ግን ቀደምብለህ እራስህ ገልጠሀቸው ለመፍትሔው ልምምድ ብታደርግ ይህ ሁሉ ነገር ባንተ ላይ አይከሰትም፡፡

#ሁሌም ራስህን ሁነህ ተገኝ፡፡በሕይወትህ ቅንነት የሚነበብብህ ሰው ሁን፡፡ መጽሐፍትን ስታነብም ሆነ ስብከት ስታዳምጥ ጉድለቶችህን እየፈለክ ይሁን፡፡ ሰምተህ ለማድረግም ተነሳሳ፡፡

#የኃጢያት ስሩ አንድ ነው፡፡ ብዙ መንገዶች ቢኖሩትም እርስ በራሳቸው የተያያዙ መሆናቸውንም እርግጠኛ ሁን፡፡ አንድ የተወሰነ የሀጢያት አይነትን ለመቅረፍ ስትነሳ ሳታውቀው
ሌሎችንም እየበጣጠስክ መሆኑን እወቅ፡፡እንዲሁም አንድ በጎ ሥነ ምግባርን ለማዳበር ስትለማመድም ቢሆን ሌሎች ብዙ ሥነ ምግባራትን እያተረፍክ መሆኑን ልብ በል፡፡ ሥነ ምግባራቱም በአንድ ሠንሰለት የተያያዙ ናቸው።

#ሼር

https://t.me/zekidanemeheret