ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
813 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
እንኳን ለዳግማይ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ

=>ለስም አጠራሩ ጌትነት ይድረሰውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ትንሳኤው በሁዋላ ለደቀ መዛሙርቱ በጉባኤ 3 ጊዜ ተገልጦላቸዋል:-

1.በዕለተ ትንሳኤ ምሽት በፍርሃት ሳሉ
2.ያላመነ ቶማስን ለማሳመን በተነሳ በ8ኛው ቀን (ማለትም ዛሬ)
3.ከተነሳ ከ23 ቀናት በሁዋላ በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ላይ ነው::

+ጌታ አርባውን ቀን ለአንዱም: ለሁለቱም በግል ይገለጥላቸው ነበር:: እመቤታችንን ግን ፈጽሞ አይለያትም ነበር::

+ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለሳምንት ተለይቷቸው ስለ ነበር በቤተ ክርስቲያን ውዳሴ ማርያም እንጂ መልክዐ ኢየሱስ በማሕበር አይደገምም::

+በዚሕች ዕለት ደቀ መዛሙርቱ በጽርሐ ጽዮን ሳሉ ጌታችን "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ብሏቸዋል:: ቶማስንም "ና ዳስሰኝ" ብሎታል:: ሐዋርያው እጁን ከተወጋ ጐኑ ላይ ቢያሳርፍ በመቃጠሉ "ጌታየ አምላኬም" ሲል ጮሆ ምስጢረ ተዋሕዶውን መስክሯል::

+ጌታም ቶማስን "እስመ ርኢከኒሁ አመንከኒ" (ማለትም ስላየኸኝ አመንከኝ)! "ብጹዐንሰ እለ እንዘ ኢይሬእዩኒ የአምኑኒ" (ሳያዩ የሚያምኑ ግን ብጹዐን (ማለትም ንዑዳን ክቡራን) ናቸው ብሎታል:: (ዮሐ. 20:24)

=>ከጌታችን ከትንሳኤው: ከቅዱሱም ሐዋርያ በረከት አይለየን::

=>+"+ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ 'ሰላም ለእናንተ ይሁን' አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን 'ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን' አለው:: ቶማስም 'ጌታዬ አምላኬም' ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም 'ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው' አለው:: +"+ (ዮሐ. 20:26-29)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
#የግንቦት_ልደታ_በዓል_አከባበር

በቤተ ክርስቲያናችን ትዉፊት መሰረት ሃና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ ይኼንን ትውፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡

ሆኖም በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸው መንፈሳዊያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን በዓል ነዉ፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለዉጋር ነዉ፣ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቂቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ፣ እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸዉ፡፡ እኛም ከእንደነዚህ ዓይነት አሰናካዮች በመለየት ይኼንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር እንድናከብረዉ መልዕክቴ ነው፡፡
ለዚህም የእመቤታችን ረድኤት በረከት አይለየን፡፡
@zekidanemeheret
Audio
ግሩም ማብራሪያ

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ(ዶ.ር)

@zekidanemeheret
ዘፈን ለምን ተከለከለ?

በኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አስተምህሮ መሠረት ዘፈን መስማት፣ መዝፈንም ሆነ በዘፈኑ መጨፈር የተከለከለ ነው። ይህም የሆነው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው። ዘፈን የአጋንንት ሥራ ነው። የአጋንንት ግብራቸው ዘፈን መዝፈን ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ ስለዘፈን በግልፅ አነጋገር እንዲህ ይላል "በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ" በማለት ስለ አጋንንት ዘፋኝነት ይናገራል (ኢሳ.13÷2)። አትዝፈኑ ማለት የአጋንንትን ሥራ አትሥሩ ማለት መሆኑን መረዳት አለብን። ይህን በተመለከተ መጽሐፈ መቃብያን ደግሞ እንዲህ ይላል:- "እየዘፈኑም ከአጋንንት ጋር ይጫወቱ ነበር። አጋንንትም ጫወታቸውንና ዘፈናቸውንም ሁሉ ያደንቁላቸው ነበር" (1ኛ.መቃ.36÷27-28)። በዚህ አገላለጥ ደግሞ ለየት የሚለው አጋንንት ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ ከዘፈን አድናቂዎች ጐራ መሰለፋቸው ነው። ታላቁ የቤተክርስትያናችን የሥርዓት መፅሐፍ "ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ" ሥራን አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ይላል:- "ስለ ተግባረ ዕድ ግን በዓለም ከሚሠሩ ሥራዎች መንፈሳዊ ሕግን ከሚቃወም ሥራ በቀር ሁሉንም ሊሠሩ ይገባል። ... እንደ ዘፋኝነት፣ እንደ መጥፎ ጫወታ፣ በእግር እንደ ማሸብሸብ (ዳንስና ጭፈራ) ካልሆነ በቀር ነው።" (ፍት.ነገ.መን.አን. 23:820)። ይህ የአበው ቃል ዘፋኝነት በመንፈሳዊ እይታ እንደ ሥራ መቆጠር እንደሌለበት ያስረዳል።

ዘፋኝነት "የሥጋ ሥራ" በመሆኑ ኃጢአት ነው። የሚዘፍን የእግዚአብሔርን መንግስት ሊያይ አይችልም። (ገላ.5÷21):: "በመንፈስ ተመላለሱ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ።" ተብሏልና (ገላ.5÷16)። ዘፈን በመንፈሳውያን መጻሕፍት ተወግዟል። ሐዋርያት በዲድስቅልያ "ኢትኩኑ ዘፈንያነ" ~ "ዘፋኞች አትሁኑ" ብለዋል። (ዲድስ.አንቀጽ 7) ቅዱስ ጳውሎስ "በቀን እንደምንሆን በአግባብ እንመላለስ:: በዘፈንና በስካር አይሁን" ብሏል። (ሮሜ.13÷13)። ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ "በስካርና በዘፈን የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።" ይለናል (1ኛ.ጴጥ.4÷3)። መጽሐፈ ሐዊ ደግሞ "ከሰይጣን የተገኘ ነውና ዘፈንንና ዳንስን ከኛ ማራቅ ይገባናል።" ይለናል (መጽ.ሐዊ አን. 50)። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞ ከማዘዝ አልፎ ዘፈንን እንተው ዘንድ "ዘፈንን ትተዉ ዘንድ እማልዳችሗለሁ" በማለት ይማጸናል። (ተግ.ዘዮሐ.አፈ.28)። ዘፈንን አንተውም ላሉ ደግሞ መጽሐፈ ሐዊ "በዘፈን ጸንተው የሚኖሩ ይፈረድባቸዋል" በማለት ሲያስጠነቅቅ እናገኛለን። (መጽ.ሐዊ.አን. 12)::

ሁላችሁ ወዳጆቼ የእኛ ሳይሆን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሆነውን ሰውነታችንን በከንቱ ዘፈን ዳንኪራ እና ጭፈራ አናርክሰው። እግዚአብሔር በባህርይው ንፁህ ይወዳልና ሰውነታችንን አንፅተን የእርሱ ማደሪያ እና መቀደሻ እንድንሆን ፈቃዱ ይሁንልን።

@zekidanemeheret
"ግመልን ስትጠይቅ ቀበሮነትህን አትርሳ"
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

ግመሉ ወንዙን እንደተሻገረ ቀበሮውም ለመሻገር መጣና ስለወንዙ ጥልቀት ለማወቅ
ከወንዙ በወድያኛው ዳር
ያለውን ግመል ጠየቀው። ግመሉም ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ እንደሆነ ነገረው።
ቀበሮውም ጉልበት ድረስ ከሆነማ አያሰምጠኝም በማለት ለመሻገር ወደ ወንዙ ገባ።
በሚያሳዝን ሁኔታ ወንዙ ያሰምጠው ጀመረ። ይሄኔ ቀበሮው ግመሉ እንደሸወደው ተረዳና እንደምንም ተፍጨርጭሮ ወደ ነበረበት ተመለሰ፤ ራሱንም ከሞት አተረፈ።

ይሄኔ በንዴት ጮክ ብሎ "አንተ ያምሀልን? ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ ነው አላልክምን?"
አለው።

ግመሉም "አዎና! ታዲያ በራሴ ጉልበት ነው እንጂ ያልኩህ ባንተ ጉልበት መች አልኩህ?"
በማለት መለሰለት። ቀበሮው በልምድ የቀደመውን አካል መጠየቁ ትክክል ቢሆንም
የግመሉን ማንነት መርሳቱ ግን ስህተት ነበር። ግመሉም ልምዱን ማካፈሉ ትክክል ቢሆንም
የቀበሮውን ማንነት ግን መርሳት አልነበረበትም።

ሁለት ሰዎች ሲነጋገሩ እንደየራሳቸው ተሞክሮ ቢነጋገሩም የአንዱ ልምድ ለሌላው
መፍትሔ ሊሆን ግድ አይደለም።
ባይሆን የአንደኛውን የህይወት ልምድ ለሌላኛው መጥፊያው ሊሆን ይችላልና ጥንቃቄ
ማድረጉ ግድ ይላል። ለምሳሌ አንድ ሁለት ሴቶች አረብ ሀገር ሰርተው ተመልሰው
ውጤታማ ቢሆኑ ሁሉም አረብ ሀገር የሄደ ሰው ውጤታማ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡
ስለዚህ የሰዎችን የህይወት ተሞክሮ ወደ እራሳችን ህይወት አምጥተን ለመተግበር
ስንዘጋጅ ማስተዋልና ጥንቃቄ አይለየን።

@zekidanemeheret
🔆👉ከድጡ ወደ ማጡ👈🔆

በጥንት ጊዜ ጉልበታቸውን ሽጠው የሚያድሩ ሁለት የሴት አሽከሮች ነበሩ። እመቤቲቱ አሽከሮቹን ሌሊት እንዲነሱ እያረገች ታሠራቸውና ማታ አምሽተው ይተኛሉ።

እመቤቲቱ አንድ ቀን ተሳስታ አርፍዳ ቀስቅሳቸው አታውቅም። ሁለቱ የሴት አሽከሮቿ ምስጢሩን ሲያጠኑት እመቤቲቷን በዚያ ሰዓት የሚያስነሳት በግቢው ውስጥ ያለው አውራ ዶሮ በሰዓቱ እየጮኸ መሆኑን ደረሱበት።

ከምንጩ ማድረቅ ነው አሉና ሌሊት መነሳት የሰለቻቸው አሽከሮቿ አውራ ዶሮውን አርደው ለአንድ ቀን የምግብ ዝግጅት አቀረቡት።

የአውራ ዶሮውን ያለመኖር ያወቀችው አሠሪያቸው ሳልቀሰቅሳቸው እንቅልፍ ይጥለኛል በሚል ስጋት እየባነነች በፊት ከምታስነሳቸው ቀደም ባለ ሰዓት ትቀሰቅሳቸው ጀመር። "ትሻልን አምጥ ብዬ ትብስን ወለድኳት" እንደተባለው የሰዎቹ መላ የባሰውን አምጥቶ አረፈው።

🔆💢🔆💢🔆💢🔆💢🔆💢🔆💢🔆💢

የአንዳንዶቻችን መፍትሔ ችግሩን የሚፈታ ሳይሆን ከድጡ ወደ ማጡ ዐይነት ነው። ስለዚህ ከደረሰብን ችግር አንጻር መፍትሔ ስናስብ ቆም ብለን ማውጣትና ማውረድ ይጠበቅብናል። ሳያሰላስሉ ውሳኔ ላይ መድረስ ሁሌም አደጋ አለው።

@zekidanemeheret
🎈🕯ጠቃሚ አባባሎች🎈🕯
፨፨፨፨፨፨፨♥️፨፨፨፨፨፨፨፨፨

💡ንስሓ ከጥቂት ቆይታ በኋላ የሚመለሱበት የኅጢአት ዕረፍት አይደለም
አቡነ ሺኖዳ

💎 ሌሊት እግዚአብሔርን ለማመስገን የተፈጠረ ልዩ ጊዜ ነው
አባ ይስሐቅ

🏮ከሰይጣን ይልቅ ልምድን ፍራ
ማር ይስሐቅ

📌እኛ ወደእርሱ መውጣት ሲያቅተን እርሱ ወደእኛ ወረደ
አቡነ ሺኖዳ

🖊የስብከት ዓላማ ሰውን ወደ ሕይወት ማምራት ነው

@zekidanemeheret
🔰ወዳጄ፦

🍇☞ወደ ዋላ ተመለስና ታሪክ አጥና ፦

1️⃣ዮሴፍን ወንድሞቹ ሸጠውት ወደ ግብፅ ሲወርድ ሰው አልነበረውም፥ እግዚአብሔር ግን በጌታው በጲጥፋራ ቤት ከፍ ከፍ አደረገው።

2️⃣በጌታው ሚስት ተንኰል ወደ ወኅኒ ቤት በተወረወረ ጊዜም ሰው አልነበረውም፥ እግዚአብሔር ግን ከወኅኒ
ቤት አውጥቶ በባዕድ ሀገር ገዥ አደረገው።

3️⃣ሙሴ በሕፃንነቱ ወንዝ ዳር ሲጣል ሰው አልነበረውም፥ እግዚአብሔር ግን ከተጣለበት አንሥቶ በፈርዖን ቤተ
መንግሥት፥ የንጉሥ የልጅ ልጅ ተብሎ እንዲያድግ አደረገው። (ዘፍ 39፥1-23፤ 41፥1-50።)

4️⃣ብላቴናው ዳዊት በኃያሉ በጐልያድ ፊት በቆመ ጊዜ ሰው አልነበረውም፥ ከወንጭፉ በስተቀር መሣሪያም አልነበረውም፥ እግዚአብሔር ግን ጐልያድን በአንዲት ጠጠር ግንባሩን ፈርክሶ ጣለለት።( ዘጸ 2፥1-10)

5️⃣ዳንኤልና ሠለስቱ ደቂቅ ተማርከው ወደ ባቢሎን ሲወርዱ ሰው አልነበራቸውም፥ እግዚአብሔር ግን ጥበብን ሰጥቶ በባቢሎን ጠቢባን እና አውራጃዎች ላይ እንዲሾሙ አደረጋቸው። (1ኛሳሙ 17፥35-55።)

6️⃣በሰዎች ተንኰል፥ ሠለስቱ ደቂቅ ወደ ዕቶነ እሳት፥ ዳንኤል ደግሞ ወደ አናብስት ጉድጓድ በተጣሉም ጊዜ
ሰው አልነበራቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ቅዱስ ሚካኤልን እና ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ አዳናቸው። (ዳን 1 እና 2፤ )

7️⃣አልዓዛር በሞት ተይዞ፥ ተገንዞ፥ ወደ መቃብር በወረደ ጊዜ ሰው አልነበረውም፤ ጌታ ግን ከመቃብር አወጣው። (ዳን 3፥24፣6፥6 )

8️⃣ቅዱስ ጴጥሮስ በሰንሰለት ታስሮ ወደ ጨለማው ወኅኒ ቤት ሲወረወር ሰው አልነበረውም፥ ጌታ ግን መልአኩን ልኰ ከወኅኒ ቤት አወጣው።(ዮሐ 11፥28-34)

9️⃣ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ ወደ ወኅኒ ቤት ተወርውረው፥ ከግንድ ጋርም አጣብቀው ሲያስሯቸው ሰው አልነበራቸውም። (የሐዋ 12፥1-11)

🍇►በመንፈቀ ሌሊትም ይጸልዩ፥ እግዚአብሔርንም በዜማ ያመሰግኑ ነበር።

🍇►ጌታም የእግር ብረቱን፥ የእጅ ሰንሰለቱን ፈትቶ፥ በሩንም ከፍቶ አውጥቶአቸዋል።(የሐዋ 16፥16-30።)

<> <> <> <> <>

🍇☞ታዲያ ወዳጄ ይህ ላንተም ነው ። ይህ ህግ ዛሬም በህይወትህ ዉስጥ ይሰራል ። ብቻህን አይደለህም ።

🔶ዘመድ ላይኖርህ ይችላል ታማኝ ጓደኛ ላይወጣልህ ይችላል

🔶እናት ወይም የስጋ አባት ላይኖርህ ይችላል

🍇ግን ከሁሉ በላይ የሆነውን ወዳጅ ፣ ዘመድ ጓደኛ የሚተካ ፤ ከሁሉ በላይ ሆኖ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ የሆነ ወዳጅ "አባት" አለህ!! በዚህ ኩራት ይሰማህ !!!

🍇ክብር ምስጋና ለዚህ ጌታ ለአባታችን ለፈጣሪያችን ለአምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ይሁን !!(አሜን)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@zekidanemeheret
👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂
👳‍♂👳‍♂👳‍♂ ምክረ አበው 👳‍♂👳‍♂👳‍♂
👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂👳‍♂

♻️ ጸጋን ያለመከራ አገኛለሁ አትበል

🌐 ዐዋቂ ነኝ ጻድቅም ነኝ አትበል፤ ዐዋቂ ጻድቅ ሳትሆን ቀርተህ እንዳታፍር

💠 መከራ ባይመጣብህ ቸርነቱን ፣ በጎ ጥበቃውን ባላወቅህም ነበር

🔆 መከራ መጥቶብህ መከራውን ለማራቅ ከምትጸልየው ጸሎት አስቀድሞ ለሚገባ ንስሐ ተዘጋጅ

🛑 ከዝሙት ትለይ ዘንድ ከዘማውያን ራቅ

⭕️ ኃጥአንን ውደዳቸው በሥራ ግን አትምሰላቸው

@zekidanemeheret
🌐 ኃጥያትን ባትሠራት መልካም ነው
ኃጥያት ከሠራህ ሳትቆይ ንስሐ
ብትገባ መልካም ነው፤ ንስሐ ከገባህ
ዳግመኛ ወደ ኃጥያት ባትመለስ ጥሩ
ነው። ወደ ኃጥያት ካልተመለስክ ይህ
በእግዚአብሔር ርዳታና ቸርነት መሆኑን
ብታውቅ መልካም ነው፤ይህን ካወቅህ
ስላለህበት ሁኔታ እግዚአብሔርን
ብታመሰግን መልካም ነው።
"ቅዱስ ባስልዮስ"
------------፨፨♥️፨፨-----------
@zekidanemeheret
አባ መቃራ የሚባሉ አንድ መነኩሴ ነበሩ። ከእለታት አንድ ቀን ድንጋይ ሲፈነቅሉ ድንገት አንዲት ትል ገደሉ። በዚህም የተነሳ በጣም አዘኑ።ሊክሱም ወደዱ።

ከዚያም ተነስተው ብዙ ትሎች ወዳሉበት ቦታ ሄደው ከመካከል ቁመው ለ፳ቀናት ጸለዩ። ትሎቹ ገላቸውን እንደብራና ፍቀው ጨረሷቸው።በትል የተበላ ሰውነታቸውን አይተው ተጽናኑ።

እመቤታችን ለተጠማ ውሻ ራርታ በወርቅ ጫማዋ ውኃ እንዳጠጣች አባ መቃራም ሳያውቁ ለገደሏት ትል አዘኑ፣ ካሱ "ጻድቅ ሰው ለእንሰሳ ነፍስ ይራራል" የተባለውን በግብር አሳዩ። ምሳ 12፣10

🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

ክርስቲያን በአርአያ ሥላሴ ለተፈጠረ ወገናችን ከማሰብ ባሻገር ለእንስሳትም ቢሆን ማሰብን ግድ ይላል።

@zekidanemeheret
ሰይጣን ክፉ ነው፡፡ ቢሆንም ደካማ ነው፡፡ እርሱ ጋር ካለው ኃይል እኛ ጋር ያለው ጸጋ እግዚአብሔር ይበልጣልና፡፡ እኛው ራሳችን በፍቃዳችን ከረድኤተ እግዚአብሔር እያራቅን በሄድን ቁጥር ግን እርሱ እየፈራ እየተንቀጠቀጠም ቢሆን እየቀረበ ይመጣል፡፡ ቤቱ ዘበኛ ከሌለው አልያም እንዲሁ ክፍት ከሆነ ሌባ እየፈራም ቢሆን እንደሚገባ፡፡ ለቀዳማይቱ ሔዋን ያደረገውም እንደዚህ በቀስታ ነበር፡፡ አስቀድሞ በኀልዮ (በሐሳብ) ይሞክራል፡፡ በጣም መንቻካ ከመሆኑ የተነሣም ይህን ደግሞ ደጋግሞ ያደርገዋል፡፡ ሐሳቡን ለመቀበል ዝግጁዎች እንደሆንን ሲረዳም ሐሳቡን ፈጥነን ወደ ገቢር (ተግባር) እንድንለውጠው ሹክ ይለናል፡፡ ይህም እንደ ሐሳቡ ደጋግሞ ያደርጓል፡፡ በተለይ ምቹ.ሁኔታዎችን ሲመለከት ይህን ደጋግሞ ይሞክራል፡፡ እንደ ተዘጋጀን ሲያውቅም ክፉ መርዙን እፍ ይልብናል፡፡ ከዚያም ሙሉ ለሙሉ ይቆጣጠረናል፡፡
በጣም የሚገርመው ደግሞ ከወደቅን በኋላ የመጀመርያው ከሳሻችን እርሱ መሆኑ ነው፡፡ “አሁን አንተ መንፈሳዊ ነኝ ትላለህ፤ ሆኖም ደግሞ እንዲህ በመሰለ ርካሽ ኀጢአት ትወድቃለህ” እያለ ሰላም ያሳጣናል፡፡ ለሁሉም ግን ወደ እግዚአብሔር መመለሱ ይሻላል፡፡ ነፍሳችንን ቃለ እግዚአብሔርን አናስርባት፡፡ በየጊዜው ምክርን ከሐኪሞቻችን (ከንስሐ አባቶቻችን) እንሻ፡፡

@zekidanemeheret
በንስሐ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደር እና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም።
አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ
@zekidanemeheret
💠በቸርነቱ እንጠቀም

ንስሐ መግባት ሲገባን በተደጋጋሚ የተለያዩ ምክንያቶችን በማብዛት መዘግየት ንስሐን እንደመቃወም የሚቆጠር ነው::

ይህም በፈርዖን ሕይወት ውስጥ የታየ ነው:: ፈርዖን እስከ ዐሥር መቅሰፍቶች ደረሰ በአሥሩም መቅሰፍቶች መማር ንስሐ መግባት አልወደደም::

በእያንዳንዱ መቅሰፍት ተመክሮ ንስሐ እንዲገባ ዕድል ተሰጠው ነገር ግን በመዘግየቱ በዕድሉ ሳይጠቀምበት ቀረ ዕድሉ በባሕረ ኤርትራ መስጠም ሆነ:: አንተስ(አንቺስ)????
@zekidanemeheret
🛑ይነበብ!!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በበዓለ ሃምሳ ንስሃ ለምን ተከለከለ?

=>በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያለ ምክንያት የሚደረግ : ያለ ምሥጢርም የሚከወን ምንም ነገር የለም:: የሃይማኖትን ትምህርት አብዝተን በተማርን ቁጥር የምናውቀው አለማወቃችን ነውና ምንም ያህል ብንማር : የአዋቂነት መንፈስም ቢሰማን ከመጠየቅ ወደ ጐን አንበል:: መጠየቅ ለበጐ እስከሆነ ድረስ ሁሌም ሸጋ ነው:: ግን ልብን እያጣመሙ ቢያደርጉት ደግሞ ገደል ይከታል::

+ወደ ጉዳዬ ልመለስና ሁሌ የሚገርመኝ የትውልዱ አመለካከት ነው:: ጾም ሲመጣ "ለምን? . . . አልበዛም? . . ." ዓይነት ቅሬታዎች ይበዛሉ:: በዓለ ሃምሳ ሲመጣ ደግሞ "እንዴት ይህን ያህል ቀን ይበላል? . . ." ባዩ ይከተላል::

+ቤተ ክርስቲያን ግን ሁሉን የምትለን ለጉዳይ : ለምክንያትና ለእኛ ጥቅም ነው:: ለምሳሌ:- በዓለ ሃምሳ ድንገት እንደ እንግዳ ደርሶ : እንደ ውሃ ፈሶ የመጣ ሥርዓት አይደለም:: ይልቁኑ ምሳሌ ተመስሎለት በብሉይ ኪዳንም ሲከወን የነበረ እንጂ::

+እንደሚታወቀው እስራኤል ከግብጽ ባርነት በ9 መቅሰፍት : በ10ኛ ሞተ በኩር ወጥተው : በ11ኛ ስጥመት ጠላት ጠፍቶላቸው ወደ ምድረ ርስት ተጉዘዋል:: ቅዱስና የእግዚአብሔር ሰው ሙሴም ከእግዚአብሔር እየተቀበለ ብዙ ሥርዓቶችን ለቤተ እስራኤል አስተምሯል::

+እነዚህ ሥርዓቶች ሁሉ ለሐዲስ ኪዳን ምሥጢረ ድኅነት ጥላና ምሳሌዎችም ነበሩ:: በኦሪት ዘሌዋውያን ላይ ጌታ እንዲህ ይላል:-
". . . ከሰንበት ማግስት ፍጹም ሰባት ጊዜ ሰባት ቀን ቁጠሩ:: እስከ ሰባተኛ ሰንበት ማግስት ድረስ አምሳ ቀን ቁጠሩ:: አዲሱንም የእህል ቁርባን ወደ እግዚአብሔር አቅርቡ::" (ዘሌ. 23:15)

+ይህም "በዓለ ሰዊት (የእሸት በዓል)" የሚባል ሲሆን ከፋሲካ 7 ሱባኤ (49 ቀን) ተቆጥሮ : በሰንበት (ቅዳሜ) ማግስት (እሑድ ቀን) በዓለ ሃምሳ ይውላል:: በዓሉ በግሪክኛው "ዸንጠቆስቴ (Pentecost)" ይባላል:: "በዓለ ሃምሳ" እንደ ማለት ነው::

+ለዚያም ነው ቅዱስ መጽሐፍ የመንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት በዚህ ቀን መሰጠትን ሊነግረን ሲጀምር "ወአመ ተፈጸመ መዋዕለ ዸንጠኮስቴ . . ." የሚለው:: (ሐዋ. 2:1) በዓለ ሃምሳ (50ው ቀናት) በብሉይ "የእሸት በዓል" ቢባሉም ለሐዲስ ኪዳን ግን "የሰዊት (እሸት) መንፈሳዊ" ዕለታት ናቸው::

+ጌታ መድኃኔ ዓለም ስለ እኛ መከራ ተቀብሎ : ሙቶ ከተነሳ በሁዋላ 50 ያሉት ቀናት የዕረፍት : የተድላ : የመንፈሳዊ ሐሴት ቀናት ናቸው:: በእነዚህ ዕለታት ማዘን : ማልቀስ : ሙሾ ማውረድ : ንስሃ መግባት ወዘተ. አይፈቀድም::

=>ለምን?

1.ለእኛ ካሣ በጌታችን መፈጸሙን የምሰናስብባቸው ቀናት ናቸውና:: በእነዚህ ዕለታት ብናዝን "አልተካሰልንም" ያሰኛልና::

2.በዚህ ጊዜ መስገድ : መጾም "ክርስቶስ በከፈለልን ዋጋ ሳይሆን በራሴ ድካም (ተጋድሎ) ብቻ እድናለሁ" ከማለት ይቆጠራልና::

3."ፍስሐ ወሰላም ለእለ አመነ - ላመን ሁሉ ደስታና ሰላም ተደረገልን" ተብሎ በነግህ በሠርክ በሚዘመርበት ጊዜ ማዘን . . . ሲጀመር ካለማመን : ሲቀጥል ደግሞ "ደስታው አይመለከተኝም" ከማለት ይቆጠራልና::

4.50ውም ቀናት እንደ ዕለተ ሰንበት ይቆጠራሉና:: መጾምና መስገድ በዓል ያስሽራልና::

5.ዋናው ምሥጢር ግን እነዚህ 50 ዕለታት የአዝማነ መንግስተ ሰማያት (የሰማያዊው ዕረፍት) ምሳሌዎች ናቸው::

ስለዚህ በእነዚህ ቀናት መጾም : መስገድ "መንግስተ ሰማያት ውስጥ ከገቡ በሁዋላ ድካም : መውጣት መውረድ አለ" ያሰኛልና ነው::

+በዚያውም ላይ "ኢታጹርዎሙ ጾረ ክቡደ (ከባድ ሸክም አታሸክሙ)" የተባለ ትዕዛዝ አለና ቅዱሳን አበው በጾም የተጐዳ ሰውነት ካልጠገነ ወጥቶ ወርዶ : ሠርቶ መብላት ይቸግረዋልና ሰውነታችን እንዲጠገን : ይህንን በፈሊጥ ሠርተዋል::

+ስለዚህም:-
"ሐጋጌ አጽዋም እምስቴ::
ወሠራዔ መብልዕ በዸንጠኮስቴ::" እያልን አበውን እናከብራለን:: (አርኬ)

+ስለዚህ በበዓለ ሃምሳ ጾም : ስግደት : ንስሃ : ሐዘን : ልቅሶ . . . የለም:: አይፈቀድምም::
<<ግን ይህንን ተከትሎ 50ውን ቀን ሙሉ ሆድ እስኪተረተር ከበላን ጉዳቱ ሥጋዊም : መንፈሳዊም ይሆናል!!>>

+አበው እንደነገሩን "እንደ ልባችሁ ብሉ" ሳይሆን የተባለው "ጦም አትዋሉ" ነው:: ለምሳሌ:-

1.በልቶ ጠጥቶ ከሚመጣ ኃጢአት : ክፋትና ፈተና ለመጠበቅ 50ውን ቀናት ጥሬ የሚበሉ አሉ::
2.ጠዋት ተመግበው ከ24 ሰዓት በሁዋላ ጠዋት የሚመገቡ አሉ::
3.መጥነው ጥቂት በልተው አምላካቸውን የሚያመሰግኑ አሉ::
4.ነዳያንን አጥግበው እነርሱ ከነዳያን ትራፊ የሚቀምሱ አሉ::

+እኛም ከእነዚህ መካከል የሚስማማንን መርጠን ልንከውን : በተለይ ደግሞ በጸሎት ልንተጋ ይገባል:: አልያ ብሉ ተብሏል ብለን ያለ ቅጥ ብንበላ : ብንጠጣ እኛው ራሳችን የሰይጣን ራት መሆናችን ነውና ልብ እንበል:: ማስተዋልንም ገንዘብ እናድርግ::

"እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና:: እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ::
ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና:: ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው::
ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና:: ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና:: መገዛትም ተስኖታል::
በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም::" (ሮሜ. 8:5)

=>አምላከ ቅዱሳን ማስተዋሉን ያድለን::

<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>

በመምህር ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

@zekidanemeheret
💠💠ንስሐ💠💠

ንሰሐ ሰው ሕይወቱን ወደተሻለ ደረጃ ለመለወጥ የሚያስችለው መንፈሳዊ ጥንካሬ ወይም ኃይል ነው::

ንስሐ በልቡናችን ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ፍቅረ እግዚአብሔር እንዲወለድ ያደርጋል::

ምክንያቱም በንስሐ ሕይወት የምንኖር ከሆነ እግዚአብሔር ስለ እኛ ብሎ የተሸከመልንን ሸክምና ይቅር ያለንን እጅግ የከፋ ኃጢአት እንድናስብ ስለሚያደርግና ለእግዚአብሔርም ያለን ፍቅር እያደገ ስለሚሄድ ነው::

@zekidanemeheret
ወዳጄ ሆይ....
"ኃጢአት ለመሥራት ቀጠሮ ትይዛለህ፤ ጽድቅ ለመሥራት ግን ጊዜ የለኝም ትላለህ፡፡ ጓደኛህን ለማግኘት ጊዜ አለህ፤ ንስሐ አባትህን ለማግኘት ግን ጊዜ የለህም፡፡ በሥጋ ስትራብ ከየትም አምጥተህ (ለምነህም ቢኾን) ትበላለህ፤ ነፍስህ የክርስቶስ ሥጋ ከራባት ግን ዘመናት ተቆጠሩ፡፡ ወዳጄ ሆይ! እባብ አሳተኝ ያለችውንና፥ ከፍርድ ያላመለጠችውን ሔዋን ታስታውሳለህን? እንግዲያውስ፥ አንተም እንደ እርሷ ምክንያት በመደርደር ራስህን ለማጽደቅ አትሞክር፡፡ ይህ ሲነገርህም በተግባር እንጂ በከንፈርህ መልስ ለመስጠት አትጣር፡፡"

@zekidanemeheret
"ብዙ ጊዜ ሰዎች ብልህ ነን እያሉ ይሳታታሉ።ነገር ግን ብልህ የሚባሉት ብዙ የተማሩና ብዙ ያነበቡ ብዙ የሚናገሩ አይደሉም።ይልቁንም ጠቢባን የሚባሉት ጥብብት መጥበቢት ብልህ ነፍስ ያላቸው፤የእግዚአብሔርና የሰይጣንን ለይተው ለእግዚአብሔር ሆነው የሚኖሩ ናቸው።ፍጹም ምልዐተ ኃጢአትንና ከጦር ይልቅ እሾሀቸውን የነቀሉ ናቸው ጠቢባን!ጠቢባንስ እግዚአብሔርን ያለጥርጥር በሙሉ ልብ የሚያምኑት፤አምነውም እንደ ፈቃዱ የተከተሉት፤በክንፈ ጸጋ ተመስጠው ከልብ በሚወጣ ውዳሴ ከእርሱ ጋር ተዋሕደው የሚኖሩ ናቸው።የነፍሳቸውን ጥቅም አውቀው ዕለት ዕለት ያንን የሚለማመዱ በእውነት ጠቢባን እነዚህ ናቸው።"

ታላቁ አበ መነኮሳት አባ እንጦንስ

@zekidanemeheret
🌺 አንተ ሰው !!! 🌺

📝 ቃለ እግዚአብሔርን ተማር !
ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር !
ኹልጊዜ ተማር !
ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር!
ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት አቅም ታገኛለህ ።
ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት አቅም አታገኝም፡፡
ስለዚህ ተማር! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን
እየወቀስክ ትሠራለህ፡፡
ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፡፡ አንድ ቀን ወደ ንስሐ ትመራሃለች !!!

"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ"
@zekidanemeheret