ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
800 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ኦርቶዶክስ_መልስ_አላት
#ክፍል_6
#የ40ቀንና_የ80ቀን_ጥምቀት
አብዛኛውን ጊዜ በፕሮቴስታንቶች በኩል ጥምቀት ላይ የሚያነሷቸው ሁለት ነገሮች ናቸው ። #አንደኛ ፦ ሕፃናት መጠመቅ የለባቸውም የሚል ሲሆን #ሁለተኛው ደሞ እምነት እንጂ ጥምቀት አያድንም የሚል ነው ። በማር 16:16 ላይ ያለውን በመጥቀስ አንድ ሰው አምኖ መጠመቅ አለበት እንጂ ሳያምን ፣ ሳያውቅ ቢጠመቅ ምን ይረባዋል ? ይላሉ ። በመሰረቱ " ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል "የሚለው ይህ ቃል ላመኑት ሳይሆን ላላመኑት የተነገረ ነው ። በተለይም ወደ ዓለም በሚሄዱበት ሰዓት ሐዋርያት አገልግሎታቸው የቀና ይሆን ዘንድ ያላመኑት ማመን ስለሚያስፈልጋቸው ነው ። ለቃሉ መነሻ የሆነው ጥቅስ እንዲህ ይነበባል "... ተነስቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውን የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ " (ማር 16:16) አለማመናቸውን ለመንቀፍ ጌታ የተናገረውን ቃል ሕፃናትን መጠመቅ የለባቸውም ብሎ ከሚያምን ቤተሰብ የተገኙትን ህፃናት ላይ እንዳይጠመቁ መፍረድ ክፋ ሀጥያት ነው ። እንደውም መፅሐፍ ቅዱስ ጥምቀተ ሕፃናትን አይቃወምም እንደውም ይደግፈዋል። ለዚህም ማረጋገጫችን ጌታችን " ሕፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው " ብሏል ። /ማቴ19:14/ ታዲያ ይህን እውነት ይዘን ስንጓዝ ወደ ብሉይ ኪዳን መለስ ብለን እናስተውለዋለን ። ይህም በዘሌ 12 ላይ ከቁ 1 - 8 ስናነብ ይህንኑ የወንድ ልጅና የሴት ልጅ ወደ እግዚአብሔር ቤት መሄድ የሚገባቸውን ጊዜ እንዲህ በማለት ገልፆታል ። "ሴት ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ ሰባት ቀን ያህል የረከሰች ናት። በስምንተኛው ቀን ከሥጋው ሸለፈት ይገረዝ ከደምዋም እስክትነፃ 33 ቀን ትቀመጥ ይላል ። 7 እና 33 ስንደምራቸው #40 ቀን ይሆናል ። #ለወንድ ልጅ ይህንን ብሏል ። #ለሴት ልጅ ደሞ 2 ሳምንት ያህል የረከሰች ናት ከደምዋም እስክትነፃ ድረስ 66 ቀን ትቀመጥ ይላል ።14 እና 66 ስንደምራቸው #80 ቀን ይሆናል ። በመፅሐፈ ኩፋሌ 4:9 ላይ ደሞ "እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረው በ40 ቀኑ ሔዋንን በፈጠራት በ80 ቀኗ መላዕክት ዕፁብ ዕፁብ እያሉ ገነት እንዳስገቧቸው ይናገራል ። ቤተክርስቲያን ይሄን ምክንያት በማድረግ ወንድ በ40 ቀን ሴት በ80 ቀን ታጠምቃለች ። ነገር ከ40 ቀን በተለያየ ችግር ምክንያት ቢያልፍ መጠመቅ አይችልም ማለት አይደለም ። ከዛ በፊትም የከፋ ለሞት የሚያደርስ ህመም ቢያጋጥመው እንዲጠመቅ ፍትሐ ነገስት ያዛል ።
#የአጠማመቅ_ሥርዓታችንና_ፍቺው
ዲያቆኑ ሕፃኑን ይዞ ፊቱን ወደ ምዕራብ አዙሮ እክህደከ ሰይጣን በማለት 3 ጊዜ ይናገራል ። ይህም ሰይጣንን እክደዋለው ማለት ነው ።
እንደገና ፊቱን ወደ ምስራቅ ሕፃኑን እንደያዘ ይመልስና አአምን በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ በማለት 3 ጊዜ ከተናገረ በኀላ ወደማጥመቂያው ያቀርበዋል። ይህም በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም አምናለው ማለት ነው ። "በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም አጥምቁ " ብሎ እንዳዘዘው ነው ። (ማቴ 28:19)
ምንጭ ። ኰኲሕ ሐይማኖት



ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት
ኢዮአታም
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_9
#የተሳሳተ_የትዳር_ጓደኛ_አመራረጥ
በዓለማችን ላይ ለምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ውሳኔዎችን እንወስናለን ። #ጋብቻም የእኛን ውሳኔ ከሚጠይቁት ቁም ነገሮች አንዱ ነው ። በመንፈሳዊ መነጽር ስንመለከተው እግዚአብሔር ያዘጋጀውን በጋብቻ ልንረከብ /ልንቀበል/ እንደምንችል የታመነ ነው ። ለአዳም ሔዋንን የሰጠ እርሱ ነውና ። ሆኖም ግን ከመወለድ ፈጽሞ የተለየ ነው ። እኛ ስንወለድ አሁን አባት እናት ከሆኑን ወላጆቻችን ዘንድ መወለድ እንዳለብን ወስነን የገባንበት አይደለም ። ወይም የአሁኗ እናታችንና አባታችን እንዲሁም ወንድምና እህቶቻችንን የኛ ቤተሰብ እንዲሆኑልን ወስነን የገባንበት አይደለም ። #ጋብቻ ግን ከዚህ ይለያል ። ም/ቱም የትዳር ጓደኛችንን የምንቀበለው ትሆነኛለች ይሆነኛል ያልነውን ወስነን ነውና ። ከዚህ ጋር አያይዘንም ለምርጫችን አሳሳች የሆኑ ነገሮችን ማየትና መመርመር መርምሮም መገንዘብ ያስፈልጋል። ለዚሁም የሚከተሉትን በምሳሌነት ማየት ይቻላል።
#ሀ_ጥንቆላ
ጥንቆላ በቤተክርስቲያናችን የተወገዘ ተግባር ነው ። ሰዎች ዕውቀታቸው እና አእምሮአቸው ውሱን ስለሆነ ስለነገ ማወቅ አይችሉም ። በመሆኑም ስለተሰወረባቸው እውቀት ለማወቅ ጉጉዎች ናቸው ። ከዚህም በመነሳት የወደፊት የትዳር ጓደኛቸው ምን አይነት እንደሆነ ፣ ወደፊት ስለሚወልዱት ልጅ እንዲነግራቸው ጠንቋይ ጋር ይሄዳሉ ።
#ለ_አሳሳች_ሕልም
ሕልም ሁለት ወገን ነው ። #አንዱ የነፍስ ወገን ሆኖ ፍሬ ፣ ቁምነገርና ውጤት ያለው ትንቢት ወይም ራዕይ ይባላል። እነ ዮሴፍ እነ ዳንኤል ያዩት ህልም ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው ። #ሁለተኛው ወገን ደሞ
ከሰይጣን የሚመጣ አሳሳች ነው ። መመንኮስ ያለበት ማግባት እንዳለበት ፤ ማግባት ያለበት ደሞ መመንኮስ እንዳለበት አድርጎ ሊያሳየው ይችላል። ስለዚህ በደፈናው እገሊትን እገሌን በህልሜ አይቻለው ብሎ ወደ ትዳር መግባት የቅዠት ትዳር ምስረታ መሆኑን መገንዘብ ይገባል ።
#ሐ_ዕጣ_ማውጣት
ዕጣ ማውጣት በብሉይም በሀዲስም የነበረ አሁንም ያለ የሰው ልጆች የኑሮ ክፍል ነው ። ስለዚህ ሰዎች ለመወሰን የተቸገሩበትን ነገር ወይም ወስነው ይበልጥ ለማረጋገጥ የፈለጉትን ነገር አስመልክቶ ዕጣ ሲያወጡ ይታያል ። በመፅሐፍም ለምሳሌ በዮናስ ታሪክ ላይ ማዕበል በመነሳቱ በመርከብ ያሉትን ሰዎች በማን ሀጥያት መሆኑን ለማረጋገጥ ዕጣ ሲጥሉ በዮናስ ላይ ወጥቷል ። የእመቤታችን ጠባቂ እንዲሆን እግዚአብሔር በልዩ ልዩ ምልክት ጻድቁንና አረጋዊዉን ዮሴፍን ከመረጠው በሗላ ካህናቱ በዕጣ አረጋግጠዋል ። ዛሬም በሀገራችን በጎ ልማድ ተይዞ ሰዎች ሲታመሙ ጠበል ለመምረጥ ዕጣ ያወጣሉ ። ከዚህ በመነሳት ብዙ ሴት የወደደ ወንድ ፤ ወይም ብዙ ወንድ የወደደች ሴት ከእነዚህ አንዱ የኔ እንዲሆን ብላ ዕጣ ልታወጣ ታስብ ይሆናል ። ነገር ግን በዚህ መመራት ከባድ ነው ። ሁልጊዜ ዕጣ ማውጣት የእግዚአብሔር ፍቃድ መገለጫ ላይሆን ይችላል። መጓዝ ያለብንን ያህል ተጉዘን እንወስን እንጂ ከላይ ባየናቸው መንገዶች የትዳር አጋርን መምረጥ ስህተት ነው ። ቀጣይ ደሞ የጋብቻ አይነቶችን እናያለን።

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#4_አንዳንድ_ሰዎች_ለራሳቸው_ ይቅርታ_የሚያደርጉት_እራሳቸውን_ ደካም_በማድረግ_እና የእግዚአብሔርን_ትዕዛዛትን_ የማይፈጸሙ_ከባድ_አድርጎ_ በማመን_ነው። በእርግጥ ከእግዚአብሔር እርዳታ ውጭ ከሆንክ ደካማ ነኝ ብለህ ልታስብ ትችላለህ ነገር ግን እንዲህ ማለት ደግሞ ትችላለህ "እኔ ችግሩንም ምቾቱንም እችላለው ራቡንም፡ጥጋቡንም፡ ማዘኑንም፡ደስታውንም ሁሉን በሁሉ ለምጀዋለው በሚያስችለኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ"(ፊል4፥12--13)።አንተ ጸሎተኛ ከሆንክ ደካማ ልትሆን አትችልም ምክንያቱም የእግዚአብሔር ኃይል ከአንተ ጋር ስለሆነ። የእግዚአብሔር ኃይል በሁሉም ኃጢአት ድል እንድትቀናጅ ያደርግሃል። ከወደክበትም ያነሳሃል። ዳዊት ራሱን እንደ ደካማ አድርጎ ቢያስብ ኖሮ ከጎልያድ ጋር አይታገልም ነበር።እንዲህ አይነት የደካማነት ስሜት ካለ ብዙ ሰዎች እንደ ጎልያድ ያለ ጠላታቸውን መዋጋት አይችሉም። ዳዊት ምክንያታዊ ሆነ ጎልያድን ከመዋጋት አላፈገፈም። ዳዊት ምክንያቶችን መደርደር ቢፈልግ ኖሮ፤ #በመጀመርያ ዳዊት ለወንድሞቹ ስንቅ ለማቀበል የተገኘ እንጂ ወታደር አልነበረም።ስለሆነም ስንቃቸውን ከሰጠ በኃላ በጎውን ሁሉ ተመኝቶ መሰናበት ይችል ነበር። #ሁለተኛው ምክንያት ሊሆን የሚችለው ጎልያድ በጣም የተፈራ ሰው ነበር አንድ ሕጻን ለምን አልታገለውም ወይም ፈሪ ብሎ የሚታዘበው አይኖርም ነበር። #ሦስተኛ ደግሞ ጎልያድን እንዲፋለመው ማንም አልጠየቀውም ነብር። ጎልያድን መታገል ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ሁሉም ሊረዳ ቢችልም ዳዊት ግን በእምነት ድልን ተቀናጀ።
የጌታ ትዕዛዛትን በጣም ከባድ እንደሆነ አታስብ። እግዚአብሔር የማይቻለውን እንድንሰራ ከቶውንም አያዘንም የሚያዘን ነገር እንኳ የፈለገውን ያህል ከባድ ቢመስለንም ለመፈጸም የሚያስችል ብርታቱን እና አቅሙን ጭምር ይሰጠናል፡ ጸጋውን ይሰጠናል። ለምንሰራው ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ያዘጋጅልናል።እየሰራንም ከእኛ ጋር ይሆናል። ይህ ካልሆነ ግን ማንም የሚያገሳውን አንበሳ እርሱንም ዲያብሎስን የሚቋቋም አይኖርም።በእውነት ሰማያዊ መንግሥት ለመውረስ እንደአለት የጠነከረ ልብን ትፈልጋለች። በመከራ ወይም በፈተና የሚቀልጥ ልብን አትፈልግም። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል"በርታ ሰውም ሁን እንደ ማዝዝህ የምታደርገውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ በሙሴም ሕግ የተጻፈውን ሥርዐቱንና ትዕዛዙን ፍርዱንና ምስክሩንም ትጠብቅ ዘንድ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ የአምላክህን የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ጠብቅ"(1ነገ2፥2)
#ከመንፈሳዊ_አገልግሎታችን፤ ለምሳሌ፣ከማስቀደስ፣ከጾም፣ሥጋ ወደሙ ከመቀበል እና ከመሳሰሉት የራቁ ሰዎች ለዚህ ችግራቸው የተለያየ ምክንያቶችን ያስቀምጣሉ። ከእንደዚህ አይነት ሰዎች መካከል አንዱ"የቤተክርስቲያን አገልግሎት ለምን አትሳተፍም ወይም ለምን አትጸልይም?'' ብላችሁ ብትጠይቁት"ኃጢአተኛ ስለሆንኩ ነው"አይላችሁም። ይልቁንም ጊዜ እንደሌለው ሥራ እንደሚበዛበት ሊነግራቹ ይችላል።ከዚህ በላይ ብዙ ምክንያቶች ሊያስቀምጥላችሁ ይችላል።ይህን ሰው በድጋሚ "ለምን በመርሃ ግብርህ እግዚአብሔር እንዲገባ አትፈቅድም?" ብላችሁ ብትጠይቁት ሌላ ማብራርያ ያቀርባል። "ዋናው ነገር የልብ ንጽህና ነው። የልብ ንጽህና ካለ ቤተ ክርስቲያን መሄድ፡ማስቀደስ፡መጸለይ፡ አያስፈልግም"ብሎ ሊነግራችሁ ይችላል። ነገር ግን ንጹህ ልብ ከጸሎት ውጭ መኖር አይችልም ሁልጊዜም በጸሎት እና እግዚአብሔርን በመውደድ ይኖራል።ከንጹህ ልብ የሚወጣ ጸሎትንም እግዚአብሔር ይቀበላል።ስለሆነም እንደተጠቀሰው አይነት እምነት ያላቸው ሰዎች የንጹህ ልብን ወይም የውስጥ ጥሩነት ትርጉም አያውቁም ማለት ነው።
በቅንነት ሼር አድርጉት!!!! 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉@zekidanemeheret👈
👉👉@zekidanemeheret👈
👉👉@zekidanemeheret👈☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
በደበረ ታቦር በዓል #ቡሄ#ጅራፍ_ማስጮህ#ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ ሃይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው?

ደብረ ታቦር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓለት ውስጥ አንዱ ነው። ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ስርዓቶችን በመፈፀም አክብራው ታልፋለች፡፡
በደብረ ታቦር በዓል የሚፈጸሙ (#ቡሄ#ጅራፍ_ማስጮህ#ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ስርዓቶች ምሳሌዎች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡

#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
"ቡሄ ከዋለ የለም ክረም ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ"
አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

#ሙልሙል_ዳቦ
ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡
አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው "ቢሄ በሉ" የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ ተመገቡ /ማቴ 10፥12/ ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ ይመሰላሉ፡፡

#ችቦ_ማብራት
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት ብርሃን ነው፡፡

#የጅራፍ_ምሳሌነት
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡
#የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣
#ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን ከትውልድ ጠብቆ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከነዚህ ሚስጢር ካላቸው ትምህርቶችና ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን
በደበረ ታቦር በዓል #ቡሄ#ጅራፍ_ማስጮህ#ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ ሃይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው?

ደብረ ታቦር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓላት ውስጥ አንዱ ነው። ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ሥርዓቶችን በመፈፀም ታከብረዋለች፡፡
በደብረ ታቦር በዓል የሚፈጸሙ (#ቡሄ#ጅራፍ_ማስጮህ#ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ሥርዓቶች ምሳሌዎች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡

#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
"ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ"
አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋግሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

#ሙልሙል_ዳቦ
ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡
አንድም እንደ ሐዋርያት የምሥራች ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው "ቡሄ በሉ" የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችሁበት ሁሉ ተመገቡ /ማቴ 10፥12/ ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ የምሥራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ ይመሰላሉ፡፡

#ችቦ_ማብራት
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት ብርሃን ነው፡፡

#የጅራፍ_ምሳሌነት
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምሥጢር በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡
#የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣
#ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምሥጢሩን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከነዚህ ምሥጢር ካላቸው ትምህርቶችና ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፌዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳሳቢ ነገሩ ደግሞ ኃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባሕሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን

https://t.me/zekidanemeheret