የቅዱሳን ታሪክ
9.29K subscribers
1.2K photos
13 videos
3 files
692 links
በዚህ ቻናል ውስጥ፦
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ የሚገኙ ስዕላትን
የቤተክርስቲያን ትውፊት የጠበቁ ስዕላት የአድባራት እና የገዳማት ፎቶዎችን ያገኛሉ


የተለያዩ ስዕለ አድዕኖ ለመላክ
@kidanemiherat_bot
Download Telegram
Audio
🌹🌹#ደብረ_ዘይት🌹🌹
መዝሙር ዘደብረ ዘይት (ጾመ ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ)

ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይትከወስ ኲሉ ኃይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኲሎሙ ኃጥአነ ምድር ወይወርድ እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ ወበ አዕላፍ መላእክቲሁ በንፍሐተ ቀርን ዘእምኀበ እግዚአብሔር ይምሐረነ አብ በይዕቲ ሰዓት እሞተ ኃጢአት እስመ ገባሬ ሕይወት ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት፡፡

ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ ተዘጋጅታችሁም ኑሩ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ እስከ መጨረሻው የጸና እርሱ ግን ይድናል የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ የሰማያትና የምድር ኃይላት ሁሉ ይናወጣሉ ያን ጊዜ በምድር ኃጢአት የአደረጉ ሁሉ ያለቅሳሉ አላቸው ጌታችንም ከባሕርይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ በመለከት ድምፅ ከአእላፍ መላእክት ጋር በግርማ መለኮቱ ከሰማይ ወደ ምድር ይወርዳል በዚች ዕለትም ከሞተ ኃጢአት አብ ይማረን የሕይወት ባለቤት የሰንበትም ጌታ ነውና።


🌹🌹#ምስባክ_ዘደብረ_ዘይት🌹🌹መዝ፡49፥3

እግዚአብሔርሰ ገኀደ ይመጽዕ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ

#ትርጉም
እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል
አምላካችን ዝምም አይልም
እሳትና ፍርድ በፊቱ ነዉና (ይነዳል)


🌹🌹#ምንባባት_ዘመጻጉዕ_ሰንበት🌹🌹

ገባሬ ዲያቆን 1ተሰ፡ 4፥13-ፍጻሜ
ንፍቅ ዲያቆን 2ጴጥ፡ 3፥7-15
ንፍቅ ካህን። ሐዋ፡ 24፥1-22

ወንጌል ማቴ፡ 24፥1-36
#ቅዳሴ_አትናቴዎስ
Forwarded from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ (Sador Sisay)
#ደብረ__ዘይት

ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ሲሆን ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ጥቂት ኪ.ሜ ራቅ ብሎ የሚገኝ ተራራ ነው።

በብሉይ ኪዳን ዘመን ዳዊት ከአቤሴሎም በሸሸ ጊዜ የደብረ ዘይትን አቀበት እንደ ወጣ እናነባለን 2ሳሙ፡ 15፥30

ዘሩባቤል ከሠራው ቤተ መቅደስ አደባባይ ደብረ ዘይት ሰባ አምስት ሜትር ገደማ ከፍ ብሎ ይገኛል ቤተ ፋጌና ቢታንያ የሚባሉት ታሪካውያን ቦታዎች ከደብረ ዘይት ግርጌ ይገኛሉ።

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሆሣዕና ዕለት ከደብረ ዘይት ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ገባ እናነብባለን። ማር፡ 1፥11

ጌታችን የጸለየበት ጌቴሴማኒ የሚባለው ቦታም ከደብረ ዘይት ሥር ይገኛል። ማቴ፡ 26፥30-36

ጌታችን ወደ ሰማይ ያረገው በደብረ ዘይት ላይ ነው ። ሉቃ፡ 24፥52፤ ሐዋ፡ 1፥12

መድኃኒታችን በደብረ ዘይት ተራራ በዓለም ፍጻሜ ዓለሙን ለማሳለፍ እንደሚመጣ ተተንብዮአል። ዘካ፡ 14፥4

መድኃኒታችንም ነገረ ምጽአቱን/ ዳግም ምጽአቱን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ በሰፊው አስተምሯል። ማር፡ 13፥3

በመሆኑም 5ኛው የዐቢይ ጾም ሰንበት የክርስቶስ ነገረ ምጽአት የሚታሰብበት የሚሰበክበት የሚዘመርበት ዕለት ስለ ሆነ በደብረ ዘይት ተሰይሟል ስያሜው የቅዱስ ያሬድ ነው።

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመቅደስ ወጥቶ ወደ ደብረ ዘይት በሄደበት ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ አጠገቡ ቀርበው ዘሩባቤል ያሳነጸውን የመቅደስ ግንቦች እያሳዩት ሳለ ‹‹እውነት እላችኋለሁ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም›› አላቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የኢየሩሳሌምን መፍረስ የእርሱን ዳግም መምጣት አስፍቶ አምልቶ ከነምልክቱ አስተማራቸው።


#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
Forwarded from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ (Sador Sisay)
#ደብረ_ዘይት

#ደብረ_ዘይት ከጌታችን ዘጠኙ ንዑሳን በዓላት መካከል ስምንተኛው ሲሆን በዚህ ዕለት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መምጣት ይታሰብበታል።

#ደብረ_ዘይት ማለት የወይራ ተራራ (የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ) ማለት ነው። ይህም ቦታ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ከቄድሮስ ሸለቆ ራቅ ብሎ የሚገኝ ተራራ ነው።

#ደብረ_ዘይት ጌታችን ዳግም የመምጣቱን ምልክት የገለጸበትና የዚህን ዓለም ተልእኮ ሲያጠናቅቅ ያረገበት ተራራ ነው። በዚህ ሰንበት የክርስቶስ ምጽአት የተነገረበት ከመሆኑ በተጨማሪ ክርስቶስ ይመጣል ተብሎም ይታመናል።

ማቴ. 24 ፥ 3 – 35፦ “ጌታችንም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀረቡና እንዲህ አሉት፦ 'ንገረን ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለሙ ፍጻሜስ ምልክቱ ምንድን ነው?'። ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ የሚያስታችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፡፡ ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርነትን የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፤ ተጠንቀቁ አትደንግጡ። ነገር ግን ፍጻሜው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣሉ። በየሀገሩም ረሃብ ቸነፈር የምድር መናወጥም ይሆናል። እነዚህ ሁሉ የምጥ መጀመሪያ ናቸው። ያን ጊዜም ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችኋልም። ስለ ስሜ በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። ያንጊዜም ብዙዎች ሃይማኖታቸውን ይለውጣሉ፣ እርስ በእርሳቸው አሳልፈው ይሰጣጣሉ፣ እርስ በእርሳቸው ይጣላሉ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያትም ይመጣሉ፤ ብዙዎችን ያስታሉ። ከዓመፅም ብዛት የተነሣ ፍቅር ከብዙዎች ዘንድ ትጠፋለች። እስከ መጨረሻው የሚታገስ ግን እርሱ ይድናል። በአሕዛብ ሁሉ ላይ ምስክር ሊሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ ያንጊዜም ፍጻሜ ይደርሳል።”

መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊትም ስለ ጌታችን ለፍርድ መምጣት ሲናገር “እግዚአብሔር ከክብሩ ውበት ግልጥ ሆኖ ይመጣል፤ ዝምም አይልም፤ እሳት በፊቱ ይነድዳል።” ይላል። (መዝ. 49 ፥ 2)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሁልጊዜ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ ሽሽታችሁም በሰንበት አሊያም በክረምት እንዳይሆንባችሁም ጸልዩ” ያለው ቃል በስፋትና በጥልቀት ይሰበካል። (ማቴ. 24 ፥ 20)

#ተዘጋጅታችሁ_ኑሩ፦ ማለት ጌታችን መቼና በምን ዓይነት ሰዓት እንደሚመጣ ስለማይታወቅ ሰው ሁልጊዜ በንስሐ ታጥቦ ሥጋ ወደሙን ተቀብሎ መኖር አለበት ማለት ነው። የጌታችን መምጣት ሲባል የመጨረሻው የፍርድ ቀን ብቻ ሳይሆን ነፍሳችን ከሥጋችን ተለይታ የምትሄድበትን ቀን ማሰብም ይገባል፤ ምክንያቱም ከሞት በኋላ ንስሐ መግባት ጽድቅን መሥራት አይቻልምና።

#ሽሽታችሁም_በሰንበት_እንዳይሆን፦ ማለቱ በአይሁድ ሕግ ሰንበት ከዘረጉበት ሳያጥፉ ካጠፉበትም ሳይዘረጉ ሳይለብሱና ሳይታጠቁ የሚውሉበት ቀን ነውና ስለዚህ እናንተ በሃይማኖት ጠንክራችሁ በንስሐ ታጥባችሁ ለሥጋ ወደሙ በቅታችሁ ኑሩ እንጂ እንደ አይሁድ ሰንበት ሳትለብሱና ሳትታጠቁ አትኑሩ ማለቱ ነው።

#በክረምትም_እንዳይሆን_ጸልዩ፦ ማለቱ ክረምት ከላይ ዶፍ እየወረደ ከታችም ምንጭ እየፈለቀ ምድር የምትጨቀይበት ጉምና ደመና ጭጋግና ጤዛ ከጭቃ ጋር አንድ ላይ ሆነው አሳዶ ለመያዝ ሩጦ ለማምለጥ የማይቻልበት ወቅት ነው። በዚህ ዓይነት በኃጢአት ጨለማ በወደቃችሁበትና በጨቀያችሁበት ወቅት እንዳትጠሩ ጸልዩ ማለቱ ነው። አንድም ክረምት ቅጠል እንጂ ፍሬ አይገኝበትምና በስመ ክርስቲያን ብቻ እየኖራችሁ ለመንግሥተ ሰማያት የሚያበቃ ፍሬ ሳታፈሩ የጌታ መምጫ እንዳይሆን ተጠንቀቁ ማለቱ ነው።

ስለሆነም በአጠቃላይ ይህ ሳምንት እነዚህንና መሰል ምሥጢራትን በስፋት የምንማርበት ነውና ይህ ምሥጢር የተገለጠበትን ቦታ መነሻ ተደርጎ ደብረ ዘይት ተብሎ ይጠራል።

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
Forwarded from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ (Sador Sisay)
#ደብረ_ዘይት_ምንድነው?

1. በዓል ነው (ጌታ በደብረ ዘይት ያስተማረው ትምህርት የሚተረጐምበት ዕለት ነው)
2. ዕለተ ምጽአት የሚታሰበብበት ዕለት ነው
3. በተለምዶ "እኩለ ጾም" የሚባልም ነው የጾሙ አጋማሽ ወይም ጾሙ እኩሌታ የሚሆንበት ነው

የምንመለከተው የ "ደብረ ዘይት" ን ወንጌል ነው

ደብረ ዘይት ማለት
• የወይራ ተራራ ማለት ነው
• በኢየሩሳሌም መቅደስ በስተምሥራቅ የሚገኝ ስፍራ ነው
• ጌታ 3 ዓመት ከ 3 ወር ያስተማረበት ተራራ ነው
• በተራራው ከተሰጡ ትምህርቶች ውስጥ ምሥጢረ ምጽአት ነው
• የማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 24 እና 25 በ ሐዋርያት 3 ጥያቄዎች ላይ የተመሠረተ መልስ የተሰጠበት ምእራፍ ነው ሁለቱም ምእራፎች የሚናገሩት ስለምጽአቱና ስለ መጨረሻው ፍርዱ ነው

• የሐዋርያት ጥያቄዎች እነዚህ ናቸው
1. ይህ መቼ ይሆናል (ማዕዜ ይከውን ዝ)
2. የመምጣትህ ምልክት ምንድነው? (ምንት ተአምሪሁ ለምጽአትከ)
3. የዓለም ፍጻሜ ምልክቱስ ምንድነው? (ወምንት ተአምሪሁ ለኅልፈተ ዓለም)

ጌታም በነዚህ ጥያቄዎች መሠረትነት አራት ዓይነት ምልክቶችን አስቀምጧል

1. ሃይማኖታዊ ቀውስ (ሐሰተኞች ክርስቶሶች ፣ ሐሰተኞች ነቢያት፣ ሐሰተኞች መምህራን)
2. ፖለቲካዊ ቀውስ (ጦርነት ፣መንግሥት በመንግሥት ላይ መነሣት)
3. ማኅበራዊ ቀውስ (ሕዝብ በሕዝብ ላይ መነሣት፣የፍቅር መቀዝቀዝ)
4. ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች (ረኀብና ድርቅ )

ምሥጢር
ደብረ ዘይት የቤተ ክርሰቲያን ምሳሌ ነው
• ወይራ ጽኑዕ ጠንካራ ነው
• ወይራ ኃይል የሚገኝበት
• ወይራ ቅብዐዘይት የሚገኝበት ነው
ቤተ ክርስቲያንም ጽኑዓን ኃያላን ነቢያት ሐዋርያት ካህናት ሊቃውንት መምህራን የሚገኙባት ደብረ ዘይት ናት
• ወዲህም በቅብዐ ሜሮን ልጅነት የሚገኝባት በቅብዐ ዘይት ኃይለ ፈውስ የሚገኝባት ቤተ ክርስቲያን ደብረ ዘይት ናት
ደብረ ዘይት ክርስቶስ 3 ዓመት ከ 3 ወር ያስተማረባት ያልተለያት ተራራ ናት ቤተ ክርስቲያንም ሙሽራዋ ክርስቶስ የማይለያት ደብረ ዘይት ናት
• በዚህች በደብረ ዘይት ቤተ ክርስቲያን የጌታን በምሕረት መምጣት እንጠብቃለን

ምልክቶቹን በማስተዋል ማንም እንዳያስተን በመጠንቀቅ እንድንኖር እስከመጨረሻውም ታግሠን እንድንድን አምላካችን ሁላችንንም ይርዳን!!!


#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏