ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
858 subscribers
3.46K photos
103 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ግንቦት 17/09/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፬፥፩(104፥1)
ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ
ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ
ሰብሑ ወዘምሩ ሎቱ


📖ወንጌል
ወንጌል ዘማርቆስ ፲፮፥፲፭-፳(16፥15-20)
ወይቤሎሙ ሑሩ …


ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ጢሞቴዎስ ፩ ም ፫፥፩-፰(3፥1-8)
እሙን ነገር ዘይፈቅድ…


👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፭፥፩-፲፬(5፥1-14)
ወለእለኒ ይትለሐቁ እምኔክሙ …


👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፳፥፳፰-፴፩(20፥28-31)
ወይእዜኒ ዕቀቡ ርእሰክሙ …

📖ምስባክ ዘቅዳሴ

እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ
ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን


👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፹፫ ቊ. ፮ - ፯

፮ በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰንኻቸው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና።

፯ ከኃይል ወደ ኃይልም ይሄዳል፥ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።


📖ወንጌል ዘቅዳሴ

የሉቃስ ወንጌል ም. ፲፱ ቊ. ፲፩ - ፳፰
ወእንዘ ይሰምዑ ዘንተ...

📜ቅዳሴ


👉ዘኤጲፋንዮስ (ዐቢይ)


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
††† እንኳን ለታላቁ የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ኤዺፋንዮስ †††

††† ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ጽድቅ ከቅድስና : ድርሰት ከጥብቅና የተሳካለት አባት ነው:: "ኤዺፋንያ" ማለት የመለኮት መገለጥ ሲሆን "ኤዺፋንዮስ" ማለት ደግሞ ምሥጢረ መለኮት የተገለጠለት ማለት ነው::

ቅዱስ ኤዺፋንዮስ የተወለደው ክርስቶስን ከሚጠሉ አይሁዳውያን ቤተሰቦች ቤተ ገብርኤል ውስጥ ነው:: ቤተሰቦቹ ከአንድ አህያ በቀር ምንም የሌላቸው ድሆች ነበሩ:: በዚያ ላይ በልጅነቱ አባቱ በመሞቱ ከእናቱና ከአንዲት እህቱ ጋር በረሃብ ሊያልቁ ሆነ:: ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ በአህያው እንዳይሠራ አህያው ክፉ ነበርና ሊሸጠው ገበያ አወጣው::

ፊላታዎስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ለግዢ ሲደራደሩ አህያው የኤዺፋንዮስን ኩላሊቱን ረግጦት ለሞት አደረሰው:: በዚህ ጊዜ አብሮት ያለው ክርስቲያኑ በትእምርተ መስቀል አማትቦ አዳነው:: በፈንታው ግን አህያው ሞተ:: ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ እያደነቀ ሔደ::

ከቆይታ በኋላ ሀብታም አጎቱ ገንዘቡን አውርሶት በመሞቱ ገና በ16 ዓመቱ ባለጠጋ ሆነ:: ያቺ ገበያ ላይ ያያት ተአምር ግን በልቡ ውስጥ ትመላለስ ነበር::

አንድ ቀን ደግሞ ሉክያኖስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ሲሔዱ ነዳይ አገኙ:: ባለጠጋው ኤዺፋንዮስ አለፈው:: ያ ድሃ ክርስቲያን ግን የለበሳትን አውልቆ መጸወተው:: በዚሕ ጊዜ መልዐኩ መጥቶ የብርሃን ልብስ ሲያለብሰው ኤዺፋንዮስ ተመለከተ::

ኤዺፋንዮስ ጊዜ አላጠፋም:: ከእህቱ ጋር በክርስቶስ አምኖ ተጠመቀ:: ሃብት ንብረቱን ግማሹን መጸወተ:: በተረፈው ደግሞ መጻሕፍትን ገዝቶ ወደ አባ ኢላርዮን ገዳም ገባ:: በዚያም መናንያኑ እስኪያደንቁት ድረስ በፍጹም ትጋትና ቅድስና ተጋደለ::

በጸሎቱ ዝናም አዘነመ : ድውያንን ፈወሰ : ብዙ ተአምራትንም አደረገ::

እግዚአብሔር ደግሞ ለሌላ አገልግሎት ሽቶታልና በቆዽሮስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኖ ተሾመ:: ብሉይ ከሐዲስ የወሰነ ሊቅ ነውና ብዙ መጻሕፍትን ተረጎመ:: በሺሕ የሚቆጠሩ ድርሳናትን ደረሰ:: በአፍም በመጽሐፍም ብሎ መናፍቃንንና አይሁድን ምላሽ በማሳጣቱ ቤተ ክርስቲያን "ጠበቃየ" ትለዋለች::

ከደረሳቸው መጻሕፍት መካከል "ሃይማኖተ አበው ዘኤዺፋንዮስ : መጽሐፈ ቅዳሴውና አክሲማሮስ (ሥነ ፍጥረት)" ዛሬም በቅርብ ይገኛሉ:: ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ በመልካም እረኝነትና በሚደነቅ ቅድስና ተመላልሶ በ406 ዓ/ም ዐርፏል:: እድሜውም 96 ዓመት ያህል ነበር::

††† አምላካችን ከቅዱሱ ሊቅ በረከት ያድለን::

††† ግንቦት 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ)
2.ቅዱስ ኢላርዮን ገዳማዊ
3.አባ ሉክያኖስ ጻድቅ
4.ቅዱስ ፊላታዎስ ክርስቲያናዊ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ

††† "የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል:: እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው:: እኛ ግን የማይጠፋውን:: ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም:: ነፋስን እንደሚጐስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም:: ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጐሰምሁ አስገዛዋለሁ::" †††
(1ቆሮ. 9:25)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
"በማመስገንህ የምትመሰገነው... ብታከብረው የምትከብር ...ብታገለግል የምትጠቀመው አንተ ነህ" ሀልዎተ እግዚአብሔር ክፍል 6 ተከታታይ ትምህርት
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/12TtdRGBM4E
https://youtu.be/12TtdRGBM4E
https://youtu.be/12TtdRGBM4E
👆👆👆👆👆
✞ እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ

+*" ዕርገተ እግዚእ "*+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ዕርገትን 2 ጊዜ ታከብራለች:: አንዱ "ጥንተ በዓል": ሁለተኛው ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል:: ጥንተ በዓል ማለት ጌታችን በትክክል ያረገበትን ቀን ያመለክታል::

+የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በኪነ ጥበቡ (በሕማሙ: በሞቱ) ዓለምን አድኖ: 40 ቀን ለሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን አስተምሯቸዋል::

+በ40ኛው ቀን 120ውን ቤተሰብ ይዟቸው ወደ ቢታንያ ወጣ:: በዚያም እስከ ሊቀ ዽዽስና ድረስ ሾሟቸው: ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡም አዟቸው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ጠብቁ ብሏቸዋል:: እየባረካቸው በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑ አርጉዋል::

+ሰማያት: ምድር: ደመናት: ነፋሳት: መባርቅትና መላእክት: ፍጥረት በሙሉ አመስግኗል:: አይሁድ መናፍቃን እርገቱን ምትሐት ነው እንዳይሉ: ጌታችን ትንሣኤውን አማናዊ እንደሆነ ለማስረዳት በ40ኛው ቀን ዐረገ::

+አንድም ራስ ባለበት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊኖሩ ይገባልና ጌታችን ዕርገቱን በገሃድ አደረገው:: "ዐርገ እግዚእ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን" እንዲል::

<<ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ::
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን::
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ:: >> (መዝ. 46:6)

=>ከበረከተ ዕርገቱ ይክፈለን::

+"+ እስከ ቢታንያም አወጣቸው:: እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው:: ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ:: ወደ ሰማይም ዐረገ:: እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ:: +"+ (ሉቃ. 24:50-53)

<<< ስብሐትለእግዚአብሔር >>>

ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ ዘጎንደር
'
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ pinned «"በማመስገንህ የምትመሰገነው... ብታከብረው የምትከብር ...ብታገለግል የምትጠቀመው አንተ ነህ" ሀልዎተ እግዚአብሔር ክፍል 6 ተከታታይ ትምህርት 👇👇👇👇👇 https://youtu.be/12TtdRGBM4E https://youtu.be/12TtdRGBM4E https://youtu.be/12TtdRGBM4E 👆👆👆👆👆»
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ግንቦት 18/09/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፫፥፴(103፥30)
ትፌኑ መንፈሰከ ወይትፈጠሩ
ወትሔድስ ገጻ ለምድር
ለይኩን ስብሐቲሁ ለእግዚአብሔር


📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፲፮፥፩-፰(16፥1-8)
ዘንተ ነገርኩክሙ…


ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቆሮንቶስ ፪ ም ፲፩፥፩-፲፮(11፥1-16)
ወርቱዕሰ ትትዐገሡኒ ኅዳጠ …


👉ንፍቅ ዲያቆን
📖 ጴጥሮስ ፩ ም ፭፥፮-፲፪(5፥6-12)
አትሕቱ እንከ ርእሰክሙ…


👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፥፵፬-፵፰(10፥44-48)
ወእንዘ ይነግሮሙ ጴጥሮስ…


📖ምስባክ ዘቅዳሴ

መንፈቀ ሌሊት እትነሣእ።
ከመ እግነይ ለከ በእንተ ኲነኔ ጽድቅከ
ከማሆሙ አነ ለኵሎሙ እለ ይፈርሁከ።


መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፲፰ ቊ. ፷፪ - ፷፫

፷፪ ስለጽድቅኽ፡ፍርድ፥በእኩለ፡ሌሊት፡አመሰግንኽ፡ዘንድ፡እነሣለኹ።

፷፫ እኔ፡ለሚፈሩኽ፡ዅሉ፥ትእዛዝኽንም፡ለሚጠብቁ፡ባልንጀራ፡ነኝ።


📖ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፮ ቊ. ፳፫ - ፳፰
ወተመይጦ ይቤሎ ለጴጥሮስ...

📜ቅዳሴ


👉ዘሠለስቱ ምዕት (ግሩም)


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
† እንኩዋን ለጥንተ በዓለ ዸራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ) እና ለጻድቁ አባ ገዐርጊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †

† በዓለ ዸራቅሊጦስ †

ከዚሕ በፊት እንደተመለከትነው የጌታችን ዓበይት በዓላቱ 2 ጊዜ (ማለትም ጥንተ በዓልና የቀመር በዓል ተብለው) ይከበራሉ:: ዛሬም ከ1,981 ዓመታት
በፊት አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መውረዱን እናስባለን::

††† ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+ቸር አምላክ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል
*ከልዑል ማዕረጉ ወርዶ:
*በማሕጸነ ድንግል ተጸንሶ:
*በኅቱም ድንግልና ተወልዶ:
*ከኃጢአት በቀር በግዕዘ ሕጻናት አድጐ:
*በ30 ዘመኑ ተጠምቆ:
*ቅድስት ሕግ ወንጌልን አስተምሮ:
*በፈቃዱ ሙቶ:
*በባሕርይ ሥልጣኑ ተነስቶ:
*በአርባኛው ቀን ያርጋል::

+ታዲያ ደቀ መዛሙርቱን የቅዱስ መንፈሱን ጸጋ ተስፋ እንዲያደርጉ ነግሯቸው
ነበርና በተነሳ በ50ኛው ቀን: በዐረገ በ10 ቀን ተስፋውን ፈጸመላቸው::

+እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንድትይዝ
በአንድ ላይ ሰብስባ ለክብረ መንፈስ ቅዱስ አብቅታቸዋለች:: 120ው ቤተሰብ
ከጌታችን እናት ጋር ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ አርአያ ወርዶ
በአምሳለ እሳት አደረባቸው::

+ቅዱሳን ሐዋርያት ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮች: አሮጌ ሕሊና የነበራቸው
ሐዲሶች ሆኑ:: በአዕምሮ ጐለመሱ: ቁዋንቁዋ ተናገሩ: ምሥጢርም
ተረጐሙ:: በቅጽበትም ብሉይ ከሐዲስ በልቡናቸው ውስጥ ተሞላ::

+ሐዋርያቱ ቅዱስ መንፈስን ተቀብለው ዓለምን በወንጌል ዕርፈ መስቀል
አርሰዋል:: አልጫውን ዓለም ጨው ሆነው አጣፍጠዋል:: ሳይሳሱም
አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተዋል::
"ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ ለለአሐዱ:
ሐዋርያት ለሰቢክ አሕጉራተ ዓለም ዖዱ:
ሰማዕትኒ ለሕማም ነገዱ::" እንዳለ ደራሲ::

+በዚህ ቀን 2 ነገሮች በትኩረት ይነገራሉ:-
1."የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት:-"
*እርሱ ከአብ የሠረጸ: ቅድመ ዓለም የነበረ: በባሕርይ ሥልጣኑ ከአብና
ከወልድ ጋር እኩል የሆነ: የራሱ ፍጹም አካል ያለው ፍጹም አምላካችን
ነውና::

2."ቅድስት ቤተ ክርስቲያን:-"
*አብ ያሰባት: ወልድ በደሙ የቀደሳት: መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ያጸናት
የክርስቲያኖች አማናዊት አንድነት: አንድም ቤት ናትና:: ዛሬ በጉባዔ
ተመስርታለች::

††† አባ ገዐርጊ †††

=>በዚችም ዕለት የአባ አብርሃም ጓደኛ የከበረ አባ ገዐርጊ አረፈ።ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገን ነው ወላጆቹ ደጎች ጻድቃን ናቸው።በአደገም ጊዜ የወላጆቹን ከብቶች የሚጠብቅ እረኛ ሆነ።ሁል ጊዜም የምንኵስና ልብስ ይለብስ ዘንድ በልቡ ይመኝ ነበር።

ዐሥራ አራት ዓመትም በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ አነሣሳችው በጎቹንም ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ።እየተጓዘም ሳለ ከሩቅ የብርሃን ምሰሶ አየ ወደ ወንዝ እስከ ደረሰ ድረስ ወደ ርሱ ሔደ ከዚህም በኃላ ያ የብርሃን ምሰሶ ከእርሱ ተሰወረ።

ያንንም ወንዝ በተሻገረ ጊዜ በሽማግሌ አምሳል ሰይጣን ተገለጠለትና ልጄ ሆይ ዕወቅ ስለ አንተ ልብሱን ቀዶ አባትህን አየሁት እርሱም ያዝናል ያለቅሳል ተመልሰህ የአባትህን ልብ ልትአጽናና ይገባሃል።የዱር አውሬ ነጥቆ የበላህ መስሎታልና አለው።

አባ ገዐርጊም ደንግጦ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ ከዚህም በኃላ የከበረ ወንጌል ከእኔ ሊሆን አይገባውም ደቀ መዝሙሬም ሊሆን አይችልም ብሏል ብሎ አሰበ።ይህንንም በአለ ጊዜ ሰይጣን እንደ ጢስ ሆኖ ተበተነ።አባ ገዐርጊም ሰይጣን እንደ ሆነ አወቀ በዚያን ጊዜም ያ የብርሃን ምሰሶ ደግሞ ተገለጠለት የእግዚአብሔርም መልአክ በመነኵሴ አምሳል አብሮት ተጓዘ ቅዱሱም መልአኩን ተከተለው እርሱም ከአባ አርዮን ገዳም አደረሰው።አባ ገዐርጊም ከአንድ ጻድቅ ሰው መነኵሴ ጋራ በዚያ ዐሥራ አራት ዓመት ወጥ ሳይቀምስ ወይን ሳይጠጣ የአትክልት ፍሬም ቢሆን በዚህ በዐሥራ አራት ዓመት ያህል ከመቀመጥ በቀር አልተኛም።

ተጋድሎውንም በጨመረ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ሥጋህ እንዳይደክም በመካከለኛ ገድል ተጋደል ብሎሃል ጌታ።ከዚህም በኃላ ሊሠራው የሚገባውን ሥርዓት ሠራለት ።ሁል ጊዜም እስከሚመሽ እንዲጾም ትንሽም እንጀራን እንዲበላ ከአራት ሰዓት እስከ መንፈቀ ሌሊት ስለ ሥጋው ዕረፍት እንዲተኛ በቀረው ሌሊት እስቲነጋ ተግቶ እንዲጸልይ።

በዚህም ተጋድሎ ብዙ ዘመናት እየተጋደለ በኖረ ጊዜ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ሊኖር ወዶ በጫካ ውስጥ እየተመላለሰ ሁለት ዓመት ኖረ።ከዚህም በኃላ ጌታ ተገለጾለት ወደ ቦታው እንዲመለስ አዘዘው።ያን ጊዜም አምላካዊት ኃይል ከከበሩ መክሲሞስና ደማቴዎስ ገዳም አደረሰችው እርሷም ለደብሩ አቅራቢያ ናት።

ወደ ደብሩም በተመለሰ ጊዜ በዚያን ወቅት አብርሃም ከዓለም ወደዚያ ገዳም መጥቶ ሁለቱም ተገናኙና በአንድነት ተስማምተው የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ወደ ሆነ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሱ።እርሱም ቦታ ሰጥቷቸው በውስጡ ኖሩ ያ ቦታም እስከ ዛሬ ታውቆ ይኖራል ።

ያቺም ዋሻ በግቢግ ትባላለች የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐለት የሆነ ጣሪያዋን ሠንጥቆ ወደ እነርሱ የወረደባት ናት ።እነርሱም ሰገዱለት ሰላምታም ሰጥቷቸው አጽናንቷቸው ከእርሳቸው ዘንድ ዐረገ።በዚያችም ጌታችን በወረደበት መስኮት ብርሃንን አዩ እስከ ዛሬም የተከፈተች ሁና ትኖራለች።

እሊህ ቅዱሳንም ለመነኰሳት የሚሆን ብዙ ድርሳናትንና ብዙ ተግሣጻትን ደረሱ።ለአባቶቹ የሚታዘዘውንና የሚገዛውን አመሰገኑት።ከዚህም በኃላ አባ አብርሃም ጥር ሁለት ቀን አረፈ።ከእርሱ በኋላም የከበረ አባ ገዐርጊ በዚች በግንቦት ወር በዐሥራ ስምንት ቀን አረፈ።መላ ዕድሜውም ሰባ ሁለት ዓመት ሆነ።በዓለም ዐሥራ አራት ዓመት በምንኩስና ኃምሳ ስምንት ዓመት ነው።ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትሁን አሜን።

=>በዚችም ዕለት የሰማዕት ሲኖዳ መታሰቢያው ነው በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።

=>አምላከ ገዐርጊ ከቅዱስ መንፈሱ ጸጋ ለኃጥአን ባሮቹ ያድለን::

=>ግንቦት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን ሐዋርያት ወአርድእት
2.አባ ገዐርጊ ገዳማዊ
3.ቅዱስ ሲኖዳ ሰማዕት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ

=>+"+ በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው
አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ::
ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው:: እንደ እሳትም የተከፋፈሉ
ልሳኖች ታዩአቸው:: በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው:: በሁሉም
መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው:: መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ
ልሳኖች ይናገሩ ጀመር:: +"+ (ሐዋ. 2:1-4)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ግንቦት 19/09/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፵፪፥፲(142፥10)
ወመንፈስከ ቅዱስ ይምርሐኒ በምድረ ጽድቅ
በእንተ ስምከ እግዚኦ አሕይወኒ በጽድቅከ
ወአውፅኣ እምንዳቤሃ ለነፍስየ

📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፲፬፥፳፭-፴፩(14፥25-31)
ወዘንተ ነገርኩክሙ እንዘ ሀሎኩ…


ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቆሮንቶስ ፪ ም ፩፥፩-፲፫(1፥1-13)
ጳውሎስ ሐዋርያሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ…


👉ንፍቅ ዲያቆን
📖 ጴጥሮስ ፩ ም ፩፥፮-፲(1፥6-10)
ወባሕቱ ኅዳጠ ይእዜ ሀለወክሙ…


👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፰፥፩-፱(8፥1-9)
ወውእተ አሚረ ዐቢይ ምንዳቤ ኮነ…

📖ምስባክ ዘቅዳሴ

የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ።
ኢይመውት ዘእንበለ ዘአሐዩ።
ወእነግር ግብሮ ለእግዚአብሔር።

👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፲፯ ቊ. ፲፮ - ፲፯

፲፮ የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገችኝ፤ የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች።

፲፯ አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ።


📖ወንጌል ዘቅዳሴ

የሉቃስ ወንጌል ም. ፫ ቊ. ፲ - ፲፱
ወተስእልዎ ሕዝብ ወይቤልዎ...

📜ቅዳሴ


👉ዘባስልዮስ


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

❖ ግንቦት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

++ አባ ዓቢየ እግዚእ ++

❖ጐንደር ከተማ ነዋሪ ከሆኑ: ወይም ከተማዋን
የሚያውቁዋት ከሆነ አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎ:: (እንደ ወትሮው ሁሉ) ከተማዋ ውስጥ ጅብና እባብን
የመሠሉ አራዊት ነዋሪውን ሲገድሉ: ወይም ሲያቆስሉ
ተመልክተው: ካልሆነም በታሪክ ሰምተው ያውቃሉ?

☞ መልስዎ "በጭራሽ አላውቅም" እንደሚሆን
እገምታለሁ:: (ምክንያቱም ሆኖ አያውቅማ!)

+ነገሬን እንዲረዱኝ ሌሎች የሃገራችን ዋና ዋና ከተሞችን
ልብ ይበሉልኝ:: እንኳን በሌሊት በቀንም አራዊቱ
አይጠፉባቸውም::

"ታዲያ ጐንደር ከተማ ውስጥ ጅብ የማይገባው: እባብና
ጊንጥ ሰው የማይገድለው ግን ለምን?" ካሉ በጻድቁ
በአባ ዓቢየ እግዚእ ቃል ኪዳን ምክንያት ነው:: (ሁሉም የሃገራችን ከተሞች የተባረኩ መሆናቸውን ሳንዘነጋ ማለት ነው)

+ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን
ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ
ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ:: አጥምቀው
'ዓቢየ እግዚእ' ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጉመ
መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም "በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው"
ማለት ነው::

+ዓቢየ እግዚእ በሕጻንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ
ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ
ከሐዲስ ጠነቀቁ::
ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ
እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኩሰዋል::

+በገዳሙ በጾም: በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ
በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን
አግኝተዋል::
በጊዜው በ40 ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ
ይበሉ ነበር::

+ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ
ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን
አፍርተዋል::
ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ
አባትም ነበሩ:: ከትግራይ እስከ ደንቢያ ደግሞ ሃገረ
ስብከታቸው ነው::

+አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት
ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ:: ቀኑ ነሐሴ 10
ነውና ተከዜ
እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ3 ቀናት ባለመጉደሉ ከ1,000 በላይ
ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ:: ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ-
አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው
ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ::

+ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ
ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ:: ይሕን ድንቅ ያዩ ከ1,000
በላይ
አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል:: ይሕም
ዘወትር ነሐሴ 10 ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር)
ይከበራል::

+ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ:: ያኔ ጐንደር በቀሃና
አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች:: ጻድቁ
ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት
ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር::

+በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሠል አራዊት
ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት:: ይሕንን የተመለከቱት አባ
ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ:: በፍጹም ልባቸውም
ስለ ሕዝቡ ለመኑ::

+የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምሕ
የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት
አይሠለጥኑባቸውም::
በሰማይም እሳትን አያዩም:: ጐንደርንም አራዊት ገብተው
ሰውን አይጐዱም::" ብሏቸው አርጓል::

+ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ
ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል::
ይሔው እኛ ምን ብንከፋ: ጻድቁንም ብንረሳቸው
እግዚአብሔር ግን ዛሬም በጻድቁ ምልጃ ከተማዋን ጠብቆ
ይኖራል:: ነገን ደግሞ እርሱ ያውቃል:: ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ቦታ (ጎንደር ቀበሌ 09 ኪዳነ ምሕረት) ጻድቁ የጸለዩበት ቦታ
ነው:: እንኳን በወርሃዊ በዓላቸው (በ19) ይቅርና
በዓመታዊ በዓላቸው (ግንቦት 19) ለንግስ የሚመጣው
ሰው ቁጥር ያስተዛዝባል::

+አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት
በቅድስና ኑረው: 3 ሙታንን አስነስተው: ብዙ ድውያንን
ፈውሰው: ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው: የድኅነት ቃል ኪዳንም
ተቀብለው: በ140 ዓመታቸው ግንቦት 19 ቀን አርፈዋል::
የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እባካችሁ እናስባቸው::

+<< ተአምሪሁ ለጻድቅ አቡነ ዓቢየ እግዚእ - - - ጸሎቱ
ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ
ዓለም:: አሜን:: >>+

+<< ከብዙ ተአምራቱ አንዱን >>+

=>ጻድቁ አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው #ተንቤን
(መረታ) ሳሉ አንዲት መበለት መጥታ "አባቴ!
የምጠጣውን ጸበል ባርከህ ስጠኝ?" አለቻቸው:: ጻድቁም
በውሃው ላይ ጸሎትን አድርሰው : በመስቀላቸው ባርከው
ሰጧት::

+ወደ ባልንጀራዋ ስትደርስ ግን ሐሳቧን ቀየረችና
"ልጠጣው" ብላ የተቀበለችውን ማይ (ጸበል)
ልትጠመቅበት (ልትጸበልበት) ወሰነች:: ባልንጀራዋንም
"በላዬ ላይ አፍሺልኝ" ስትል አዘዘቻት::

+ባልንጀራዋም "እሺ" ብላ ልታፈስላት (ልትጸብላት) በፋጋ
(ግማሽ ቅል) ያለውን ጸበል አነሳች:: ልታፈሰው
ስትዘቀዝቀው ግን ከሆነው ነገር የተነሳ 2ቱም ደነገጡ::
ጸበሉ የረጋ ደም ወደ መሆን በቅጽበት ተለውጧልና::

+ፍጹም ፍርሃት የወደቀባቸው ሴቶቹ እየተሯሯጡ ወደ አባ
ዓቢየ እግዚእ በዓት ደረሱ:: ከውጭ ሆነውም "አባ! አባ!
የሰጠኸን ጸበልኮ የረጋ ደም ሆነ" አሏቸው:: ጻድቁም
እንዳላዋቂ "ምን አጠፋችሁ?" ሲሉ ጠየቁ::

+"አባታችን! ምንም አላጠፋንም:: ብቻ አፍሺልኝ ብየ
ስሰጣት እንዲህ ሆነ" ስትል አንዷ መለሰች:: ጻድቁ ግን
በየውሃት "ልጆቼ! ሁሌም : 'ምንም አላጠፋንም'
አይባልም:: ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና::

+ . . . አንቺም ልጄ! እኔን ያልሺኝ 'የምጠጣው ጸበል
ስጠኝ' ነበር:: ግን ልትጸበይበት ወደድሽ:: ስሕተትሽ ከዚህ
ይጀምራል:: (የቅዳሴ ጸበል ለመጸበል አይሆንምና)
¤በዚያ ላይ "አልቦ ዓቢይ ኃጢአት ከመ ወልጦ ቃል . . .
ከውሸት በላይ ከባድ ኃጢአት የለም::" (ዮሐ. 8:44)

+ . . . በተጨማሪ ደግሞ ያለ ስልጣኗ እህትሽን
'አጥምቂኝ' አልሻት:: ስለነዚህ ነገሮች ጸበሉ
ተለውጦባቹሃል" ብለው ወደ ጸበሉ በመስቀል አማተቡ::
"እፍ" ሲሉትም የረጋ ደም የነበረው ማይ ወደ ጸበልነቱ
ተመለሰ:: ይህንን ያዩ ሴቶቹ በግንባራቸው ተደፍተው
ለጻድቁ ሰገዱ::

=>ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን
ለዓለመ ዓለም:: አሜን::

❖አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ
ይሠውርልን::

❖ግንቦት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
2.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም (የ12ቱ ሐዋርያት መቃብር
ከጌታ የተገለጠላቸው ኢትዮዽያዊ)
3.አቡነ ብስጣውሮስ ዘሐይቅ እስጢፋኖስ (ኢትዮዽያዊ)
4.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ታላቁ (7 ጊዜ ሙቶ የተነሳ)
5."805,007" ሰማዕታት (በአንድ ቀን ብቻ የተገደሉ)
6.አባ ይስሐቅ ገዳማዊ

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2፡ ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3፡ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ
4፡ አባ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ
++"+ በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ::
አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ::
በእኔ ተማምኗልና አስጥለዋለሁ::
ስሜንም አውቁዋልና እጋርደዋለሁ::
ይጠራኛል እመልስለትማለሁ::
በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ::
አድነዋለሁ: አከብረውማለሁ::
ረጅም እድሜን አጠግበዋለሁ::
ማዳኔንም አሳየዋለሁ:: +"+ (መዝ. 90:13-16)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>