ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
854 subscribers
3.46K photos
103 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
🌻በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን 🌻

ሰኞ ነሐሴ ፱, ፳፻፲፬ ዓ.ም

❇️የቅዱሳን አበው ታሪክ መልመጃ ፩ ❇️

መልመጃውን የምትሠሩት #የተማራችኹትን ብቻ በማስታወስ ይኹን እንጂ ከትምህርቱ እያያችሁ ወይንም ሰው በመጠየቅ አይኹን። "ትምህርቱን ምን ያህል ተረድቼዋለኹ?" ብላችኹ ራሳችኹን የምትገመግሙበት ነውና!

ስማችሁን፦
ከተማችሁን፦

መልሳችሁን @Zekidanemeheretbot
ላይ አስቀምጡ።

ለተጠየቁት ጥያቄዎች በተቻላችሁ አቅም አጭር መልስ አስቀምጡ።

1.መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ምን ማድረግ አለብን? ቢያንስ ሁለቱን ጥቀሱ።


2.ስለቅዱሳን አበው ታሪክ ለምን ዓላማ እንማራለን? ቢያንስ ሁለቱን ጥቀሱ።


3.በገነት ስንት ዓይነት እጽዋት አለ? ስማቸውን ጥቀሱ።

4.እግዚአብሔር አዳምን ከዕጸ በለስ ስለምን አትብላ አለው?


5.አባታችን አዳም እና እናታችን ሔዋን ለስንት ዘመን አልቅሰዋል?


6.በመምታት መግደልን ሁሉ ለሰው ልጆች ያስተማረ፤ ሔዋንን ያሳታት ስሙ ማን ይባላል?


7. ቅዱስ አዳም እና ቅድስት ሔዋን በአቤል ሞት............. ዘመን ቢያለቅሱ ለደግ ሰው ምትክ ሴትን ሰጥቷቸዋል።


8. ......... 22ቱን አሌፋት በጸፍጸፍ ሰማይ የተመለከተ ነው።


9. መጽሐፈ ሔኖክ የተጻፈው ለምንድነው?


10.ቅዱስ ማቱሳላ 969 ዓመት ሲኖር ሐዘንተኛ የነበረበት ምክንያት ምንድንነው?


11.ለ 500 ዓመታት በድንግልና የኖረው አባት ነው?


12.ደቂቀ ሴት ተለይተው ለምን የእግዚአብሔር ልጆች ተባሉ?


13.ቅዱስ ኖኅን ከጥፋት ውኃ ያዳነው መልአክ ማነው?


14.ቅዱስ ኖኅ መርከቡን የሰራው ከምን እንጨት ነው?


15.እግዚአብሔር ኖኅን መርከብ ሰርቶ በዛ እንዲድን ያደረገው ለምንድንነው?


16.እግዚአብሔር ከጥፋት ውኃ በኋላ ሰዎች የእንስሳትን ሥጋ እንዲበሉ ለምን ፈቀደ?


17.በኲረ ምውታን-የመጀመሪያው ሟች ማነው?


18.የአቤል መንትያ ማናት የቃኤልስ ማናት?


19.በ.......... ዘመን ደቂቀ ሴት ከደብር ቅዱስ ወርደዋል።


20.የቅዱስ አባታችን ኖኅ ሚስቱ ማን ትባላለች?


21.ቅዱስ ኖኅ የጥፋት ውኃ በምድር ላይ በሆነ ጊዜ የ........ ዓመት ዕድሜ ነበረው።


መልስ ሠርታችሁ የምትልኩልኝ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ በፈለጋችኹት ሰዓት እስከ ነገ #ማግሰኞ_ማታ_12_ሰዓት ድረስ #ብቻ ይኾናል። ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ መላክ እንዳለመላክ ይቈጠራል።

(መልመጃውን ሠርቶ ለመላክ 36 ሰዓታት ተሰጥቷችኋል ማለት ነው።)

#ረቡዕ_ማታ 3:00 ሰዓት ላይ ትክክለኛውን
መልስ እልክላችኋለሁ።
🌻በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን 🌻

ረቡዕ ነሐሴ ፲፰ ፳፻፲፬ ዓ.ም

❇️ክርስቲያናዊ ሥነምግባር መልመጃ ፩ ❇️

መልመጃውን የምትሠሩት #የተማራችኹትን ብቻ በማስታወስ ይኹን እንጂ ከትምህርቱ እያያችሁ ወይንም ሰው በመጠየቅ አይኹን። "ትምህርቱን ምን ያህል ተረድቼዋለኹ?" ብላችኹ ራሳችኹን የምትገመግሙበት ነውና!

ስማችሁን፦
ከተማችሁን፦

መልሳችሁን @Zekidanemeheretbot
ላይ አስቀምጡ።

ለተጠየቁት ጥያቄዎች በተቻላችሁ አቅም አጭር መልስ አስቀምጡ።

1.የክርስቲያናዊ ሥነምግባር ትምህርት ዓላማዎች ቢያንስ 3ቱን ዘርዝሩ።

2.በክርስቲያናዊ ሥነምግባር ውስጥ የምንማራቸው 10ቱ ትዕዛዛት ለምን 10 ሆኑ?

3.ከ10ቱ ትዕዛዛት ውስጥ በሐልዮ(በማሰብ)፣ በነቢብ(በመናገር) እና በገቢር(በተግባር፣በማድረግ) የሚፈጸሙት ትዕዛዛት ስንት እና ስንት ናቸው?

4.ክርስቲያን ምን ማለት ነው? 5ቱን ትርጉሞች ጻፉ።

5.ክርስቲያናዊ ሥነምግባር በመማር የምናገኘው ጥቅም ምንድንነው? ቢያንስ ሁለቱን ጥቀሱ።

6.ከ10ቱ ትዕዛዛት አንዷ............................. ትባላለች።

7.ክርስቲያናዊ ሥነምግባር ማለት ምን ማለት ነው?

8.10ቱ ትዕዛዛት ለእስራኤላውያን የተሰጠበትን ምክንያት ምንድንነው? ቢያንስ ሁለቱን ጥቀሱ።


መልስ ሠርታችሁ የምትልኩልኝ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ በፈለጋችኹት ሰዓት እስከ ነገ #ሐሙስ_ማታ_12_ሰዓት ድረስ #ብቻ ይኾናል። ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ መላክ እንዳለመላክ ይቈጠራል።

(መልመጃውን ሠርቶ ለመላክ 21 ሰዓታት ተሰጥቷችኋል ማለት ነው።)

#አርብ_ማታ 3:00 ሰዓት ላይ ትክክለኛውን
መልስ እልክላችኋለሁ።
🌻በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን 🌻

❇️ ሥርዓተ ጸሎት ❇️

መልመጃውን የምትሠሩት #የተማራችኹትን ብቻ በማስታወስ ይኹን እንጂ ከትምህርቱ እያያችሁ ወይንም ሰው በመጠየቅ አይኹን። "ትምህርቱን ምን ያህል ተረድቼዋለኹ?" ብላችኹ ራሳችኹን የምትገመግሙበት ነውና!

ስማችሁን፦

ለተጠየቁት ጥያቄዎች በተቻላችሁ አቅም አጭር መልስ አስቀምጡ።

1.ጸሎት ማለት ምን ማለት ነው ቢያንስ 3ቱን ጥቀሱ።

2.የጸሎት ጥቅሙ ምንድንነው? ቢያንስ 3ቱን ጥቀሱ።

3.እግዚአብሔር የለመንነውን ነገር በምን አይነት መንገድ ሊያደርገው ይችላል? ቢያንስ ሁለቱን ጥቀሱ።

4.እግዚአብሔር ጸሎታችንን እንዲሰማን ምን እናድርግ? ቢያንስ 3ቱን ጥቀሱ።

5.አንድ ክርስቲያን እንዴት መጸለይ አለበት? ዘጠኙን ጥቀሱ።

6.የማይሰገድባቸው ቀናት እነማን ናቸው?ዘርዝሩ።

7.እግዚአብሔር ለጸሎታችን መልስ የማይሰጥባቸው ምክንያቶች እነማንናቸው? 2ቱን ጥቀሱ።

8.ከላይ ወደታች እና ከግራ ወደቀኝ ማማተባችን የምን ምሳሌ ነው?

9.ስንት አይነት ጸሎት አለ?ዘርዝሩ።

10.ሰጊድ አስተብርኮ አድንኖ ምን ማለት ነው።

ቦነስ
11................ የክርስቲያኖች መመሪያ ነው።