ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
854 subscribers
3.46K photos
103 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
መጸለይ አለመቻልና መጸለይ አለመፈለግ የተለያዩ ናቸው መጸለይ ያልቻለ ሰው ጌታ ሆይ መጸለይ እፈልግ ነበር ነገር ግን አልቻልኩም ማለት ይኖርበታል ቅዱሳንም የሚራዱት እየሞከሩ አቅም ያጡትን የደከሙትን ነው ስለዚህም መዳንን ይወርሱ ዘንድ ያላቸውን የሚራዱ ያለው ሐዋርያው ይህንን ነው ፡፡
ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ አንዱ አንዱን ያድናል እርስ በእርስ በወንጌል ስንማማር ወንድማችንን ከክፉ ስንመልሰው ከኃጢዓት መክረን ስናመጣው ተስፋ ከመቁረጥ ስንመልሰው ማዳን ይባላል ይሄ ማዳን ማለት ደግሞ በድኅነቱ መንገድ ማሳየታችን ነው ማዳን የተባለው ወዳጄ ከክፉ ነገር አወጣኝ ከጸጸት አተረፈኝ ተስፋ ከመቁረጥ አዳነኝ ብለን የምንናገረው ማለት ነው ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ በመልዕክቱ ይህን አይነቱን ማዳን እንዲህ ጽፎታል ‹‹ወንድሞች ሆይ ከእናንተ ማንም በእውነት ቢስት አንዱም ቢመልሰው ኃጢዓተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን የኃጢዓትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ›› (ያዕ 5÷20)
ይሄ ማዳን ግን እንደ ቅዱሳኑ ያለ ማዳንም አይደለም፣ እንደ ጠበሉና እምነቱ ያለም ማዳን አይደለም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳዳነውም ያለ አይደለም፣ መምከር ማስተማር መመለስ ሲሆን ይህ ማዳን ይባላል፡፡
በመሆኑም ማዳን ብለን ስንል ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል፣ መስቀል ያድናል፣ ቅዱሳን ያድናሉ፣ መላዕክት ያድናሉ፣ ስንል ዓይነቱንና ልዩነቱን ተረድተን ነው፣ መጻሕፍትም ይህን ቀላቅሎ አይደለም የጻፈው ሁሉን በምስጢር በዓይነትና በልዩነት ነው በአጠቃላይ የሁሉም ማዳን ከእግዚአብሔር ማዳን የሚመነጭ ነው እግዚአብሔር በባሕርይው ያለውን ለቅዱሳን በጸጋው ስለሰጠ አምላክ ነው በባሕርይው አማልክት ዘበጸጋ ይባሉ ዘንድ ሰጥቷል፣ ሕያው ነው በባሕርይው ሕያዋን እንሆን ዘንድ ሰጥቷል፡፡ ዘላለማዊ ነው በባሕርይው ዘላለማዊውን ሕይወት እንድንወርስ ፈቅዷል ሰማያዊ ነው ሰማያውያን እንድንሆንም ፈቅዷል ያልፈቀደውና ያልተሰጠን ጸጋ የለም ነገር ግን በትዕቢት በኩራት በኑፋቄ ወይም በጥርጥር አናገኘውም እንጂ በጽድቅ በትህትና የማናገኘው ምንም ነገር የለም በመሆኑም ማዳን የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ቢሆንም እንኳን ቅዱሳን በጸሎታቸውና በምልጃቸው መላዕክት በተራዳኢነታቸው መምህራን በትምህርታቸው ባልንጀሮች በምክራቸው በተግሳጻቸው እንዲያድኑ ፈቅዷል ጸጋውንም ሰጥቷል፡፡
መዳን ስንል ይህን ማለታችን ነው በተለያየ ጊዜ መጻሕፍትን ስናነብ ወይም የተለያየ ነገር ስናይ ስለ ቅዱሳን ማዳን፣ ስለ መላዕክት ማዳን ስለጠበሉ ማዳን ሲነገር ሌላ ነገር የሚመስላቸው ወገኖች አሉ ‹‹እውነተኛ የወይን ሐረግ እኔ ነኝ ተካዩም አባቴ ነው... እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ ነው ያለው›› (ዮሐ 15÷1-5) በመሆኑም ስለ ዛፉ በአጠቃላይ መናገር ስለ ቅርንጫፍ መናገር ነው፣ ስለግንዱም መናገር ነው ቅርንጫፍ ደረቀ ስንል ዛፉ ደረቀ ማለታችን ነው ወይም ቅርንጫፍ ለመለመ ስንል ዛፉ ለመለመ ማለታችን ነው፡፡
እንደዚሁ ሁሉ ስለ ተክለሃይማኖት ቅርንጫፍ ስለሆኑት፣ ስለ ገብረመንፈስ ቅዱስ ስለ ሌሎችም ቅዱሳን መናገር ስለ ክርስቶስ የወይን ግንድ (የወይን ዛፍ) ስለሆነው መናገር ነው ወይም ደግሞ በሌላ ምሳሌ እርሱ አካል ነው እኛም ብልቶች ነን ተብሏል፡፡ እናም አንድ እጅ ቢታመም፣ እግሩ ቢታመም እጅና እግሩን አይደለም ሐኪም ቤት የሚልከው አንድ ብልት ቢታመም መላ አካል ነው ወደ ሐኪም ቤት የሚሄድ ይህም የሆነበት ስለ ብልቱ ሕመም ማውራት ስለ ሰውየው አካል ማውራትና መናገር ስለሆነ ነው፡፡
ለዚህም ነው በአንድ ኃጢዓተኛ ንስሐ መግባት በሰማይ መላዕክት ዘንድ ታላቅ ደስታ ይሆናል የተባለው (ሉቃ 15÷10) በእኛና በመላዕክት መካከል ያለው ግንኙነት አንድ አካል ብልቶች ስለሆን ነው ሚካኤል አዳነን ስንል እግዚአብሔር አዳነን ማለታችን ነው ለቅዱስ ሚካኤል ጸጋውን ባይሰጠው ፈቃዱን ባይሰጠው አያደርገውምና፡፡ ተክለሃይማኖት አዳነን፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አዳነን፣ ቅድስት አርሴማ አዳነችን ስንል እግዚአብሔር አዳነን ማለታችን ነው ምክንያቱም እግዚአብሔር በተክለሃይማኖት ላይ አድሮ ስራውን ሰራ አዳነን ማለታችን ነው እኛ ድንግል ማርያም ታድነናለች ስንል እግዚአብሔር በሰጣት ቃል ኪዳን የማማለድ ጸጋ ሞገስ ታድነናለች የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ማለታችን ነው፡፡ ይህንንም ስንናገር የማዳንን ልዩነት ከላይ በተገለጸው መሠረት ተረድተንና አውቀን ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

@zekidanemeheret
ሰላም ተወዳጆች "መዳን በማንም የለም" ሐዋ4÷12 የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይዘው ተልባ ጥቅስ እየጠቀሱ በየመንገዱ... በየአውቶቢስ ማቆምያው..ባነር ይዘው እየሰበኩት ያሉት መናፍቃን (ግማሽ ጸጉር ግማሽ መላጣ)😜 ውሸታሞች መሆናቸውን ተረዱልኝ፡፡ከላይ ያሉትን መልእክቶችም ለጓደኞቻችሁ አጋሩልኝ፡፡

"መናፍቃንን ከሩቅ ሆነህ ስትመለከታቸው ለክርስቶስ የተቆረቆሩ ይመስሉሀል ቀርበህ ስታያቸው ግን ክርስቶስን ይሰድቡታል" ቅዱስ አትናቴዎስ

🕊አስተውሉ🕊
#የዘንባባ_ቀለበት_የማሰራችን_ምሳሌ

#1ኛ/ ጌታ ለአዳም "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" ያለውን የተስፋ ቃል (ቃል ኪዳን) ለማስታወስ

#2ኛ/ ጌታ ለእመቤታችን የገባላት የምህረት ቃል ኪዳን ተምሳሌት በመሆኑ፤

#3ኛ/ ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት በመሆኑ ይህንንም ለማሰብ ነው

#4ኛ/ አንድም ጌታ አዳምን ከሰይጣን ግዞት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዞት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስኃ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት በመሆኑ ዘንባባ በጣታችን በቀለበት መልክ እናስራለን፡፡

እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ

@zekidanemeheret
ሰላም ለእናንተ ይሁን ተወዳጆች እንደምን አመሻቹ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የምንመልስላችሁ ማንኛውም ሃይማኖታዊ ጥያቄዎች ካላችሁ ምንም ሳትሳቀቁ በ 👇👇👇
@zekidanemeheretbot ላይ ይላኩልን፡፡
የሰሙነ ሕማማት ሰኞ፡-

#መርገመ_በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው

ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11÷11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡

በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡

በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡

#አንጽሆተ_ቤተ_መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦

ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡

በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስቱ፣ በስድስቱ፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5500 ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡


@zekidanemeheret
“በዐቢይ ጾም መጀመሪያ ሱባኤ ፀሐይ እስኪገባ ይጹሙ፣ ሌሎቹን ሳምንታት እስከ 11 ሰዓት ይጹሙ፥ በሰሙነ ሕማማት ግን ኮከብ እስኪወጣ ይጹሙ" ብለዋል። (ፍት.ነገ.አን 15፥596)።

ፍትሐ ነገሥት ቁጥር 578 ላይ ደግሞ “(የሰሙነ ሕማማትን) ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ይጹሟቸው፣ የሚችል እስከ ሌሊት ዶሮ ጩኸት ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው፣ ሁለቱን በአንድነት መጾም የማይቻለው ግን ቅዳሜን ይጹም” ተብሎ ህግ ተሠርቷል።

👉 @zekidanemeheret
ሰሙነ ሕማማት

ዕለተ ሠሉስ (ማግሰኞ)

👉 ሀ. የጥያቄ ቀን፡-
ዕለተ ሠሉስ የጥያቄ ቀን በመባል ይታወቃል፤ ምክንያቱም ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰኞ ዕለት ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ በዚች ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋል፡፡ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ያቀረቡለት ጥያቄም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለ ትምህርት በማስተማር ተአምራት ማድረግ ገበያ መፍታትን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር

እርሱም መልሶ ‹እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፣ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ፣ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው?ብሎ ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል ከሰው ነው ብንልም ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ያከብሩታል እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን›› ተባባሉና ከወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፤ እርሱም እኔም በማን ሥልጣን እንደዚሁ እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው፡፡ ልቡናቸው በክፋት ሥራና በጥርጥር ስለተሞላ ነው እንጂይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንደሚያደርግ ሳያውቅ ቀርቶ አልነበረም፡፡ (ማቴ.፳፩፥፳፫-፳፮፣ማር.፲፩፥፳፯-፴፫፣ሉቃ. ፳፥፩-፰)

👉 ለ. የትምህርት ቀን፡-
ይህቺ ዕለት ዕለተ ትምህርት ወይም የትምህርት ቀን በመባልም ትጠራለች፡፡ ጌታችን በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት በማስተማር የተሰጠው ስያሜ ሲሆን ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ መክሮ መመለስ እንደሚገባን ሲገልጽልን ነው(ማቴ.፳፩፥፳፰፣፳፭፥፵፮፣ማር.፲፪፥፪፣፲፫፥፴፯፣ ሉቃ.፳፥፱፣፳፩፥፴፰)

እግዚአብሔር አምላክ የሁላችንም መጨረሻ ያሳምርልን።

ምንጭ:- ከማኅበረቅዱሳን ድረገጽ የተወሰደ

@zekidanemeheret
​​በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ እንግዳ ቃላት እና ትርጉማቸው ፡-

በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

#ኪርያላይሶን
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን»ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ «አቤቱ ማረን»ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ«ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡

#ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡

#እብኖዲ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው

#ታኦስ
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡

#ማስያስ
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው

#ትስቡጣ
«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው

#አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

#ሼር
@zekidanemeheret
​​​​በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸሙ ሥርዓቶች

1, ስግደት :-
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።

2, ጸሎት :-
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው።

በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።

3, ጾም :-
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

4, አለመሳሳም :-
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29

5. አክፍሎት :-
እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው።

6, ጉልባን :-
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው።

7, ጥብጠባ :-
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው።

8, ቄጠማ :-
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።

@zekidanemeheret
#የሰሙነ_ሕማማት_ረቡዕ

#ምክረ_አይሁድ_ይባላል
ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማቴ. 26÷1-14፣ ማር. 14÷1-2፣ ሉቃ. 22÷1-6) የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡

#የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል
ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለሽቱዋ ማርያም) "ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ" ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ረቡዕ የመዓዛ ቀን ይባላል፡፡

#የእንባ_ቀንም_ይባላል
ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና። (ማቴ. 26÷6-13፣ ማር. 14÷9፣ ዮሐ. 12÷8) ኃጢአትን በማሰብ ማልቀስና ራስን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ከምታስተምረን ማርያም እንተ እፍረት እንባን ለንስሐ ሕይወት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡


@zekidanemeheret
#የሰሙነ_ህማማት_ሐሙስ

#ጸሎተ_ሐሙስ
በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ፣ መሆኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ተባለ፡፡ (ማቴ. 26፥36-46 ዮሐ.17)

#ሕፅበተ_ሐሙስ_ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፤ «በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ እኛም የአንተን አርአያ አንዘነጋም የሌላውን እግር እናጥባለን፤» ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙትን ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡

#የምስጢር_ቀን_ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፡፡ ይኸውም «ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ» ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ «ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ» በማለት፤ እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምስጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡

#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡-
ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ «ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱ ጠጡ» በማለቱ ይታወቃል (ሉቃ. 22፥20) ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለሆነ የሐዲስ ኪዳስ ሐሙስ ተባለ፡፡

#የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር «ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባርያ ጌታዉ የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ» በማለት (ዮሐ. 15፥15)፤ ከባርነት የወጣንበት ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመሆኑ ሊቃውንቱ የነጻነት ሐሙስ አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች አልላችሁም ተብለናልና፡፡


@zekidanemeheret
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕለተ አርብ መከራ

በሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ አዲስ

ለማውረድ Wifi ብትጠቀሙ ይመከራል

@zekidanemeheret
#የሰሙነ_ሕማማት_ዓርብ

ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያን ልዩ ቀን ነው፡፡ የማይታመመው ታሞ የዋለበት፣ የወደቁ ከተረሱበት ከትቢያ የሚያነሳ እሱ ሲወድቅ ሲነሳ የዋለበት፣ ሕመምተኞችን የሚፈውስ እሱ ሲያቃስት የዋለበት፣ ከሲኦል የዲያብሎስ ግብር ነፃ የሚያወጣ ሲገረፍ የዋለበት፣ ወልደ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ድኅነት በመስዋዕትነት ሙሽራ የሆነበት የደስታ ቀን፤ አሳዳጅ ዲያብሎስ ከነወጥመዱ ድል የተነሳበት ቀን ነው። ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን የተለያየ ምስጢራዊ ስያሜዎች ተሰጥቶታል፡፡

#የስቅለት_ዓርብ ይባላል
የዓለም ሁሉ መድኀኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለዓለም ድኅነት መስዋዕት ሆኖ የዋለበት ዕለት በመሆኑ የስቅለት ዓርብ ተብሏል። (ማቴ 27፡35)

#መልካሙ_ዓርብ ይባላል
ይህም የሚያስገነዝበን ከስቅለተ ክርስቶስ በፊት ማንም ሰው ሲያጠፋ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት ይደረግ ነበር፡፡ በተለይ በሮማውያንና በፈሪሳውያን ሕግ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ነበረ። በዚህ ዕለት ግን ታሪክን የሚቀይር ነገርን የሚገለብጠው አምላክ የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል በደሙ ቀድሶ የምህረት ምልክት፣ የሕይወት አርአያ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ ፣ የቤተክርስቲያን ጌጥ፣ የገዳማት ዘውድ ስላደረገውና በዕለተ ዓርብ በሞቱ ሕይወትን ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ተብሏል፡፡

በዚህ ዕለትም ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱ ፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ ተአምራት አሳይቷል፦
1. ፀሐይ ጨልማለች
2. ጨረቃ ደም ሆናለች
3. ከዋክብት ረግፈዋል
4. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀዷል
5. ምድር ተናውጣለች (ተንቀጥቅጣለች)
6. መቃብሮች ተከፍተዋል
7. ሙታን ተነስተዋል

በዓመት አንድ ጊዜ የምናገኘው ይህ ዕለት ቀራንዮን የምናስብበት ነገረ መስቀሉን የምናስተውልበት እንጂ ስለምድራዊ ኑሮአችን ስንባክን የምንውልበት ስለሆነ በዋዛ ፈዛዛ ልናሳልፈው አይገባም፡፡

@zekidanemeheret
✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
# ሰባቱ_የመስቀሉ_ቃላት
1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46)
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ 23፡34)
3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43)
4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27)
5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28)
6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46)
7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30)
​​"​​ሕማማት መስቀል" ተብለው የሚዘከሩት አሥራ ሦስት ሲሆኑ እነዚህም፦

1. በብረት ሐብለ መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የኋሊት መታሰሩ
2. ከአፍንጫው ደም እስኪወጣ ድረስ 25 ጊዜ በጡጫ መመታቱ
3. 65 ጊዜ ከግንድ ማጋጨታቸው
4. 120 ጊዜ በድንጋይ ፊቱን መመታቱ
5. 365 ጊዜ በሽመል መደብደቡ
6. 80 ጊዜ ጽህሙን መነጨቱ
7. 6666 ጊዜ መገረፉ
8. አክሊለ ሦክ በራሱ ላይ መደፋቱ
9. 136 ጊዜ በምድር ላይ መውደቁ
10. ሳዶር፡ አላዶር፡ አዴራ፡ ዳናትና ሮዳስ በሚባሉ 5ቱ ቅንዋተ መስቀል በችንካር መቸንከሩ
11. መራራ ሐሞትን መጠጣቱ
12. መስቀሉን ተሸክሞ መንገላታቱ
13. በመስቀል መሰቀሉ ናቸው።

@zekidanemeheret
#ክርስቲያኖች_ሁላችሁ_ኑ_እናፅናናት

"ክርስቲያን ሁላችሁ ኑ ድንግል ማርያምን እናፅናናት፤ በልጇ ስቃይ ሆድ ብሷታልና፥ እንባን ከመጠጧ ጋር አመድንም ከምግቧ ጋር ቀላቅላለችና። የተወደደ ልጇ በመስቀል ተሰቅሎ ስታየው አንድ ጊዜ ከእሾህ አንድ ጊዜ ከድንጋይ ላይ እየወደቀች አለቀሰች። ወንድም የሌለው አንድ ልጇ እንዲህ ሲሰቃይ የወለደ አንጀቷ እንደምን ይቻል? ምንስ ብላ ትፅናና? ያፅናኗት ዘንድ ሊቃነ መልአክት በዙሪያዋ መጡ ግን አልተፅናናችም፤ ልጄ እያለ የሚጠራት አባቷ ዳዊትም መጣ ድንግል ግን እርቃኑን የተሰቀለው ልጇን እያየች መሪር እንባን አፈሰሰች። ስለ ልጇ ብዙ መከራ አሳልፋለች፥ ያሁኑ የልጇ መከራ ግን ከሀዘኖች ሁሉ የከፋ ሆነባት። አንድ ልጇ እየሞተ ምን ብላ ትፅናና ? የእናቱን አለመፅናናት ያየ ጌታ ኢየሱስ ከሃዘን ብዛት እንዳትሞት ያፅናናት ዘንድ ቁጽረ ገፅ ለተባለው ለዮሐንስ እነኋት እናትህ አለው። በእውነት እነኋት እናታችን በልጇ ስቃይ ሆድ ብሷታልና ክርስቲያን ሁላችሁ ኑ እናፅናናት።"

@zekidanemeheret