ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
803 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
የዓለም ብርሃን፡ አርከ ሐዋርያት (የሐዋርያት ወዳጅ)፡ ወገባሬ መንክራት (ድንቅ አድራጊው) #አቡነ #ዮሴፍ ዘእንጅፋት (ዘወለቃ)

=>ጣዕመ በረከቱ ይደርብን፡፡

ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ ዘጎንደር
'
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
እንኳን አደረሳችሁ

☞በዓለ ልደቱ ለቅዱስ ወክቡር ይምርሃነ ክርስቶስ (ካህን፡ ወንጉሥ፡ ወጻድቅ) #ዘኢትዮጵያ፡፡

"" ከበረከቱ ይክፈለን፡፡ ""


ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ ዘጎንደር
'
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
እንኳን አደረሰን!



•ዓቢየ እግዚእ ውዱስ፤
•ትርሲተ ሞገስ፤
•ንስእለከ በክርስቶስ፤
•ከመ ታድኅነነ ነዓ እመሪር ተጽናስ፡፡

ደብሩሰ ለዓቢየ እግዚእ ትመስል ደብረ ሲና ደብረ መድኃኒት
ዘኀደረ ቃል ላዕሌኀ ሐጹር የዐውዳ ወፅጌረዳ በትዕምርተ መስቀል።
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ግንቦት 20/09/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፴፪፥፳(32፥20)
ነፍስነሰ ትሴፈዎ ለእግዚአብሔር
እስመ ረዳኢነ ወምስካይነ ውእቱ
እስመ ቦቱ ይትፈሣሕ ልብነ


📖ወንጌል
ወንጌል ዘማርቆስ ፲፭፥፴፫-፵፪(15፥33-42)
ወሶበ ኮነ ጊዜ ቀትር…


ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ሮሜ ፲፫፥፩-፲፩(13፥1-11)
ለኵሉ ነፍሰ መኰንን ተኰነኑ…


👉ንፍቅ ዲያቆን
📖 ጴጥሮስ ፩ ም ፪፥፲፩-፳(2፥11-20)
አኃውየ ፍቁራን እስእለክሙ…


👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፫፥፵፬-፶፪(13፥44-52)
ወበካልእት ሰንበት ተጋብኡ…

📖ምስባክ ዘቅዳሴ

ዝርዎሙ ለአሕዛብ እለ ይፈቅዱ ቀትለ
ይምጽኡ ተናብልት እም ግብጽ።
ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር።

👉 ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፷፯ ቊ. ፴ - ፴፩

፴ በሸምበቆ ውስጥ ያሉትን አራዊት፥ በአሕዛብ ውስጥ ያሉትን የበሬዎችንና የወይፈኖችን ጉባኤ ገሥጽ፥ እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ፤ ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው።

፴፩ መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ታደርሳለች።


📖ምስባክ ዘቅዳሴ ተለዋጭ

ወአንሰ ጽድቀ እኴንን።
ተመስወት ምድር ወኵሎሙ እለ ይነብሩ ውስቴታ
ወአነ አጽናእኩ አዕማዲሃ

👉 ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፸፬ ቊ. ፪ - ፫

፪ ጊዜውን ስቀበል እኔ በቅን እፈርዳለሁ።

፫ ምድርና በእርስዋ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ ቀለጡ፥ እኔም ምሰሶችዋን አጠናሁ።


📖ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፮ ቊ. ፳፬ - ፳፰
ወእምዝ ይቤሎሙ ኢየሱስ...

📜ቅዳሴ


👉ዘባስልዮስ


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
††† እንኳን ለመናኙ ንጉሥ ቅዱስ አፄ ካሌብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† መናኙ ንጉሥ ካሌብ †††

††† ቅዱሱን ንጉሥ አፄ ካሌብን በዓለም ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በትልቁ ያከብሩታል:: ኢትዮጵያ ውስጥ ግን አክሱም አካባቢ ካልሆነ ከነ ስም አጠራሩ እንኳ እየተዘነጋ ይመስለኛል::

ነገር ግን ውለታው : ምናኔውና ቅድስናው የማይረሳ ነውና እንኳን በእምነት የሚመስሉን ይቅርና የማይመስሉን ምሥራቅ ኦርቶዶክሶችና ካቶሊኮች ዓመታዊ በዓሉን በወርኀ ጥቅምት ያከብራሉ::

ከአክሱም ነገሥታት በኃይሉም ሆነ በሃይማኖታዊ ቅድስናው አፄ ካሌብ ዋናው ነው:: ቅዱሱ የነገሠው በ485 ዓ/ም አካባቢ ሲሆን እስከ 515 ዓ/ም ድረስ በዙፋኑ ላይ ቆይቷል:: ከመልካም ትዳሩ አፄ ገብረ መስቀልን ጨምሮ ልጆችን ወልዷል::

††† ስለ ቅዱስ አፄ ካሌብ እስኪ እነዚህን ነገሮች ብቻ እናንሳ:-

1.በንግሥና ዙፋን ከመቀመጡ በፊት የሚገባውን መንፈሳዊ ትምሕርት ጠንቅቆ ተምሯል::

2.ሃይማኖቱ የጠራና እጅግ የሚደነቅ ነበር:: በእርሱ ዘመን ሃይማኖት ለነገሥታቱ የፖለቲካ ማስፈጸሚያ ነበር:: እርሱ ግን እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ አምልኳል::

3.ለእመቤታችንና ለቸር ልጇ የነበረው ጥልቅ ፍቅር የተገለጠና የሚያስቀና ነበር::

4.ገና በዙፋኑ ሳለ ጸሎትን ያዘወትር ነበር::

5.ዛሬም ድረስ ሁሉም ክርስቲያኖች የማይረሱትን መንፈሳዊ ቅንዓትን አሳይቷል::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
*በወቅቱ ዐመፀኛው የአይሁድ መሪ ፊንሐስ በሃገረ ናግራን (የአሁኗ የመን) ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖችን ክርስቶስን ካዱ በሚል ጨፈጨፋቸው::

ከተማዋንም ለአርባ ቀናት በእሳት አነደዳት:: ዜናው በመላው ዓለም ሲሰማ በርካቶቹ ቢያዝኑም የተረፉትን ለመታደግ የሞከረ አልነበረም::

ቅዱስ አፄ ካሌብ ግን የሆነውን ሲሰማ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ በግንባሩ ሰገደ:: ወደ ፈጣሪም ጸለየ:- "ጌታዬ ሆይ! የክርስቲያኖችን ደም እመልስ ዘንድ እርዳኝ? እኔ በጦሬ ብዛት አልመካም:: እኔ ተሸንፌ ክርስትና ከሚናቅ እዚሁ ግደለኝ" ብሎ በበርሃ ላሉ መነኮሳት እንዲጸልዩ ላከባቸው::

ጊዜ ሳያጠፋ በመርከብና በፈረስ : በበቅሎና በግመል ናግራን (የመን) ደረሰ:: ፊንሐስን ገድሎ ሠራዊቱንም ማርኮ ክርስቲያኖችን ነጻ አወጣ:: ደምና እንባቸውንም አበሰ:: አብያተ መቅደሶችን አንጾላቸው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ::

ወዲያው እንደተመለሰ ወደ አክሱም ጽዮን ገብቶ "ጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ ስላደረክልኝ የምሰጥህ ሰውነቴን እንጂ ሐብቴን አይደለም" ብሎ መንግስቱን ለልጁ ገብረ መስቀል አውርሶ ከዙፋኑ ወጣ:: የወርቅ አክሊሉን ወደ ኢየሩሳሌም ልኮ እርሱ በአባ ጰንጠሌዎን እጅ መንኩሶ መነነ::
(በፎቶው ላይ የምታዩት አፄ ቅዱስ ካሌብ የመነነበት : አክሱም አካባቢ የሚገኝ የአባ ጰንጠሌዎን ገዳም ነው)

ከዚሕች ዓለም ከአንዲት ረዋት (ኩባያ) : ከአንዲት ሰሌንና ከአንዲት ቀሚስ በቀር የወሰደው አልነበረም:: ከዚያም በበዓቱ ውስጥ በጾምና በጸሎት ተወስኖ አንድም ሰው ሳያይ በሰባ ዓመቱ (በ529 ዓ/ም) ዐርፏል:: ጌታችንም በሰማይ ክብርን አጐናጽፎታል::

††† ለቅዱስ አፄ ካሌብ የተለመነ አምላክ ለእኛም ይለመነን:: በጻድቁም ጸሎት ከመከራ ይሠውረን::

††† ግንቦት 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አፄ ካሌብ (መናኙ ንጉሠ ኢትዮጵያ)
2.ቅዱስ አሞንዮስ ገዳማዊ (ታላቁ አሞኒ ዘቶና)
3.ቅድስት ሳድዥ የዋሂት
4.አባ ሖር ጻድቅ
5.አባ ዳርማ ገዳማዊ
6.ቅዱስ ዘካርያስ አንጾኪያዊ
7.አባ በትረ ወንጌል ዘደብረ ሊባኖስ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ

††† "አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል::
በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል::
የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው::
የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም::
በበጐ በረከት ደርሰህለታልና::
ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ::
ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም::
ለረጅም ዘመን ለዘላለሙ::
በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው::" †††
(መዝ. ፳፥፩-፭)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
"" ግንቦት ፳ (20) ""

ቅድስት ልድያ (Saint Lydia)

"" ከትያጥሮን ከተማም የመጣች ቀይ ሐር ሻጭ እግዚአብሔርን የምታመልክ #ልድያ የሚሉአት አንዲት ሴት ትሰማ ነበረች፤ ጳውሎስም የሚናገረውን ታዳምጥ ዘንድ ጌታ ልብዋን ከፈተላት። ""

(ሐዋ. 16:14)

"" ቃልህ ሲነገር ልስማ ጌታ ሆይ እባክህ!
ልቤን ክፈተው(2) የልድያን ልብ እንደከፈትከው! ""

<<< ከበረከቷ ይክፈለን፡፡ >>>


ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ ዘጎንደር
'
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ግንቦት 21/09/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፵፬፥፲፪-፲፫(44፥12-13)
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር
ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን
በዘአጽፋረ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት


📖ወንጌል
ወንጌል ዘሉቃስ ፩፥፴፱-፶፯(1፥39-57)
ወተንሥአት ማርያም...


ምንባባት ዘቅዳሴ

         👉  ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቆሮንቶስ ፩ ም ፮፥፱-፳(6፥9-20)
ኢተአምሩኑ ከመ ዓማፅያን...


         👉ንፍቅ ዲያቆን
📖 ራእየ ዮሐንስ ፲፪፥፩-፭(12፥1-5)
ወአስተርአየ ተአምር ዐቢይ...

ዓዲ 📖 ጴጥሮስ ፪ ም ፩፥፩-፲፪(1፥1-12)
ስምዖን ኬፋ ገብሩ ወልዑኩ...

         👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፯፥፵፬-፶፩(7፥44-51)
ወደብተራ ስምዕ እንተ ነበረት ኀበ...


             📖ምስባክ ዘቅዳሴ

ሰወርከኒ በዕለተ ቀትል መልዕልተ ርእስየ 
ኢትመጥወኒ እግዚኦ እምፍትወትየ ለኃጥአን 
ተማከሩ ላዕሌየ ኢትኅድገኒ ከመ ኢየዘኀሩ

                     👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፴፱ ቊ. ፯ - ፰

፯ አቤቱ፥ ጌታዬ፥ የመድኃኒቴ ጕልበት፥ በሰልፍ ቀን ራሴን ሸፈንህ።

፰ አቤቱ፥ ከምኞቴ የተነሣ ለኃጢአተኞች አትስጠኝ፤ በላዬ ተማከሩ፤ እንዳይጓደዱ አትተወኝ።

            📖ምስባክ ዘቅዳሴ ተለዋጭ

ኢትሚጦ ለልብየ ውስተ ነገር እኩይ 
ለአመክንዮ ምክንያት ለኃጢአት 
ምስለ ሰብእ ገበርተ ዐመፃ።

                     👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፵ ቊ. ፬

፬ ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዓመፃን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለኃጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ፤ ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር።



📖ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፰ ቊ. ፮ - ፲፱
ወዘሂ አስሐቶ ለ፩ እምእሉ ንዑሳን...

📜ቅዳሴ


👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
🌷 እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል (ደብረ ምጥማቅ) በሰላም አደረሳችሁ †🌷

🌷 ደብረ ምጥማቅ 🌷

=>የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች::

+ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:

+ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ: ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር::

+ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች::

+በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት:-
እንኩዋን የአርያም ንግስት: የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን: የመዝናኛው ኢንዱስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል::

+እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው::

+የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር::

+እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች::

††† 🌷አባ መርትያኖስ 🌷†††

=>አባ መርትያኖስ በበርሃ ከ68 ዓመታት በላይ በቅድስና የኖሩ አባት ናቸው:: ሰይጣን እርሳቸውን ፊት ለፊት ተዋግቶ መጣል ቢያቅተው በዝሙት በተለከፉ ሴቶች ያስቸግራቸው ነበር::

+አንድ ቀን አንዷ ሽቶ አርከፍክፋ በዝሙት ልትጥላቸው ብትል እግራቸውን እሳት ውስጥ ጨምረው እግራቸው እየተቃጠለ በሚወጣው ጠረን አጋንንትን አርቀዋል:: እሷንም በንስሃ መልሰው ለቅድስና አብቅተዋታል:: ጻድቁ ከፈተና ለመራቅ በ108 ሃገራት 108 በዓቶች የነበሯቸው ብቸኛ አባት ናቸው::

††† ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን:: †††

=>ግንቦት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ደብረ ምጥማቅ (የእመቤታችን መገለጥ)
2.አባ መርትያኖስ ጻድቅ (በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት)
3.ቅዱስ አሮን ሶርያዊ
4.ቅዱስ አሞጽ ነቢይ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.አበው ጎርጎርዮሳት
2.አቡነ ምዕመነ ድንግል
3.አቡነ አምደ ሥላሴ

=>+"+ የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ::
ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው::
ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው::
በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . .
በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ::
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ::
ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ:: +"+ (መዝ. 44:12-17)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ግንቦት 22/09/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፳፪፥፬(22፥4)
በትርከ ወቀስታምከ እማንቱ ገሠፃኒ
ወሠራዕከ ማእደ በቅድሜየ
በአንጻሪሆሙ ለእለ ይሣቅዩኒ


📖ወንጌል
ወንጌል ዘማቴዎስ ፳፯፥፳፯-፴፩(27፥27-31)
ወእምዝ ነሥእዎ መስተራትዓተ ሐራ…


ምንባባት ዘቅዳሴ

         👉  ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ሮሜ ፲፮፥፯-፲(16፥7-10)
አምኁ  እንድራኒቆን ወዩልያን…


         👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ዮሐንስ ፩ ም ፪፥፳፯-፳፱(2፥27-29)
ወአንትሙሰ ቅብዐት ብክሙ…


         👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፳፩፥፲፭-፳፩(21፥15-21)
ወእምድኅረ እማንቱ መዋዕል…


             📖ምስባክ ዘቅዳሴ

አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ
ውስተ ኲሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ።
ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ።

👉ትርጉም


መዝሙረ ዳዊት ም. ፲፰ ቊ. ፫ - ፬

፫ ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም።

፬ ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።


📖ወንጌል ዘቅዳሴ

የሉቃስ ወንጌል ም. ፲ ቊ. ፩ - ፲፪
ወእምዝ አርአየ እግዚእነ...

📜ቅዳሴ


👉ዘሐዋርያት (ዘበደኃሪ)


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ ቅዱስ እንድራኒቆስ +"+

=>ቅዱስ ወብጹእ እንድራኒቆስ ሐዋርያ ትውልዱ ነገዱ
ከቤተ እሥራኤል ሲሆን ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው::
ጌታችን በመዋዕለ
ስብከቱ 120 ቤተሰቦቹን ሲመርጥ እርሱን ከአርድእት ጋር
ደምሮ አስተምሮታል::

+ሰብዐው አርድእት በጌታችን ተልከው አጋንንት
ሲገዙላቸው ከእነርሱ አንዱ ቅዱስ እንድራኒቆስ ነበር::
ይሕ የተፈጸመ ገና
መድኃኔ ዓለም ከመሰቀሉ በፊት ነው:: (ሉቃ. 10:1-20)

+ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከሐዋርያት ጋር ለ10
ቀናት በሱባኤ ሰንብቶ የመንፈስ ቅዱስን ሐብት
ተቀብሏል:: እንደ
ባልንጀሮቹም ወደ ዓለም ወጥቶ ወንጌልን
ሰብኳል:: በተለይ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ለበርካታ ዓመታት
አምላኩን
አገልግሏል:: ቅዱስ ዻውሎስም በቆሮንቶስ እያለ ቅዱስ
እንድራኒቆስ በሮም ያስተምር ነበር:: ለዛም ነው በሮሜ
መልዕክቱ
16:7 ላይ "እንድራኒቆስን ሰላም በሉ" ያለው::

+ቅዱስ ዻውሎስ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ ከቅዱስ
ዮልዮስ ጋር ሆነው የአህዛብን ልቡና በወንጌል
አብርተዋል:: እጅግ ብዙ
መከራ ደርሶባቸዋል:: ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው
ትዕግስት ድል ነሥተዋል:: በዚሕም በርካታ የጣኦት
ቤቶችን አፍርሰው
አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል::
በአሕዛብም ፊት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አሳይተዋል::

+ቅዱስ እንድራኒቆስ ብዙ መከራን ቢቀበልም አንገቱን
ይቆረጥ ዘንድ የጌታ ፈቃዱ አልነበረምና ጥቂት ታሞ
በዚሕች ቀን
አርፏል:: ባልንጀራው (ሐዋርያው) ቅዱስ ዮልዮስ በክብር
ገንዞ ቀብሮታል::

+"+ ቅዱስ ያዕቆብ +"+

=>ዳግመኛ በዚሕ ቀን ጻድቅና ተአማኒ (ታማኝ) የተባለ
የምሥራቅ ሰው ቅዱስ ያዕቆብ መታሠቢያ ይደረግለታል::

+ቅዱስ ያዕቆብ ቁስጥንጥንያ አካባቢ በርሃ ውስጥ ይኖር
የነበረ አባት ነው:: ከቅድስና ሕይወቱ ባሻገር በደፋርነቱ
(ጥብዐቱ) ይታወቃል:: በ340ዎቹ ዓ/ም ታናሹ
ቆስጠንጢኖስ አርዮሳዊ በሆነ ጊዜ ይሔ አባት በይፋ
ገስጾታል:: በዚህም
ምክንያት መከራ ተቀብሏል: ታስሯል: ተገርፏል::
እግዚአብሔርም መናፍቁን ንጉሥ ለጦርነት በወጣበት
ቀስፎታል::

❖የአባቶቻችን አምላክ ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስ ጸጋ
ክብራቸውን ያድለን::

❖ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ እንድራኒቆስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ (ለክርስቶስ የታመነ)

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2፡ ቅዱስ ደቅስዮስ
3፡ ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
4፡ ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
5፡ አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
6፡ አባ ጳውሊ የዋህ

++"+ ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ
አቅርቡልኝ:: በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ:
ደግሞም
ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ: አብረውኝም ለታሰሩ
ለዘመዶቼ ለአንድራኒቆንና ለዮልያን (እንድራኒቆስና
ዮልዮስ) ሰላምታ
አቅርቡልኝ:: +"+ (ሮሜ. 16:6)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>