፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
2.43K subscribers
2.86K photos
42 videos
355 files
172 links
ይህ የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ህጋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።
This is the official Channel of 6 kilo Gibi Gubae.
በግቢ ጉባኤው ላይ ያለዎትን አስተያየት ወይም ጥያቄ በ @fesehatsion12 ወይም @Hoping7 ላይ ይላኩልን።
Download Telegram
ሥርዓተ ጸሎት ሰሙነ ሕማማት ከሰኞ እስከ ዕሮብ ካህናት እያዜሙ እየሰገዱ እኛም እየተቀበልን እያዜምን የምንሰግድበትን ሥርዓት ለማውቅ እና ለመፈፀም ከስር ያንብቡ

❖ የጸሎተ ሐሙስና የዕለተ ዓርብ ሥርዓተ ጸሎት

👉 ከሰኞ ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ በመጀመሪያ ዲያቆኑ ቤተ ክርስቲያኑን ሦስት ጊዜ ዞሮ ደወል ካሰማ በኋላ መቶ አምሳው ዳዊት ይታደልና ይደገማል፡፡ የሰባት ቀናት ውዳሴ ማርያምና አንቀጸ ብርሃን እስከ ይዌድስዋ ድረስ ታድሎ ይደገማል፡፡ ከዚያም “እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ አግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም” ተብሎ አቡነ ይደገምና በዐራቱም ወንጌላት መሠረት ለእያንዳቸው በእየዕለቱና ሰዓቱ የተመደበውን አቡነ ካህናቱ በቀኝና በግራ እየተፈራረቁ ይመራሉ፡፡ ካህናቱና ሕዝቡም ይቀበላሉ፡፡ በመቀጠል፡- (ትእዛዝ፡ ሕዝቡ በጸሎት በተሰበሰቡ ጊዜ ጠዋት ወይም በ3፣ በ6፣በ9፣ በ11ሰዓተ መዓልት መጀመሪያ ሕዝቡ እየሰገዱና እየተከተሉ እንዲህ ይበሉ፡፡ )

✥ "ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም ፡፡"

✥ "አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡"

✥ " ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡ "
✥ " ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ፤ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኰቴት ፡፡"

ትእዛዝ፡ በዚህ ጊዜ ካህኑ እየተከተሉ አቡነዘበሰማያት ይድገሙ ።
ይህን የላይኛውን ጸሎት እያመላለሱ ከአቡነ ዘበሰማያት ጋር 12 ጊዜ ይበሉ

❖ " ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

❖ "ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለማሕየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለዕበዩ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖"ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ስለልጣኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

"ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለሕማሙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡ "

ትእዛዝ፡- ይህ ሦስት ጊዜ እየተመላለሰ ይባላል፡፡በመጨረሻም የሚከተለውን ሦስት ጊዜ እያመላለሱ ይበሉ፡፡

❖ "ለከ ይደሉ ኃይል፣ ወለከ ይደሉ ስብሐት ወለከ ይደሉ አኰቴት ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም"

ትእዛዝ፡- ካህኑ ‹ጸልዩ በእንተ ጽንዓ ዛቲ . . .› ብሎ በሚያነብ ጊዜ በየምዕራፉ "እግዚኦ ተሳሃለነ" እየተባለ ይሰገዳል፡፡

ትእዛዝ፡- ከዚህ ሁሉ በኋላ ሕዝቡ የሚከተሉትን ጸሎት በግራና በቀኝ ይበሉ፤

"ክርስቶስ አምላክነ፤ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ በሕማማቲሁ ቤዝወነ፤ ንሰብሖ ወናልዕል ስሞ ኅቡረ፤ እስመ ውእቱ ገብረ መድኃኒተ በዕበየ ሣህሉ" (በዐርብ) ዘሐመ ወሞተ በእንቲአነ ይባላል፡፡

ትእዛዝ፡- ቀጥሎም ሕዝቡ በሁለት ክፍል ሆነው የሚከተለውን ጸሎት ሁለት ጊዜ በመከታተል አንድጊዜ በማስተዛዘል ይበሉት፡፡

ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤#ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#አብኖዲ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን

#ናይን፣ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን ፤

#ታዖስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ማስያስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ኢየሱስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ክርስቶስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#አማኑኤል ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ትስቡጣ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን

ትእዛዝ፡- ከዚህ በኋላ ኪርያላይሶን አርባ አንድ ጊዜ ይባላል፡፡

ይኸውም በአንድ ወገን 20 ጊዜ በሌላው ወገን 21 ጊዜ በጠቅላላው 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን እየተባለ ይሰገዳል፡፡

በመጨረሻ ጊዜ፡-

✥ ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ (እናመልከው ዘንድ ለፈጠረን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል)፡፡

✥ ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግእዝትነ ወመድኃኒትነ (እመቤታችንና መድኃኒታችን ለሆነች ለአምላክ እናት ለማርያም ምስጋና ይገባል)፡፡

✥ ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወፀወንነ(ኃይላችን መጠጊያችን ለሆነ ድኅነት ለተገኘበት ለክርስቶስ ምስጋና ይገባል)፤፤ ጸሎተ ሃይማኖትን ሐመ እስከ ሚለው ድረስ መድገም ነው፡፡ /ከሰኞ እስከ ረቡዕ ይባላል/

#ሼር
የእግዚአብሔር ምህረትን የምናገኝበት ስምንት ይሁንልን!!!

https://t.me/SidistKiloGibiGubae
ሰላም ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንኳን ለህማማቱ በሰላም አደረሰን እንዲሁ ደግሞ ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም ያድርሰን።

እየሱስ ክርስቶስ ቤቴ የእግዚአብሔር ቤት ተብላ ትጠራለች እናንተ ግን መነገጃ አደረጋችሁት ብሎ ሲነግዱ የነበሩትን አስወጣቸው።

ሰኞ:- አንጽሖተ ቤተ መቅደስ እና መርገመ በለስ

በለስ-ቤተ እስራኤል ናት-
ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባርን አላገኘባቸውምና።

የ፮ኪሎ ግቢ ጉባኤ
          📲Join & Share👥
                   👇👇👇
  Telegram @SidistKiloGibiGubae
YouTube https://youtube.com/@6Kilogbigubae?si=JPyZjTwMFI-i2HxR
Forwarded from Biruk T.
ውድ የግቢ ጉባኤያችን ተማሪዎች ለመጪው የትንሳኤ በዓል ዋዜማ ለማኖረን መርኃ ግብር ዝግጅት በዲኮር ሞያ ማገዝ የምትችሉ በ @Ameram04 ላይ በመመዝገብ ለወንጌል አግልግሎቱ የድርሻችሁን በመወጣት የትንሳኤው በረከት እንደትሳተፉ በታላቅ ትህትና ተጋብዛቹሀል።
የትንሳኤ በዓል ዝግጅት ኮሚቴ
ጥያቄ ፦

፩ . በስሙነ ሕማማት ማማተብ ፣ ማዕድ መባረክ ፣ መልክዐ መልክ መድገም አይፈቀድምን?


፪ . ሰሙነ ሕማማት ከገባ ጊዜ ጀምሮ ማማተብ ፣ ማዕድም ሲቀርብ ባርኮ መቁረስና ስለ እነሱ ብሎ ቡራኬ መስጠት የተከለከለ ነው ይባላል፡፡ ትክክል ነውን? ለምን?

፫ . በተጨማሪም መልክዐመልኮች አይደገሙም ፣ የሃይማኖት ጸሎት ሲደገም "ስለኛ ተሰቀለ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ ሞተ ተቀበረ  በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ..." እስከሚለው ድረስ ከሰኞ እስከ ሐሙስ አይደገምም ይዘለላል ምክንያቱ ምንድን ነው?

-----------------------------------------------

[      ምላሽ     ]

- ማማተብ !

ይህ የሚያመለክተው በጉባዔ ፣ በአደባባይ ፣ በይፋ የሚደረገውን ነው፡፡ በብዙኃን ፊት ቡራኬ መስጠት ፣ የሞተ መፍታት ፣ መስቀል ማሳለም አይፈቀድም፡፡ ይህም ፭ ሺህ ፭ መቶ ዘመን ዓለም በማእሠረ ሰይጣን እንዳለ ፣ በግዞት በመርገም ውስጥ እንደነበረ ለማስታወስ ነው እንጂ ማዕዳችሁን አትባርኩ የሚል ሥርዓት አልተደነገገም፡፡

በግሉ አንድ ሰው ፊቱን በትእምርተ መስቀል አማትቦ መጸለይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰው ካላማተበ የአጋንንትን ውጊያ ድል መንሣት አይችልም፡፡ ስለዚህ በግል ጸሎት አታማትብ አይባልም፡፡ አይከለከልም፡፡

-  ጸሎት !

የሃይማኖት ጸሎትም ሲደገም ፦ "ስለ እኛ ተሰቀለ ፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ ፣ ሞተ ፣ ተቀበረ ፣ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ" እስከሚለው ድረስ ከሰኞ እስከ ሐሙስ አይደገምም "ሐመ" ብለው ይተውታል፡፡ ይሄ ታሪኩን ለማስታወስ ነው፡፡ ጸሎቱ የሚከለከል ሆኖ አይደለም፡፡ ወቅቱን እየጠበቅን ድርጊቱን ለማስተማር ነው፡፡ ይኸውም ሰኞ ፣ ማክሰኞ ፣ ረቡዕ ፤ ሐሙስ መከሩ ከሐሙስ እስከ ዓርብ ሌሊት መከራውን ተቀበለ ፤ ዓርብ ስድስት ሰዓት ላይ ተሰቀለ እንላለን ፤ ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ "ሞተ ተቀበረ" ይባላል፡፡ "ተነሣ" የምንለው ደግሞ ቅዳሜ በሌሊት ስድስት ሰዓት ነው፡፡ ያንን በየሰዓቱ የተደረገውን ታሪክ ለማስታወስ ፣ ለመግለጽ ፣ ለማስተማር ነው፡፡

መልክዐ መልኮች አለመደገማቸው ደግሞ ወደ ነገረ መስቀሉ ለማድላት ነው፡፡ ነገረ መስቀሉ ከሁሉ በላይ ነውና፡፡ ዓለም የዳነው በጌታችንና በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካሳነት ነው ፤ ይህንን የምናስታውስበት በስሙነ ሕማማት የእርሱን ካሳነት በፍጹም ተመስጦ እናስባለን እንጸልያለን፡፡ በዚህ ወቅት በቂ ጊዜ ስለማይኖር ወደ ቅዱሳን ገድል ትሩፋት ድጋም [ጸሎት ፣ ንባብ] አንሄድም፡፡

ነገር ግን ጊዜ ከተገኘ በሕማማት ቢሆን የቅዱሳንን ገድሎች እናነባቸዋለን፡፡ የሰዓት ቁጠባ ነው እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት የለውም፡፡ ግብረ ሕማማቱ እራሱ በየሰዓቱ የተዘጋጀ የራሱ ጸሎት አለው፡፡ በእረፍት ሰዓት ግን ገድሎችንም ሆነ ስንክሳርን እናነባለን፡፡ ከሰዓት አንጻር የሚታይ ነው፡፡ ወደ ነገረ መስቀሉ ለማድላት ሕማሙን ሞቱን መከራውን ለእኛ ያደረገውን ካሳ በስሙነ ሕማማት በፍጹም ልቡና ለማሰብ ቅድሚያ ለእርሱ እንዲሰጥ ነው፡፡

የ፮ኪሎ ግቢ ጉባኤ
          📲Join & Share👥
                   👇👇👇
  Telegram @SidistKiloGibiGubae
  YouTube https://youtube.com/@6Kilogbigubae?si=JPyZjTwMFI-i2HxR
#ማክሰኞ
#የጥያቄ_ቀን_ይባላል
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

#የትምህርት_ቀን_ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።

የ፮ኪሎ ግቢ ጉባኤ
          📲Join & Share👥
                   👇👇👇
           Telegram @SidistKiloGibiGubae
  YouTube https://youtube.com/@6Kilogbigubae?si=JPyZjTwMFI-i2HxR
፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
በ2016_ዓ_ም_ለመጽሔት_የተመለመሉ_ተማሪዎች.pdf
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ከላይ በዝርዝሩ ላይ የተመዘገባችሁ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ ነገ ማክሰኞ ሚያዚያ 22:2016 ዓ.ም ከሰዓት 7 ሰዓት ጀምሮ እና ረቡዕ ሚያዚያ 23:2016 ዓ.ም ጠዋት 3 ሰዓት ጀምሮ ፎቶ እንድትነሱ እያሳሰብን

‼️‼️‼️‼️ፎቶ ለመነሳት የሚከተሉትን ማሳሰቢያዎች መተገበር ይጠበቅባችኋል።‼️‼️‼️‼️

➡️ ፎቶ የምትነሱት ምስካየ ኅዙናን  መድኃኔዓለም ገዳም ፊት ለፊት አለው ትልቁ ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ፍቃዱ ፎቶ ቤት ነው
➡️ ለፎቶ እና ለመጽሔት በአጠቃላይ 120 ብር መክፈል ይጠበቅባችኋል።
➡️ፎቶ ከተነሳችሁ በኋላ የፎቶ ኮድ መቀበል እና መያዝ ስትጠየቁ ማቅረብ ግዴታ ነው።
➡️ ከላይ ከተቀመጠው ዝርዝር ውስጥ ስማችሁ ከሌለ አሳማኝ ምክንያት በመያዝ ቅሬታ ማቅረብ ትችላላችሁ። ከዛ ውጪ ፎቶ ብትነሱም መጽሔት ላይ አትገቡም።
➡️ ለፎቶ የሚያገለግል ጋውን፣ ነጠላ እና መስቀል እዛው የሚኖር ይሆናል።

ማሳሰቢያ በተጠቀሱት ሁለት ቀናት ፎቶ ተነስቶ የፎቶ ኮድ ማቅረብ ለማይችል ተማሪ ኮሚቴው ኃላፊነቱን አይወስድም!

ከላይ ካለው ዝርዝር ውስጥ የሌለ ተማሪ ረቡዕ ጠዋት ከ4:00-6:30 ወይም ሐሙስ ከ3:30- 5:00 ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን በሚገኘው 6 ኪሎ ግቢ ጉባኤ ጽ/ቤት የቅሬታ ወረቀት ማስገባት ትችላላችሁ።
በተጨማሪም
ዋና ግቢ
+251920009082
FBE ግቢ
+251967015381 በማንኛውም ሰዓት በመደወል ቅሬታ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ የG.C ኮሚቴ
ረቡዕ
የምክር ቀን
ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍትጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማቴ. 26÷1-14፣ ማር. 14÷1-2፣ ሉቃ. 22÷1-6) የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡
የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል
ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት "ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ" ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ረቡዕ የመዓዛ ቀን ይባላል፡፡
የእንባ_ቀንም_ይባላል
ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና። (ማቴ. 26÷6-13፣ ማር. 14÷9፣ ዮሐ. 12÷8)
📣📣📣አዋጅ!📣📣📣

🔔 "እንግዲህ ከቅዱስ ቁርባን ተሳትፈን፤
እሳት እንደሚያገሳ አንበሳ ለዲያብሎስ አስፈሪ ሆነን እንመለስ።"🥰
(ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ)

እግዚአብሔር ቢረዳን በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት  ቅዱስ ቁርባን የመቀበል መርሐግብራችን እነሆ ደረሰ!🥰

📌መቼ?:- ነገ የጸሎተ ሐሙስ/የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ/አረንጓዴው ሐሙስ/ትዕዛዘ ሐሙስ እየተባለች ለምትጠራዋ ክርስቶስ አምላካችን ምስጢረ ቁርባንን በመሰረተባት ዕለት



🔔"ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር ንትፈሣሕ ወንትሐሰይ ባቲ"

🍁 የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ጉዳዩ አዲስ እንደሆነ አናስብ እናታችን ቤተ ክርስቲያን ሁሌም የምታደርገው ጥሪ ነው! የሚበላ የሚጠጣ ብታጣ እንኳን የማትተወው ግብዣ ነው! ሙሽራው የሚታረድበት ብቸኛው ሠርግ ነው !

ቦታ:- ምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም
ሰአት:- ከቀኑ 5:00 ጀምሮ

በዕለቱ :ስጋወደሙን ተቀብለው ለሚወጡ ልጆች አፋቸውን አፍነው ወደ ግቢ እንዳይመለሱ ግቢ ጉባኤው ያዘጋጀው ማቁረሪያ ስላለ ሁሉም በዕለቱ የተዘጋጀውን እየቀመሰ ወደ ግቢ መምጣት ይችላል!!!
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

ክርስቲያን የሚጀምር ብቻ ሳይሆን የሚፈጽም ነው! አደራ ወደኋላ እንዳንል🙏

🔔 “እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።”ዮሐ 6፥63

🤲 እግዚአብሔር እንዲያከናወንልን ጸሎትን አናስታጉል።


፮ኪሎ ግቢ ጉባኤ
ከመቀበል በፊት

አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ርኲስ ከሆነች ከቤቴ ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባህ አይደለህም። እኔ በዚህ ዓለም አሳዝኜሃልሁና በፊትህም ክፉ ሥራ ሥርቻለሁና፣ በአርኣያህና በአምሳልህ የፈጠርከው ነፍሴንና ሥጋዬን ትእዛዝህን በማፍረስ አሳድፌኣለሁና፣ ሥራ ምንም ምን የለኝምና፣ ነገር ግን ስለ መፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰው ሰለመሆንህ፣ ስለክቡር መስቀልህም ማሕየዊ ስለሚሆን ስለሞትህም፣ በሦስተኛው ቀን ስለመነሣትህ፣ ጌታዬ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከበደልና ከመርገም  ሁሉ ከኃጢያትና ከርኲሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፣ እማልድሃለሁም። የቅድስናህንም ምሥጢር በተቀበልሁት ጊዜ ለወቀሳና ለምፈራረጃ አይሁንብኝ፣ ማረኝ ይቅርም በለኝ እንጂ።
የዓለም ሕይወት ሆይ በርሱ የኀጢያቴን ሥርየት የነፍሴንም ሕይወት ስጠኝ እንጂ። በሁለት ወገን ድንግል በምትሆን በወለደችህ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም በመጥምቁ በዮሐንስ አማላጅነት ክቡራን በሚሆኑ በመላእክት፣ በሰማዕታት ለበጎ ነገር በሚጋደሉ በጻድቃን ሁሉ ጸሎት እስከዘላለሙ ድረስ አሜን።

በሚቀበሉ ጊዜ የሚጸለይ ጸሎት

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይህ ምሥጢርህ በእኔ በደል አይሁንብኝ ሥጋዬንና ነፍሴን ለማንጻት ይሁንልኝ እንጂ። ወይም ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሥሉስ የሚለውን ምሥጋና በቃል ይዞ ማመስገን ነው።

ከተቀበሉ በኋላ የሚጸለይ ጸሎት

ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ቅዱስ ሥጋህንና ክቡር ደምህን እነሆ ተቀበልሁ። ለኀጢያቴ ማስተሥረያ ይሁንልኝ ስለ በደሌም ሁሉ።
ሰውን የምትወድ ውልድ ዋሕድ ሆይ ምስጋናህን በአንደበቴ ሙላ። ምስጋናህን አመሰግን ዘንድ ቀድሞ አንተ ሰው የሆንክ በሱም የተግለጽህ አስከዘላለሙ ታድነኝ ዘንድ ነውና፣ ስለቅዱስ ስምህም ለዘላለሙ አዳንከኝ። ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በአግልጋይህ በዚህ ካህን እጅ ሥጋህንና ደምህን አንድ አድርገህ ስለሰጠኸኝ ለአንተ ምስጋና ይገባሃል፤ አመሰግንሃለሁ፤ እለምንህማለሁ። 
ከምዕመናን ጋር አንድ እሆን ዘንድ ከወዳጆችህም ጋር ትቆጥረኝ ዘንድ ተቀበለኝ አሁንም ኀጢያቴን አትቁጠርብኝ፤ ለኔ ስለሰጠኸኝ ፀጋህና በኔ ስላለችው ረድኤትህ አመሰግንሃለሁ።https://youtube.com/@6Kilogbigubae?si=JPyZjTwMFI-i2HxR
ጸሎተ ሐሙስን ከግቢ ጉባዔያችን ጋር

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንኳን ለጸሎተ ሐሙስ አደረሳችሁ እያልን ግቢ ጉባኤያችን ልዩ የሆነ መርኃ ግብር አዘጋጅቷል!

በዕለቱ የሚኖሩ መርኃ ግብራት
➡️ መዝሙር
➡️ ትምህርተ ወንጌል
➡️ ሥነ -ጽሑፍ
➡️ ሕጽበተ እግር
➡️ ጉልባን

ስለሆነም ነገ ሐሙስ ሚያዚያ 24:2016 ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን 3ኛ ወለል ምሽት 11:00 ጀምሮ ተገኝው የመርኃ ግብሩ ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል!

የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባዔ

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ የግቢ ጉባዔያችን አባላት እንደምን ናቸሁ።



የቅዳሜ ስዑር ዕለት የምታከፍሉ የግቢ ጉባዔያችን ዓባላት በሙሉ የቅዳሜ ምሳችሁን ለነድያን ለማውጣት እና ለማስፈሰክ ስለታሰበ የምታከፍሉ ተማሪዎች በዚህ @Mi121919
➡️ ስም
➡️ መመገቢያ ቁጥር እና
➡️ ካፌ
በመላክ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን ።

©የ፮ ግቢ ጉባዔ ሙያና በጎ አድራጎት ክፍል
ጸሎተ ሐሙስን ከግቢ ጉባዔያችን ጋር

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንኳን ለጸሎተ ሐሙስ አደረሳችሁ እያልን ግቢ ጉባኤያችን ልዩ የሆነ መርኃ ግብር አዘጋጅቷል!

በዕለቱ የሚኖሩ መርኃ ግብራት
➡️ መዝሙር
➡️ ትምህርተ ወንጌል
➡️ ሥነ -ጽሑፍ
➡️ ሕጽበተ እግር
➡️ ጉልባን

ስለሆነም ነገ ሐሙስ ሚያዚያ 24:2016 ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን 3ኛ ወለል ምሽት 11:00 ጀምሮ ተገኝው የመርኃ ግብሩ ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል!

የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባዔ
ሰላም ለናንተ ይሁን በክርስቶስ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን  በዛሬው እለት በምስካዬ ህዙናን ተገኝታችሁ በእግዚአብሔር ቸርነት ከክርስቶስ ምሥጢረ ቁርባን የተሳተፋችሁ ሁላችሁም አፋችሁን ሳታድፉ እንዳትወጡ ቦታ ትንሿ ክርስትና ቤት ምስካዬ ህዙናን ቦታው ከጠፋባችሁ 0912920081ደውላችሁ እንድትጠይቁ በትህትና እናሳውቃለን

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ የግቢ ጉባዔያችን አባላት እንደምን ናቸሁ።



የቅዳሜ ስዑር ዕለት የምታከፍሉ የግቢ ጉባዔያችን ዓባላት በሙሉ የቅዳሜ ምሳችሁን ለነድያን ለማውጣት እና ለማስፈሰክ ስለታሰበ የምታከፍሉ ተማሪዎች በዚህ @Mi121919
➡️ ስም
➡️ መመገቢያ ቁጥር እና
➡️ ካፌ
በመላክ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን ።

©የ፮ ግቢ ጉባዔ ሙያና በጎ አድራጎት ክፍል
ወየው ወየው ወየው

❖  "አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ፡ #ወዮ

❖  በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ፡ #ወዮ

❖ በአዳም ፊት የህይወት መንፈስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋራ የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ ፡ #ወዮ

የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምን አንደበት ነው? የፍቅር ጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ፡ ህሊናም ይመታል ፡ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች ፡ ስጋም ይደክማል፡፡

የማይሞተው ሞተ ፡ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ፡ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ ፤ የምትወዱት ሰወች ፈፅሞ አልቅሱለት ፤

❖ ወየው ወየው ወየው አማኑኤል አምላካችን፡፡

❖ ወየው ወየው ወየው መድሃኒታችን ኢየሱስ ፤

❖ወየው ወየው ወየው ንጉሳችን ክርስቶስ ፤

❖ ወየው ወየው ወየው ፃድቃን ከእንጨት አወረዱት ስጋውንም ለመገነዝ ከርቤ የሚባል የጣፈጠ ሽቱንና ንፁህ በፍታን አመጡ፡፡

ሞተም ተቀበረም ፤ ሙስና ሳይኖርበት ከሙታን ተለይቶ ፈፅሞ ተነሳ ፤ ከሃጢአት ቀንበርም ነፃ አደረገን ፤ በዚያች ስጋ በመለኮት ሃይል ወደ ሰማይ ወደ ቀደመ አኗኗሩ አረገ፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ