ከአንጾኪያ ተገኝቶ በዓለም ላይ የሚያበራው ኮከብ፣ በ447 ዓ.ም ተወልዶ ለዘመናት የገነነው ሊቅ እንዲህ ይላል፦
በዚህ ዓለም የምንፈራው ምንድን ነው? ሞትን ነው? በጭራሽ! ለእኔ ሕይወቴ ክርስቶስ ነው፡፡ ሞትም እንዲሁ፡፡ ስደት ነው? ዓለምና በውስጡ ያለው ሁሉ የእግዚአብሔር ነው፡፡ የሀብት መጥፋት ነው? ወደ ዓለም ምንም አላመጣንም፡፡ ከዓለምም ምንም ነገር ይዘን እንዳንወጣ የታወቀ ነው፡፡ የዓለምን ሽብርና ፍርሀት እንደ ቁም ነገር አልቆጥረውም፡፡ ሀብቱንና ሕይወቱንም እንደ ኢምንት አየዋለሁ፡፡ ድህነትንም አልፈራም፡፡ ሀብትንም አልመኝም፡፡ ለሞት አልሸበርም፡፡ በሃይማኖትና በምግባር እንድትጎለብቱ ምናልባት ትንሽም ቢሆን እንድረዳችሁ ካልሆነ በቀር በዚህ ዓለም ስለ መኖር ወደ ፈጣሪዬ አልጸልይም፡፡ ስለዚህ የተወደዳችሁ ወገኖቼ ሆይ! እየሆነ ባለው ነገር አትጨነቁ እላችኋለሁ፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ!

https://t.me/zekidanemeheret
🕐 ግንቦት 14/09/2015 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፴፥፲፩(30፥11)
ወእለኒ ይሬእዩኒ አፍኣ ይጐዩ እምኔየ
ቀብፁኒ እምልብ ከመ ዘሞተ
ወኮንኩ ከመ ንዋይ ዘተኀጕለ
📖ወንጌል
ወንጌል ዘማርቆስ ፲፬፥፰፮-፸፪(14፥66-72)
ወእንዘ ሀሎ ጴጥሮስ…
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ገላትያ ፮፥፲፩-፲፰(6፥11-18)
ርእዩ ዘከመ ጸሐፍኩ ለክሙ…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖 ጴጥሮስ ፩ ም ፬፥፲፪-፲፯(4፥12-17)
አኃዊነ ኢታንክርዋ…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፬፥፴፩-፴፯(4፥31-37)
ወእንዘ ይጼልዩ አድለቅለቀ…
📖ምስባክ ዘቅዳሴ
ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር
እግዚኦ አነ ገብርከ።
ገብርከ ወልደ አመትከ።
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፲፭ ቊ. ፲፭ - ፲፮
፲፭ የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።
፲፮ አቤቱ እኔ ባሪያኽ ነኝ ባሪያኽ ነኝ የሴት ባሪያኽም ልጅ ነኝ፤ሰንሰለቴን ሰበርኽ።
📖ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲ ቊ. ፯ - ፲፮
ወሐዊረክሙ ስብኩ...
📜ቅዳሴ
👉ዘሠለስቱ ምዕት (ግሩም)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️

✝✝✝ እንኩዋን የመነኮሳት አባት ለተባለው "ቅዱስ ዻኩሚስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝
+*" ቅዱስ ዻኩሚስ (አባ ባኹም) "*+
=>ዛሬን አያድርገውና ምንኩስና ማለት መላእክትን መስሎ የሚኖርበት ሕይወት ነበር:: ምንኩስና በእግዚአብሔር ፈቃድ በአባ እንጦንስ ቢመሠረትም ሕይወቱን በማስፋፋት ደረጃ የቅዱስ ዻኩሚስን ያሕል የደከመና የተሳካለት ግን የለም::
+ቅዱሱ በትውልዱ ግብፃዊ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን ከቀደመ ሕይወቱ ጋር በተያያዘ የሚተረክ ነገር በመጽሐፈ ገድሉ ላይ አለ:: ዻኩሚስ ወደ ምንኩስናው ዓለም የመጣ በታላቁ አባ ዸላሞን አማካኝነት ነው:: ለተወሰነ ጊዜም መንፈሳዊ አባቱን እየረዳ ሕይወተ መነኮሳትን አጥንቷል::
+በመንፈሳዊ ሕይወቱና በተጋድሎ እየበረታና እየደረጀ ሲሔድ ከአባ ዸላሞን ተለይቶ : ማሕበር መስርቶ ለመኖር አምላኩን ጠይቆ ፈቃድ በማግኘቱ በሕግ የሚመራ የመጀመሪያውን ገዳም መሥርቷል::
+ቅዱስ ዻኩሚስ ጸሎቱ አጋንንትን ከአካባቢው አያስቀርባቸውም ነበር:: አካሉ አልቆ በአጥንቶቹ እስኪቆም ድረስ ጾሟል:: ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ሕማማት እያሰበ ከእንባ ጋር ይሰግዳል:: እንባውና ላበቱ ከፊቱ እየወረደ አካባቢው ጭቃ ይሆን ነበር:: ጌታችንም መስቀል ተሸክሞ ይታየው ነበር::
+ስለ ክብሩም መላእክት ወደ ሰማይ ወስደው ገነትና ሲዖልን አሳይተውታል:: አባታችን ቅዱስ ዻኩሚስ ከርሕራሔው የተነሳ አጋንንት ያደሩባቸውን ሰዎች ሲያገኝ በቀጥታ ከመፈወስ ይልቅ ደዌውን : ርኩሳን መናፍስቱንም ወደ እርሱ እንዲገለበጡ ያዛቸው ነበር::
+ከዚያም በጾም : በጸሎትና በስግደት ያማስናቸዋል:: ያኔ በግዳቸው እየጮሁ ሲወጡ ደጉ አባት "ምነው ትንሽ ቆዩ እንጂ" ይላቸዋል::
+አጋንንቱም እያደነቁ "ከገነት ካስወጣነው ከአዳም በቀር እንዲህ ዓይነት ፍጡርስ ዓይተን አናውቅም" ብለው እንደ ጢስ በነዋል:: አጋንንት ስለሚፈሩት "አርበኛው መነኩሴ" ይሉታል::
<<< የቅዱስ ዻኩሚስ ፍሬዎች >>>
1.በግብፅ በርካታ ገዳማትን አቁዋቁሟል::
2.ለሁሉም ገዳማት አበ ምኔቶችን ሹሞ እየዞረ ይጠብቃቸው ነበር::
3.የመጀመሪያውን ሥርዓተ መነኮሳት አዘጋጅቷል::
4.መነኮሳት ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ሹመት እንዳይሾሙ ከልክሏል::
5.መነኮሳት ከገዳማቸው በፍፁም እንዳይወጡ ከልክሏል::
6.ከግብፅ ውጪ ምንኩስናን ያስፋፉ አባቶችን አስተምሮ አመንኩሷል:: (ለምሳሌ በኢትዮዽያ ምንኩስናን ያስፋፉት አቡነ አረጋዊ የዚህ አባት ደቀ መዝሙር ናቸው)
+ከዚሕም ባለፈ በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል:: ቅዱስ ዻኩሚስ ጫማ ሳይጫማ: እሾህን ሳይሰቀቅ ይረግጥም ነበር:: የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እጥፍ ሆኖ የበዛለት ቅዱሱ መነኮስ ወደ ወደደው እግዚአብሔር በዚህች ቀን ሔዷል::
=>የጻድቁ መነኮስ ጸጋና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::
=>ግንቦት 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ዻኩሚስ (አበ መነኮሳት ሣልሳዊ)
2.አባ ሲማኮስ ሰማዕት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
5.አባ ስምዖን ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት
=>+"+ ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም:: በእናት ማሕጸን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ:: ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ:: ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ:: ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው:: +"+ (ማቴ. 19:11)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

የሚያምኑ ፍጥረታት እነማንናቸው? የሚያምኑ ፍጥረታት ምን አላቸው? || ክፍል 5
👇👇👇👇
https://youtu.be/NhAoGcxNJBc
https://youtu.be/NhAoGcxNJBc
https://youtu.be/NhAoGcxNJBc
👇👇👇👇
https://youtu.be/NhAoGcxNJBc
https://youtu.be/NhAoGcxNJBc
https://youtu.be/NhAoGcxNJBc
https://t.me/zekidanemeheret
🕐 ግንቦት 15/09/2015 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፴፩፥፪(31፥2)
ብፁዕ ብእሲ ዘኢኈለቈ ሎቱ እግዚአብሔር ኃጢአቶ
ወዘአልቦ ጽልሑት ውስተ ልቡ
እስመ አርመምኩ በልያ አዕፅምትየ
📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፩፥፵፬-፶፪(1፥44-52)
ወበሣኒታ ፈቀደ ይሑር ገሊላ…
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ሮሜ ፰፥፳፬-፴፭(8፥24-35)
ወተሰፍዎስ ለዘያስተርኢ ኢኮነ ተስፋ…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ይሁዳ ፩፥፲፯-፳፫(1፥17-23)
ወአንትሙሰ አኃዊነ…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፩፥፲፪-፲፭(1፥12-15)
ወእምዝ ተሠውጡ ኢየሩሳሌም…
📖ምስባክ ዘቅዳሴ
አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ
ውስተ ኲሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ።
ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ።
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፲፰ ቊ. ፫ - ፬
፫ ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም።
፬ ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።
📖ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲ ቊ. ፩ - ፲፮
ወጸውዖሙ ለ፲ወ፪ አርዳኢሁ...
📜ቅዳሴ
👉ዘሐዋርያት (ዘበደኃሪ)

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ግንቦት 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ቅዱስ ናትናኤል +"+
+በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት
መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ
ሐዋርያ ነው::
+ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእሥራኤላውያን ወላጆቹ
ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው:: ይህ በምን
ይታወቃል ቢሉ
እርሱ ሕጻን እያለ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ
እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል:: እናቱ
በቅርጫት ውስጥ
አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው
ነበር::
+ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል::
በባልንጀሮቹ
ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና አካባቢ
ስላደገ): አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር::
ምሑረ ኦሪት
ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር::
+በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል
የአጎት ልጅ ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ
የጠራበት አንዱ
ምክንያትም ይሔው ነው::
+ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ: ከበለስ ቁጭ
ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ" እያለም
ይተክዝ
ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን
አውቆ በፊልዾስ አማካኝነት ጠርቶታል::
+ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በኋላ ግን የጌታችንን
ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት
ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እሥራኤላዊ" ሲል
አመስግኖታል::
+ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር
ምስጢረ መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ
ቅዱስም ሰክሮ ብዙ
አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ
ክርስቶስ) መልሷል:: እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል::
+የጌታችን ወንድም የተባለ ቅዱስ ያዕቆብ በአይሁድ
ከተገደለ በኋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም 2ኛ
ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ
አገልግሏል:: ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ ደርሶበታል::
በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት አልፏል::
በገድለ
ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሱ ሰማዕት የሆነው
በ150 ዓመቱ ነው:: ያ ማለት ደግሞ ከሐዋርያት አባቶች
በመጨረሻ
ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል::
❖እግዚአብሔር በቅዱስ ናትናኤል ምልጃ ሃገራችንን
ከጥፋት: ሕዝቦቿንም ከመቅሰፍት ይሰውርልን::
ከበረከቱም አይለየን::
=>ግንቦት 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን)
2.ቅዱስ ሚናስ ባሕታዊ
3.ቅዱስ ቀርጢኖስ ሰማዕት
4."400" ቅዱሳን ሰማዕታት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
3.ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ
4.ቅድስት እንባ መሪና
5.ቅድስት ክርስጢና
=>+"+ ጌታ ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ 'ተንኰል የሌለበት በእውነት የእሥራኤል ሰው እነሆ' አለ:: ናትናኤልም 'ከወዴት ታውቀኛለህ?' አለው:: ጌታ ኢየሱስም መልሶ 'ፊልዾስ ሳይጠራህ ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ' አለው:: ናትናኤልም መልሶ 'መምሕር ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ:: አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ' አለው:: +"+ (ዮሐ. 1:48-51)

🕐 ግንቦት 16/09/2015 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፶፥፲፱(50፥19)
አመ ትሠምር መሥዋዕተ ጽድቅ
መባዕኒ ወቍርባነኒ
አሜሃ ያዐርጉ ውስተ መሥዋዒከ አልሕምተ
📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፲፬፥፳፱-፴፩(14፥29-31)
ወይእዜኒ ነገርኩክሙ ዘእንበለ…
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቈላስይስ ፪፥፩-፮(2፥1-6)
ወእፈቅድ ታእምሩ መጠነ እትጋደል…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ራዕይ ዮሐንስ ፩፥፩-፲፪(1፥1-12)
ራእዩ ለዮሐንስ …
ዓዲ፦ 📖ዮሐንስ ፩ ም ፩፥፩-፲(1፥1-10)
ንዜንወክሙ በእንተ ውእቱ...
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፰፥፲፬-፳፮(8፥14-26)
ወሶበ ሰምዑ ሐዋርያት…
📖ምስባክ ዘቅዳሴ
ወአርመመ ማዕበል
ወተፈሥሑ እስመ አዕረፉ
ወመርሆሙ ውስተ መርሶ ኀበ ፈቀዱ
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፮ ቊ. ፳፱ - ፴
፳፱ ሞገዱም፡ዝም፡አለ።
፴ ዝም፡ብሏልና፥ደስ፡አላቸው፤ወደ፡ፈለጉትም፡ወደብ፡መራቸው።
📖ወንጌል ዘቅዳሴ
የዮሐንስ ወንጌል ም. ፳፩ ቊ. ፳ - ፳፭
ወተመይጦ ጴጥሮስ ርእዮ...
📜ቅዳሴ
👉ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
🕐 ግንቦት 16/09/2015 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፶፥፲፱(50፥19)
አመ ትሠምር መሥዋዕተ ጽድቅ
መባዕኒ ወቍርባነኒ
አሜሃ ያዐርጉ ውስተ መሥዋዒከ አልሕምተ
📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፲፬፥፳፱-፴፩(14፥29-31)
ወይእዜኒ ነገርኩክሙ ዘእንበለ…
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቈላስይስ ፪፥፩-፮(2፥1-6)
ወእፈቅድ ታእምሩ መጠነ እትጋደል…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ራዕይ ዮሐንስ ፩፥፩-፲፪(1፥1-12)
ራእዩ ለዮሐንስ …
ዓዲ፦ 📖ዮሐንስ ፩ ም ፩፥፩-፲(1፥1-10)
ንዜንወክሙ በእንተ ውእቱ...
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፰፥፲፬-፳፮(8፥14-26)
ወሶበ ሰምዑ ሐዋርያት…
📖ምስባክ ዘቅዳሴ
ወአርመመ ማዕበል
ወተፈሥሑ እስመ አዕረፉ
ወመርሆሙ ውስተ መርሶ ኀበ ፈቀዱ
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፮ ቊ. ፳፱ - ፴
፳፱ ሞገዱም፡ዝም፡አለ።
፴ ዝም፡ብሏልና፥ደስ፡አላቸው፤ወደ፡ፈለጉትም፡ወደብ፡መራቸው።
📖ወንጌል ዘቅዳሴ
የዮሐንስ ወንጌል ም. ፳፩ ቊ. ፳ - ፳፭
ወተመይጦ ጴጥሮስ ርእዮ...
📜ቅዳሴ
👉ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
†✝† በስመ አብ: ወወልድ: ወመንፈስ ቅዱስ: አሐዱ አምላክ †✝†
†✝† ግንቦት 16 †✝†
†✝† ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ †✝†
=>አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው:: ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ: በገሊላ አካባቢ አድጐ: ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል::
+ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር:: ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው:: ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል::
+ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ:: ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ:: ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል:: ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል:: ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው::
+ቅዱስ ዮሐንስ በታናሽ እስያ ለ7ቱ አብያተ ክርስቲያናት መስበኩ ይታሰባል:: ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው:: ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል::
+3 መልዕክታት: ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል:: ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል:: ከእሳት እስከ ስለት: እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል::
††† ቅዱሱ በኤፌሶን †††
=>ይህቺ ኤፌሶን የሚሏት ሃገር መገኛዋ በቀድሞው ታናሽ እስያ (አሁን ቱርክ አካባቢ) ሲሆን ብዙ ሐዋርያት አስተምረውባታል:: ያም ሆኖ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ያመጣች አልነበረችምና ቅዱስ ዮሐንስ ሊሔድ ተነሳ::
+ከደቀ መዛሙርቱ መካከልም ቅዱስ አብሮኮሮስን (ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው) አስከትሎ እየጸለዩ በመርከብ ላይ ተሳፈሩ:: ሐዋርያት አበው መከረኞች ናቸውና ማዕበል ተነሳባቸው:: በጥቂት አፍታም መርከባቸው በማዕበሉ ተበታተነች::
+ቅዱስ አብሮኮሮስ በስባሪ ላይ ተሳፍሮ ወደ አንዲት ደሴት ደረሰ:: ከንጹሑ መምሕሩ ቅዱስ ዮሐንስ ተለይቷልና አለቀሰ:: ፍቁረ እግዚእ ግን ያለ ምግብና ውሃ ማዕበለ ባሕር እያማታው ለ40 ቀናት ቆየ::
+እርሱ በፈጣሪው ፍቅር የተመሰጠ ነበርና አለመመገቡ አልጐዳውም:: በ40ኛው ቀን ግን ደቀ መዝሙሩ ወዳለበት ደሴት ማዕበሉ አደረሰው:: 2ቱ ቅዱሳን ተፈላልገው ተገናኙ:: እጅግም ደስ ብሏቸው ፈጣሪን አመሰገኑ::
+አምላካቸው ወደዚህች ደሴት ያመጣቸው በጥበቡ ነውና ሲዘዋወሩ 2 ነገርን አስተዋሉ::
1ኛ የደሴቷ ሁሉም ነዋሪ የሚያመልኩት ጣዖትን ነው::
2ኛ አብዛኞቹ የቤተ መንግስት ውላጆች ናቸው:: ሮምና የሚሏት አንዲት ሴት ደግሞ እነዚህን ሁሉ እየመገበች ታስተዳድራለች::
+ቅዱሳኑ በቦታው በቀጥታ ትምሕርተ ወንጌልን ቢናገሩ እንደ ማይቀበሏቸው ስለ ተረዱ ሌላ ፈሊጥን አሰቡ:: እንዳሰቡትም ወደ እመቤት ሮምና ቤት ሒደው በባርነት ተቀጠሩ::
+ለእርሷም "ድሮ የአባትሽ ባሮች የነበርን ሰዎች ነን" ስላሏት 2ቱን ቅዱሳን እሳት አንዳጅና ገንዳ አጣቢ አደረገቻቸው:: ለሰማይ ለምድሩ የከበዱ እነዚህ ቅዱሳን የካዱትን ይመልሱ ዘንድ በባርነት ግፍን ተቀበሉ:: የመከር (የማሳመኛ) ጊዜ ሲደርስም አንዳች አጋጣሚ ተፈጠረ::
+ቅዱሳኑ ዮሐንስና አብሮኮሮስ ወደ መታጠቢያ ቤቱ ሲገቡ ሰይጣን በውስጥ ኖሮ ደንግጧልና እወጣለሁ ብሎ ሲሮጥ የንጉሡን ልጅ ረግጦ ገደለው:: ሮምናና የአካባቢው ሰዎች ከበው ሲላቀሱ ቅዱሳኑ ቀረቡ::
+ሮምና ግን በቁጣ "ልትሣለቁ ነው የመጣችሁ?" በሚል ቅዱስ ዮሐንስን በጥፊ መታችው:: መላእክት እንኩዋ ቀና ብለው ሊያዩት የሚከብዳቸው ሐዋርያ ይህንን ታገሰ:: በጥፊ ወደ መታችው ሴት ቀረብ ብሎም "አትዘኚ! ልጁ ይነሳል" አላትና ጸለየ::
+ወደ ሞተውም ቀረብ ብሎ በጌታችን ስም አስነሳው:: በዚህ ጊዜም ሮምናን ጨምሮ በሥፍራው የነበሩ ሰዎች ለቅዱስ ዮሐንስ ሰገዱ:: እርሱ ግን ሁሉንም አስነስቶ ትምሕርተ ሃይማኖትን: ፍቅረ ክርስቶስን ሰበከላቸው::
+በስመ ሥላሴ አጥምቆ: ካህናትን ሹሞ: ቤተ ክርስቲያንም አንጾላቸው ወጥቷል:: በሁዋላም ለሮምናና ለደሴቷ ሰዎች ክታብ (መልዕክትን) ጽፎላቸዋል:: ይህች መልዕክት ዛሬ 2ኛዋ የዮሐንስ መልዕክት ተብላ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትታወቃለች::
+ቅዱስ ዮሐንስ ቀጥሎ የተጉዋዘው ወደ ኤፌሶን ነው:: በዚህች ከተማ የምትመለክ አርጤምስ (አርጢሞስ) የሚሏት ጣዖት ነበረች:: አርጤምስ ማለት መልክ የነበራት ትዕቢተኛ ሴት ስትሆን አስማተኛ ባሏ ነው እንድትመለክ ያደረጋት::
+ቅዱስ ዻውሎስ ብዙ ምዕመናን ከእርሷ እንዲርቁ ማድረግ ችሏል:: ጨርሶ ያጠፋት ግን ቅዱስ ዮሐንስ ነው:: በቦታውም ብዙ ግፍ ደርሶበት: በርካታ ተአምራትን አድርጉዋል:: ቤተ ጣዖቱንም በተአምራት አፍርሶታል::
††† የፍቅር ሐዋርያ †††
=>ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን 'የፍቅር ሐዋርያ' ትለዋለች:: ለ70 ዘመናት በቆየ ስብከቱ ስለ ፍቅር ብዙ አስተምሯል:: ፍቅርንም በተግባር አስተምሯል:: በየደቂቃውም "ደቂቅየ ተፋቀሩ በበይናቲክሙ - ልጆቼ ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ" እያለ ይሰብክ ነበር::
+በተለይ ደግሞ ከፈጣሪው ክርስቶስ ጋር የነበረው ፍቅር ፍጹም የተለየ ነበር:: በዚህ ምክንያትም ጌታ ባረገ ጊዜ እንዲህ ብሎታል:- "ለፍጡር ከሚገለጥ ምሥጢር ከአንተ የምሠውረው የለኝም" ብሎታል::
+ቀጥሎም በንጹሕ አፉ ስሞታል:: ሊቁ:-
"ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ:
ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ" እንዳለው:: (መልክዐ ኢየሱስ)
=>ቅዱስ ዮሐንስ ከእመቤታችንም ጋር ልዩ ፍቅር ነበረው:: እርሷ እንደ ልጇ ስትወደው: እርሱ ደግሞ እንደ እናቱ ልቡ እስኪነድ ድረስ ይወዳት ነበር:: እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ ተከትሎ ያገኛት እመቤቱ ናትና::
+ከዚያ ሁሉ ጸጋና ማዕረግ የመድረሱ ምሥጢርም ድንግል ናት:: ለ15 ዓመታት በጽላሎተ ረድኤቷ (በረዳትነቷ ጥላ) ተደግፎ አብሯት ሲኖር ብዙ ተምሯል:: ከመላእክትም በላይ ከብሯል:: ከንጽሕናዋ በረከትም ተካፍሏል::
+ስለ ድንግል ማርያምም "ነገረ ማርያም" የሚል ድርሰት ሲኖረው "የሰኔ ጐልጐታንም" የጻፈው እርሱ ነው::
+ድንግል ባረፈችበት ቀንም ልክ እንደ ልጇ ክርስቶስ እርሷም ስማው: ታቅፋው ዐርፋለች:: ሊቃውንቱ ለዚህ አይደል በንጹሕ ከንፈሮቿ መሳምን (መባረክን) ሲሹ:-
"በከመ ሰዓምኪ ርዕሰ ዮሐንስ ቀዳሚ:
ስዒሞትየ ማርያም ድግሚ" ያሉት::
+ታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነው ጊዜ ተሰውሯል:: ከዚያ አስቀድሞም የዓለምን ፍጻሜ ተመልክቷል:: ዛሬ ያለበትን የየሚያውቅ ቸር ፈጣሪው ነው::
††† ይሕች ዕለት ለሐዋርያው ቅዳሴ ቤቱ ናት:: †††
=>እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው:-
*ወንጌላዊ
*ሐዋርያ
*ሰማዕት ዘእንበለ ደም
*አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
*ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
*ወልደ ነጐድጉዋድ
*ደቀ መለኮት ወምሥጢር
*ፍቁረ እግዚእ
*ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
*ቁጹረ ገጽ
*ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
*ንስር ሠራሪ
*ልዑለ ስብከት
*ምድራዊው መልዐክ
*ዓምደ ብርሐን
*ሐዋርያ ትንቢት
*ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
*ኮከበ ከዋክብት

=>በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር::
=>ቅዱስ ዮሐንስን የወደደ ጌታ በፍቅሩ ይጠግነን:: ከእናቱ ፍቅር አድርሶ በሐዋርያው በረከት ያስጊጠን::
=>ግንቦት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ስብከቱና ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ኢያሱ ሲራክ ነቢይና ጠቢብ (መጽሐፈ ሲራክን የጻፈ)
3.ቅድስት እናታችን ዐስበ ሚካኤል (ኢትዮዽያዊት)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ (የቅ/ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
7.አባ ዳንኤል ጻድቅ
=>+"+ በጌታ ኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ: የእናቱም እህት: የቀለዮዻም ሚስት ማርያም: መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር:: ጌታ ኢየሱስም እናቱን: ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን 'አንቺ ሆይ! እነሆ ልጅሽ' አላት:: ከዚህ በሁዋላ ደቀ መዝሙሩን 'እናትህ እነሁዋት' አለው:: ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት:: +"+ (ዮሐ. 19:25)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††