ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
813 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_10
#በዓለማችን_የሚታዩ_የጋብቻ_አይነቶች
በዓለማችን ላይ የሚታዩትን የጋብቻ አይነቶችን የመስኩ ባለሙያዎች አንድ ለአንዲት /Monogamy/ ከአንድ በላይ ጋብቻ /Polygamy/ በማለት #በ2 ታላላቅ መደቦች ይከፍሏቸዋል ።
#ሀ_ከአንድ_በላይ_ጋብቻ/Polygamy/ ፦ ይህ በራሱ በሁለት ይከፈላል ። አንዳንዱ ማህበረሰብ አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን እንዲያገባ ይፈቀድለታል ። ይህ /Polygyny/ ፖሊጂኒ የሚባል ነው ። ለምሳሌ በሙስሊሞች ዘንድ 1 ወንድ ከ 1 ሴት በላይ እስከ 4 ሴት እንዲያገባ ይፈቀድለታል ። ሴቷ ግን ከዚህ ተከልክላለች ። ሁለተኛው አይነት ደግሞ አንዲት ሴት ብዙ ወንዶችን የምታገባበት ነው ። ይህ ፖሊአንድሪ /Polyandry/ ተብሎ የሚጠራው ነው ። በተወሰኑ የሩቅ ምስራቅ ሕዝቦች መካከል የሚፈፀም መሆኑ ጥናቶች ያረጋግጣሉ። ከዚህ ውጭ ቡድናዊ ጋብቻዎች /Group Marriage / የሚፈፀምባቸው የአለማችን የህብረተሰብ ክፍሎች እንደነበሩ ጥናቶች ይጠቁማሉ ። ይህ ማለት ብዙ ወንዶችና ብዙ ሴቶች በአንድ ላይ እየኖሩ የጋራ ባሎችና የጋራ ሚስቶች የሚሆኑበት አይነት ነው ። በዓለማችን በስፋት ተለምዶ የሚገኘው የ1 ወንድ ከ1 በላይ ሴቶችን የማግባት ሥርዓት ነው ። በክርስትና እምነት ድርጊቱ የማይደገፍና በእግዚአብሔርም ዘንድ የተጠላ ቢሆንም በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ እንደምናገኘው በብሉይ ኪዳን ብዙ ሚስቶች የነበራቸው ወንዶች ነበሩ። ብዙ ባል ያገባች ማግኘት ግን ይከብዳል ። ይህ ከጋብቻ ባህርይ ውጪ ነው ።
#ለ_አንድ_ለአንድ /Monogamy/ ጋብቻ አንድ ለአንዲት ፤ አንዲት ለአንድ መሆን እንደሚገባ ተገልጿል ።ለአዳም ብዙ ሴቶች አለመፈጠራቸው ለአንድ ወንድ አንዲት ሴት እንጂ ብዙ ሴቶች ያልተፈቀደ መሆኑን ፤ ለሔዋንም ብዙ ወንዶች አለመፈጠራቸው ለአንዲት ሴት አንድ ባል እንጂ ብዙ ወንዶች ያልተፈቀዱ መሆኑን ያመለክታል ። በሃገራችን ኢትዮጵያ በልዩ ብሔር ብሔረሰቦችና በተለያዩ የእምነት ድርጅቶች የሚፈጸሙ በርካታ የጋብቻ አይነቶች አሉ ። የኦርቶዶክስ ተከታዮች የሚፈጽሟቸው የጋብቻ አይነቶች የሚከተሉት ናቸው ። #1ኛ ሐይማኖታዊ ጋብቻ #2ኛ የሠማንያ ጋብቻ #3ኛ የሲቪል ጋብቻ በመባል ይታወቃሉ ።
#1ኛ_ሃይማኖታዊ_ጋብቻ ፦ ሃይማኖት አለን የሚሉ ክፍሎች እንደየሥርዓተ ሃይማኖታቸው የሚፈጽሙት ነው ። በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት የሚጋቡ በተክሊል ፣ በሥጋወደሙ ወይም እንደ ስርዓቱ በመአስባን ጸሎት እና በቁርባን የሚወሰኑ ናቸው ።
#2ኛ_የሠማንያ_ጋብቻ ፦ ይህ ጋብቻ ዓይነቱና ይዘቱ ሰፊ የሆነ እና በብዙ ሰዎች የሚፈጸም የተለመደ ባሕላዊ የጋብቻ አይነት ነው ።
#3ኛ_የሲቪል_ጋብቻ ፦ በመንግስት በተቋቋመ አካል ፊት ቀርቦ የሚፈጸመው የጋብቻ አይነት ነው ።ይህ እንግዲ በከተሞች የሚፈጸም ነው ። በተለምዶ የመዘጋጃ ቤት ጋብቻ ተብሎ ይጠራል ።
#የመዐስባን_ጋብቻ ፦ መዐስብ ማለት ብቸኛ ፣ ፈት ፣ ጋለሞታ ሚስት የሌለችው ባል የሌላት በሞት ወይም በነውር ምክንያት ተፈትታ ወይም ተፈትቶ በብቸኝነት የሚኖር የምትኖር ማለት ነው ። በመዐስብነት የሚኖሩ ሰዎች የብቸኝነት ኑሮ የሚዘልቁት ሆኖ ባለማግኘታቸው ምክንያት እንዲያገቡ ውሳኔ ላይ በሚደርሱበት ጊዜ ዳግም ያገቡ ዘንድ ይፈቀድላቸዋል ። #መዐስባን ጋብቻ በሚፈጽሙበት ጊዜ የማስተሰሪያ ጸሎት ይጸለይላቸዋል እንጂ ተክሊል አይደረግላቸውም

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret