ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
800 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
††† እንኳን ለጻድቃንና ሰማዕታት አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

†††
#አባ_ኢያሱና_አባ_ዮሴፍ †††

††† እነዚህ 2 ቅዱሳን የደብረ ኮራሳኑ ጻድቅና ኮከብ የቅዱስ ሜልዮስ ደቀ መዛሙርት ናቸው:: የቅዱስ ሜልዮስ ነገርስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ቅዱስ ሜልዮስ ልጅነቱን በመንፈሳዊ ትምሕርት ያሳለፈ: በጉብዝናው ወራት ፈጣሪውን ያሰበ ደግ ክርስቲያን ነው:: ይሕችን ዓለም ከነ ክፋቷ ንቆ ኮራሳት ወደሚባል በርሃ ሔዶ በተራራውና በደኑ ውስጥ በጾምና በጸሎት: በትሕርምትም ለበርካታ ዓመታት ተጋድሏል::

በነዚህ የብሕትውና ዘመናቱ ልብሱን ፀሐይና ብርድ ቆራርጦ ስለ ጨረሳቸው ፈጣሪው ጸጉርን አልብሶታል:: የአባ ሜልዮስ ጸጉሩ እስከ እግሩ: ጽሕሙ እስከ ጉልበቱ ነበር::

እድሜው ገፍቶ ሲያረጅ እንዲያገለግሉት እግዚአብሔር ሁለት ወጣት ምስጉን ክርስቲያኖችን ላከለት:: እነርሱም አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ ይባላሉ:: ሁለቱ ቅዱሳን አምላካቸውን እግዚአብሔርንና አባታቸው ቅዱስ ሜልዮስን በፍጹም ቅንነት አገልግለዋል::

ከቆይታ በሁዋላ ግን በአካባቢው የነበሩ ጣዖት አምላኪዎች አራዊት እናጠምዳለን ብለው በዘረጉት መረብ ቅዱስ ሜልዮስን ያዙት:: ክርስቲያን መሆኑን ሲያውቁ "ለፀሐይ ስገድ" ብለው ደበደቡት::

ደቀ መዛሙርቱ ተሯሩጠው መጥተው አባታቸውን በመከራ መሰሉት:: ክርስቶስን አንክድም ስላሉ ሁለቱንም በሰይፍ አንገታቸውን መቷቸው:: ቅዱስ ሜልዮስን ግን ለ15 ቀናት ካሰቃዩት በሁዋላ በቀስት በተደጋጋሚ ወግተው ገድለውታል:: ጻድቅና ሰማዕት ቅዱስ ሜልዮስ ብዙ ተአምራትን አድርጉዋል::

ገዳዮች ግን ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ የሜዳ አህያ ሊያድኑ የወረወሩትን ቀስት የእግዚአብሔር መልአክ ወደነርሱ መልሶባቸው ልብ ልባቸውን ተወግተው ሙተዋል::

††† ይህች ቀን ቅዱሳን አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ ሰማዕትነትን የተቀበሉባት ናት::

††† ቸር አምላክ ከቅዱሱ ሜልዮስና ከደቀ መዛሙርቱ በረከትን ያካፍለን::

††† ሚያዝያ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅድስት ዲዮኒስ ዲያቆናዊት (የሐዋርያት ተከታይ የነበረች)
2.አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ (ሰማዕታት)
3.ቅዱስ መናድሌዎስ
4.አባ አኮላቲሞስ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

††† "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን'
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" †††
(ሮሜ. 8፥35-38)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††