✝ #ሰኔና_ሰኞ ✝
=>ሰኔና ሰኞ በልማዳዊ አነጋገር በ7 ዓመት አንዴ ብቻ የሚፈጠር መገጣጠም ነው:: (በቀመር ትምህርት ግን በዘመነ ዮሐንስ ምክንያት በ5 እና በ6 ዓመታት ይመላለሳል)
☞በሃገራችን ብዙ ሰው ነገሮች ድንገት ሲደራረብበት የሃዘኔታ አግራሞቱን ለመግለጽ "#ወይ_ሰኔና_ሰኞ!" ይላል::
☞ነገሩም እየዋለ ሲያድር ወደ ምልኪነት (ባዕድ አምልኮ) እየተቀየረ በመሔዱ በተለይ በገጠሩ የሃገራችን አካባቢ ሰኔና ሰኞ ሲገናኙ (ሰኔ ሰኞ ሲብት) መፍራቱ አለ:: (ልክ በሰንበት ላይ #ደብረ_ዘይት እንደሚከብደው ሁሉ)
☞በተቃራኒው ደግሞ የሰኔና ሰኞ መግጠም በትክክልም የፈጣሪ ማስጠንቀቂያ ነው የሚሉም አሉ፡፡ በተለይም ለቀመር መምህራንና ልጆቻቸው፡፡
☞ዋናው ነገር ግን ሰኔና ሰኞ: ታሪካዊ ዳራውን ሳንዘነጋ ደስ የሚል ቀን ማድረግ እንችላለን:: ይገባልም:: ምክንያቱም:- ሰኔ እና ሰኞ ሥርወ ቃላቸው (የወጡበት ግስ) ተመሳሳይና ጥሩ መሆኑን ማየት እንችላለን::
☞የ2ቱም መሠረታቸው "ሰነየ (አማረ)" የሚል ነውና:: ሰኔም: ሰኞም ማማርን: መበጀትን: መልካምነትን የሚገልጹ ናቸውና::
☞በዚያውም ላይ ከሠራን የማናተርፍበት፡ ከጸለይን ጸጋውን የማናገኝበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ችግሩ ከግጥምጥሞሹ ሳይሆን ከያዝነው #ሰብእና እና #ጎዳና ላይ ነው፡፡
☞ስለዚህ #እንጸልይ ፤ #እንሥራ ፤ ስለክፋታችንም #እንጸጸት ፤፤
☞ከዚህ በሁዋላ ሰኔና ሰኞ የሚገናኙት ከ6 ዓመታት በሁዋላ (በ2018) መሆኑ ነው::
☞እስኪ ደግሞ የዚያ ሰው ይበለን!
" መቼም ዕድሜ አይጠገብ! "
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret