ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
800 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
✥ አባቶቻችን እንዲህ አሉ ✥

💦"እሳትና ውኃን ማዋሐድ እንደማይቻል በሌሎች ኃጢአት መፍረድም በራስ ኃጢአት ከመጸጸት ጋር አብሮ አይሔድም" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

💦"የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው" አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ

💦"እግዚአብሔር ለኃጢአተኛ ሰው ያለው ፍቅር ጻድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል"
አባ አርሳኒ

💦"ሕፃን ልጅ እናቱ ስታጥበው ያለቅሳል:: ሕፃን እምነት (ትንሽ እምነት) ያላቸው ሰዎችም ነፍሳቸውን የሚያጥብ መከራ ሲመጣባቸው እግዚአብሔርን ያማርራሉ" አባ ስምዖን

💦"ዕለትን የሠጠህ እርሱ ለእለት የሚበቃህንም ይሠጥሃል" ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

💦"እጅግ ምርጡ ጸሎት "ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ" ማለት ነው"
ባሕታዊ ቴዎፋን

💦"ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንጹሕ ብትሆንም አትናቀው:: ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድም ብሏል" አባ ቴዎዶር

💦"አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ ብታይ እንኳን አትፍረድበት:: አንዳንዴ ዓይንህም ሊሳሳት ይችላል"
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

💦"ለኃጢአተኛው ክንፍህን ዘርጋለት:: ኃጢአቱን ልትሸከምለት ባትችል እንኳን ሸፍንለት"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

💦ከአበው አንዱን ትሕትና ምንድርን ነው? ብለው ጠየቁት:: እርሱም "ትሕትና ማለት ወንድምህ በበደለህ ጊዜ እርሱ ይቅርታ ሳይጠይቅህ በፊት ቀድመህ ይቅር ማለት ነው" አለ::

💦"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ" አባ ኤፍሬም አረጋዊ [ If you don’t forgive, forget heaven]

#ሼር
__

#share #share ⤵️

@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
​​👉መወለድ በቃሉ ለማደግ


ዛሬ የተወለድኩበት ቀን ነው! እስካሁን በኖርኩባቸው ዓመታት ውስጥ እጅግ በጣም የሚገርመኝ የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእናቱ አማላጅነት ነው።

መወለዴን በሁለት ምክንያት እወደዋለሁ።
፩ኛ. ኦርቶዶክስ በመሆኔና
፪ኛ. ኢትዮጲያዊ በመሆኔ

በዚህች አጭር ዕድሜዬ ደጉን፣ ክፉን፣ ጣፋጩን መራራውን ሁሉንም አየው አሁንም ግን የአንተ ፍቅር፣ የአንተ ቸርነት እጅጉኑ ይበዛብኛል።ጌታዬ አባቴ ሆይ "እንዲህ የወደድከኝ እኔ ማን ነኝ?" ስለቃልህ እንድናገር አንደበቴን ያከናወንክ እኔ ምንድነኝ?

ወዳጆቼ "መወለድ" ትርጉም የሚኖረው ትናንት ካለንበት ማንነት ተሽለን ስንገኝ ነው! ዕድሜ ሚጨመርልን ከትናንት ይልቅ መልካም ሆነን፣ እግዚአብሔርን በመፍራት እንድንኖር ነው። አንድ ዓመት ሲጨመርልን ወደ ንስሐ ምንገባበት የ365 ቀን ዕድል እየተሰጠን ነው።

አባቴ ሁሌም ምስጋናውንና ክብሩን አንተ ውሰድ
(መልካም ልደት ለእኔ😊 በዚሁም መልካም ምኞታችሁን ብትገልጹልኝ ደስታዬ እጥፍ ነው🙏)
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

👉 @Zetaodokos

#share_and_support_us.
#አብሮነታችሁ_ያበረታናል
ቤተክርስቲያን ስንሳለም ሶስት ጊዜ የምንሰገድበት
ምሥጢር......

መጀመሪያ
ሰግደን ስንነሳ አፈር ነበርን ሰዉ አድርገህ ፈጥረህ ቁመን እንድንሄድ ቀና ብለን እንድንራመድ አደረከን ብለን ነዉ

ሁለተኛ
ሰግደን ስንነሳ በኃጢአት ምክንያት ተሰነካክለን ብንወድቅም
በንስሃ ታነሳናለህ ስንል ነዉ

ሶስተኛ
ሰግደን ስንነሳ ሙተን ወደመቃብር ብንወርድም በኋለኛዉ ዘመን በትንሣኤ ዘጉባኤ ከመቃብር ታነሳናለህ ስንል ነዉ

ወድቀን መስገዳችን ተፈጥሮአችን ከመሬት መሆኑን ለመግለጽ ሲሆን መነሳታችን ሀገራችን በሰማይ መሆኑን ለመግለጽ ነዉ

የምሥጢር ባለቤት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምታደርገዉ ሥርዓት ሁሉ በምሥጢር የተሞላ ነዉ ሰማያዊ ቤተ ክርስቲያን ለዘለዓለም ኑሪልኝ
ያለአንቺ መኖር የከንቱ ከንቱ ነዉና

አስተማሪ ከሆነ ለጓደኞቻችን #share እናድርግ

ለሃሳብ አስተያየት
@zekidanemeheretbot

ለመቀላቀል
@zekidanemeheret
እስካሁን ስናገለግላቹ ነበር አሁን ደሞ እናንተ ግዴታቹን ተወጡ 🙏
👇👇👇
🙏 ቢያንስ 1ሰው ለ5ሰው ሼር🙏
👏👏👏
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ !
#ዝማሬዎችን
# ብሂለ አበው
#ራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ትምህርቶች ለማግኘት
#ይቀላቀሉን
#join_share
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @zekidanemeheret
@zekidanemeheret
@zekidanemeheret
ከእግዚአብሔር ጋር መታገል

ክፍል አንድ

ንስሐ ገብተህ ኃጢያትን ለማስወገድ ትፈልጋለህ ?አንድ ነገር አስታውስ።ኃጥያትን ለማሸነፍ የሚደረገው ትግል በሰው ጉልበት ብቻ ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል። በመጀመሪያ ኃጥያት ጠንካራ በመሆኑ"ወግታ የጣለቻቸው ብዙዎች ናቸው።እርሷም የገደለቻቸው ብዙዎች ናቸው"ምሳሌ (7፥26)ተብሎለታል።


ይህ አዳምን፣ሶምሶንን፣ዳዊትና ሰለሞንን ወግቶ የጣለ ኃጢአት ያለ እግዚአብሔር አጋዥነት አንተ ብቻዬን እወጣዋለው ብለህ ታስባለህ?አስቀድመህ የወደቅህበት ኃጢያት ያለ እግዚአብሔር እርዳታና ድጋፍ አንተን እንደሚቆጣጠርህ አትጠራጠር።


ውጊያው ውጫዊ የሆነ ጦርነት ብቻ አይደለም።በተለይ የኃጢያት ዝንባሌ የምታሳይ ከሆነ ውጊያው እጥፍ ነው ሚሆነው።የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ እንዲህ ይላል።"እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል"(መዝሙር 127፥1)።ጌታ እራሱ "ያለ እኔ አንዳች ነገር ማድረግ አይቻላችሁም"(የሐዋ 15፥5)ይላል።እግዚአብሔርን ሳትይዝ የምታደርገው ትግል ፍጻሜው ውድቀት መሆኑን አትጠራጠር።ውጊያውን ማሸነፍ ቢቻልህ እንኳን በከንቱ ውዳሴ ተጠልፈህ መውደቅህን አትዘንጋ።ምክንያቱም በራስህ ኃይል ታግለህ እንዳሸነፍከው ይሰማኻልና።


ትሕትና ሰይጣንን ልናሸንፍበት የምንችለው መሣሪያ መሆኑ ተደጋግሞ ተገልጿል።

ቅዱስ እንጦንስ በትሕትና ሰይጣንን አለው "ከአንተ ከትንሹ የባስኩኝ ደካማ
ነኝ"ወደ እግዚአብሔርም አዘውትሮ እንዲህ በማለት ይጸልይ ነበር።ጌታ ሆይ አንዳች ነገር የሌለኝን እኔን እንደባለጸጋ አድርጎ ከሚቆጥረኝ ከጠላቴ ሰይጣን ወጥመድ ጠብቀኝ።ምን ያህል ጊዜ ለመነሣት ሞከርክ?ምንስ ያህል ጊዜ ሳይሳካልህ ወደቅህ?ለወዳጄ የምሰጥህ ጠቃሚ ምክር ይህ ነው።ንስሐ ለመግባት ቃል እገባልኻለው ብለህ ለአምላክህ ከመናዘዝ ይልቅ "አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና መልሰኝ እኔም እመለሳሁ"(ኤር 31፥18)በለው

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
#share_join
@zekidanemeheret
@zekidanemeheret
@zekidanemeheret
*NEW* "የአምላክ አቃቤ ሕግ"| "Ye Amlak Akabe Heg"
ማኅቶት ቲዩብ - Mahtot Tube
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ !
ለአሰቦት ሥላሴ ገዳም
    እጃችንን እንዘርጋ
        *~★★~*

#ይሄ ጦማር ብዙ ሺ #SHARE መደረግን ይፈልጋል። ሼር… ሼር… ሼር

#ETHIOPIA | ~ በእሳት አደጋ እንዲወድም የተደረገውን የአሰቦት ሥላሴ ገዳምን እንታደግ።

… ሰሞኑን በምሥራቁ የሃገራችን ክፍል በምዕራብ ሐረርጌ በሚገኘው በታላቁ ደብረ ወገግ የአሰቦት ሥላሴ አባ ሳሙኤል ገዳም የተነሣው ሰው ሠራሽ እሳት በታላቁ ገዳማችን ላይ ከፍተኛ ውድመት ማስከተሉን ሁላችንም አይተናል። በትናንትናው ዕለት በባለማዕተቦቹ የተዋሕዶ ልጆችና በገዳማውያኑ ከፍተኛ ርብርብ ጠፍቶ የነበረው እሳት ዛሬ ደግሞ ስውሩ መድኃኔዓለም በሚባለው የገዳሙ ክፍል ላይ ጠላት እንደ አዲስ እሳቱን ለኩሶ የቀረው ደን መንደድ ጀምሯልም ተብሏል። አይዟችሁ እሱም ይጠፋል። አንዳጆቹም ይጠፋሉ።

• አሁን በገዳመ አሰቦት ሥላሴ ሃገር በቀል የሆኑት ጥንታውያኑ እጸዋት ሙሉ በሙሉ በእሳቱ ወድመዋል። የቅዱሳን መሸሸጊያ፣ መሠወሪያ እና የአርምሞ የሱባኤ መያዣው ተፈጥሮአዊው ጥብቅ ደን ወድሟል።

• የከብቶቻቸው ቀለብና መኖ የነበረው ሳር ሙሉ ለሙሉ በእሳቱ ወድሟል።
• እሳቱን ለማጥፋት የመጣውን ሠራዊት በመመገባቸው አሁን ገዳማውያኑ የዓመት ልብስም ሆነ የዕለት ጉርስም የሚሆን ነገር የላቸው።
• የውኃ ችግራቸውም የቆየ እና የተለመደ ነው።

… ገዳሙ እርሻ በማረስ ፣ እንዲሁም በዓመት ሁለት ጊዜ በጥርና በሐምሌ ሥላሴ ወደገደሙ ለበረከት ሥራ ከሚመጡ ምእመናን ከሚያገኘው ሙዳየ ምጽዋት በቀር ሌላ ገቢም አልነበረውም። ይሄ ገቢ ደግሞ በኮሮናውና በአካባቢው በኦሮሚያ በአሰቦት ከተማ ተነሥቶ በነበረው ግጭት ምክንያት ምእመናን ወደገዳሙ ባለመሄዳቸው የገቢ ምንጫቸው ቆሟል። እናም አሁን ባዶ ገዳማውያኑ ባዶ እጃቸውን ቀርተዋል። 

… ስለዚህ ከገዳሙ አበምኔት ከአሰቦት አባቶች ለእኔ ለወንድማችሁ ለዘመዴ ደብዳቤ ደርሶኛል። " ዘመድኩን ጓደኞችህን አሰባስበህ በፍጥነት ድረስልን " የሚል በገዳሙ ማኅተም የታተመ ደብዳቤ ነው የደረሰኝ።

… እናም ከገዳሙ በደረሰኝ ደብዳቤ ላይ በተገለጸው መሠረት ለገዳማውያኑ አባቶች የዕለት ጉርስ የሚሆን ቀለብ እና በገዳሙ ውስጥ ለሚገኙት እንስሳትም መኖ ይሆን ዘንድ በሃገር ውስጥም፣ ከሃገር ውጪም ያላችሁ የተዋሕዶ ልጆችና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ወንድሞች እና እህቶች ከታች በተቀመጠው የባንክ ሂሳብ ቁጥር የተቻላችሁን አምስትም አስርም የአቅማችሁን በባንክ ቁጥራቸው ታስገቡላቸውና በበረከት ሥራው ትሳተፉ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ። 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰቦት ቅርንጫፍ
ለአሰቦት ደብረ ወገግ ገዳም
የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000153218618
አሰቦት – ኢትዮጵያ

#ማስታወሻ |~ ማኅበራት… የኋትስአፕና የቴሌግራም፣ የቫይበር ግሩፖች… የዩቲዩብ ሠፈር ልጆችም ይህንን መልእክት በየማኅበር ግሩፓችሁ ሼር… ሼር… ሼር አድርጉት።

¶ድልና ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ሀገሬና ለተዋሕዶ ሃይማኖታችን ! ውድቀትና ጥፋት፤ ለሁለቱም ጠላቶች። አራት ነጥብ።

•••

ሻሎም !   ሰላም !  

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
መጋቢት 16/2013 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
የዓይን ፍቅር

🛐🛐🛐 ክፍል 13


🛐🛐 ለጊዜው ፍቅር እንዳይዛችሁ


+++አንዳንድ ልጆች ፍቅር ምን እንደሆነ እንኳን ሳያውቁ በፍቅር ታስረው ይገኛሉ ።
ትምህርታቸውን መማር ያቅታቸዋል፣
ብቸኞችና ነጭናጮች ይሆናሉ ።
የስሜት መጎዳት ስለሚበረታባቸዉ ማገገም እስኪያቅታቸው ይቸገራሉ ።
የዓይን ፍቅር ልንቀልድበት የማንችለው ሞኝ መሳይ ተዋጊ ነው ።
ከዚህ ብርቱ ጦር ራሳችሁን መጠበቅ አለባችሁ ።
ያለ ዕድሜያችሁ ወደ ልባችሁ እንዲገባ አትፍቀዱለት ።
በጓሮ የሚበቅሉ ተክሎች እስቲ ተመልከቱ
በመጀመሪያ ይፀድቃሉ ከዛ ያብባሉ በመጨረሻም ፍሬ ያፈራሉ።
ዕድገታችሁ ወቅትን የጠበቀ ይሁን ።
እንደ ጸደቁ ፍሬ አያፈሩም ጊዜውን መጠበቅ አለባቸው ።
እናንተም እንዲሁ ናችሁ ።
+++ መማር ባለባችሁ ዕድሜ ተማሩ ።
+++ ማፍቀር ባለባችሁ ዕድሜ አትከለከሉም ።
#ፍጻሜውም ወደ ፍሬ /ቁምነገር/ ያደርሳቸዋል ።
#ያለ ዕድሜያችው ከተያዛችሁ ግን ብዙ መከራን መጋፈጥ ግድ ይላችኋል።


በዚህ ስሜታዊ ፍቅር ተይዞ ከዚህ ለማምለጥ ከመታገል ላለመያዝ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እጅግ የተሻለ ነው ።
አላስፈላጊ ቅርርቦች ፣ በፊልምና በመጻሕፍት በስልካችሁ ከምታዩዋቸው የፍቅር ታሪኮች ተጽዕኖ መጠንቀቅ ፣ ከምትደነግጡለት ሰው ፊት መራቅ ፣ ሙዚቃ ማቆም በዚህ ፈንታ በትምህርታችሁና በመንፈሳዊ ልምምዶች ውስጥ መቆየት እጅግ ማትረፊያ ነው ።
"ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማል፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።"
1ጢሞ 4÷8

ክፍል 14

❤️❤️ እንዳትታሉ

ይቀጥላል ............


ትምህርቱን ከወደዳችሁት ለጓደኞቻችሁ #share አድርጉ



ለሃሳብ አስተያየት👇👇👇👇👇
@zekidanemeheretbot

የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇
@zekidanemeheret
@zekidanemeheret
@zekidanemeheret
ተመስገን አለማወቅ
ባልና ሚስቱ በባህር ዳርቻ ሽርሽር ይላሉ። ድንገት ማዕበል ይመጣና ባልን ቀምቶ ወደ ባሕሩ ጥልቅ ይሸሻል።

ሚስት በሁኔታው ተደናግጠው የእንባቸውን ጎርፍ እያወረዱ ዐይናቸውን ወደ ሰማይ አንጋጠው እግዚአብሔር ሆይ! እባክህን ባለቤቴን መልስልኝ እያሉ ይጮሁ ጀመር እግዚአብሔርም የቅርብ አምላክ ነውና ጸሎታቸውን ሰምቶ ባለቤታቸውን ውሃው ተፍቶ ወደ ዳር አወጣቸው።

ሴትየዋ አላመኑም ሮጡ ተጠግቱው ሲያዩ ባለቤታቸው ከነሕይወታቸው ከውሃው ተርፈዋል። ሴትየዋም ምን አሉ መሰላችሁ "እግዚአብሔር ሆይ የእኔን የድሃውን ጸሎት ሰምተህ ባለቤቴን ስለመለስክልኝ አመሰግናለው። ዳሩ ግን በአናቱ ላይ አድርጎት የነበረው ባርኔጣ የታል?" አሉ በሐዘን። አቤት የሰው ነገር ።
☺️☺️☺️☺️☺️☺️☺️☺️☺️☺️☺️

እስቲ ቆም ብለን እናስብ እግዚአብሔር በሕይወታችን ዘመን ከሰጠንና ካደረገልን ነገሮች ሁሉ እና እኛ አላደረገልንም ከምንላቸው ነገሮች የቱ ይበዛል? እርግጠኛ ነኝ የሰጠን እና የተደረገልን ነው ሚበዛው።

© @zekidanemeheret

🔴 አብሮነታችሁ ያበረታናል። #Share በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩን።
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንደምን ሰንብታችኋል የፍኖተ መንግስተ ሰማያት ቤተሰቦች? ከማያልቀው ፍቅሩ ፍቅርን የሰጠን ከማይቀንሰው ሰላሙ እነሆ ለበረከት ያለን የቅዱሳን አምላክ የተመሰገነ ይሁን።

እግዚአብሔር በፈቀደ መጠን የቻናላችንን የትምህርት አድማስ ለማስፋት:- ሁላችሁም በቻላችሁት መጠን የቻናላችንን #link #Share እንድታደርጉ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። እባካችሁ ቢያንስ በዚህ እንኳን እንተጋገዝ፣ ክርስቲያናዊ ግዴታችንን እንወጣ ሁላችሁም እንደምታዩት መናፍቃንም አህዛብም ምን ያህል ዕቅድ ነድፈው ሊያጠፉን እንደሆነ በየቀኑ የምትሰሙት ነው። እና እባካችሁ ቸልተኛ አትሁኑ። በቅዱስ መፅሀፍ " የቆማችሁ የሚመስላችሁ እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ" ይላል።

እናንተም እንዲለቀቁላችሁ የምትፈልጓቸው ፅሁፎች፣ ግጥሞች፣ መዝሙሮችና፣ ቪዲዮዎች ካሏችሁ 👉 @zekidanemeheretbot ላይ አድርሱን።

@zekidanemeheret
@zekidanemeheret
@zekidanemeheret
@zekidanemeheret

#SHARE #SHARE #SHARE
በጣም አስተማሪ ታሪክ ይነበብ
♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️

አንድ በሥራው ታታሪ የሆነ ዓሳ አጥማጅ ነበር።ይህ አጥማጅ በየቀኑ ዓሳ ያጠምድና
አስከሚያልቅ ድረስ ይጠቀማል። ልክ ሲያልቅ ወደ ባህር ዳርቻ
በመሄድ ሌላ ያጠምዳል።

ከእለታት አንድ ቀን የዓሳ አጥማጁ ሚስት ባሏ ያመጣላትን ዓሳ
በመቆራረጥ ላይ ሳለች አሰገራሚ ነገር ታያለች። ይህች ሰው የተመለከተችው እጅግ የከበረ ሉል ነው ። በጣም እየተገረመች በዓሳ ሆድ ውስጥ ሉል ...? አያለች ባሌ... ባሌ... ባሌ... እያለች ባሏን
መጥራት ጀመረች ከዚያም "ምን እንዳገኘሁ ተመልከት ሉል እኮ
ነው!! ሉል ... ከዓሳው ሆድ ውስጥ " አለችው ።

እሱም " እንዴት አሰደሳች ሚስት ነሽ እስኪ አቅርቢው ለዛሬ ለቤት
ቀለባችን መግዣ ትሆነናለች ..... ከዓሳ ሌላ ምግብ እንበላለን!!" አላት..... ይህ ዓሳ አጥማጅ ሉሉን በመያዝ ወደ ሉል ገዢና ሻጭ በመሄድ ያሳየዋል። ገዢውም "እኔ ይህንን ሉል የመግዛት አቅሙ
የለኝም፤ ዋጋው ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ይህንን ሱቄንና መኖሪያ
ቤቴን ብሸጠው እንኳን ልገዛህ አልችልም። ይልቁንስ እከሌ
የሚባል ሀብታም ነጋዴ አለ እርሱ ሊገዛህ ይችላልና ወደርሱ
ሂድ። አለው ።

ዓሳ አጥማጁ ሉሉን በመያዝ ወደ ተባለው ሀብታም ሰው በመሄድ ጉዳዩን ነገረው። ይህ ታላቅ ነጋዴም "እኔ አልችልም ይህ የያዝከው ሉል በገንዘብ የሚተመን አይደለምና እኔ መፍትሔ ብዬ የማስበው ወደ ከተማው አስተዳዳሪ ሄደህ ብታሳየው ነው
እንደዚህ አይነት ውድ ሉል ከርሱ ውጭ የመግዛት አቅም አለው
ብዬ የማስበው ሰው የለም " አለው።

ጉዞውን ወደ ተባለው አስተዳዳሪ በማድረግ ቤቱ እንደደረሰ ወደ
ህንፃው ለመግባት ፈቃድ እስኪያገኝ ድረስ መጠበቅ ጀመረ።
(እንደገባም) ለአስተዳዳሪው የያዘውን ሉል ሲያሳየው አጅግ
ተገረመ። "እንደዚህ አይነት ሉል ስፈልገው የነበረ ነው… እንዴት
ተመኑን እንደምከፍልህ አላውቅም… ነገር ግን ለየት ወዳለው ካዝናዬ እንድትገባ እፈቅድልሃለሁ። እዛ ውስጥም ለስድስት ሰዓታት በመቆየት የቻልከውንና የፈለከውን ንብረት ተሸክመህ መውጣት ትችላለህ። ይህ እንግዲህ የሉልህ ክፍያ ነው።" በማለት ወደ ካዝናው እንዲገባ ጋበዘው።

ዓሳ አጥማጁም "አለቃዬ ሆይ! ስድስት ሰዓት…!! እንደኔ ላለ ዓሳ አጥማጅ በጣም ብዙ ነው እንደው ሁለት ሰዓት ብታደርግልኝ " ሲል
ጠየቀው። አስተዳዳሪውም "በጭራሽ አይሆንም ስድስት ሰዓት ሙሉ ከካዝናዬ የፈለከውንና የምትችለውን ያህል ይዘህ
መውጣት አለብህ " አለው።
ዓሳ አጥማጁ ወደ ካዝናው ሲገባ በጣም የሚያስደንቅ ሁኔታን
ተመለከተ። በሦስት የተከፈለ ሰፊ ክፍል

☞ አንደኛው ክፍል በአልማዝ፣ በወርቅና በተለያዩ ጌጣጌጦች
የተሞላ ክፍል ነው።
☞ሁለተኛው ክፍል ለመተኛት ምቹ የሆኑ ለየት ያሉ ፍራሾች ያሉበት ክፍል ነው።
☞ ሦስተኛው ክፍል አጠቃላይ በሚፈለጉና ውድ በሆኑ የምግብና
የመጠጥ ዓይነቶች የተሞላ ነው።
ዓሳ አጥማጁ ከራሱ ጋር መነጋገር ጀመረ። "ስድስት ሰዓት!! እንደኔ
ላለው ድሃ ዓሳ አጥማጅ በጣም ብዙ ነው በዚህ ስድስት ሰዓት
ምን ማድረግ አለብኝ? ጥሩ! በሦስተኛው ክፍል ባሉት ምግብና
መጠጥ መጀመር አለብኝ ምክንያቱም ብዙ ወርቅ ለመሸከም
የሚያስችለኝን ኃይል አገኝበታለሁ። " በማለት ወደ ሦስተኛው
ክፍል በመሄድ መብላት ጀመረ። ይበላል… ይበላል… ይጠጣል…
ከስድስቱ ሰዓታት በመብላት ሁለቱን ሰዓት ተጠቀመ። ልክ
ሲጨርስ ወርቁንና ጌጣጌጡን ለመሸከም ወደ አንደኛው ክፍል
በመሄድ ላይ ሳለ በሁለተኛው ክፍል ያለውን ያማረ ምቹ ፍራሽ
ተመለከተና እራሱን ማናገር ጀመረ። "አሁን በጣም ጠግቤያለሁ ለምን ትንሽ በመተኛት በደንብ ለመሸከም የሚያስችለኝን እረፍት
አልወስድም? ይህንን እድል ደግሜ አላገኘውምና ለምን
አበላሸዋለሁ?" በማለት ወደ ፍራሹ በመሄድ በጀርባው ተዘረጋ
በጣም ጭልጥ ያለ እንቅልፍም ወሰደው።

ከተወሰነ ሰዓታት በኃላ "ተነስ ተነስ ቁም አንተ ጠባብ የሆንክ ዓሳ
አጥማጅ ተነስ… ቁም...... ጊዜው አልቋል " አለው። ዓሳ
አጥማጁም " እ እ እንዴ ምንድነው...?" አለ። ሰውዬውም
" አዎ! ወደ ውጭ ውጣ " አለው። አጥማጁም "ኧረ ምንም በቂ ዕድል አላገኘሁም " አለ። ሰውዬውም "ስድስት ሰዓታት
ሙሉ በዚህ ካዝና ውስጥ ሆነህ ጊዜህን ሳትጠቀም ቀርተህ
አሁን ትባንናለህ? ከዚያም ሰዓት እንዲጨመርልህ ትጠይቃለህ? እነዚህን አልማዝና ወርቆች በፍጥነት ሰብስበህ በመውጣት የፈለከውን ምግብና መጠጥ እንዲሁም ያሰኘህን አይነት የመኝታ ፍራሽ መግዛት ትችል ነበር። ነገር ግን አንተ ዝንጉና ጠባብ በመሆንህ በዙሪያህ ያለውን እንጂ ሩቅ ያለውን
ነገር አታስብም።" በማለት "ወደ ውጭ አስወጡት! " አለ።

አጥማጁም "ኧረ ባካችሁ!! ኧረ!…
እባካችሁ አንድ እድል ይሠጠኝ " ቢልም ሊሆንለት አልቻለም።

ታሪካችን አለቀ በውስጡ ያለው ትምህርት ግን አላለቀም....

◼️◼️◻️◻️⬛️⬛️⬜️⬜️🔳🔳🔲🔲
ልብ በሉ ይህ ሰውዬ እጅግ የከበረ ጸጋ ተሰጥቶት አልተጠቀመበትም ባለችው ጊዜያዊ ምግብና መኝታ ተታሎ ጥቅሙን አጣ እኛም ምድራዊ ነገር አታሎን ጥርስ ማፏጨትና ልቅሶ ወዳለበት እንዳንጣል በጊዜ ንስሐ ገብተን ተዘጋጅተን ልንኖር ግድ ነው።
⚠️ #SHARE ማድረጋችሁን አትዘንጉ።

👉@zekidanemeheret
#በእንተ _ጸሎት

#(፲ ነጥቦች)
፩. ‹‹ጸሎት የማያፈቅር ሰው ብታይ ምንም ዓይነት በጎ ነገር በውስጡ እንደሌለ ትረዳለህ፣ ወደ እግዚአብሔር የማይጸልይ ከሆነ በመንፈሳዊነቱ ሞቷል….ሕይወትም የለውም›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
፪. ‹‹ጸሎት ችላ የሚል ሰው እንዲሁም ለንስሐ የሚያበቃ  ሌላ በር አለ ብሎ የሚያስብ በዲያቢሎስ ተሸንግሏል›› የሶሪያው ማር ይስሐቅ
፫. ‹‹ጸሎት አዕምሮን ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ ነው ›› የሶሪያው ማር ይስሐቅ
፬. ‹‹ጸሎት ጸጋን ይጠብቃል፣ ቁጣንም ያሸንፋል… ትዕቢትንም የመከላከል ዝንባሌ ያሳድርብናል››
 የሶሪያው ማር ኤፍሬም
፭. ‹‹የመንፈስ ፍሬዎችን ያለ ጸሎት ገንዘባችን ልናደርጋቸው አንችልም››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
፮. ‹‹ጸሎት የማያረጅ ትዕግስትን ገንዘብ የምናደርግበት ታላቅ የጦር መሣሪያ ነው››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
፯. ‹‹በጸሎት ግዜ ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገርክ አይደለምን? እንዴት ያለ መብት ነው!!!››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
፰. ‹‹ጸሎትን ለማድረግ አታቅማማ፣ ሥጋ ከመብል(ከምግብ) በተከለከለ መጠን ደካማ እንደሚሆን ነፍስም ከጸሎት ስትከለከል ደካማ ትሆናለች››
አቡነ ማቴዎስ ግብጻዊ
፱. ‹‹ያለ ጸሎት የምናደርገው ወይም የምንናገረው ነገር መጨረሻው ውደቀት ነው፡፡ፍጻሜው ኃጢአት ወይም ጉዳት ነው፡፡በማናውቀው ምሥጢራዊ በሆነ መልኩ ሲጎዳን እንመለከተዋለን››
 አባ አጋቶን
፲. ‹‹ሰው እራሱን ኃጢአተኛ እንደሆነ እያሰበ ወደ እግዚአብሔር ካልጸለየ ጸሎቱ ተቀባይነት አይኖረውም››
አባ አጋቶን


#share #share #share

https://t.me/zekidanemeheret
መርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን

አንድ ሲኖዶስ
አንድ ፓትርያርክ
አንዲት ቤተክርስቲያን


#Share
"በጆሮ መብላት"

   በአንድ መንደር ለረጅም ሰዓት በመጾም የሚታወቅና ከዚህም ተግባሩ የተነሣ "ጾመኛው" ተብሎ እስኪጠራ የደረሰ አንድ ሰው መኖሩ ይወራ ነበር።
  የአባ ስልዋኖስ ደቀ መዝሙር የነበረው አረጋዊው አባ ዜኖ (Abba Zeno) ስለዚህ ጸዋሚ በሰማ ጊዜ እርሱ ወዳለበት ገዳም እንዲመጣ መልእክት ላከበት። መልእክቱም የደረሰው ይህ ሰው በደስታ ወደ ገዳሙ መጣ። ከአባ ዜኖም ጋር አብረው በጸሎት ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ። 
   ሲጨርሱም  በኋላ አረጋዊው አባት በጸጥታ የራሱን ሥራ መሥራት ጀመረ። ጸዋሚው ሰው ቢያይ ቢያይ የሚያዋራው (ስለ ጾም ሕይወቱ) በማጣቱ እየደበተውና ዝምታው እየሰለመቸው መጣ።
  ስለዚህም አረጋዊውን አባት "አባ፣ ልሄድ ስለሆነ ይጸልዩልኝ" አላቸው። አባ ዜኖም "ለምን?" ሲሉ ጠየቁት።
   ጸዋሚውም "እውነት ለመናገር በመንደር ሳለሁ እስከ ምሽት ድረስ እጾም ነበር። እንዲህ ዓይነት ነገር ያለ ዛሬም ገጥሞኝ አያውቅ። ምን እንደ ሆነ ባላውቅም ልቤ ልክ በእሳት ላይ እንደተቀመጠ ነገር ተቃጠለብኝ " በማለት መለሰ።
   አረጋዊውም "በመንደር ሳለህ የምትመገበው በአፍህ ሳይሆን በጆሮህ ነበር። በል ወደ መጣህበት ተመለስ። ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጾመህ ተመገብ። የምታደርገውንም ሁሉ በምሥጢር አድርግ" ሲሉ ገሰጹት።

  ጸዋሚው ወደ መጣበት ተመልሶ ይህን ምክር ተግባራዊ ማድረግ ሲጀምርም ጭራሽ እስከ ዘጠኝ እየጾሙ መቆየትም ከባድ ሆነበት። በቀድሞ ሥራው የሚያውቁትም የመንደሩ ሰዎች "ጾመኛው ሰው በሰይጣን ተያዘ" እያሉ አስወሩበት።
ይህንንም ነገር ለአረጋዊው(አባ ዜኖ) በነገራቸው ጊዜ "እግዚአብሔር የፈቀዳት መንገድ ይህች ነች" ሲሉ መለሱለት።

   ከልብ ሳይሆን የሰውን ከንቱ ውዳሴና ጩኸት ብቻ ተደግፈን መንፈሳዊውን ሥራ ለምንሠራ ሰዎች ታሪኩ ምን ዓይነት መልእክት ያለው ይመስላችኋል?

   #share

https://t.me/zekidanemeheret
የዕለቱ ምስባክ፦

ደቂቀ እጓለ እመሕያው እስከ ማዕዜኑ ታከብዱ ልበክሙ፤
ለምንት ታፈቅሩ ከንቶ ወተኀሡ ሐሰተ፤
አእምሩ ከመ ተሰብሐ እግዚአብሔር በጻድቁ። መዝ፬፥፪

ትርጕም፦

እናንተ የሰው ልጆች እስከመቼ ድረስ ልባችሁን ታከብዳላችሁ?
ከንቱ ነገርን ለምን ትወዳላችሁ? ሐሰትንስ ለምን ትሻላችሁ?
እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተመሰገነ እወቁ።

ምሥጢር፦

እናንተ የመነናውያን ልጆች እስከመቼ ድረስ ልቡናችሁን ታጸናላችሁ? ሠራዒ መጋቢ የለም በማለት ልቡናችሁን ለምን ታጸናላችሁ?
ከንቱ ነገርን ማለትም ሠራዒ መጋቢ የለም ማለትን ለምን ትወዳላችሁ?
ሐሰትን ለምን ትናገራላችሁ? እግዚአብሔር የለም ማለትን።
እግዚአብሔርማ ኖሮ በጻድቁ በኖኅ በጻድቁ በሎጥ በጻድቁ በሕዝቅያስ እንደተመሰገነ እወቁ።


ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ !
      #join_share


https://t.me/sinkisar_gisawe_z_tewahedo
                   ✥