ለንግድዎ አሪፍ መላ
👍👍👍👍
አፕ ነው
👇👇👇👇👇👇👇
በመጀመሪያ
👉 https://cashbooket.com ሊንኩ ነው።
👉 ክፈተው Register ንካ የተጠየቅከውን ሙላ።
👉 በቴሌግራም በመጣልህ username and Password ግባ።
1ኛ, የሱቅህን ስም እንደ ቢዝነስ መዝግብ
ከዛስ?
2ኛ, በስራ ቦታ ያሉህን ደብተሮች
ለምሳሌ የግዢ፣የዱቤ(የገዛህበት)፣ የወጪ ደብተሮችህን በቢዝነሱ ስር ትፈጥራላህ
በእያንዳንዱ ደብተር እየከፈትክ ገቢ ወጪ መፅሐፍ
ከዚያማ
👌👌👌👌👌👌👌
ማስታወሻ ሁሉ በጄ ሁሉ በደጄ
ቀሪ ባላንስ ብትል፤
ጠቅላላ ወጪ፤
ያለኝ ብትል ያለብኝ፤
መቼ ነበር ብትል በቀን፤
ለማን ብትል በስም፤
ለምን ብትል በሪማርክ፤
ሁሉንም ሰርተህ ስጨርስ ለደንበኞችህ መላክ ብትል ለስራ አጋር ለማጋራት
🫴🫴🫴🫴
ዘምኖ የሚያዘምን
እየዘመነ ያለ ምርጥ አፕፕ
cashbooket.com
የቴሌግራም ቻናል አለው ለመረጃ
https://t.me/allstanderdcoder

በአንድ ወቅት በእንሰሳት አለም አንድ ወሬ ተሰማ ይህም ሰማይ ሊወድቅ ነው የሚል። ይህንን የሰማው ዝሆን መደበቂያ ፍለጋ ወደጫካ በመሮጥ ለይ እንዳለ አንዲት በጀርባዋ ተኝታ እግሮቿን ወደለይ የዘረጋች እርግብ በማየቱ በድርጊቷ ተገርሞ አጠገቧ በመቆም ምን እያደረግሽ ነው ሰማይ ሊወድቅ መሆኑን አልሰማሽም እንዴ? ሲላት ሰምቻለሁ እሱን ለመከላከል ነው እኮ እግሬን ዘርግቼ የተኛሁት አለችው። በዚህ ጊዜ ዝሆን በንቀት እየተመለከታት እኔ በዚህ ግዙፍ ሰውነቴ ፈርቼ መደበቂያ እየፈለኩ አንቺ ሰማይን በእግሮችሽ ልትደግፊው ሲላት ከሚወድቀው ሰማይና ከሚሸሸው ዝሆን ትልቅነት ምን አለኝ እኔ ማድረግ የሚገባኝ የአቅሜን እና የምችለውን ነው ብላዋለች ይባላል።
#አሁን ትምህርት ለይ ከገጠመን የውጤት ማጣት ችግር ትልቅነትም ይሁን እኔ ምን ላድርግ ብለው ከተቀመጡ ተቋማት እና ግለሰቦች አቅም አንጻር እራሳችንን ሳናወዳድር እኛ የምንችለውን በማድረግ ግዴታችንን እንወጣ።
#ለጊዜው አሁን በእጃችን ያለውን የክረምት ወቅት በመጠቀም በየአካባቢያችን በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ስለሆነ በምንችለው እናግዝ።
#ቀጥሎ ያለውን ሊንክ በመጠቀም ፈቃደኞችን ለመመልመል ወደተከፈተው ግሩፕ ተቀላቀሉ። ወደ ግሩፑ ስትቀላቀሉ የት አካባቢ በምን ትምህርት ድጋፍ እንደምታደርጉ መግለጽ እንዳትረሱ።
https://t.me/+PQdswm3PXRw2NGI8

«እውነት ነው። አዎ የሆነ ነገርማ አለ»
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
አሕመዲን ጀበል
♦♦♦♦♦
ከመጅሊስ ምርጫ ጋር በተያያዘ የተለያዩ መልዕክቶችን እያስተላለፍኩ መሆኔ ይታወቃል። በዚህ ረገድ ሰዎች የተለያዩ ሀሳቦችን እያደረሱኝ ነው። በርካቶች ወሳኝ መልዕክቶች መሆናቸውን የጀመርኩትን እንድገፋበት የሚጠይቁ ናቸው። ሌሎች በተለይም በተለያየ የመጅሊስ እርከን ላይ ያሉና ወደ መጅሊስ ለመግባት እየተራወጡ ያሉት ደግሞ አሕመዲን ጀበል እንዲህ የሚጽፈው «እኛ እንዳንመረጥ ለማድረግ ነው» በሚል ቂም እስከመቋጠር የደረሱም አሉ።
ጥቂት ቢሆኑን «የዚህ ሰው ሀሳብና ቀጣይ አቅጣጫ ወዴት ነው? » ብለው ነገሩን በመተንትን ለመረዳት እየተጣጠሩ ያሉም አሉ። ሌሎች ደግሞ ለምን በውስጥ ከነሱ ጋር ለመፍታት አትሞክርም ያሉም አሉ።
የመጅሊስ ችግሮች የሁላችንም በመሆናቸውና ምርጫውም ሀገር ዓቀፍ እና ከ10ሺህ በላይ ሰዎች የሚመረጡበት በመሆኑ ንግግሩም ሆነ ጥረቱ ከጥቂት ሰዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በማንቃትና በመነሳሳት የመፍትሄው አካል እንዲሆኑ ማገዝ ይገባዋል። ይህ ሲሆን ሁሉም ችግሮችን በመረዳትና በየአከባቢው በጉዳዩ ላይ በመነጋገር ሌላው ቢቀር የአከባቢውን መጅሊስ ለማስተካከል እንዲተጋ ማድረግ ይችላል። ለዚህ ደግሞ እጅግ ወሳኝ አጋጣሚው ምርጫው በመሆኑ በዚህ ምርጫ በንቃት በመሳተፍ ይሆነኛል የሚለውን ሊሰራለት የሚችለውን የመጅሊስ አመራር በየእርከኑ በመምረጥ ሚናውን መወጣት ይገባል።
ጥቂቶች ደግሞ ሆን ብለው መልእክቴን ያልተረዱ በመምሰል ሆን ብዬ አቋም እየቀያየርኩ በማስመሰል ረጅም ጽሑፍ የማያነቡ ሰዎች ላይ ብዥታ ለመፍጠር የሞከሩ ጥቂትም ቢሆኑ እንደነበሩ ታዝቢያለሁ። ሌሎች ደግሞ «አሕመዲን ጀበል ያለምክንያት በዚህ ደረጃ አጀንዳውን ወጥሮ አልያዘውም። የሆነ ነገርማ አለ» በማለት ሀሳባቸውን ሲገልጹ ታዝቤያለሁ።
በዛሬ ጽሑፌ «የሆነ ነገርማ አለ» ለሚሉት ወገኖችቻችን የምለው «አዎ እውነት ነው የሆነ ነገርማ አለ»። በማለት በማስከተል ካሉት ነገሮች እስከ አሁን ከጠቀስኳቸው በተጨማሪ ጥቂት ንጥቦችን ለማንሳት እሞክራለሁ። መልዕክቱ ለሌሎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ ለሌሎች ሳያደርሱ አይለፉ። የተሰማዎትን ሀሳብ በነጻነት ከስር ያስፍሩ። መልካም ንባብ።
1. የኔ ዓላማ ከምርጫው በኋላ ደካማ የመጅሊስ አመራር እንዳይኖረንና ዛሬ ተገቢውን ሰው እንድንመረጥ ማገዝ ነው። ይህም «ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ» እንደሚባለው ባለን የመምረጥ መብት ሚናችንን በአግባቡ እንድንወጣ ነው።
ዛሬ ሚናችንን በአግባቡ ሳንወጣ የነገው መጅሊስ የማይሰራ፥ ደካማ፥ ሙሰኛና ለሕዝበ ሙስሊሙ ያልቆመ ቢሆን «መጅሊስ ዋጋ የለውም። ያሁሉ ዋጋ የከፈንለት ለዚህ ነው? » ከማለታችሁ በፊት መጅሊስ ዋጋ እንዲኖረው የሚያደርግ አመራሮችን እንድትመርጡ ነው።
2. «መጅሊስ በአዋጅ ተቋቁሞ የለም ወይ? ምነው እንዲህ ሰጋህ? » ለሚሉት መጅሊስ በአዋጅ መቋቋሙ በመጅሊስ ታሪክ ትልቁ ስኬት ነው። ለዚህም መንግስትን እናመሰግናለን። ሆኖም በአዋጅ ስለተቋቋሙ ብቻ የምንፈልገው መጅሊስ ይሆናል ማለት አይደለም።
መጅሊስ በአዋጅ ከተቋቋመ 5ኛ ዓመቱን ይዟል። ሆኖም በነዚህ ጊዜያት መጅሊስ ሕዝቡ ከርሱ የሚጠብቀውን ሁሉ ማሳካት ችሏል ማለት አይቻልም። ለነገም በአዋጅ መቋቋሙ ብቻውን የችግሮቻችን ሁሉ መፍትሄ ነው ማለት አይደለም። ተቋምን ተቋም የሚያደርገው መሪዎቹ ስለሆኑ ተገቢ ሰዎችን ምረጡ የምለው ለዚህ ነው።
3. መጅሊስ የሕዝበ ሙስሊሙ እንጂ የመሪዎቹ አይደለም። ለዚህም ነው ባለቤቶቹን በጉዳዩ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና ቸል እንዳይሉ እያደረግኩ ያለሁት።
4. መጅሊስ ጠንካራ እንዲሆን እኔ መሪዎችን ልምረጥላችሁ አላልኩም ። እያልኩ ያለሁት ተገቢውን ሰው መምረጥ ይገባችኋል ነው።የኔ ጥረት እኔ እንድመረጥ አይደለም። ከዚህ በኋላ በመጅሊስ ጉዳይ ቀጥተኛ ሚና እንደማይኖረኝ፥ በዚህ ምርጫም በተመራጭም፥ መራጭም፥ አስመራጭም ምንም ሚና እንደማይኖረኝ ገልጫለሁ።
«መመረጡንስ እሺ እንደማትፈልግ ገልጸኻል። ቢያንስ እንደማትመርጥ መግለጽ አስፈላጊ ነበር ወይ?» ለሚሉት ወገኖች የምለው ከምርጫው ምንም የግል ፍላጎት እንደሌለኝ በመግለጽ በነጻነት ሀሳቤን ለማንሸራሸር ጠቃሚነቱ ስለታየኝ እንጂ ሰዎች እንዳይመርጡ ለማድረግ አይደለም። እንዲያውም እኮ ለራሴ የወሰድኩት ሚና ሕዝበ ሙስሊሙ ስለመጅሊስ ተገንዝቦና ከባለፉት ስህተቶች ተምሮ ተገቢውን መሪዎችን በሁሉም እርከን እንዲመርጥ አቅጣጫ ማመላከት ነው።
5. የኔ ጽሑፍ መጅሊስ እንዲዳከም ሳይሆን እንዲጠናከር ነው። ሰዎች ዑለሞችን እንዲንቁ ሳይሆን በሚገባ እንዲረዷቸውና ብቃት ባላቸው ስፍራ ሚናቸውን እንዲወጡ እንዲያግዟቸው፥ ዑለሞችም ብቁ የሆኑበትንና ስኬታማ በሚሆኑበት ስፍራ ሚናቸውን እንዲወጡ እንዲሁም የዛሬውን ጉድለታቸውን ተረድተው ራሳቸውን ለማብቃት እንዲተጉ ነው።
6. የሕዝብን ጥቅም መጠበቅ የተቋምን ጥቅም ከመጠበቅ ይቀድማል። የተቋምን ጥቅም መጠበቅ ደግሞ የግለሰቦችን ጥቅም ከማስጠበቅ ይቀድማል። እውነታው ይህ ነው!
በመጅሊስ ጉዳይ ዋጋ የከፈላችሁ ሁሉ!
በመጨረሻም ማስታወስ የምፈልገው የመጅሊስም ሆነ የሕዝበ ሙስሊሙ ችግሮች ሁሉ በአንድ ጀንበር አንደማይፈታ ጠፍቶኝ አይደለም። የኔ ዓላማም በማነሳቸው ሀሳቦች ግንዛቤያችን በማጎልበት በምርጫው በንቃት በመሳተፍ በሁሉም እርከን ተገቢ ሰዎችን መምረጥ እንዲቻል ማድረግ ነው።ይህ ሲሆን በሁሉም እርከን ያለውን መጅሊስን ከእስካሁኑ አንድ እርከን ከፍ ማድረጉ መሠረት ይጣላል።
ፍላጎቴ ሚናችሁን በአግባቡ እንድትወጡ እንጂ ተስፋ ቆርጣችሁ እንድትዘናጉ አይደለም። ስለሆነም በማህበራዊ ሚዲያ በጉዳዩ ላይ ከመነጋገር ወደ መሬት ወርዳችሁ በተቃረበው ምርጫ ተገቢ ሰዎችን ምረጡ! በተለይ በመጅሊስ ጉዳይ ዋጋ የከፈላችሁ ሁሉ! አበቃሁ። አላህ ቸሩን ያሰማን።
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል

🔥1
☪️ አል-በያን ወላጅ-አጥ ህጻናትን በ1997 ዓ/ል ላይ ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ ለመመሥረት የገፋፋቸው ዋነኛው ምክንያት ከስልጤ በአጎራባች ዞኖችና ድንበሮች አካባቢ እና በውስጥም የሚገኙ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ከዲናዊ ጥቃትና ተጋላጭነት ለመታደግ በማለም ነው:: ኢማም! እንዳቀዱትም ተሳካላቸውና በቤታቸው ውስጥ በ4 የቲም ልጆች የጀመሩት ጉዞ ሰመረና አል-በያንን አቋቁመው፣ መሬት ተቀብለው በመገንባት እውን አደረጉት:: ከየወረዳውና ከአጎራባች ዞኖችም የተሰባሰቡ ልጆችን ዲናዊውንና ዓለማዊውን የትምህርት ሥልጠና መስጠት ጀመረ::
በርካታ ኡስታዞች እነ ሐጂ ሻፊ ረዲ፣ እነ ኡስታዝ ሙከሚል ከማል( Mukemil Kemal Abdelah )፣ እነ ኡስታዝ ሙሐመድ ሐምዱ ረሾና ሌሎችም ሁነው በተለያዩ ኃይማኖታዊ እና ዓለማዊ መስኮች በማስተማርና በማሠልጠን በ5 ዙሮች ብዙዎችን «ሓፊዝ» እና የሌላም ሙያ ባለቤት በማድረግ አበቁ:: ከእነሱ ውስጥም በአሁኑ ወቅት በወራቤው ቢላል መስጂድ ኢማምና ኻጢብ ኡስታዝ ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት ኡስታዝ ኸሊል አላህዋቦን፣ ኡስታዝ ተውፊቅ ኑርገባን(ከመዲና ዩኒቨርሲቲ በቁርኣን ጥናት ዘርፍ በዲግሪ ተመርቀው አ/አበባ ላይ በሥራ የሚገኙ/ሚቃት ትራቭል) እና ሌሎችንም ማፍራት የቻለ ተቋም መሆኑን በቅርቡ ለሕትመት የሚበቃው «ናትራር/የኢማም ሐጂ አብዱልሃዲን የህይወት ታሪክን» የያዘው መጽሐፍ በዝርዝርና በሰፊው ጥናቱን እየተነተነ እንደሚያቀርብ ለማወቅ ተችሏል:: በዘመናዊና በተደራጀ አካሄድ ስልቱን እየቀያየረ፣ በተለያዩ ደካማ ጎኖቻችን እየገባ የሚያጠቃንን የአክፍሮተ-ኃይላትን፤ በጋራ ጥረትና ሕብረት መከላከያ መፍትሔዎች ከሆኑት አንዱና ዋነኛው አል-በያን ተቋም ነው::
ይህ ወሳኝ ተቋም አሁን የሁላችንንም ድጋፍ የሚሻበት ጊዜ ላይ ደርሷል:: በመሆኑም! #በነገው_ዕለት-ቅዳሜ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅቷል:: በፕሮግራሙም ላይ በሁሉም ዓለም ላይ የሚገኙ የመልካም ሥራ ባለቤቶች (አህለል-ኸይራት) እንዲሳተፉ በየቲሞቹ ስም ተጋብዘዋል:: እርሶም በዚህ የማይቋረጥ አጅር(ሠደቀተን-ጃሪያ) መቋደሻ መድረክ ላይ በአካል ተገኝተው፣ ካልተመቸዎትም በ Onlieም ሆነው የድርሻውን እንዲያበረክቱ በአላህ ስም ጥሪ ቀርቧል::
ነገ የማይቀርበት፣ የየቲም ልጆችን የምንደግፍበት፣ ቀጠሮ ነውና እንዳይቀሩ ይላሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎቹ❗️
የአላህ ሠላምና እዝነት በሁላችንም ላይ ይሁን‼️

●●● ፈር-ቀዳጅ ታጋዮች እና መነሻቸው ●●●
¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢|||¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢
የስልጤን የማንነትና የመብት ትግልን በቀዳሚነት አደረጃጀት በመፍጠርና በመምራት፣ በሌሎችም ሐሳቡን እያሰረጸ ወደ እንቅስቃሴ በማስገባቱ ረገድ የአንበሳውን ድርሻ እንደተወጣ የሚታወቀውን አክመል ሼኽ ሣሎን{አላህ ይዘንለት ሥራውንም ይውደድለት} በጊዜው አንድ ጓደኛው እንደሚከተለው ይጠይቁታል: ❝በዚያን ጊዜ ማህበረሰቡ በየቦታው በተለያየ ስያሜ ነበር ራሱን የሚጠራው፤ ጉራጌ ላለመሆናችሁ የተደራጀ መረጃ ሳይኖር ሐሳቡ እንዴት መጣልህ⁉️❞ ብሎ ጠየቀው::
ብርቱ እና ንቁ ታጋይ የነበረው አክመል ሲመልስላቸው : “ጉራጌ አለመሆናችንን እንኳን እኛ ሁሉም ያውቃል:: ለዚህ አንድ ምሣሌ ላንሳልህ” አለው:: ታዋቂው ጀግና ኢማም ሱጋቶ ዘይኔ በ1943 ዓ/ል አካባቢ በ«ዱና» የሞተ ዕለት፣ ለህዝቡ ከባድ ሐዘን ነበር:: እንደባህላችን ለእንግዳ ማስተናገጃ ይታረዳልና አሞራዎች ሰማዩን ሸፍነው ይመላለሳሉ:: ፍየሎች በዳገቱ መስክ ተሠማርተው አካባቢውን ሞልተውት እያለ ከሆሳዕና አማራዎች፣ ሀዲያና ሌሎችም ሆነው የአካባቢውን ጀግና ሥርዓተ-ቀብር በክብር ለመሸኘት በመጡበት እንደሚከተለው እየገጠሙ አለቀሱ:
👉አሞራው በሰማይ ይላል ዳኛ ዳኛ፣
ፍየሉ ዳገቱ ላይ ይመስላል ሠርገኛ፣
የዘይኔው ሱጋቶ «የኢስላሞቹ» አርበኛ፣
ታከተው መሠለኝ ተከናንቦ ተኛ ፤ 👈
ብለው ሐዘናቸውን ሲገልጹ «የእስላሞቹ» አርበኛ ነው እንጂ የጉራጌዎቹ አለማለታቸው ራሱ ብቻውን ማንነታችንን ከእኛ አልፎ ሀገር ያወቀው፣ ጸሐይ የሞቀው የዓደባባይ ሚስጥር እንደሆነ ነው እኮ የሚገልጸው::” በማለት አብራራላቸው::
፨ከአቶ መሐመድ ደድገባ(#Mohammed_Dedgeba) የተገኘ ታሪካዊ መረጃ
●በታጋይ አክመል ሼኽ ሣሎ እና በባልደረቦቹ በነ ታጋይ(ገራድ) ሃሺም ሐምደግባ፣ በታጋይ ኸይረዲን አህመድ፣ በታጋይ ሹክሪ ረዲና በመሣሠሉት አባላት የተጀመረው የማህበረሰባዊ የማንነትና የመብት ጥያቄ ያስከተለው እንቅስቃሴ አ/አበባ ላይ ሐምሌ 1983 ዓ/ል «ስአመወገዲድ» የሚል አደረጃጀትን ወደ ማዋቀር ገቡ:: በመስከረም 4/1984 ዓ/ል ላይ የድርጅቱን እንቅስቃሴንና ምሥረታውን ይፋ አድርጎ ወደ ሕዝብ ለማውረድ በአሁኑ ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በኢማም ሱጋቶ መቀበሪያ ምድር «ዱና ከተማ» ላይ ጉባኤ ተካሄደ:: ጉባዔውም ድርጅቱ «ጎጎት/ስአመወገዲድ» ተብሎና
1/ ታጋይ አክመል ሼኽ ሣሎን በሰብሳቢነት፣
2/ አቶ ኸይረዲን አዝማች ሁሴንን በም/ተሰብሳቢነት፣
3/ ገራድ ሃሺም ሐምደግባን በዋና ጸሐፊነት መርጦ በማጽደቅ ወደ እንቅስቃሴ ተገባና ቀጠለ●●● በ1987 ዓ/ል ላይ ስልጤነትን የጋራ መጠሪያ አድርጎ የቀጠለው ትግል፤ በስተመጨረሻም ከ10 ዓመታት በኋላ #በመጋቢት_23_1993 በተደረገው ሕዝበ-ውሳኔ ብሔረሰብነቱን አረጋግጦ፣ ይብዛም ይነስ የራሱን ዞን አዋቅሮ፣ ህልውናውን አስከብሮ ወደ ሌላኛው ምዕራፍ ቀጠለ●●●

♦️እስከ 600 ሚሊዮን ብር ወጪ ወጥቶበት የተሠራው የንግድ ባንኩ ሎጎ፣ በጠ/ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ይፋ እንዳይደረግ መታገዱ የታወቀ ሲሆን በከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘንድም ሎጎውን የመቀየሩ ጉዳይ ተቀባይነትን እንዳጣም ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል::
●ያን ወርቃማ እና ሽክርክር አርማ ለመተካት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ለማውጣት የመወሰኑ ተገቢነት እና አስፈላጊነት ላይ ጥያቄ እንድናነሳ የሚያስገድድ ከመሆኑም በላይ በቀጣይም ከሎጎ መቀየሩ ሥራ ጋር ተያያዥ የሆኑ በርካታ ወጪዎች እንደሚከተሉ ስንረዳ ደግሞ የጉዳዩ አሳሳቢነት ይጨምራል:: በተለይም በየህንጻዎቹ ላይ ያሉትን አርማዎች አፍርሶ አዲሱን መተካት፣ ያሉትን የጽህፈት መሣሪያዎችን፣ የቼክና የቁጠባ ደብተሮችን፣ የኮምፒዩተር ሶፍትዌሮችንና ወዘተ ለመቀየር የሚወጣው ወጪ የትየሌሌ ከመሆኑም ባሻገር አዲሱን አርማ በመላው ዓለም ላሉ ባንኮች፣ የፋይናንስ ድርጅቶች፣ ለባንኩ ደምበኞች -ሀ- ብሎ እንደገና ለማስተዋወቅ ሊወጣ የሚችለውንና በሚሊዮን የሚገመት በጀትን ስናክልበት፤ እንዴት ነው ትርፍና ኪሣራው የተጠናው⁉️ ያሰኛል❗️ ለማንኛውም እንደዜጋ ሐሳቤን ይህን ያህል ካጋራሁኝ ነገሩን ለያዘውና ይበልጥ ለሚመለከተው መንግሥታችን ሰጥቼ ወደ ተነሳሁበት የአርማው ታሪካዊ ጉዳይ ልዝለቅ...
● አቶ ናሥር ሐሰን(ጩምሰሮ) ይባላሉ የኢኮኖሚያችን አንቀሳቃሽ ሞተር፣ ዋልታና ማገር የሆነውን ንግድ ባንክን በምክትል ሥራ አስኪያጅነት በመምራት፣ ዕውቀታቸውን፣ ጊዜና ጉልበታቸውን ያለ ስስት በመለገስና ሌት-ተቀን በማገልገል፤ ድርጅቱ በሁለት እግሩ ቆሞ ለመቀጠሉ ከፍተኛ እና ወደር-የለሽ አስተዋፅኦን ያበረከቱ::
◆በወቅቱ የባንኩ የሒሣብና የኢንቨስትሜንት(መዋዕለ-ንዋይ) መምሪያ ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ናሥር ሐሰን፣ ለንግድ ባንኩ የሚከተሉትን ታሪካዊ ተግባራትን መፈጸማቸው ተረጋግጧል ፦
●ሥራ ላይ የሚገኘውን «ሎጎ እና አርማ»ን
ግዴታቸው ሳይሆንና በዜግነት ስሜት ተነሳስተው ያለ አንዳች ክፍያ ዲዛይን በማድረግ፣ ክሊሼውን እንግሊዝ ሀገር በነጻ አሠርተው በወቅቱ የባንኩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ለነበሩት ለአቶ ዓለሙ አበራ አቀረቡ፤
●ሎጎው ሥራ ላይ እንዲውል ተደረገና አርማው በቼኮች፣ በቁጠባ ሒሣብ ደብተሮችና በባንኩ የጽህፈት መሣሪያዎች ላይ እንዲታተም አደረጉ፤
❝ከ80 ዓመት በላይ ታሪክ ያለውን ባንክን(ሎጎውን) በዚህ መልኩ በአንዴ መቀየሩ፣ የባንኩን ዕሴት እና ታሪክ(heritage) አውጥቶ ይጥላል::❞ ያለው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት፣ የአንድን የብራንድ ዲዛይን ባለሙያን አስተያየት ያጋራል: ❝ክቡ አርማ ግን ልዩ ነው:: በርካቶችም በዚያን ዘመን ኮምፒውተር በሌለበት እንዴት ሊሠሩት ቻሉ!? ብለው እንደሚነቁባቸው::❞ መግለጻቸውን ይናገራል:: @EliasMeseret
◆አቶ ናሥር! በወቅቱ የቃል ምሥጋናን እንኳን ያላገኙበት ይህ ሥራቸው፣ ላለፉት 50 ዓመታት እያገለገለ መዝለቁም ይታወቃል::
◆ “ባንኩን ለማዘመንና ኮምፒዩተራይዝድ ለማድረግም ከፍተኛ ጥረት አድርጌያለሁኝ:: የመጀመሪያዎቹን የብር መቁጠሪያ ማሽኖችን ከጀርመን፣ ከፈረንሳይ እና ከኢንግሊዝ ተጻጽፌ ለባንኩ አስመጥቻለሁኝ በቅቤና በጭቃ የላመ ብራችንን ይቆጥራል ወይ? ብለን በማጥናትና በማረጋገጥ ጭምር::” ሲሉኝ ጊዜ፤ በተግባር የተገለጸ ሀገራዊ ፍቅራቸውን ከእኛ ከዘመኖቹ ተወላጆች ሥራና ስሜት እንዲሁም ተቆርቋሪነት ጋር እንኳን ማወዳደር ማሰብም እንደማይቻል ስለገባኝ ተውኩትና ለማንኛውም ዕወቁት ብዬ አጋራኋችሁ::

♦️ያልተነገረው የሐጂ ረህመቶ ሙክታርን አጭር የህይወት ታሪክ፣ ስኬትና አስተምህሯቸውን የያዘው «ጎፍታ» መጽሐፍን በ Word file ቀርቦላችኋል:: እናንተ ብቻ አንብቡ፣ ዕወቁ፣ ጠይቁ፣ አሳውቁ፣ ሌላ ታሪክ በመሥራትም አስቀጥሉ ◆◆◆ 👉👇
https://eu.docworkspace.com/d/sIHDY5cC5AebQ7sQG?sa=601.1074

ሰው ይህን በነጻ ለሀገሩ ቀርጾ ይሰጣል!
ሌላው ደግሞ እራሱን ትንሽ ቀይሮ 600 ሚ ይጠይቃል¡ አቤት ልዩነት!?
በዚህ ዘመን በነጻ ቀርጸው ያስረክቡ ማለቴ አይደለም:: ግን ትንሽ ማመጣጠን የሚባል ነገር የለም እንዴ? አስገራሚው ዋጋ/አሃዝ ምንም እንኳን የዲጂታል መድረኮችን እንደገና ለመሥራት፣ ምልክቶችን ለመተካት፣ የደብዳቤ ካርዶችን፣ የሠራተኛ መታወቂያዎችንና ሌሎችንም አካቶ የንግድ ባንኩን ከ1,900 በላይ ቅርንጫፎችን ለመተካት ወጪዎችን ይጨምራል ቢባልም በጣም ተጋኗል:: ያውም ሀገራዊ ፊደላትን አስወግዶ፣ Always reliable bank የሚለው ራሱ Grammatical error አለው እያሉን እኮ ነው ምሁራኖቻችን!!
ኦኦ ይህን ነገር አበዛሁት መሠለኝ፣ ማነህ balance ስለሌለህ ነው የምትለው ሰውዬ እንዳላስቆጥርህ ¡¡¡
🤣🤣🤣

❤1
ማሻአላህ❗️ ዑለማዎቻችን በአንድ በኩል ኡማውን እያገለገሉ፣ በሌላ ጎን ደግሞ በዘመናዊው የትምህርት ዘርፍም በርትተው እየተማሩ ተመርቀልናል አልሐምዱ ሊላህ‼️
የዚህን ዘመን ዲናዊ ጥቃትን መመከት፣ ማህበረሰብን መታደግና መጥቀም የሚቻለው በዕውቀት ብቻ እና ብቻ ነው ሌላው ከዚያ በኋላ ነው:: ለዚህ ደግሞ ጥልቅ ዲናዊ ዒልም፣ ዘመኑን የዋጀ ዕውቀትና ሥልጠና፣ ሰፋ ያለ ግንዛቤና አመለካከት እንዲሁም ብቃት፣ ንቃትና ቅንነትን አጣምሮ መያዝና ተግባራዊ ማድረግ ግድ እየሆነ ከመጣ ሰነባብቷል::
እናም ዓሊም ወገኖቻችን ሆይ❗️
እንደ ኡስታዝ መሐመድ ፈረጅ፣ እንደ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፣ እንደ ኡስታዝ መሐመድ ሐምዱ ረሾ፣ እንደ ኡስታዝ ሙስጠፋ ጀማል፣ ... እንደ ሌሎችም ምን ትጠብቃላችሁ⁉️ አመቻቹና ተማሩ፣ በአጭሩም በረዥሙም ኮርስና ሥልጠና በመሳተፍ የዕድሉ ተጠቃሚ ሁኑ!! ቀድሞም በተሸከማችሁት ዕውቀት ላይ ቅመም ጨምራችሁ በማዋሀድ ሕዝባችሁን እንደተለመደው መግቡ!!!
◆እኔ በተለይ ይህን የትምህርት እና የሥልጠና ዕድል አርቆ በማየት ያዘጋውን የሚኒሶታውን ኮሌጅ በጣም ማመሥገን ይገባል ባይ ነኝ!!!
◆ማሻአላህ! ሁላችሁንም እንኳን ደስ አላችሁ!! እኛም ደስ ብሎናልና በርቱልን!!!

በንጉሥ አብዱልዐዚዝ የቁርኣን ድርጅት አዘጋጅነት በተሠናዳው የቁርኣን ሒፍዝ ውድድር፣ የ127 ሀገራት ተወዳዳሪ ሓፊዞች በተሳተፉበት ዓለምአቀፍ የሒፍዝ እና የተፍሲር ውድድር ላይ 3ኛ ወጥቶ 250 ሺህ ሪያል የተሸለመው ኢትዮጵያዊ ቃሪእ ኢብራሂም ሼኽ ኸይረዲን(ማሻአላህ አትሉም የባድ ወልዶች!?)
https://www.facebook.com/share/16kFrxpJPb/

👏2