Setaweet (ሴታዊት)
1.82K subscribers
1.08K photos
40 videos
24 files
417 links
Setaweet Movement aims to articulate Ethiopian feminism. The movement creates a space for dialogue, research and activism by Ethiopian women and men!🇪🇹
More info call +251118225451
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia

በረቂቅ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲው ላይ 8 የሰብዓዊ መብት የሲቪክ ድርጅቶች አስተያየት አቅርበዋል።

አስተያየት ያቀረቡት ፦
የመብቶች እና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል (CARD)
የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች (LHR)፣
የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA)፣
ሴታዊት
የኢትዮጵያ ሠራተኞች መብት ተሟጋች (ELRW)፣
ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ (AHRE)
ሁሉን አቀፍ ራዕይ ለዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያ (IVIDE)
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል (EHRDC) ናቸው።

ካቀረቡት አስተያየት መካከል ፦

" የሽግግር ፍትህ ረቂቅ ፖሊሲው እስካሁን ለህዝብ ይፋ ባይደረግም፣ ባጭር ጊዜ ውስጥ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደሚፀድቅ መረጃዎች በመውጣት ላይ ይገኛሉ።

ነገር ግን ረቂቅ ፖሊሲውን በሚመለከት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ለጋሾች ጋር ከተደረጉ አጫጭር ውይይቶች በስተቀር በቂ ውይይት አልተደረገም።

ሰነዱ ይፋ ስላልሆነ ደርዝ ያለው አስተያየት ለመስጠትም ዕድል አልተገኘም።

ረቂቅ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ሰነዱ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ከመፅደቁ በፊት ለህዝብ ይፋ ተደርጎ በባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጥበት በአፅንኦት እንጠይቃለን።

በዚህ ረገድ በሽግግር ፍትህ አማራጮች ላይ ሰፊ ውይይቶች መካሄዳቸውን በበጎ የምንወስደው ቢሆንም፣ በፖሊሲ ዝግጅቱ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደምንገኝ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ በረቂቅ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲው ላይ በቂ እና ፍሬያማ ውይይት እንዲደረግ አስቀድሞ ረቂቅ የፖሊሲ ሰነዱ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን እንጠይቃለን።

ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተጨማሪ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ፦
- የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣
- የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን፣
- የእምባ ጠባቂ ተቋም፣
- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣
- የመገናኛ ብዙሃን፣
- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣
- ምሁራን እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ረቂቅ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ሰነዱን በዝርዝር ተመልከተው ከመፅደቁ በፊት አስተያየታቸውን እንዲያቀርቡ ዕድል እና በቂ ጊዜ ሊሰጥ ይገባል።

ይህን ማድረግም ለፖሊሲ ሰንዱ ጠቃሚ ግብዓት ከማስገኘት በተጨማሪ ፣ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲው በህዝብ ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት እና ተፈጻሚነት እንዲኖረው ለማድረግ ያግዛል ብለን እናምናለን። "

(ሙሉ አስተያየታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
# አሁንም_አልረፈደም!
Listen to an insightful interview where Reeyot Alemu interviews Setaweet's director, discussing transitional justice and the continuing violence against women. https://youtu.be/cISWKkgYvuY?feature=shared
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የ5 ዓመቷን ህፃን የደፈረው የ17 ዓመት ወጣት 6 ወር ተፈረደበት ይለናል የወምበራ ኮሚኒኬሽን።

የ5 ዓመቷን ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው የ17 ዓመቱ ወጣት #በ6ወር እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል።

የ10ኛ ክፍል ተማሪና የ17 ዓመት ወጣት የሆነው ግለሰብ በአስገድዶ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ በደብረ―ዘይት ከተማ 02 ቀበሌ በተለምዶ " ሳንቂ በር " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

በዕለቱ የ5 ዓመቷ ህፃን ላይ አስገድዶ የመድፈር ድርጊት ከፈፀመ በኃላ በመኖሪያ ቤቱ ነው የተያዘው።

ጉዳዩን የተከታተለው የወምበራ ወረዳ ፍርድ ቤት  መጋቢት 9 በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ወጣት የ6 ወር እስራት ፈርዶበታል።

ይህን መረጃ በ @tikvahethMagazine ላይ የተመለከቱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት " ቀልድ ነው ? ምን አይነት ፍርድ ነው ? ወንጀሉን ፍፁም የማይመጥን አሳዛኝ ፍርድ ነው " ብለውታል።

@tikvahethiopia
Happy World Autism Awareness Day
እንኳን ለ1445ኛዉ የኢድ አል-ፈጥር በዓል አደረሳችሁ!
የሽግግር_ፍትህ_ሂደት_ዙርያ_ከሴታዊትና_አጋሮችዋ_የተሰጠ_ረቂቅ_የአቋም_መግለጫ.pdf
267.9 KB
በታቀደዉ የሽግግር ፍትህ ሂደት ዙርያ ከሴታዊትና አጋሮችዋ የተሰጠ ረቂቅ የአቋም መግለጫ
We're excited to announce our Project Kickoff in the Sidama Region that started with Key Stakeholders Consultative Dialogue event, 'Uniting for Respect, Empowerment, Equality, and GBV-Free Communities, at Lewi Piassa Hotel, Hawassa, on Thursday, April 18th, 2024. Representatives from various sectors, including governmental institutions, one-stop center, youth group, disability organization, media women’s group, and student group gathered to address the root causes of challenges facing women, as well as preventive and responsive measures. Discussions focused on systemic factors contributing to gender-based violence (GBV) and inequality, with a shared commitment to fostering inclusive and safe communities. The event showcased promising collaborations, emphasizing inclusiveness and collective action. We are grateful for AFD (Agence Française de Développement’s) financial support, we look forward to implementing this crucial project.
We are thrilled to announce the formalization of our partnerships with Mizan Young Lawyers Center (MYLC) and Talita Rise Up, through the signing of Memorandums of Understanding (MOUs). The MoUs formalize our joint commitment to addressing prevalent issues of  gender-based violence (GBV) and women's rights violations in the Sidama Region. These collaborations mark a milestones in our collective efforts to combat GBV and uphold women's rights in the Sidama Region.
Join the April installment of our Emerging Practice Webinar series which will take place on Wednesday, 24 April from 2:00 - 3:00 (EAT).
''Principles of Prevention of GBViE" will be the topic for the webinar.

To register use the link below:
https://unfpa.zoom.us/j/83005966572?pwd=K2hkUS95RW0reXU0TWlLdzk2bUI2dz09
ሴት ልጅ ማሳደግ የቸገረበት ኮሬ ዞን

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን እጅግ በተባባሰው ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ልጆች ጠለፋ ምክንያት ቤተሰብ ልጆቹን ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ እየከለከለ ነው።
በዞኑ በ2015 ብቻ ከአንድ ቀበሌ 15  በዚህ አመት 7 ወራት ደግሞ ከሦስት ቀበሌዎች 10 ህፃናት እና ልጃገረዶች ከትምህርት ቤታቸው ደጃፍ፣  ከመንገድ ላይ፣ ባስ ሲልም ከመኖሪያ ቤታቸው ተጠልፈው ተወስደዋል።

ነገሩን የከፋ ሚያረገው ደግሞ አንድ ግዜ ጠለፋው ከተከናወነ በዃላ"ሽምግሌ" የሚባሉ የወንጀለኛ ተባባሪዎችን በመላክ ቤተሰቦች ነገሩን እንዲቀበሉ ማግባባት እየተለምደ መምጣቱ ነው።

"ሽምግልናውን" እምቢ ብለው ወደ ክስ ያመሩ ቤተሰቦችም በእርግጥ የሚጠብቃቸው "በሽማግሌ ጨርሱ" አይነት ምክር፣ሲብስም "እራሳችሁ ፈልጓት " የሚል መልስ እንጂ ወንጀለኞቹንም ለህግ የሚያቀርብም ሆነ ተባባሪ ሽማግሌዎችንም ይዞ የሚመረምርም የፍትህ አካል የለም።

ጉዳዩን ሪፖርት ለማድረግ በሚሞክሩ ዜጎች ላይም የዞኑ ገፅታ እንዳይበላሽ በሚል ተፅእኖ ስለሚደረግባቸው ችግሩ ካምናው ዘንድሮ እጅግ ተባብሷል።
#Sexual Assault Awareness Month