#ቀዳም_ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ)
የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ብዙ ስያሜዎች አሏት፦
#ቀዳም_ሥዑር፡-
በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡
#ለምለም_ቅዳሜ፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡
(የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡)
#ቅዱስ_ቅዳሜ፡-
ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡
(ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም)
@zekidanemeheret

እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ ብልህ አገልጋይ ቢኖር፥ እርሱ ወደ ጌታው ሐሴት ገብቶ ዕልል ይበል፡፡
በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡
በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡ በስድስተኛው ሰዓት የደረሰ ቢኖር፥ አይጎድልበትምና አይጠራጠር፡፡ እስከ ዘጠነኛ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ሳይጠራጠር ይቅረብ፡፡ እስከ ዐሥራ አንደኛዋ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ስለ መዘግየቱ አይደንግጥ፡፡ ጌታ ቸር ነውና፤ በመጨረሻ የመጣውንም እንደ መጀመሪያው አድርጐ ይቀበሏልና፡፡ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ለመጣው ከመጀመሪያው ሰዓት አንሥቶ ሲደክም ከነበረው ጋራ እኩል ይሰጧልና፡፡
መጨረሻ ለመጣው ጌታ ምሕረቱን ይለግሰዋል፤ መጀመሪያ ለመጣውም ያስብለታል፡፡ ለአንደኛው ይሰጠዋል፤ ለሌላኛውም ጸጋውን ያድለዋል፡፡ ለአንደኛው መልካም ምግባሩን ይቀበልለታል፡፡ ለሌላኛውም መልካም ፍቃዱን ይቀበልለታል፡፡ ለአንዱ ምግባሩን ያከብርለታል፤ ለሌላኛውም በቅን ልቡና የሚያደርገውን ጥረት ያደንቅለታል፡፡ ስለዚህ ኹላችሁም ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ፡፡
ፊተኞች ኋለኞችም ሆይ! እኩል ደመወዛችሁን ተቀበሉ፡፡ ባለጸጐች ድኾችም ሆይ! በአንድነት ዘምሩ፡፡ እናንተ ብርቱዎች ደካሞችም ሆይ! በዓሉን አክብሩት፡፡ እናንተ የጾማችሁ መጾም ያልቻላችሁም ሆይ! ዛሬ ላይ ደስ ይበላችሁ፡፡
መሠዊያው ሙሉ ነውና ኹሉም በማዕዱ ደስ ይበለው፡፡ ፍሪዳው የሰባ ነውና አንድ ሰው ስንኳ እንደ ተራበ እንዳይሔድ፡፡ ኹላችንም የእምነት በዓሉን እንካፈል፤ ከቸርነቱና ከፍቅሩ ሀብትም እንቋደስ፡፡
ማንም ስለ ድኽነቱ አይዘን፥ ኵላዊቷ መንግሥት ተገልጣለችና፡፡ ማንም በኃጢአቱ አያንባ፥ ከመቃብሩ የይቅርታ ብርሃን ተንቦግቧልና፡፡ ማንም ሞትን አይፍራ፥ የመድኃኒታችን ሞት ከዚህ ነጻ አውጥቶናልና፡፡ ለእርስዋ በመታዘዝም ጌታ አጥፍቷታልና፡፡
በሞቱ ሞትን ገደለው፡፡ ወደ ሲዖል በመውረድ ሲዖልን በዘበዘው፡፡
ኢሳይያስም አሰምቶ እንደ ተናገረ ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም! ከንቱ አድርጓታልና መረራት! ሸንግሏታልና መረራት! ሽሯታልና መረራት!
ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት!
[መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤ ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም!
ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

"በእርግጥም በዓል ተከበረ የሚባለው ሰዎች ነፍሳቸውን ካዳኑበት፣ ውስጣዊ ሰላምንና ፍቅረ ቢጽን ገንዘብ ካደረጉበት፣ እለት እለት ከሚያጋጥማቸው የነፍስ መታወክ ካረፉበት፣ ያለሁካታና ጋጋታ እንዲሁም እንስሳትን በማረድ ከልክ በላይ ከሆነ መብልና መጠጥ ርቀው ያከበሩ እንደሆነ ነው።"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንልን
@zekidanemeheret
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንልን
@zekidanemeheret
ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ pinned «"በእርግጥም በዓል ተከበረ የሚባለው ሰዎች ነፍሳቸውን ካዳኑበት፣ ውስጣዊ ሰላምንና ፍቅረ ቢጽን ገንዘብ ካደረጉበት፣ እለት እለት ከሚያጋጥማቸው የነፍስ መታወክ ካረፉበት፣ ያለሁካታና ጋጋታ እንዲሁም እንስሳትን በማረድ ከልክ በላይ ከሆነ መብልና መጠጥ ርቀው ያከበሩ እንደሆነ ነው።" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንልን @zekidanemeheret»
"በወንጌል መምጣት ኦሪት እንደቀረች፣ በሐዋርያትም ስብከት የነቢያት ትንቢት እንደጠፋ፣ ሰንበት ትንሳኤ በኾነባት በእሑድ እንደተሻረች የሚናገሩ አሉ፡፡ እኛ ግን ኦሪት በወንጌል ስብከት ከበረች፣ ነቢያትም በሐዋርያት ስብከት ከፍ ከፍ አሉ፣ ዓለምን ከመፍጠር የማረፍ ሰንበትም በዓለም አዳኝ ትንሳኤ ዘውድ ተቀዳጀች እንላለን፡፡"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)
@zekidanemeheret
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)
@zekidanemeheret
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-
#ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡-
ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡
#ማግሰኞ- ቶማስ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29
#ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡
#ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡
#አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡
#ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡
#እሁድ- ዳግም ትንሳኤ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

"አንድ ወንድና አንዲት ሴት የተጋቡት (የሚጋቡት) መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ አብረው እየተጋገዙ ለመሔድ ከኾነ፥ ትዳራቸው ታላቅ የኾነ ደስታን ያመጣላቸዋል፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@zekidanemeheret
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@zekidanemeheret
#ባርኩልኝ
ሴትየዋ የንስሐ አባታቸውን በተደጋጋሚ እየጠሩ ማቡኪያዬን ውሻ ለከፈችብኝ ይባርኩልኝ ይላሉ። ካህኑ ከአንዴም ሁለቴም ሦስቴም የሴትየዋን ትእዛዛቸውን ፈጸሙ። ሲበዛባቸው ግን ሴትየዋን ጠርተው ይኧውልሽ ይሄ ነገር እኮ በዛ አንቺ ማቡኪያሽን መጠበቅ ካቃተሽ ውሻዋን አምጪና አፏን ልባርክልሽ አሉ ይባላል።
😊😊😊😊😊😊😊
ወደ ቤተክርስቲያን ለምን አትመጣም ? ስትባል የማይሆን ተልካሻ ምክንያት አትደርድር ሥራዬ ነው፣ ትምህርቴ ነው ወዘተ አትበል አንተ እንድትመጣ የግድ ሥራህንና ትምህርትን ማበላሸት (ማጥፋት) ከእግዚአብሔር አይጠበቅበትም.....ለጽድቅ ሥራ ካንጀት እናልቅስ
@zekidanemeheret
👉 ይህንን የመሳሰሉ አስተማሪ መልዕክቶች እንዲደርስዎ ለወዳጅዎ ያጋሩ።

🐴የአህያዋ ፍትሀት☦
ለመንደሩ ሰው ውሃ እየቀዱ በሚያገኙት ገቢ የሚተዳደሩ አንድ አዛውንት👳 ነበሩ።ሥራቸው ባለቻቸው አንዲት አህያ ለአካባቢው ኅብረተሰብ ውሃ በመቅዳት የዕለት ጉርሳቸውንና የዓመት ልብሳቸውን ተጣጥሮ መሸፈን ነው።
ጉልበቱ ከምላሱ ላይ የሆነ አንድ አለሌ መናፍቅ ውሃውን ሊቀዱ ሲወርዱና ሲወጡ ከመንገድ እየጠበቀ ማብቂያ በሌለው ንዝንዝ ሲያውካቸው ይኖራል።ከእለታት አንድ ቀን አህያቸው ትሞትባቸውና የውሃውን መቅጂያ እራሳቸው ተሸክመው ማመላለሱን ይቀጥላሉ።
በሸክም ውሃ የሚቀዱትን ሽማግሌ የታዘበው መናፍቅ "አባቴ አህያዋ የት ገባች?" ይላቸዋል "አዬ! እሷማ ሞተች እኮ" ቢሉት "በጣም ያሳዝናል ለመሆኑ ፍትሐት ተፈጽሞላታል? የትስ ተቀበረች" አለ። ብልሁ ሽማግሌም "አዬ ልጄ! አህያዋማ መናፍቅ ስለነበረች አልተፈታችም የጅብ ራት ሆና ቀረች" አሉትና እንደ እባብ በጥበብ አናቱን አሉት ይባላል"
👳👏👏👏👏👏👏👏👏
👉 share

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በግሪክ መንግስት እውቅና ተሰጣት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በግሪክ አገር ከ41 ዓመት በላይ ቋሚ አገልግሎት የሰጠች ሲሆን እስካሁን ድረስ ሕጋዊ እውቅና ሳይኖራት ቆይታለች፡፡
በግሪክ ሁሉም አኃት አብያተ ክርስቲያናትም ሆኑ ሌሎች ቤተ እምነቶች ለመንግስት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እያሟሉ የእምነት ተቋምነት ማረጋገጫ እውቅና የተቀበሉ እና ህጋዊ ማምለኪያ ያላቸው ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ግን የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ሳትሆን ከአራት አስርት ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል፡፡
በተለይ ከ2014 በኋላ የግሪክ መንግስት ሁሉም ቤተእምነቶች ፈቃድ እንዲኖራቸው የሚያስገድድ አሰራርን ተግባራዊ ቢያደርግም ቤተክርስቲያናችን የዚህ እድል ተጠቄሚ ሳትሆን በመቅረቷ የክርስትና፣ የሠርግ፣ የሞት፣ እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ሕጋዊ ሰነዶችን በግሪክ ሀገር መስጠት አትችልም ነበር፡፡
ይሁንና ይህን ህጋዊ አሰራር በቤተክርስቲያናችን ተግባራዊ በማድረግ የቤተክርስቲያናችንን ህጋዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ሰጪነት አዲስ በተመደቡት አስተዳዳሪ በቆሞስ አባ ገብረኢየሱስ አበበ ትጋትና በግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከፍተኛ እገዛ፣ቤተክርስቲያናችን በግሪክ የሃይማኖትና ትምህርት ሚኒስቴር አማካኝነት የዚህ ህጋዊ የእውቅናው ማረጋገጫ ባለቤት መሆን ችላለች።
የግሪክ ሃይማኖትና ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን እውቅና ለቤተክርስቲያናችን የሰጠው፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በግሪክ አገር የተመሠረተችበትን ረጅም ጊዜ ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ከሰነዱ ላይ እንደምትመለከቱት እ.ኤ.አ ከ1938 እስከ 2014 የወጡ በርካታ የሀገሪቱን ሕጎች እና ማሻሻያዎችን መነሻ በማድረግ ከዚህ በኋላ ቤተክርስቲያናችን የተሰጣትን ፈቃድ የማሳደስ እና ሌላ የፈቃድ ጥያቄ ማቅረብ ግዴታ እንዳይሆን ባደረገ መልኩ በማስተካከል በማያዳግም መልኩ እውቅናውን ሰጥቷታል፡፡
ይህ እውቅና፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንደ እምነት ተቋምነት እንድትታወቅ እና ማንኛም ሕጋዊ ተቋም የሚኖረው ሙሉ መብት እንዲኖራት ያስቻላት ከመሆኑም በላይ ከዚህ በፊት ሲታዩ የነበሩ የምእመናን እንግልቶችን የሚቀርፍ ሲሆን ቤተክርስቲያኗ የምትሰጣቸው መረጃዎች (ለምሳሌ፦ የክርስትና፣ የጋብቻ፣ የተሳትፎ፣ የአባልነት፣ የፍትሐት....) ሰነዶችና አገልግሎቶች ሁሉ በማንኛውም መሥሪያ ቤት ዘንድ ተቀባይነት ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ከዚህ እውቅና መረጋገጥ ጀምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ በግሪክ አገር የራሷን ሕንጻ ቤተክርስቲያን መገንባት፣ መግዛት ፣ ማስተዳደር እና ማንኛውንም ንብረቷን በስሟ ማንቀሳቀስ ትችላለች። በሌላ በኩል በአምልኮ መፈጸሚያ አጸዶች በር እና መድረኮች ላይ የቤተክርስቲያኗን ስም እና ፈቃድ በመጥቀስ ለመንቀሳቀስ፣ እንዲህም በግሪክ አገር ባሉ የማኅበራዊ ሆነ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስን እና ቤተክርስቲያንን በመወከል መሳተፍ ያስችላታል፡፡
ይህ ስኬት ከኢትዮጵያ ውጪ ላለችዋ ቤተክርስቲያናችን ትልቅ ፋና ወጊ እና አብነት የሆነ፣ በግሪክ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን የ2ሺህ ዓመታት ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ያደረገ ሲሆን በሌላ በኩል በአጥቢያችን ውስጥ ተፈጥሮ በነበረው የ“ሶማትዮ/የግል ድርጅት” ምክንያት ተበጥሶ የነበረውን የአጥቢያዋ እና የቅዱስ ሲኖዶስን ግንኙነትን የበለጠ የሚያጠናክርና እና ቤተክርስቲያችንን በግሪክ አገር ቋሚ ባለ መብት እንድትሆን ያደረገ ሥራ መሆኑን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የውጭ ግንኙነት መምሪያ መረጃ ያሳያል።
© EOTC

#ይድረስ_ለሴቶች_እህቶቼ____
አዲስ ተች ስልክ [smart phone] የገዛችውን ልጅ አባቷ ሲያያት . . . . . . .
አባት ፡- “ስልኩን ስትገዢ በመጀመሪያ ያደረግሽው ምንድነው?” ብሎ ጠየቃት፡፡
ልጅ ፡- “በመጀመሪያ ያደረኩት . . . ስክሪኑ እንዳይጫጫር መከላከያ ስቲከር ለጠፍኩበት . . .”
አባት ፡- "እንደዚ እንድታደርጊው የገፋፋሽ እለ?"
ልጅ ፡- "የለም!"
አባት ፡- "ያመረቱትን እንደ ማንቋሸሽ አይሆንም ግን . . . "
ልጅ ፡- "ኧረ አባዬ ! እንደውም የሚመክሩን እንድንለጥፍበት ነው!"
አባት ፡- "የሸፈንሽው ግን ርካሽ ስለሆነ ወይም ስለሚያስጠላ ነው?"
ልጅ ፡- "በነገራችን ላይ የሸፈንኩት . . .እንዳይበላሽብኝ እና ብዙ ግዜ እንዲያገለግለኝ ስለምፈልግ ነው!"
አባት ፡- "ስትሸፍኝው. . .ውበቱን አልቀነሰውም?"
ልጅ ፡- "እንደውም በጣም አምሮበታል በዛ ላይ እንዳይበላሽ ይከላከልልኛል"
አባት ፡- በአባትነት ዓይን እያያት "አንድ ጥያቄ ብጠይቅሽስ?" አላት
ልጅ:- "እሺ አባዬ ጠይቀኝ" አለች።
አባትም እንዲህ አለ: - "ከስልክሽ የሚበልጠውን ገላሽን እንድትሸፍኝው? እሺ ትይኛለሽ"?
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ሁሌም አባታችን እግዚአብሔር በሰው ላይ አድሮ ይጠይቀናል . . . . ብቻ በብዙ
ነገር ራሳችንን እንድንሸፍን ይጠይቀናል !
☞የምናስተውል ካለን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል"፤
✅ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸፍኑ (1 ኛ ጢሞ 2፥9)
✅ በሚሞት ስጋችሁ ሐጢያት አይንገስ ብልቶቻችሁን የፅድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ (ሮሜ 6፥12-14)
✅ ከሴት ጋር አለመገናኘት መልካም ነው። ካልተቻለ ዝሙትን ለመከላከል በአንድ ይፅና ከዚህ ውጭ ጉዞ ወደ እሳት ነው (1ኛ ቆሮ 7፥1)
✅ ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱ ያፈርሰዋል ቤተ መቅደሱም እናንተው ናችሁ (1ኛ ቆሮ 3፥17)
✅ የወንድ ልብስ የለበሰች ሴት በአምላክ ዘንድ የተጠላች ናት (ዘዳ 22፥5; ዘፀ 39፥28)
✅ ፀጉሯን ሳትሸፍን የምትፀልይ ሴት እራሷን ያዋረደች ናት(1ኛ ቆሮ 11፥5)
☞☞☞☞☞☞☞☞☞ እንድናስተውል እና እንደ እግዚአብሔር ቃል እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን። 🙏አሜን።

ተመስገን አለማወቅ
ባልና ሚስቱ በባህር ዳርቻ ሽርሽር ይላሉ። ድንገት ማዕበል ይመጣና ባልን ቀምቶ ወደ ባሕሩ ጥልቅ ይሸሻል።
ሚስት በሁኔታው ተደናግጠው የእንባቸውን ጎርፍ እያወረዱ ዐይናቸውን ወደ ሰማይ አንጋጠው እግዚአብሔር ሆይ! እባክህን ባለቤቴን መልስልኝ እያሉ ይጮሁ ጀመር እግዚአብሔርም የቅርብ አምላክ ነውና ጸሎታቸውን ሰምቶ ባለቤታቸውን ውሃው ተፍቶ ወደ ዳር አወጣቸው።
ሴትየዋ አላመኑም ሮጡ ተጠግቱው ሲያዩ ባለቤታቸው ከነሕይወታቸው ከውሃው ተርፈዋል። ሴትየዋም ምን አሉ መሰላችሁ "እግዚአብሔር ሆይ የእኔን የድሃውን ጸሎት ሰምተህ ባለቤቴን ስለመለስክልኝ አመሰግናለው። ዳሩ ግን በአናቱ ላይ አድርጎት የነበረው ባርኔጣ የታል?" አሉ በሐዘን። አቤት የሰው ነገር ።
☺️☺️☺️☺️☺️☺️☺️☺️☺️☺️☺️
እስቲ ቆም ብለን እናስብ እግዚአብሔር በሕይወታችን ዘመን ከሰጠንና ካደረገልን ነገሮች ሁሉ እና እኛ አላደረገልንም ከምንላቸው ነገሮች የቱ ይበዛል? እርግጠኛ ነኝ የሰጠን እና የተደረገልን ነው ሚበዛው።
© @zekidanemeheret
🔴 አብሮነታችሁ ያበረታናል። #Share በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩን።

🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንደምን ሰንብታችኋል የፍኖተ መንግስተ ሰማያት ቤተሰቦች? ከማያልቀው ፍቅሩ ፍቅርን የሰጠን ከማይቀንሰው ሰላሙ እነሆ ለበረከት ያለን የቅዱሳን አምላክ የተመሰገነ ይሁን።
✝ እግዚአብሔር በፈቀደ መጠን የቻናላችንን የትምህርት አድማስ ለማስፋት:- ሁላችሁም በቻላችሁት መጠን የቻናላችንን #link #Share እንድታደርጉ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። እባካችሁ ቢያንስ በዚህ እንኳን እንተጋገዝ፣ ክርስቲያናዊ ግዴታችንን እንወጣ ሁላችሁም እንደምታዩት መናፍቃንም አህዛብም ምን ያህል ዕቅድ ነድፈው ሊያጠፉን እንደሆነ በየቀኑ የምትሰሙት ነው። እና እባካችሁ ቸልተኛ አትሁኑ። በቅዱስ መፅሀፍ " የቆማችሁ የሚመስላችሁ እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ" ይላል።
እናንተም እንዲለቀቁላችሁ የምትፈልጓቸው ፅሁፎች፣ ግጥሞች፣ መዝሙሮችና፣ ቪዲዮዎች ካሏችሁ 👉 @zekidanemeheretbot ላይ አድርሱን።
@zekidanemeheret
@zekidanemeheret
@zekidanemeheret
@zekidanemeheret
#SHARE #SHARE #SHARE

"የብርሃናት ንጉሥ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ ዛሬ የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ተወለደች። ከሊባኖስ ተራሮች ርግብ ጸዐዳ ተወለደች፤ በሔዋን ምክንያት የተዘጋው የሕይወት መንገድ ይከፈትልን ዘንድ የሕይወት እናት ዛሬ ተወለደች፡፡ የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመብርሃን ዛሬ ተወለደች፡፡
ኢያቄምና ሐና ዳግሚት ሰማይ ተብላ የተጠራችውን ድንግልን ወለዱ፤ እውነተኛው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመ ፀሐይ (የፀሐይ እናት) ቅድስት ድንግል ዛሬ ተወለደች፤ ብርሃንን ለማስገኘት መወለድ መታደል ነው፤ ከሰው ልጆችም መካከል መመረጥ ዕፁብ ድንቅ ነው፤ የመድኃኔዓለም እናት ለመሆን መወለድ ሰማያዊ ፀጋ ነው።
በእውነት እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት። ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን እመብርሃን ዛሬ ተወልዳልናለችና ደስ ይበለን እልልም እንበል።"
የአለሙን ሁሉ መድኃኒት ለወለደች ለብርሃናት ጌታ እናት በቀራንዮ በመስቀሉ ስር እናት ትሆነን ዘንድ ለተሠጠችን ለመመኪያችን ዘውድ ለተወዳጇ ለቅድስተ ቅዱሳን እናታችን ልደት በዓል እንኳን አደረሰን