ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
854 subscribers
3.46K photos
103 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
"እየጾማችሁ ነውን?"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

እንግዲያስ መጾማችሁን በተግባር አሳዩኝ፡፡ "እንዴት
አድርገን እናሳይህ?" ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስላችኋለሁ፡- ድኻው እርዳታችሁን ፈልጎ እንደሆነ ቸርነትን አድርጉለት፤ የጠላችሁትን ሰው ካያችሁት ከእርሱ ጋር ፈጥናችሁ ታረቁ፤ ባልጀራችሁ ተሳክቶለት ስታዩት በእርሱ ላይ ቅናት አትያዙ፤ ቆነጃጅትን በመንገድ ሲያልፉ ስታዩ በዝሙት ዓይን አትመኙ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያደረጋችሁ በትክክል መጾማችሁን አሳዩኝ፡፡

በሌላ አገላለጽ አፋችሁ ብቻ ሳይሆን ዐይናችሁ፣ እግራችሁ፣ እጃችሁ፣ በአጠቃላይ የሰውነታችሁ ሕዋሳቶች በሙሉ መጾም አለባቸው፡፡
       + እጆቻችሁ ከመስረቅና የእናንተ ያልሆነውን
          ከመውሰድ ይጹሙ፤
       + እግሮቻችሁ የኃጢአት ሥራን ለመፈፀም
           ከመፋጠን ይጹሙ፤
       + ዐይኖቻችሁ ውጫዊ በሆነ ውበት ምክንያት
          ከመቅበዝበዝ ይጹሙ፡፡

ጥሉላትን (የፍስክ ምግብ) እየበላችሁ አይደለም አይደል? እንግዲያስ በዐይኖቻችሁም ክፉ ነገርን አትብሉ፡፡ የሚታዩ ነገሮች ለዐይን ምግቦች ናቸውና፡፡ ጀሮዎቻችሁም ይጹሙ፡፡ የጀሮ ጾም ሐሰተኛ ወሬንና ሐሜትን አለመስማትና ይህን የመሳሰለ ነው አንደበታችሁም ከከንቱ ንግግር ይጹም፡፡ ዓሣንና ሌሎች ጥሉላትን ከመብላት ተከልክለን ሳለ ነገር ግን ወንድሞቻችንን በሐሜት የምናኝካቸውና የምንበላቸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው?

ወንድሙን የሚያማና የሚነቅፍ ሰው እርሱ የወንድሙን አካል ያቆስላል፤ ሥጋውንም ይበላል፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ይህን አስመልክቶ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- "እርስ በእርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በእርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" /ገላ.5፡15/፡፡ ስታሙ በጥርሳችሁ የወንድማችሁን ሥጋ አትነክሱም፡፡ በክፉ ንግግራችሁ ግን የወንድማችሁን ነፍስ ትነክሳላችሁ፤ ታቆስሉትማላችሁ፡፡ እንዲህ በማድረጋችሁ ራሳችሁን፣ ወንድማችሁንና ሌሎች ብዙ ሰዎችን ትጎዳላችሁ፡፡

አንደበታችሁ ክፉ ነገርን ከመናገር ካልጾመ ጉዳቱ
በዚህ ብቻ አያበቃም፡፡ በሐሜታችሁ እናንተን የሚሰማ ወንድማችሁም የሐሜታችሁ ተባባሪ ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት እርሱንም በደለኛ ታደርጉታላችሁ ማለት ነው፡፡ እርሱም የራሱን ኃጢአት እንዳይመለከት ስላደረጋችሁት ሳያውቅ ከሐሜተኞች ጎራ ይቀላቀላል፡፡ በዚህም የሌሎች ወንድሞቹን ድካም እየተመለከተ እርሱ ግን በመጾሙ ትልቅ የጽድቅ ሥራን እንደፈጸመ ቆጥሮ ይኩራራል ስለዚህ አንደበታችሁም ክፉ ከመናገር ይጹም፡፡

https://t.me/zekidanemeheret
#አትርሳ!

አንድ ሰው ወደ ቤተ መንግሥት አንዲት ሴተኛ አዳሪን ይዞ መጥቶ በንጉሡ ፊትም ሩካቤ ቢፈጽም፣ ወይም ቢሰክር፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ተግባር ቢፈጽም የቅጣት ቅጣት ይደርስበታል፡፡

አሁን ራሳችንን ጥያቄ እንጠይቅ፡፡ እግዚአብሔር የሰማይም የምድርን ንጉሥ ነው ወይስ አይደለም? ነው! የምናደርገውን ማንኛውም ድርጊት ይመለከታል ወይስ አይመለከትም? ኧረ ይመለከታል!
ታዲያ በምድራዊ ንጉሥ ፊት ከላይ የጠቀስናቸውን ነውሮች ደፍሮ የፈጸመ ሰው ጽኑ ቅጣት የሚቀጣ ከኾነ እንደዚህ ያሉ ተግባራትን በእግዚአብሔር ፊት ለማከናወን የምንደፍረው ለምንድን ነው? ምድራዊው ንጉሥ ቢቀጣ ምድራዊ ቅጣትን ነው፡፡ ሰማያዊው ንጉሥ ሲቀጣ ግን ሰማያዊ ቅጣት እንደ ኾነ አናውቅምን? ...

ሰው ሆይ! እያንዳንዷን ድርጊትህ የሚመለከት የሰማይም የምድርም ንጉሥ እንዳለ በፍጹም አትርሳ፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ- አምስቱ የንስሐ መንገዶች እና ሌሎች - ገጽ 119)

#ይቀላቀሉ

https://t.me/zekidanemeheret
"ስለ እግዚአብሔር ብለህ ለሰዎች ታዘዝ እንጂ ስለ ሰዎች ብለህ ለእግዚአብሔር አትታዘዝ፡፡"

#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"የተሳሳተ እምነት ይዘን መልካም ሕይወት ብንኖር ምንም ጥቅም የለውም፡፡ ልክ እንደዛውም ቀጥተኛ ሃይማኖት ይዘን የኃጢአት ኑሮ ብንኖር ምንም ፋይዳ የለውም፡፡ እምነት ብቻ ለመዳን በቂ አይምሰለን ንጹሕ ሕይወትም አስፈላጊና ወሳኝ ነው፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
"ጀግና ከሆንክ በራስህ ላይ ጦርነት አውጅበት!!!
መቆጣት ከፈለግህ መጀመሪያ በራስህ ላይ ተቆጣ።

ልክስክነትህን፤ ስግብግብነትህን፤ ክፋትህን፤ ዝርክርክነትህን፤  ዘማዊነትህን ተቆጣው፤ ስንፍናህን ተቆጣው።

በዲያብሎስ ላይ ጦርነት ክፈትበት፤ የዘለዓለም ዕረፍትህን ለሚነጥቅህ፤ ከዘለዓለማዊ ርስት ለነጠቀህ፤ ከልጅነት ለሚያዋርድህ፤ ከእግዚአብሔር ከሚያጣላህ፤ ከክብር ካዋረደህ በእርሱ ላይ መጀመሪያ ተነሥ።››

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
"ሌቦች ወርቅና ብር ያለውን እንጂ ድርቆሽና ገለባ እንዲሁም ሰንበሌጥ ያለውን ቤት አይበረብሩም፡፡ ዲያብሎስም የሚያጠቃው (የሚፈትነው) መንፈሳዊ ምግባራትን የሚያበዙትን ሰዎች ነው፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
“ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ እግዚአብሔርን ለአምላክነቱ እንደሚገባ አምልከህ ከዚያ በኋላ ወደ ሥራህ ብትሔድ የምትሠራው ሥራ የተባረከና የሰመረ እንደሚሆንልህ አታውቅምን?"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#አትርሳ!

አንድ ሰው ወደ ቤተ መንግሥት አንዲት ሴተኛ አዳሪን ይዞ መጥቶ በንጉሡ ፊትም ሩካቤ ቢፈጽም፣ ወይም ቢሰክር፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ተግባር ቢፈጽም የቅጣት ቅጣት ይደርስበታል፡፡

አሁን ራሳችንን ጥያቄ እንጠይቅ፡፡ እግዚአብሔር የሰማይም የምድርም ንጉሥ ነው ወይስ አይደለም? ነው! የምናደርገውን ማንኛውም ድርጊት ይመለከታል ወይስ አይመለከትም? ኧረ ይመለከታል!
ታዲያ በምድራዊ ንጉሥ ፊት ከላይ የጠቀስናቸውን ነውሮች ደፍሮ የፈጸመ ሰው ጽኑ ቅጣት የሚቀጣ ከኾነ እንደዚህ ያሉ ተግባራትን በእግዚአብሔር ፊት ለማከናወን የምንደፍረው ለምንድን ነው? ምድራዊው ንጉሥ ቢቀጣ ምድራዊ ቅጣትን ነው፡፡ ሰማያዊው ንጉሥ ሲቀጣ ግን ሰማያዊ ቅጣት እንደ ኾነ አናውቅምን? ...

ሰው ሆይ! እያንዳንዷን ድርጊትህ የሚመለከት የሰማይም የምድርም ንጉሥ እንዳለ በፍጹም አትርሳ፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ- አምስቱ የንስሐ መንገዶች እና ሌሎች - ገጽ 119)