ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
803 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
እኛ ኦርቶዶክስ አይደለንም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶከክስ #ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነው የኛ መለያ እንጂ ኦርቶዶክስ አይደለም ።

ደሞ በእመቤታችን ጨዋታ የለም ለሁለት ቀን አርገን ከነገ ወዲያ የምናጠፋ አይደለም ዘለአለም በልባችን ላይ የምትኖር እንጂ

ስለዚህ የእመቤታችን ክብር በዚህ አይገለፅም ፍቅሯ ውስጥህ ሲገባ ቋንቋህም እሷ ትሆናለች ።

ስጠቀልል ይህ እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን አይወክልም ።

የኛ ሳይሆን የመናፍቃን ነው ።

አስተወሉ

ባለፈው ሼር በማድረግ ክብሯን ግለፁ እየተባለ ነበር ተአምር በጣልያን ሰርታለች ሼር ካላረጋቹ መከራ ይደርሳል ምናምን

No

ይህ እኛን አይወክልም

ኦርቶዶክስ የምትለዋን ቃል አይታችሁ ነው አይደል ? ግን የኛ መለያ ተዋህዶ ነው #ተዋሕዶ

ለምሳሌ ካቶሊክም ክርስቲያን ነን ይላሉ እና መናፍቃንም አሉ ተሀድሶም አለ ክርስቲያን ነን ብሎ በኦርቶዶክስ የሚጠራ ብዙዙዙዙ አለ ግን የኛ መለያ ተዋሕዶ አስተውል

ተዋሕዶ ነው ።

❤️❤️

እባካችሁ ይህን ሼር በማድረግ የመናፍቃንን ስራ እንቃወም ።

ቅድስተ ቅዱሳን ንፅሕተ ንፁሀን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ መጫወቻ አይደለችም ።
👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† እንኩዋን ለስደተኛው ሊቀ ዻዻሳት "አባ ቴዎዶስዮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

+*" አባ ቴዎዶስዮስ "*+

=>ጻድቁ ሊቀ ዻዻሳት ተወልዶ ያደገው በምድረ ግብጽ በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ከልጅነቱ መጻሕፍትን ተምሮ በመንኖ ጥሪት የሚኖር ደግ ሰው ነበር:: ያ ዘመን መለካውያንና ልዮናውያን (ክርስቶስን 2 ባሕርይ የሚሉ) የሰለጠኑበት ዘመን ነበር:: በአንጻሩ ደግሞ ተዋሕዶን የሚያምኑ ሊቃውንትና ምዕመናን ቁጥራቸው የተመናመነ ነበር::

+ችግሩ ግን ይህ ብቻ አልነበረም:: በጊዜው ተዋሕዶን አምኖ መገኘት እስከ ሞት የሚደርስ ዋጋንም ያስከፍል ነበር:: ለዚሕም ነው ሮማውያን ሃይማኖትን በግድ ለማስለወጥ ከነገሥታቱ ጋር የተቆራኙት:: #ቅዱስ_ዲዮስቆሮስ ጋግራ ደሴት ውስጥ ከተገደለ በሁዋላ በግብፅ የተሾሙ ሊቃነ ዻዻሳት አብዛኞቹ መከራና ስደትን ቀምሰዋል:: ትልቁን ቦታ ግን #አባ_ቴዎዶስዮስ ይወስዳል::

+አባ ቴዎዶስዮስ ለእስክንድርያ (ግብፅ) 33ኛ ፓትርያርክ ነው:: እረኝነት (ዽዽስና) እንዳሁኑ ዘመን ሠርግና ምላሽ አይደለምና ገና እንደ ተሾመ የቀረበለት ጥያቄ አንድ ነበር:: "ተዋሕዶን ትተህ መለካዊ ትሆናለህ ወይስ የሚከተልብህን ፍርድ ትቀበላለህ?" አሉት:: ይህንን ያሉት ከንጉሡ ዮስጢያኖስ የመጡ መልእክተኞች ነበሩ:: መልሱ ፈጣን ሆነባቸው:: "እኔንም ሆነ ሕዝቤን ከቀናችው እምነታችን በምንም ልትለዩን አትችሉም" አላቸው::

+በዚህ ምክንያት በቀጥታ ግዞት (ስደት) ተፈረደበት:: ወደ በርሃ ሲያግዙት ካህናት : መምሕራንንና ምዕመናንን አደራ ብሏቸው ነው የሔደው:: መናፍቃኑ እሱን ካሰደዱ በሁዋላ ሕዝቡን ለመቀየር ብዙ ደክመዋል:: ግን ሊሳካላቸው አልቻለም:: ምክንያቱም አደርነትን የማይረሱ ደጋግ መምሕራን ነበሩና ነው::

+በዚያ ላይ አባ ቴዎዶስዮስ #ጦማር (መልእክት) በየጊዜው ይጽፍላቸው ነበር:: እጅግ ብዙ ከሆኑት መልእክቶቹ የተወሰኑት ዛሬም ድረስ #ሃይማኖተ_አበው መጽሐፍ ውስጥ ይገኛሉ::

+በዚሕ አስቸጋሪ ዘመን መልካም ነገሮችም ነበሩ:: ቀዳሚው #ማሕቶተ_ተዋሕዶ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘእልበረዳይ ሲሆን 2ኛው ደግሞ የንጉሡ ሚስት የተባረከችው #ታኦድራ ናት::

+አባ ቴዎዶስዮስ በግዞትና በስደት ሳለ ንግሥቲቱ ትራዳው : ምዕመናንንም ትንከባከብ ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ከሊቀ ዻዻሱ ዘንድ ክህነትን ተቀብሎ ከሶርያ እስከ ምድረ ግብጽ ስለ #ተዋሕዶ ሕልውና ተጋድሏል:: ምናልባትም ከሐዋርያው #ቅዱስ_ዻውሎስ በሁዋላ በፈሊጥ ክርስትናን በማስፋፋት ቀዳሚ አባት ነው:: (በነገራችን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማዕተብ ማሰርን ያስተማረ አባትም ነው)

+2ቱ (አባ ቴዎዶስዮስና ቅዱስ ያዕቆብ) ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ ስለ ደከሙ የዘመኑ ምዕመናን በስማቸው "#ያዕቆባውያን እና #ቴዎዶስዮሳውያን" ተብለው ተጠርተዋል:: አባ ቴዎዶስዮስ ግን ሲታሠር ሲፈታ : ሲሰደድ ሲመለስ ብዙ ተሰቃየ::

+ሕዝቡን ግን በመልካም እረኝነት ጠብቆ : ከተኩላ አፍ ታደገ:: በዚህች ቀንም ዐርፎ ተቀብሯል:: በፓትርያርክነት ያገለገለባቸው ዘመናት 32 ዓመታት ሲሆኑ ከእነዚህ ዓመታት 28ቱ ያለቁት በስደትና በመከራ ነው::

=>እግዚአብሔር የአባቶቻችን ስደት አስቦ ከነፍስ ስደት ይሰውረን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

=>ሰኔ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ቴዎዶስዮስ ሊቀ ዻዻሳት
2.ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዳይ
3.ቅዱስ ባስልዮስ
4.ቅዱስ ባሊዲስ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን
2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)
3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
4.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)

=>+"+ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዷችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና:: +"+ (ማቴ. 5:10)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ታላቁ ሊቅ #ቅዱስ_ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ

¤የመናፍቃንን ትምህርት ቀጥቅጦ ያጠፋ አንበሳ::
¤ስለ ሃይማኖት (#ተዋሕዶ) የተዋጋ አርበኛ::
¤ስለ እውነት የተሰቃየ ስደተኛ ነው::

በረከቱ ይደርብን: በምልጃውም ይጠብቀን !!!

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
=>+"+ እንኩዋን ለስደተኛው ሊቀ ዻዻሳት "አባ ቴዎዶስዮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ታላቁ ሊቅ #ቅዱስ_ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ ስደቱ

¤የመናፍቃንን ትምህርት ቀጥቅጦ ያጠፋ አንበሳ::
¤ስለ ሃይማኖት (#ተዋሕዶ) የተዋጋ አርበኛ::
¤ስለ እውነት የተሰቃየ ስደተኛ ነው::

በረከቱ ይደርብን: በምልጃውም ይጠብቀን !!!

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር

+አባ ቴዎዶስዮስ ለእስክንድርያ (ግብፅ) 33ኛ ፓትርያርክ ነው:: እረኝነት (ዽዽስና) እንዳሁኑ ዘመን ሰርግና ምላሽ አይደለምና ገና እንደ ተሾመ የቀረበለት ጥያቄ አንድ ነበር:: "ተዋሕዶን ትተህ መለካዊ ትሆናለህ ወይስ የሚከተልብህን ፍርድ ትቀበላለህ?" አሉት:: ይህንን ያሉት ከንጉሡ ዮስጢያኖስ የመጡ መልእክተኞች ነበሩ:: መልሱ ፈጣን ሆነባቸው:: "እኔንም ሆነ ሕዝቤን ከቀናችው እምነታችን በምንም ልትለዩን አትችሉም" አላቸው::

+በዚህ ምክንያት በቀጥታ ግዞት (ስደት) ተፈረደበት:: ወደ በርሃ ሲያግዙት ካህናት : መምህራንንና ምዕመናንን አደራ ብሏቸው ነው የሔደው:: መናፍቃኑ እሱን ካሰደዱ በሁዋላ ሕዝቡን ለመቀየር ብዙ ደክመዋል:: ግን ሊሳካላቸው አልቻለም:: ምክንያቱም አደራነትን የማይረሱ ደጋግ መምህራን ነበሩና ነው::

+በዚያ ላይ አባ ቴዎዶስዮስ #ጦማር (መልእክት) በየጊዜው ይጽፍላቸው ነበር:: እጅግ ብዙ ከሆኑት መልእክቶቹ የተወሰኑት ዛሬም ድረስ #ሃይማኖተ_አበው መጽሐፍ ውስጥ ይገኛሉ::

+በዚሕ አስቸጋሪ ዘመን መልካም ነገሮችም ነበሩ:: ቀዳሚው #ማሕቶተ_ተዋሕዶ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘእልበረዳይ ሲሆን 2ኛው ደግሞ የንጉሡ ሚስት የተባረከችው #ታኦድራ ናት::

+አባ ቴዎዶስዮስ በግዞትና በስደት ሳለ ንግሥቲቱ ትራዳው : ምዕመናንንም ትንከባከብ ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ከሊቀ ዻዻሱ ዘንድ ክህነትን ተቀብሎ ከሶርያ እስከ ምድረ ግብጽ ስለ #ተዋሕዶ ሕልውና ተጋድሏል:: ምናልባትም ከሐዋርያው #ቅዱስ_ዻውሎስ በሁዋላ በፈሊጥ ክርስትናን በማስፋፋት ቀዳሚ አባት ነው:: (በነገራችን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማዕተብ ማሰርን ያስተማረ አባትም ነው)

+2ቱ (አባ ቴዎዶስዮስና ቅዱስ ያዕቆብ) ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ ስለ ደከሙ የዘመኑ ምዕመናን በስማቸው "#ያዕቆባውያን እና #ቴዎዶስዮሳውያን" ተብለው ተጠርተዋል:: አባ ቴዎዶስዮስ ግን ሲታሠር ሲፈታ : ሲሰደድ ሲመለስ ብዙ ተሰቃየ::

+ሕዝቡን ግን በመልካም እረኝነት ጠብቆ : ከተኩላ አፍ ታደገ:: በዚህች ቀንም ዐርፎ ተቀብሯል:: በፓትርያርክነት ያገለገለባቸው ዘመናት 32 ዓመታት ሲሆኑ ከእነዚህ ዓመታት 28ቱ ያለቁት በስደትና በመከራ ነው::

=>እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ስደት አስቦ ከነፍስ ስደት ይሰውረን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

=>ሰኔ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ቴዎዶስዮስ ሊቀ ዻዻሳት
2.ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዳይ
3.ቅዱስ ባስልዮስ
4.ቅዱስ ባሊዲስ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን
2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)
3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
4.ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ
5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)

=>+"+ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው:: መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዷችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና:: +"+ (ማቴ. 5:10)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Forwarded from 🕊ኢዮአታም🕊
ታላቁ ሊቅ #ቅዱስ_ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ

¤የመናፍቃንን ትምህርት ቀጥቅጦ ያጠፋ አንበሳ::
¤ስለ ሃይማኖት (#ተዋሕዶ) የተዋጋ አርበኛ::
¤ስለ እውነት የተሰቃየ ስደተኛ ነው::

በረከቱ ይደርብን: በምልጃውም ይጠብቀን !!!

@zeortodox_kidusan_pic