Shewa Educational Channel
8.94K subscribers
1.12K photos
18 videos
2.27K files
312 links
የዚህ ቴሌግራም ዋናው ዓላማ ተከታዮቹን ትምህርታዊና ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎች ለህብረተሰቡ የሚለቀቅበት ገጽ ሲሆን በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ከሚለቁት መረጃዎች መካከል፦
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን የመሳሰሉት ይገኙበታል።እርሶም ይህንን ቻናል ሼር በማድረግ ያጋሩ
Download Telegram
Natural or Social ናቹ?
5+5×5-5 = ?
ተማሪ ናቹ?
የቋቁቻ መንስኤዎችና መፍትሄዎቹ | Pityriasis Versicolor

የቋቁቻ መንስኤ እና መፍትሄዎች
ቋቁቻ ማላሴዚያ (Malassezia) በሚባል የፈንገስ ዓይነት የሚመጣ ሲሆን፤ አብዛኛውን ጊዜ ወጣቶችን የሚያጠቃ በሽታ ነው።
ይህ የፈንገስ አይነት በሁላችንም ሰዉነት የሚገኝ ሲሆን፤ ለምን አንዳንድ ሰዎች ላይ ብቻ በሽታዉን እንደሚያመጣ በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር የለም።
ይህ በሽታ ገርጣ ገርጣ ወይም ጠቆር ጠቆር በሚሉ የቆዳ ለውጦች ተለይቶ ይታወቃል።
አብዛኛውን ጊዜ ደረትና ጀርባን የሚያጠቃ ሲሆን፤ አልፎ አልፎ ፊት፣ እጅና እግርን ሊያጠቃ ይችላል።
ቋቁቻ በአብዛኛው በሞቃታማ የአየር ሁኔታ ወይም የአየር ንብረት የሚከሠት ሲሆን በይበልጥ ወንዶችን ያጠቃል።
አብዛኛዉን ግዜ ምልክት ባይኖረዉም አንዳንድ ግዜ ግን ልያሳክክ ይችላል፤ ይሁንና ቋቁቻ ከሰዉ ወደ ሰዉ አይተላለፍም።
ቋቁቻ በብዛት ሊከሰት የሚችል ከሰዉ ወደ ሰዉ የማይተላለፍ በፈንገስ ምክንት የሚመጣ የቆዳ
ላይ ችግር ነው።
ፈንገሱ የቆዳ ተፈጥሮዊ መልክን በማሳጣት ትናንሽ፣ ነጣ ወይም ጠቆር ያሉ መልካቸዉን የለወጡ ነገሮች በቆዳ ላይ እንዲወጡ ያደርጋል፡፡
ሞቃታማ እና እርጥበት አዘል የአየር ፀባይ፣ ወዛማ ወይም ቅባታማ ቆዳ ካለዎት፣ የሆርሞን ለውጦች፣ የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅም መዳከም ቋቁቻ እንዲከሰት የሚያደርጉ ሁኔታዎች ሲሆኑ፤ ቋቁቻን በሚቀቡ እና በሚዋጡ የተለያዩ መድሃኒቶች ማከም ይቻላል።
ሆኖም ግን ሁኔታዎች ሲመቻቹለት ቋቁቻ የመመለስ ወይም የማገርሸት ባህሪ አለው።
የቋቁቻ ሕክምና
ቋቁቻ በፈንገስ ምክንያት የሚመጣ የቆዳ ችግር ስለሆነ የሚከተሉት መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡
የተወሰኑት መድሃኒቶች በቆዳ ላይ ሊቀቡ የሚችሉ ሲሆን ቀሪዎቹ የሚዋጡ ናቸው።
1️⃣ የፍሉኮናዞል እንክብል ወይም ፈሳሽ መድሃኒት።
2️⃣ ኢትራኮናዞል (እንክብል፣ ካፕሲዩል ወይም ፈሳሽ)።
3️⃣ ኬቶኮናዞል (ክሬም፣ ጄል ወይም ሻንፖ) ናቸው።
ምንም እንኳን ህክምናዉን በደንብ ቢከታተሉትና ህመሙ ቢሻልዎትም ለሳምንታት ወይም ለወራት የቆዳዎ ቀለምዎ ሳይለወጥና እንደሻከረ ሊቀጥል ይችላል፡፡
አንዳንዴ ደግሞ ህመሙ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል (በተለይ በሞቃታማና እርጥበታማ የአየር ፀባይ ወቅት)፡፡
ስለሆነም ኢንፌክሽኑ ተመልሶ እንዳይመጣ መድሃኒት በወር አንድ ወይም ሁለት ጊዜ መውሰድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
መልካም ጤንነት!!
ጠቃሚ መረጃ ነውና ለወዳጆችዎ ያካፍሉ
ምንጮች | Sources
Health line, NIH & WHO.
ጽሑፉን ከወደዱት (Like) በማድረግ ለሌሎችም (Share) ያድርጉት፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/addlist/3tl-9Fg37Io2MzM0
https://t.me/addlist/3tl-9Fg37Io2MzM0
#ጥብቅ መረጃ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለግለሰቦች እንዲሁም ለተቋማት በቆሻሻ አወጋገድ ዙሪያ እንዲሁም ሌሎች ህገወጥ ተግባራት በሚያከናውኑት ላይ አዲስ የተሻሻሉ የቅጣት እርከኖችን ይፋ አደረገ!!
በዚህም መሠረት :-
🎯ማንኛውም ሰው ያመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በግቢው ውስጥ በአግባቡ አለመያዝ፤በዓይነት አለመለየት፤ ማዝረክረክ፤ ለጤናና የአካባቢ ገጽታ በሚጎዳ መልኩ ማከማቸት፤ ለግለሰብ ብር 2 ሺህ ድርጅት 50 ሺህ ብር

🎯ማንኛውም የጽዳት አገልግሎት ሰጭ ድርጅት/ማህበር ደረቅ ቆሻሻ ሲሰበስብ ገጽታ ካበላሸ ብር  25000.00

🎯በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ለደንበኛው ተገቢውን አገልግሎት ካልሰጠ ብር 50,000.00

🎯ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እውቅና ውጭ የአገልግሎት ክፍያ ከደንበኛው ከተቀበለ ብር 50,000.00

🎯ጊዜያዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስቀመጫ ቦታዎችን እስከ 5 ሜትር ዙሪያ ድረስ ጽዱ ካላደረገ ብር 50,000.00

🎯ማንኛውም በመንገድ የሚንቀሳቀስ ሰው የሲጋራ ቁርጥራጭ፣ የሶፍት ወረቀት፣ ፌስታል፣ የጫት ገለባ፣ የፍራፍሬ ተረፈ-
ምርቶች፣የትራንስፖርት ቲኬት፣የሞባይል ካርዶችን፣ የማስቲካና ከረሜላ ሽፋኖች፣ የመሳሰሉት ጥቃቅን ደረቅ ቆሻሻን ባልተፈቀደ ቦታ ወይም በፓርኮች፣ በአረንጓዴ ቦታ፣ በኮሪደር ከጣለ ብር 2000.00

🎯ከመኖሪያ ቤት ወይም ከድርጅት ግቢ ውጭ ያለውን የአካባቢ ንጹህና አረንጓዴ አድርጎ አለመጠበቅ ከመኖሪያ ቤት አጥር ግቢ ውጭ እስከ 5 ሜትር ርቀት አለማጽዳት፤ ብር 20000.00

🎯ከድርጅት/ተቋም አጥር ግቢ ውጭ እስከ 10 ሜትር አለማጽዳት፤ብር 100,000.00

🎯ወቅታዊና ልዩ ዝግጅት አከናውኖ በዓሉ ሲጠናቀቅ በዕለቱና ወዲያው ዝግጅቱ የተከናወነበትን አካባቢ ከቆሻሻ ያላጸዳ
የፕሮግራሙ አዘጋጅ፤ ብር 50,000.00

🎯ዓመታዊ፤ ወርሃዊና ሳምንታዊ የእምነት በዓላት ሲከናወኑ ዝግጅቱ ሲጠናቀቅ  የዝግጅቱ ባለቤት በዕለቱና ወዲያው አካባቢውን ካላጸዳ፤ብር 20,000.00 የሚቀጡ መሆኑም ተመላክቷል።
Natural or Social ናቹ?
የአዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር_የወንዞች_ዳርቻ_ልማት_እና_ብክለት_መከላከል_ደንብ_ቁጥር.pdf
992.3 KB
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 12/2017 ዓ.ም