✅ስንክሳር
🚩ጥር 30
✅ቅድስት ሶፍያና ልጆቿ ፦
✏በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ታዋቂ ከሆኑ የእናቶቻችን ስሞች "ሶፍያ" ቀዳሚው ነው:: ቃሉ በጥሬው ሲተረጐም "ጥበብ (ጥበበ ክርስቶስ) ማለት ነው:: ከጻድቃንና ከሰማዕታት ወገን በዚህ ስም የተጠሩ እናቶች አሉ::
✏ከእነዚህ መካከል አንዷ የሆነችው በዕለቱ የምናስባት እናት ቁጥሯ ከሰማዕታት ነው:: ዋናው ዘመነ ሰማዕታት ከመጀመሩ በፊት የነበረችው ቅድስት ሶፍያ ከሕግ ትዳር 3 ሴቶች ልጆችን አፍርታለች::
✏ስማቸውንም:- ጲስጢስ (ሃይማኖት) : አላጲስ (ተስፋ) : አጋጲስ (ፍቅር) ስትል ሰይማቸዋለች:: እንደሚገባም በሥርዓቱ አሳድጋ እድሜአቸው 9 : 10 እና 12 ሲደርስ ለሰማያዊ ሙሽርነት አጭታቸዋለች::
✏በዘመኑ "ክርስቶስን ካዱ" የሚል መሪ ተነስቶ ነበርና ቅዱሳቱ በመድኃኒታችን አምነው : ጣዖትን ዘልፈው አንገታቸውን ሰጥተዋል:: ክብረ ሰማዕትን : ሃገረ ክርስቶስንም ወርሰዋል::
✅ቅድስት ኦርኒ ሰማዕት፦
✏ "ኦርኒ" ማለት በምሥራቃውያን ልሳን "ሰላም" ማለት ነው:: ቅድስቲቱ አርበኛ የዘመነ ሐዋርያት የቤተ ክርስቲያን ፍሬ ስትሆን ተወልዳ ያደገችውም በቀድሞው የሮም ግዛት ውስጥ ነው::
✏ምንም ዛሬ ያለ ትውልድ ቢዘነጋት ቅድስት ኦርኒ ተወዳዳሪ የሌላት ሰማዕት : ሐዋርያዊት : ድንግል ናት:: እርሷ ውበቷን : ንግሥናዋን : ክብሯን : ሃብቷን : ወጣትነቷንና ያላትን ሁሉ ስለ ፍቅረ ክርስቶስ ሰውታለችና ክብርት ናት::
✏በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ቤተ መንግስት የተወለደችው ቅድስት ኦርኒ እስከ ወጣትነቷ ድረስ ክርስቶስን ልታውቀው አልተቻላትም ነበር:: ምክንያቱ ደግሞ ንጉሡ አባቷ ጣዖትን ማምለኩ ነበር::
✏ንግሥት እናቷ ምንም ክርስቲያን ብትሆንም ስለ ክርስትና ልትነግራት አልደፈረችም:: ይህን ብታደርግ የሚደርስባትን መከራ ታውቃለችና:: ግን ደግሞ ውስጥ ውስጡን ትጸልይላት ነበርና ፈጣሪ መንገዱን ሊከፍት ጀመረ::
✏መምለኬ ጣዖት አባቷ ሰው እንዳያያት ቤተ መንግስት ሠርቶ : 12 ሞግዚቶችን መድቦ ጣዖት ከፊቷ አቁሞ ለዘመናት ዘጋት:: የሚገርመው ግን መልኳን እንዳያይ በበር ሆኖ የሚያስተምራት ፈላስፋ ተቀጥሮ ነበርና የዚህ ሰው ማንነቱ ነው::
✏መምለኬ ክርስቶስ ደግ ሰው ነበርና ፈሊጥን ይሻላት ገባ:: በዚህ መካከል ቅድስት ኦርኒ ራዕይን ታያለች:: የቤቷ መስኮቶች ተከፍተው ሳሉ በስተምሥራቅ ነጭ ርግብ : የዘይት (የወይራ) ዝንጣፊ ይዛ ገብታ : ከማዕዷ ላይ ጥላው ወጣች::
✏እርሷን ተከትሎ ቁራ በምዕራብ ገባ:: እባቡን ማዕዷ ላይ ጣለው:: በ3ኛው ደግሞ ንስር ገብቶ አክሊል ትቶላት ወጣ:: ቅድስቲቱም እየገረማት አረጋዊ መምህሯን "ተርጉምልኝ" አለችው::
🚩እርሱም:-
"•ርግብ=ጥበብ (መንፈስ ቅዱስ)
•ዘይት=ጥምቀት
•ቁራ=ክፉ ንጉሥ
•እባብ=መከራ
•ንስር=ድል ነሺነት (ልዑላዊነት)
•አክሊልም=ክብረ ሰማዕታት ነው" ብሎ ተርጉሞ : ክርስቲያን ሆና ይህ ሁሉ እንደሚደረግ ነግሮ ተሰናበታት::
✏እርሷም ስትጸልይ ቅዱስ መልአክ ተገልጦ አጽናናት:: ያጠምቃትና ያስተምራት ዘንድም ሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስን ልኮላታል:: ሐዋርያውም የቤተ መንግስቱን ግድግዳ ሰንጥቆ ገብቶ : ለሰማያዊ ሙሽርነት የሚያበቃ ትምህርትና ጥምቀትን ሰጥቷት ሔዷል::
✏ቅድስት ኦርኒም የአባቷን ጣዖታት ቀጥቅጣ ሰብራ ከአባቷ ጋር ተጣላች:: እርሱም "እገድላታለሁ" ብሎ በእንስሳት ጅራት ላይ ጸጉሯን ሲያስር እንስሶቹ ደንብረው : እጁን ገንጥለው መሬት ላይ ጥለው ገደሉት:: ቅድስት ኦርኒ ግን ጸሎት አድርሳ አባቷን ከሞት አስነሳችው:: እጁንም ቀጠለችለት::
✏በዚህ ምክንያት በዚያች ዕለት ብቻ አባቷና 30,000 የከተማው አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል:: ቅድስት ኦርኒ ግን ኃይለ መንፈስ ቅዱስ ታጥቃ ክርስትናን ሰበከች:: ብዙም ተሰቃየች:: ንጉሡ ዳኬዎስ : ልጁና ሌሎች 2 ያህል ነገሥታት በእሳት : በአራዊት : በግርፋትና በጦር ፈትነዋታል::
✏እርሷ ግን ሁሉን በኃይለ ክርስቶስ ድል ነስታለች:: ሙታም የተነሳችበት ጊዜ አለ:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ወደ ሰማያዊ ርስት (ገነት) ተመስጣለች:: በዘመነ ስብከቷ ካሳመነቻቸው ባሻገር 130,000 የሚያህሉ ሰዎች ለሰማዕትነት እንዲበቁም ምክንያት ሆናለች::
✅ቅዱስ ጐርጐርዮስ ታኦሎጐስ ፦
🚩ቅዱሱ:-
•የዘመነ ሊቃውንት ፍሬ:
•የእንዚናዙ ኤጲስ ቆጶስ:
•የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ:
•የጉባዔ ቁስጥንጥንያ (በ381 ዓ/ም) 3ኛ ሊቀ መንበር:
•ባለ ብዙ ድርሳን:
•የቂሣርያ (ቀጰዶቅያ) ኮከብ:
•ብሩህ ገዳማዊ:
•መልካም እረኛ የነበረ አባት ነው::
✏መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በጻፋቸው ብዙ መጻሕፍትና በስብከቱ ከሊቃውንት ወገን "ታኦ(ዎ)ሎጐስ" ተብሎ የተጠራ እርሱ ብቻ ነው:: ትርጉሙም በግዕዙ "ነባቤ መለኮት" ማለት ነው:: በአማርኛም "አንድነትን : ሦስትነትን የተናገረ (ያመሠጠረ) እንደ ማለት ነው:: ቅዱሱ ዛሬ ዕረፍቱ ነው::
🚩አምላከ ቅዱሳን ከበረከታቸው ይክፈለን፡፡
በመጽናታቸውም ያጽናን፡፡
🚩 ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦
1.ቅድስት ሶፍያና ሦስቱ ሰማዕታት ልጆቿ (ጲስጢስ አላጲስና አጋጲስ)
2.ቅድስት ኦርኒ ሰማዕት ( (በ5 ነገሥታት እጅ የተሰቃየች : የሐዋርያው ጢሞቴዎስ ተከታይና ወደ ብሔረ ሕያዋን የተነጠቀች እናት)
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.አባ አክርስጥሮስ
5.አምስቱ ደናግል ሰማዕታት (ጤቅላ: ማርያ: ማርታ: አበያ: ዓመታ)
6.ጻድቃነ ዴጌ (የተሠወሩበት)
7.አባ ሚናስ ሊቀ ጳጳሳት
8."130,000" ሰማዕታት (የቅድስት ኦርኒ ማኅበር)
🚩ወርኀዊ በዓላት፦
1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ
2.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
3.አባ ሣሉሲ ክቡር
↗ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተፀመድኩ ፥ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውክፈ እምእለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሂቅ እምንኡስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ።

🚩የካቲት 3
✅ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ፦
✏እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ቅዱስ ኤፍሬም
የተወለደው ንጽቢን በምትባል የሶርያ ግዛት ውስጥ
በ298 / 306 ዓ/ም ነው:: ወላጆቹ በክርስቶስ የማያምኑ አላውያንነበሩ::
(ምንም አንዳንድ ምንጮች ክርስቲያኖች ነበሩ
ቢሉም)
✏ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ንጽቢን ዽዽስናን የተሾመ
ቅዱስ ያዕቆብ የሚባል ታላቅ ሰው ነበር:: የሰማዕትነት:
የሐዋርያነት: የጻድቅነትና የሊቅነት ግብር ያለው አባት
ነው:: ታዲያ ቅዱስ ኤፍሬም ይሔ አባት ሁሌ ሲያስተምር ይሰማው
ነበርና በስብከቱ ተማርኮ ደቀ መዝሙሩ ለመሆን በቃ::
✏ቅዱስ ኤፍሬም በቅዱስ ያዕቆብ እጅ ከተጠመቀ በሁዋላ ሙሉ የጣትነት ጊዜውን ያሳለፈው በትምሕርት ነው:: የሚገርመው መምሕሩ ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን እመቤታችን ድንግል ማርያምን በፍጹም ልቡ የሚወድና ጠርቷት የማይጠግብ አባት ነውና ለልጁ
ለቅዱስ ኤፍሬም ይሕንኑ አጥብቆ አስተምሮታል::
✏ቅዱስ ኤፍሬም ክርስትናን ሲመረምር የእመቤታችን
ፍቅር ይበዛለት ጀመር:: ምክንያቱም እመ ብርሃንን
ሳይወዱ ክርስትና የለምና::
እንደ እርሱ የሚወዳት የለም እስኪባል ድረስ
ያገለግላት: ይገዛላትም ገባ::
✏እንዲህ እንደ ዛሬ የድንግል ማርያም ምስጋና በአንደበት እንጂ በመጽሐፍ አይገኝም ነበር:: እርሱ ግን ከወንጌለ ሉቃስ በስድስተኛው ወርን (ይዌድስዋን) እና ጸሎተ ማርያምን (ታዐብዮን) አውጥቶ በየዕለቱ በዕድሜዋ ልክ 64 64 ጊዜ
ያመሰግናት ነበር::
✏በእንዲህ ያለ ግብር እያለ አርዮስ በመካዱ እርሱን
ለማውገዝና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ለማጽናት በ317 /
325 ዓ/ም 318ቱ ሊቃውንት በኒቅያ ሲሰበሰቡ አንዱ መምሕረ ኤፍሬም ቅዱስ ያዕቆብ ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱስ ኤፍሬም
ከሊቃውንቱ ትምሕርትና በረከትን አግኝቷል::
✏ከጉባዔ መልስ መንገድ ላይ በራዕይ የብርሃን ምሰሶ
አይቶ "ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?" ብሎ ቢጠይቅ "ይህማ
ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ነው" አለው:: እርሱም መምሕሩን ቅዱስ ያዕቆብን ተሰናብቶ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ (ቂሣርያ) ወረደ::
ተገናኝተውም በአንድ ሌሊት ቁዋንቁዋ ተገልጦላቸው
ሲጨዋወቱ አድረዋል::
✏በቦታው ብዙ ተአምራት ተደርጉዋል:: ቅዱስ ኤፍሬም
ከታላቁ ባስልዮስ ከተማረ በሁዋላ ሃገረ ስብከት
ተሰጥቶት ያስተምር ጀመር:: ሁል ጊዜ ታዲያ ጸሎቱ ይሔው ነበር:: "እመቤቴ ሆይ! ምስጋናሽ እንደ ሰማይ ከዋክብት: እንደ ባሕር አሽዋ
በዝቶልኝ: እንደ እንጀራ ተመግቤው: እንደ ውሃ ጠጥቼው: እንደ ልብስም ተጐናጽፌው" እያለ ይመኝ ነበር::
✏አፍጣኒተ ረድኤት: ፈጻሚተ ፈቃድ እመ ብርሃንም በገሃድ ተገልጻ የልቡን ፈቃድ ፈጸመችለት:: ዛሬ ጸጋ በረከት የምናገኝበትን ውዳሴ ማርያምን ደረሰላት:: ሲደርስላትም እርሷ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላ ወርዳ:
በፊቱም ተቀምጣ ሲሆን እርሱ ደግሞ ባጭር ታጥቆ:
በፊቷ ቆሞ: በመንፈስ ቅዱስም ተቃኝቶ ነው::
✏ውዳሴዋን በ7 ቀናት ከደረሰላት በሁዋላ በብርሃን
መስቀል ባርካው: ሊቀ ሊቃውንትም እንዲሆን ምስጢር
ገልጣለት ዐረገች:: ከዚህ በኋላ በምስጢር ባሕር ውስጥ ዋኝቶ 14 ሺህ ድርሰቶችንም ደርሷል:: ዛሬ ሶርያ ውስጥ የምንሰማውን
ዜማም የደረሰው ይህ ቅዱስ ነው::
✏እንዲያውም አንድ ቀን የምሥጢር ማዕበል ቢያማታው "አሃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" ብሎ ጸልዩዋል:: (የጸጋህን ማዕበል
ያዝልኝ) እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
በመጨረሻ ሕይወቱ ተክሪት በምትባል ሃገር ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል::
✏በጣፋጭ ስብከቱ ብዙዎችን ካለማመን መልሷል:
የምዕመናንንም ሕይወት አጣፍጧል:: ለመናፍቃንና
ለአርዮሳውያን ግን የማይጋፉት ግድግዳ ሆኖባቸው ኑሯል:: በዘመኑም ብዙ ተጋድሎ አፍርቷል: ተአምራትንም ሠርቷል:: በተወለደ በ67 ዓመቱ
በ365 / 373 ዓ/ም ዐርፎ ተቀብሯል::
✏ቅዱሱ ለሶርያ ብቻ ሳይሆን እመቤታችንን ለምንወድ
የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ሞገሳችን ሆኗል:: ስለዚህም
እንዲህ እያልን እንጠራዋለን:-
1.ቅዱስ ኤፍሬም
2.ማሪ ኤፍሬም
3.አፈ በረከት ኤፍሬም
4.ሊቀ ሊቃውንት
ኤፍሬም
5.ጥዑመ ልሳን ኤፍሬም
6.አበ ምዕመናን
ኤፍሬም
7.ርቱዐ ሃይማኖት ኤፍሬም . . . አባታችን አንተ ነህ::
❖የካቲት ፫ ቀን ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዓመታዊ የፍልሠት በዓሉ ነው፡፡
✞ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን
ለቅዱስ ኤፍሬም የሰጠሽውን ጸጋውን: ክብሩን:
አእምሮውን: ለብዎውን
በልቡናችን ሳይብን: አሳድሪብን . . . አሜን::
✅አባ ያዕቆብ ገዳማዊ ፦
✏ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት "ለስሒት መኑ ይሌብዋ-
ስሕተትን ማን ያስተውላታል" (መዝ) ሲል የተናገረው
ይፈጸም ዘንድ ይህ ታላቅ ቅዱስ ሰው በኃጢአት ብዙ ተፈተነ:: ወደ በርሃ ወጥቶ: በምናኔ ጸንቶ: በጾምና በጸሎት ተግቶ ዘመናትን ስላሳለፈ
ሰይጣንን አሳፈረው::
✏ግን ደግሞ ክፉ ጠላት ባልጠረጠረው መንገድ መጥቶ መከራ ውስጥ ከተተው:: የአገረ ገዢው ልጅ ታማ "ፈውሳት" አሉት: ፈወሳት:: ወደ ቤቷ ስትመለስ ግን አመማት:: "ከአንተ ጋር ትቆይ" ብለው ትተዋት ቢሔዱ ከመለማመድ የተነሳ በዝሙት ወደቀ::
✏እንዳይገለጥበት ስለ ፈራም ገደላት:: በሆነው ነገር
ተስፋ ቆርጦ ወደ ዓለም ሲመለስ: ቸር ፈጣሪ የሚናዝዝ
አባትን ልኮ ንስሃ ሰጠው:: ጉድጓድ ምሶ: ድንጋይ ተንተርሶ ለ30 ዓመታት አለቀሰ:: እግዚአብሔርም ምሮት: የቀደመ ጸጋውን ቢመልስለት: ዝናምን አዝንሞ ሕዝቡን ከእልቂት ታድጓል::
በዚህች ዕለት ዐርፎም ለርስቱ በቅቷል::
✅ታላቁ አባ ዕብሎይ፦
✏ይህ ቅዱስ የአቡነ አቢብ ደቀ መዝሙር ሲሆን በዚህ
ስም ከሚጠሩ ቅዱሳንም ቀዳሚው ነው:: ብዙ መጻሕፍት 'ርዕሰ ገዳማውያን' ይሉታል:: የቅዱሱ ተጋድሎ እጅግ ሰፊ ነው::
🚩ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦
1.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት-በዓለ ፍልሠቱ)
2.ቅዱስ አባ ዕብሎይ ገዳማዊ (ሕይወቱ መላዕክትን
የመሰለ ግብፃዊ አባት)
3.አባ ያዕቆብ መስተጋድል

👍1
✅ስንክሳር
🚩የካቲት 7
✅አባ ቴዎድሮስ ሊቀ ጳጳሳት፦
✏በዚች ዕለት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባ ቴዎድሮስ አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ አምስተኛ ነው።
✏ይህም አባት መርዩጥ በሚባል አገር በአንድ ገዳም ውስጥ መነኮሰ የዚያም ገዳም ስም ጠንቡራ ነው ለአንድ ፍጹም ጻድቅ የሆነ ሽማግሌ ነው ደቀ መዝሙሩ ሆነ እርሱ ልጁ ቴዎድሮስ በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና እንደሚሾም በመንፈስ ቅዱስ አይቶ ይህን ለመነኮሳቱ ነገራቸው።
✏ይህጨአባት ቴዎድሮስ በገድል የተጠመደ ሆነ መልኩ የሚያምር ነው በሰውነቱም ላይ ከውስጥ ማቅ በመልበስ በላዩ የብረት ልብስ መንቆርጰይለብስ ነበር በቅንነቱና በትህትነው ፍጹም ሆነ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ተመርጦ በእስክንድርያ አገር ላይጰሊቀ ጵጵስና ተሾመ።የክርስቶስንም መንጋዎች በበጎ አጠባበቅ ጠበቀ ሁልግዜ መጽሐፍትን በማንበብ ያስተምራቸው ነበር ይልቁንም በሰንበትና በበአላትጨቀን።
✏የሹመቱም ዘመን ጸጥታና ሰላም ነበር ቤተክርስትያንም በሰላም ኖረችበወንጌላዊ ማርቆስ ወንበርም ላይዐስራጨአንድ አመት ተኩል ከኖረ በኋላ በሰላም አረፈ።
🚩ለእግዚአብሔር ምሰሰጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✅ቅዱስ አባዲር እና አባ አብዱልማዎስ ገዳማዊ፦
✏በዚች ቀን የከበሩ የአብራቅያ የአባዲር የአባርያኖስ የአብዱልማስ ዕብሎይ ያረጋጋ የገዳማዊውም የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው። በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይገባል አሜን።
🚩 ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦
1.አባ አብዱልማዎስ ገዳማዊ
2.አባ ቴዎድሮስ ሊቀ ጳጳሳት
3.አባ እለ እስክንድሮስ ሊቀ ጳጳሳት
4.ቅዱስ አባዲር
🚩ወርኀዊ በዓላት፦
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ

🚩የካቲት 12
✅"30,000" ሰማዕታተ ኢትዮዽያ (ሮማዊው ፋሽስት የገደላቸው)፤ቅዱስ ሶምሶን ረዓይታዊ (የእስራኤል መስፍን)፤ቅዱስ አባ ገላስዮስ ገዳማዊ፤ቅድስት ዶርቃስ
✅ቅዱስ ሶምሶን ረዓይታዊ፦
✏በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው
✏የከበረ ሚካኤልን እግዚአብሔር ወደ ረዓይታዊ ወደ ሶምሶን ላከው የፍልስጤም ሰዎች ሊገድሉት በጠላትነት በተነሱ ጊዜ ድል እስከ አደረጋቸውና እስከገደላቸው ድረስ እረደው።
✏ኃይልም ሰጥቶ በአህያ መንጋጋ ከእርሳቸው አንድ ሽህ ሰዎችን ገደለ ተጠምቶም ለሞት በተቃረበ ጊዜ የመላእክት አለቃ ማካኤል ተገለጸለትና አጸናው እግዚአብሔር ከአህያ መንጋጋ አጥንት ውኃን አፈለቀለትና ጠጥቶ ዳነ።
✏ዳግመኛም ከሚስቱ ጋር ተስማምተው አይኖቹንም አሳወሩ የእራሱንም ጸጉር ላጩ አሰሩትም ከዚህም በኋላ ለጣዖቶቻቸው በዓልን በአዘጋጁ ጊዜ ሶምሶንን ወደ ጣኦቶቻቸው ቤት ወሰዱት በዚያም ሦስት ሽህ ያህል ሰዎች ተሰብስበው ነበር።
✏የከበረ ሚካኤል ተገለጠለትና ኃልን መላው የዚያንም ቤት ምሰሶች ነቀላቸው ቤቱም በላያቸው ወድቆ ከእርሱ ጋር ሁሉንም ገደላቸው።
✏ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ መልአክ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✅ኢትዮዽያውያን ሰማዕታት፦
✏በ1929 ዓ/ም: የካቲት 12 ቀን ከ30,000 በላይ ኢትዮዽያውያን አባቶች: እናቶች: ወጣቶችና ሕፃናት በሮማዊው የፋሽስት ጦር ደማቸው ፈሷል:: እነዚሕ ወገኖቻችን ደማቸው እንደ ጐርፍ አዲስ አበባ ላይ የፈሰሰው ስለ ሃገር ፍቅር ብቻ አልነበረም:: ስለ ቀናች ሃይማኖት ተዋሕዶ ጭምር ነው እንጂ::
🚩ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ግፃዌ ላይ ስማቸውን ጽፋ በቅዱስ ዳዊት መዝሙር እንዲህ ታስባቸዋለች::
🚩ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦
1."30,000" ሰማዕታተ ኢትዮዽያ (ሮማዊው ፋሽስት የገደላቸው)
2.ቅዱስ ሶምሶን ረዓይታዊ (የእስራኤል መስፍን)
3.ቅዱስ አባ ገላስዮስ ገዳማዊ
4.ቅድስት ዶርቃስ
🚩ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት
2.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ድሜጥሮስ
4.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
6.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
7.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
8.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ

🚩የካቲት 13
✅ቅዱስ አውሳብዮስ ጻድቅ (ጥዑመ ዜና)፣ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት (ልደቱ)፣ቅዱስ ሰርግዮስ ሰማዕት
፣ቅዱስ መፁን ቀሲስ፣ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት (የቅ/ፋሲለደስ ልጅ)፣አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት፣አባ ክፍላ
፣አባ ኅብስ
✅አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት፦
✏በዚች ዕለት የከበረ አባት የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ጢሞቴዎስ አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሁለተኛ ነው።
✏ይህንንም አባት ስለቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራና ችግር ደርሶበታል እንዲህም ሆነ በዚያ ወራት የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሳዊሮስ ወደ ግብጽ ሐገር መጣ እርሱም ከዚህ አባት ጢሞቴዎስ ጋር ምዕመናንን እያጸናና ከሃገር ወደ ሃገር ከገዳም ወደ ገዳም ከቦታ ወደ ቦታ የሚዘዋወር ሆነ።
✏በዚህ አባት ጢሞቴዎስ ዘመን ከቁስጥጥንያ የመጡ ክፉዎች ሰዎች በግብጽ አገር ተገለጡ እነርሱም የክርስቶስን ተዋሕዶ ምትሐት በሚያደርግ መከራውንና ትንሳኤውን በሚክድ በረከሰ በአውጣኪ ትምህርት የሚያምኑ ናቸው ይህም አባት አውግዞ ከግብጽ አገር አሳደዳቸው።
✏ዳግመኛም በዘመኑ ምእመን ንጉሥ አንስጣስዮስ አረፈና በእረሱ ፈንታ ኬልቄዶናዊ መናፍቅ ዮስጣትያኖስ ነገሰ እርሱም በአባ ጢሞቴዎስ ፈንታ ሊናርዮስን ሊቀ ጵጵስና ሾመው ሃይማኖታቸው የቀና ምእመናንን ሁሉ በኬልቄዶን ጉባኤ ወደተወሰነ ሃይማኖት ሊመልሳቸው ወዶ በቆስጥንጥንያ ጉባኤ ሰብስቦ የአንጾኪያውንጨሊቀ ጳጳሳት አባ ሳዊሮስን ከኤጲስ ቆጶሳቶቹ ጋር አስመጣው
✏በኬልቄዶን ጉባኤ በተወሰነች በተበላሸች ሃይማኖቱ ያምኑ ዘንድ አስገደዳቸው እነርሱም ግን አልተቀበሉትም ትእዛዙንም አልሰሙም ስለዚህም ሃይማኖታቸው በቀና ምእመናንጨሁሉ ታላቅ መከራጨአደረሰባቸው።
🚩ይህ አባት ጢሞቴዎስ በመንበረ ሢመቱ አስራ ሰባት አመት ኑሮ በሰላም አረፈ በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል አሜን።
✅ማር ፊቅጦር፦
✏ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በደማቸውና በገድላቸው ያስጌጡ ብዙ ሰማዕታት አሉ:: ነገር ግን ከኮከብም ኮከብ ይበልጣልና ማን እንደ ጊዮርጊስና እስጢፋኖስ! ከእነርሱ ቀጥለው ከሚጠሩ ሰማዕታት ደግሞ አንዱና ዋነኛው ቤተ ክርስቲያን "ማር" የምትለው ቅዱስ ፊቅጦር ነው::
✏ገድለ ፈፊቅጦር፦
+ቅዱስ ፊቅጦር አባቱ ኅርማኖስ ይባላል:: አረማዊና
ጨካኝ ነው:: እናቱ ግን የተመሰገች ቅድስት ማርታ
ትባላለች:: ልጇን እንደሚገባ አሳድጋው 20 ዓመት
ሲሞላው የአንጾኪያ ንጉሥ የሠራዊት አለቃና በመንግሥቱ
3ኛ አድርጐ ሾመው::
✏የድሮዋ አንጾኪያ (ሮም) እንደ ዛሬዋ አሜሪካ ዓለምን
የተቆጣጠረች ሃገር ነበረች:: ቅዱስ ፊቅጦር ደም ግባቱ
ያማረ: በጦርነትም ኃይለኛ ስለ ነበር ሁሉ ያከብሩት:
ይወዱትም ነበር::
✏እርሱ ግን ቀን ቀን ሲጾም: ነዳያንን ሲያበላ ይውል
ነበር:: ሌሊት ደግሞ እኩሉን ሲጸልይና ሲሰግድ እኩሉን
የእስረኞችን እግር ሲያጥብ ያድር ነበር:: ይህ ሁሉ ሲሆንኮ እርሱ የንጉሡ 3ኛ: የሠራዊትም አለቃ ነው:: በዘመኑ የሚያገድፍ ምግብና የወይን ጠጅ በአፉ ዙሮ አያውቅም::
✏ከነገር ሁሉ በሁዋላ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ካደ:: ዘመነ ሰማዕታትም ጀመረ:: አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ:: ከ47 ሚሊየን በላይ ክርስቲያኖች በመንኮራኩር ተፈጩ:: በመጋዝ ተተረተሩ:: ለአራዊት ተሰጡ:: በግፍም ተጨፈጨፉ:: ቀባሪ አጥተውም ወደቁ::
✏በዚሕ ጊዜ ማር ፊቅጦር እናቱን ቅድስት ማርታን በዕንባ ተሰናብቶ ወደ ንጉሡ ቀርቦ በክርስቶስ ስም ታመነ:: ክፉ አባትም በልጁ ላይ ሞትን መከረ::
✏ከዚያም ቅዱሱን አፉን በብረት ለጉመው ወደ ምድረ
ግብፅ አወረዱት:: መሪያቸው እንዳልነበረ ወታደሮቹ
መኩዋንንቱ ሁሉ ተዘባበቱበት:: እርሱ ከምድራዊ ንግሥና ሰማያዊ መንግስትን: በሰዎች ፊት ከመክበር ስለ ክርስቶስ ሲል መናቅን መርጧልና::
✏ለቀናት: ለወራትና ለዓመታት መኩዋንንቱ እየተፈራረቁ
አሰቃዩት:: በርሱ ላይ ያልሞከሩት የስቃይ ዓይነት
አልነበረም:: አካሉን ቆራርጠዋል: ዓይኖቹን አውጥተዋል: ምላሱንም ቆርጠዋል:: ሚያዝያ 27 ቀን ግን በሰይፍ አንገቱን ቆርጠውታል:: ስለዚህም እናት ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ማክበር ታከብረዋለች::
✏እግዚአብሔርም ለቅዱስ ፊቅጦር እንዲህ አለው:-
"እንደ አቅሙ ስምህን የጠራ: መታሠቢያህን ያደረገ:
ስምህን ያከበረ: የብርሃን ልብስ አጐናጽፌ ወደ መንግስተ ሰማያት አስገባዋለሁ::
🚩ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦
1.ቅዱስ አውሳብዮስ ጻድቅ (ጥዑመ ዜና)
2.ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት (ልደቱ)
3.ቅዱስ ሰርግዮስ ሰማዕት
4.ቅዱስ መፁን ቀሲስ
5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት (የቅ/ፋሲለደስ ልጅ)
6.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት
7.አባ ክፍላ
8.አባ ኅብስ
🚩ወርኀዊ በዓላት፦
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

👍2
✅ስንክሳር
🚩የካቲት 14
✅ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ፣ቅዱስ ቄርሎስ ሊቀ ጳጳሳት፣አባ ያዕቆብ ሊቀ ጳጳሳት፣ቅዱስ ዳርዮስ፣ቅድስት ሊድና
✅አባ ያዕቆብ ሊቀ ጳጳሳት፦
✏በዚችም ዕለት የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት አባ ያዕቆብ አረፈ እርሱም የአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ኃምሳኛ ነው።
✏ይህ አባት እልመቱዝ የተባለ የግብጽ ንጉስ በነገሠ በአስራ ሰባት አመት ተሾመ እርሱ ለመኮንኑ ለወልደ ጎሮን ረሽድ ወንድም የሆነ ነው በዚህም አባት ዘመን የአስቄጥስ ገዳማት ታድሰው መነኮሳቱ ወደ እርሳቸው ተመለሱ።
✏አፎን በሚባል አገር ስሙ መቃርስ የሚባል ሰው ነበር ወደዚህ አባት ወደ ያዕቆብ መጥቶ ወደቤቱ በመሔድ ቤቱን ይባርክለት ዘንድ ለመነው እርሱም አብሮት ሔደ ታሞ የነበረው ልጅም ሞተ ወደ አባ ያዕቆብም አቅርቦ እንዲህ ብሎ ለመነው ከእርሱ በቀር ልጅ የለኝምና አባቴ ሆይ ራራልኝ እርሱም እነሆ ሞተ ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ትማልድ ዘንድ እለምንሀለው አለው።
✏አባ ያዕቆብም እንደ እምነትህ ይሁንልህ አትፍራ አለው ህጻኑንም ከአባቱ ተቀብሎ ታቀፈውና በላዩ ጸለየ በመስቀል ምልክትም አማተበበት ስለ እረሱም ወደ እግዚአብሔር ለመነ ጌታችንም ልመናውን ተቀበለው የህጻኑ ነፍስ ተመልሳ አይኖቹን ገለጠ ከሞትም ድኖ ተነሳ አባቱንም ልጅህን ውሰድ የሞተ አይደለም ያንቀላፋ ሆኖ ነው እንጂ አለው።
✏የሕፃኑም አባት ይህን ድንቅ ስራ እጅግ ፈራ የገንዘቡንም እኩሌታ ለምጽዋት ብሎ ሰጠው እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም ልኮ ሐይማኖታቸው ለቀና ምዕመናን ሁሉ ወደ እርሷ በመጡ ጊዜ መጠጊያ ይሆን ዘንድ ቤተክርስትያን ሰራበት።
✏የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ድዮናስዮስም ወደ ምስር በመጣ ጊዜ ከአባ ያዕቆብ ጋር ተገናኝቶ ከእርሱ ዘንድ ጥቂት ቀኖች ተቀምጦ ወደ ሐገሩ ተመለሰ።
✏ይህም አባት ያዕቆብ በሹመቱ ዓሥር አመት ከስምንት ወር ከሦስት ቀን ኑሮ በሰላም አረፈ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።††† እንኳን ለታላቁ ሊቅና የተዋሕዶ ጠበቃ ቅዱስ ሳዊሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
✅ ታላቁ ቅዱስ ሳዊሮስ ፦
✏ቅዱስ ሳዊሮስ በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በሶርያ አንጾኪያ የተነሳ አባት ነው። ወቅቱ መለካውያን (ሁለት ባሕርይ ባዮች) የሰለጠኑበት እንደ መሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ያነሱበትና የሚሰደዱበት ጊዜ ነበር። በዚህ ጊዜ ነበር ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ሳዊሮስ በሥላሴ ፈቃድ ለቤተ ክርስቲያን የተነሳው። ሊቃውንት አንበሳ ሲሉ ይጠሩታል።
✏ቅዱሱ ለተዋሕዶ ሃይማኖት ብዙ ሆኖላታል። የመናፍቃን ጸር በመሆኑ ብዙ ድርሰቶችን ደርሷል። ንጉሡን ዮስጢያኖስን (Justinian) ሳይቀር በይፋ ይገስጸው ነበርና ንጉሡ ሊገድለው ቆረጠ።
✏ሃይማኖቷ የቀና ንግሥቲቱ ታኦድራ ግን ይህንን ስትሰማ በሌሊት ወደ ሊቁ ሒዳ "እባክህን ሽሽ።" አለችው። እርሱ ግን "ሞት ለእኔ ክብር ነውና አልሔድም።" ሲል መለሰላት። አባቶችን ሰብስባ "ስለ ቤተ ክርስቲያን ስትል" ብለው ለምነው ወደ ግብጽ ሸኙት።
✏እርሱ እየሔደ ገዳዮቹ ያሳድዱት ገቡ። መንገድ ላይ ቢደርሱበትም ተሰወረባቸው። ለብዙ ቀናትም አብሯቸው ተጓዘ። እነርሱ ተስፋ ቆርጠው ሲመለሱ እርሱ ግን ምድረ ግብጽ ደረሰ።
✏በምድረ ግብጽም የጵጵስና ልብሱን ትቶ የመነኮሳትን አሮጌ ልብስ ለብሶ ሕዝቡንና መነኮሳቱን አስተማረ፤ አጸና። በየቦታውም ብዙ ተአምራትን ሠራ።
✏አባቶች መነኮሳትም ማንነቱን ባወቁ ጊዜ ሰገዱለት። ዶርታኦስ (ዱራታኦስ) በሚባል አንድ ደግ ሰው ቤትም በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ የካቲት ፲፬ ቀን ዐርፏል።
🚩 አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት የድንግል እመቤታችንን ጣዕሟን ፍቅሯን ያሳድርብን። የአበውን ሃብትና በረከትም አይንሳን።
🚩ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦
1.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
2.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቀ ጳጳሳት
3.አባ ያዕቆብ ሊቀ ጳጳሳት
4.ቅዱስ ዳርዮስ
5.ቅድስት ሊድና
🚩ወርኀዊ በዓላት፦
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
3.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
5.አባ ስምዖን ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት

❤1
✅ስንክሳር
🚩የካቲት 17
✅ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት ፣ ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ (ኁለተኛው)
✅ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት፦
✏ቅዱሳን ነቢያት እጅግ ብዙ ናቸው:: ከፈጣሪያቸው የተቀበሉት ጸጋም ብዙና ልዩ ልዩ ነው:: ያም ሆኖ ከሁሉም ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ይበልጣል:: መጽሐፍ እንደሚል ከእርሱም በፊት ቢሆን ከእርሱ በሁዋላ እንደ እርሱ ያለ ነቢይ አልተነሳምና:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
✏ዓለም በተፈጠረ በ3,600 ዓመት እሥራኤል በረሃብ ምክንያት 75 ራሱን ወደ ምድረ ግብፅ ወረደ:: በዚያም ልጆቹና የልጅ ልጆቹ ለ215 ዓመታት ተከብረው: ለ215 ዓመታት ደግሞ በባርነት: በድምሩ ለ430 ዓመታት በምድረ ግብፅ ኑረዋል::
✏በባርነት ዘመናቸውም 'ራምሴና ጋምሴ' የሚባሉ 2 ከተሞችን (ዛሬ ፒራሚዶች የምንላቸውን) ገንብተዋል:: ግፋቸው እየበዛ ሲሔድ ግን ጩኸታቸው ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰ:: ያድናቸውም ዘንድ አንድ ቅዱስ ሰው እንዲወለድ አደረገ:: ይኽም ሰው ሙሴ ይባላል::
✏ወላጆቹ መታመናቸውን በፈጣሪያቸው ያደረጉ 'እንበረም'ና 'ዮካብድ' ሲሆኑ ከሌዊ ነገድ ናቸው:: ከሙሴ ውጪም አሮንና ማርያምን ወልደዋል:: ቅዱስ ሙሴ በተወለደበት ወራት ወንድ የእሥራኤል ሕጻናት ይፈጁ ነበር:: ጌታ ግን በገዳዮቹ ልቡና ርሕራሔን አምጥቶ አትርፎታል::
✏በሁዋላም በ3 ወሩ ዓባይ ወንዝ ላይ ጥለውት ተርሙት (የፈርኦን ልጅ ናት) ወስዳ በቤተ መንግስት አሳድጋዋለች:: 'ሙሴ' ያለችውም እርሷ ናት:: 'ዕጉዋለ ማይ / እማይ ዘረከብክዎ' (ከውሃ የተገኘ) ለማለት ነው:: ወላጆቹ ያወጡለት ስም ግን 'ምልክአም' ይባላል:: ገና ሲወለድ ፊቱ እንደ መልአክ ያበራ ነበርና::
✏ቅዱስ ሙሴ 5 ዓመት በሆነው ጊዜ ፈርኦንን በጥፊ በመማታቱ ለፍርድ ቀርቦ እሳትን በመብላቱ አንደበቱ ኮልታፋ ሆኖ ቀርቷል:: እናቱ ዮካብድ ሞግዚት ሆና ስላሳደገችው 40 ዓመት በሆነው ጊዜ የፈርኦንን ቤት ምቾትና የንጉሥ ልጅ መባልን ናቀ:: ቅዱስ ዻውሎስ እንደሚለው በአሕዛብ ቤት ካለ ምቾት ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን ሊቀበል ወዷልና:: (ዕብ. 11:24)
✏አንድ ቀንም ለዕብራዊ ወገኑ ተበቅሎ ግብጻዊውን ገድሎት ወደ ምድያም ሸሸ:: በዚያም ለ40 ዓመታት የካህኑን ዮቶርን በጐች እየጠበቀ: ኢትዮዽያዊቱን ሲፓራን አግብቶ ኖረ:: ልጆንም አፈራ:: 80 ዓመት በሞላው ጊዜ እግዚአብሔር በደብረ ሲና ተናገረው:: ሕዝቡንም ከባርነት ቀንበር እንዲታደግ ላከው::
✏ቅዱስ ሙሴም ከወንድሙ አሮንና ከአውሴ (ኢያሱ) ጋር ግብጻውያንን በ9 መቅሰፍት: በ10ኛ ሞተ በኩር መታ:: እሥራኤልንም ነጻ አወጣ:: ሊቀ ነቢያት የሠራቸው ሥራዎች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም::
🚩እርሱ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ ሕዝቡን በደረቅ አሻግሯል::
*ግብጻውያንን ከነሠረገሎቻቸው በባሕር ውስጥ አስጥሟል::
*ለሕዝቡ መና ከደመና አውርዷል::
*ውሃን ከጨንጫ (ከዓለት) ላይ አፍልቁዋል::
*በብርሃን ምሰሶ መርቷቸዋል::
*በ7 ደመና ጋርዷቸዋል::
*ጠላቶቻቸውን ሁሉ ድል ነስቶላቸዋል::
✏ስለዚህ ፈንታ ግን ወገኖቹ ብዙ አሰቃይተውታል:: እርሱ ግን ደግ: ቅንና የዋህ ሰው ነውና ብዙ ጊዜ ራሱን ለእነሱ አሳልፎ ሰጥቷል:: "ሙሴሰ የዋህ እምኩሎሙ ደቂቀ እሥራኤል" እንዲል:: (ዘኁ. 12:3) ቅዱስ ሙሴ ለ40 ዓመታት ሕዝቡን ሲመራ ከእግዚአብሔር ጋር ለ570 ጊዜ ተነጋግሯል::
✏ከጸጋው ብዛትም ፊቱ ብርሃን ስለ ነበር ሰዎች እርሱን ማየት አይችሉም ነበር:: ታቦተ ጽዮንንና 10ሩ ቃላትን ተቀብሎ ጽላቱ ቢሰበሩ ራሱ ሠርቶ በጌታ እጅ ቃላቱ ተጽፈውለታል:: "የቀረው የቅዱሱ ሕይወት በመጻሕፍተ ኦሪት (በብሔረ ኦሪት) ውስጥ የተጻፉ አይደሉምን?"
✏እኔ ግን ደካማ ነኝና ይህቺ ትብቃኝ:: ቅዱስ: ክቡር: ታላቅ: ጻድቅ: ነቢይና ደግ ሰው ቅዱስ ሙሴ በ120 ዓመቱ ዐርፎ በደብረ ናባው ሊቃነ መላእክት ቅዱሳን ሚካኤል: ገብርኤልና ሳቁኤል ቀብረውታል:: መቃብሩንም ሠውረዋል:: (ይሁዳ. 1:9)
🚩አምላከ ሊቀ ነቢያት ደግነቱን አስቦ ከግራ ቁመት: ከገሃነመ እሳት ይሰውረን:: በረከቱንም አብዝቶ ያድለን::
🚩 ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት (በ120 ዓመቱ ደብረ ናባው ላይ ተቀብሯል)
2.ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ (ኁለተኛው)
🚩ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዘቆዽሮስ
4.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
5.አባ ገሪማ ዘመደራ
6.አባ ዸላሞን ፈላሢ
7.አባ ለትጹን የዋህ

🚩የካቲት 18
✅ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ፦
✏ቅዱስ ያዕቆብ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያደገ:
የአረጋዊው ቅ/ዮሴፍ የመጨረሻ ልጅ : በንጽሕናውና
ድንግልናው የተመሠከረለት : ከጸሎትና ገድል ብዛት እግሩ ያበጠ የመጀመሪያው የኢየሩሳሌም ኤዺስ ቆዾስ ሲሆን ቁጥሩም ከ72ቱ አርድዕት ነው::
✏ይህ ቅዱስ ሐዋርያ በአባቶቻችን ሐዋርያት መካከል
ትልቅ ሞገስ የነበረውና የጌታችን ወንድም ተብሎ የተጠራ ነው:: ቅዱስ ያዕቆብ ወላጅ አባቱ አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ (የእመቤታችን ጠባቂ) ሲሆን በልጅነቱ ጥላው የሞተችው
እናቱ ደግሞ ማርያም ትባላለች:: በቤት ውስጥም
ስምዖን ዮሳና ይሁዳ የተባሉ ወንድሞችና ሰሎሜ
የምትባል እህትም ነበረችው::
✏እናቱ ማርያም ከሞተች በሁዋላ ዕጉዋለ ማውታ (ደሃ
አደግ) ሆኖ ነበር:: ነገር ግን በፈቃደ እግዚአብሔር አረጋዊ ዮሴፍ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከቤተ መቅደስ ሊጠብቃት (ሊያገለግላት) ተቀብሎ ሲመጣ ያ ቤተሰብ ተቀየረ::
የበረከት: የምሕረትና የሰላም እመቤት
የአምላክ እናቱ ገብታለችና ያ የሐዘን ቤት ደስታ ሞላው::
✏እመ ብርሃን ግን ገና ወደ ዮሴፍ ልጆች ስትደርስ
አለቀሰች:: የአክስቷ ልጆች የሚንከባከባቸው አጥተው
ቆሽሸው ነበር:: በተለይ ደግሞ ትንሹ ቅዱስ ያዕቆብ
ያሳዝን ነበር:: እመ ብርሃን ማረፍ አልፈለገችም::
ወዲያው ማድጋ አንስታ ወደ ምንጭ ወርዳ ውሃ አምጥታ የሕጻኑን ገላ አጠበችው:: (በአምላክ እናት የታጠበ ሰውነት ምስጋና በጸጋ ይገባዋል!)
✏እመቤታችን ጌታ ከመወለዱ በፊት ለ9 ወራት: ከተወለደ በሁዋላ ደግሞ ለ2 ዓመታት ሕጻኑን ያዕቆብን
ተንከባከበችው::ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ግን ድንግል ማርያም አምላክ ልጇን ይዛ ተሰዳለችና ተለያዩ:: ከስደት መልስ ግን ለ25 ዓመታት ቅዱስ ያዕቆብ ከጌታችን ጋር ሲያድግ ወላጅ እናቱ ትዝ ብላው አታውቅም:: አማናዊቷ እናት ከጐኑ ነበረችና::
✏ሊቃውንት እንደ ነገሩን እመቤታችን ለቅዱስ ያዕቆብ
ያልሰጠችው ነገር ቢኖር ሐሊበ ድንግልናዌ (የድንግልና
ወተትን) ብቻ ነው::
ስለዚህም:-
"እመ ያዕቆብ በጸጋ ማርያም ንግሥተ ኩሉ" ይላል
መጽሐፍ:: (መልክዐ ስዕል)
✏ቅዱስ ያዕቆብ "የጌታ ወንድም" ተብሎ በተደጋጋሚ
በሐዲስ ኪዳን ተጠርቷል:: ለዚህ ምክንያቱ:-
1.ለ30 ዓመታት ሳይነጣጠሉ አብረው በማደጋቸው፡፡
2.የጌታችን የሥጋ አያቱ (የቅድስት ሐና) የእህት ልጅ
በመሆኑ፡፡
3.በዮሴፍ በኩልም የአንድ ቅድመ አያት ልጆች
በመሆናቸው፡፡
4.ጌታችን ከትህትናው የተነሳ ደቀ መዛሙርቱን
"ወንድሞች" ይላቸው ስለ ነበር ነው:: (ሥጋቸውን ተዋሕዶ
ተገኝቷልና)
✏ራሱ ቅዱስ ያዕቆብ ግን "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ነኝ" ብሎ በፈጣሪና በፍጡር መካከል ያለውን ልዩነት ገልጧል:: (ያዕ. 1:1) ቅዱስ ያዕቆብ ጌታችን ሲያስተምር ተከተለው::
*ከ72ቱ አርድእት ተቆጠረ
*3 ዓመት ከ3 ወር ወንጌልን ተማረ
*ለመጀመሪያ ጊዜ ከድንግል ማርያምና ከቅዱስ ዮሐንስ
ጋር ሆኖ "የጌታን ትንሳኤ ሳላይ እሕል አልቀምስም" ብሎ
ማክፈልን አስተማረ
*መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ወንጌልን አስተማረ
*የኢየሩሳሌም የመጀመሪያው ሊቀ ዻዻስ ሆኖ አገለገለ
*በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ዘመናት የሐዋርያት
ሲኖዶሶችን በሊቀ መንበርነት መራ
*ሙታንን አስንስቶ: ድውያንን ፈውሶ: የመካኖችን ማሕጸን
ከፍቶ: አጋንንትንም አስወጥቶ ብዙ ተእምራትን ሠራ::
እጅግ ብዙ አይሁዳውያንን ወደ አሚነ ክርስቶስ መልሶ
መልካሙን ገድል ተጋደለ::
✏በመጨረሻ ዘመኑ ያላመኑ የአይሁድ አለቆች ወደ ቤቱ ተሰብስበው "የናዝሬቱ ኢየሱስ ማነው? የማንስ ልጅ
ነው?" ሲሉ ጠየቁት:: እነርሱ ሰይጣን በሰለጠነበት
ልቡናቸው "የዮሴፍ ልጅ ነው: የእኔም ወንድሜ ነው"
እንዲላቸው ጠብቀው ነበር:: (ሎቱ ስብሐት ወአኮቴት!)
✏በልቡናቸው ያሰቡትን ተንኮል የተረዳው ሐዋርያ ወደ ቤቱ ጣራ ወጥቶ መናገር ጀመረ:: "ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ወልደ አብ ወልደ ማርያም: ሥግው ቃል: እግዚአብሔር ነው:: እኔም ፍጡሩና ባሪያው እንጂ እንደምታስቡት ወንድሙ አይደለሁም" አላቸው::
✏ንዴታቸውን መቆጣጠር ያልቻሉት አይሁድ ከላይ
ወጥተው ወደ መሬት ወረወሩት:: በገድል የተቀጠቀጠ
አካሉንም እየተፈራረቁ ደበደቡት:: አንዱ ግን ከእንጨት
የተሠራ ትልቅ ገንዳ አምጥቶ የቅዱሱን ራስ ደጋግሞ
መታው:: ጭንቅላቱም እንዳልነበር ሆነ:: ሰማዕቱ ሐዋርያ ቅዱስ ያዕቆብ ወደ ወደደው ክርስቶስ በዚህች ቀን ሔደ::
✏ቅዱሱ ሐዋርያ ያዕቆብ ቤቱን እንደ ቤተ መቅደስ አበው ሐዋርያት ይጠቀሙባት ነበር:: በመላ ዘመኑ የሚያገድፍ ነገር (ጥሉላት) ቀምሶ: ጸጉሩን ተላጭቶ: ገላውን ታጥቦና ልብሱን ቀይሮ አያውቅም::
"ወዝንቱ ጻድቅ እኅወ እግዚእነ::
ኢያብአ ውስተ አፉሁ ሥጋ ወወይነ::
ወኢገብረ ሎቱ ክልኤተ ክዳነ::" እንዲል::
✏ከጾም: ከጸሎትና ከመቆሙ ብዛትም እግሩ አብጦ
አላራምድህ ብሎት ነበር:: ስለዚህም አበው "ጻድቁ
(ገዳማዊው) ሐዋርያ" ይሉታል:: ቅዱሱ ሐዋርያ
"የያዕቆብ መልዕክት" የሚለውን ባለ 5 ምዕራፍ
መልዕክት ጽፏል::
🚩ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንድሙ ይባል ዘንድ
ካደለው ሐዋርያ በረከትን ያድለን:: በምልጃውም
ምሕረትን ይላክልን::
🚩ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦
1.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (የቅዱስ ዮሴፍ ልጅ : ከ72ቱ
አርድእት አንዱ)
2.ቅዱስ አባ መላልዮስ ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት (በአንጾኪያ
ሊቀ ዽዽስና ተሹሞ በአርዮሳውያን ብዙ ግፍ የደረሰበትና
በስደት ያረፈ አባት ነው)
🚩ወርሐዊ በዓላት፦
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ

👍4❤2