ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
813 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
እንኩዋን ለቅዱስ እና ጻድቅ አባ ገሪማ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" አባ ገሪማ (ይስሐቅ) ዘመደራ "*+

=>አቡነ ገሪማ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሮም ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸው መስፍንያኖስና ሰፍንግያ እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ:: ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑ::

+እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን #ይስሐቅ ብለው አሳደጉት:: ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ:: ለ7 ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ : መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል::

+አንድ ቀን ግን ከግብፅ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው:: ላኪው #አባ_ዸንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና" የሚል ነበር::

+ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ:: ድንገት ግን #ቅዱስ_ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ ዸንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው::

+እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው አመነኮሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ #ኢትዮዽያ መጡ:: ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና ታላቁ አባ ይስሐቅ (ገሪማ) ናቸው:: ሰውነታቸውን በገድል ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር::

+አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው አባ ዸንጠሌዎን አዘኑ:: ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ የሰማውብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ" አሉ:: አባ ይስሐቅ ግን "ሰዎች ብቻ አይደሉም:: ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ ተጠራርጎ ሸሸ::

+ይሕንን የተመለከቱት አባ ዸንጠሌዎን "ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ" (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ) አሏቸው:: ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "#አቡነ_ገሪማ" ተብለው ቀሩ::

+አቡነ ገሪማ ወደ #መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ" እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል:: ይህም የተደረገው በዚህች ቀን (መስከረም 30) ነው::

+ጻድቁ ወንጌልን : ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:-

1.ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር::
"ነግሃ ይዘርዕ ኪነቶ:: ወሠርከ የዓርር ገራኅቶ::" እንዲል::

2.ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር::

3.አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጠበል ሆኖ ዛሬም አለ::

4.ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች::

5.አንድ ቀን ድርሳን እየደረሱ (ወንጌለ ዮሐንስን ሲጽፉ) ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይን አቁመዋታል::

+ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በሁዋላ #ጌታችን ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው:: "ስምሕን የጠራ : መታሰቢያህን ያደረገ : እስከ 12 ትውልድ እምርልሃለሁ:: አንተ ግን ሞትን አትቀምስም" ብሏቸው ተሰወረ:: ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ #ብሔረ_ሕያዋን አድርሰዋቸዋል::

=>ቸሩ አምላካችን ከታላቁ ቅዱስ ጸጋ በረከት ይክፈለን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን::

=>+"+ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ::
ግርማው በእሥራኤል ላይ : ኃይሉም በደመናት ላይ ነው::
እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው::
የእሥራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን : ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል::
እግዚአብሔርም ይመስገን:: +"+ (መዝ. 67:34)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

3.አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ::

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
እንኳን ለቅዱስ እና ጻድቅ አባ ገሪማ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

†   🕊   አባ ገሪማ (ይስሐቅ) ዘመደራ    🕊   †

እግዚአብሔርም ይመስገን
:: +"+ (መዝ. 67፥34)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ  ]

💚💛@sinkisar_gisawe_z_tewahedo
💚💛
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪   
        ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ