ሰንፔር ሚዲያ Sapphire Media
435 subscribers
290 photos
4 videos
8 files
104 links
መንፈሳዊ መጣጥፎችን ግጥሞችን ወጎችን አጫጭር ልቦለዶች አስደናቂ ታሪኮችን ትምህርታዊ ፅሁፎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን።

"ትውልድ ሆይ ወደ እግዚአብሔር ቃልና ወደ ተሰቀለው ክርስቶስ ተመልከቱ!!!"


https://youtu.be/KRKo3x7iYNw

http://Instagram.com/sapphiremedia4god

tiktok.com/@sapphiremedia1
Download Telegram
የሙሴ ወንድም ሙሐመድ

ሙስሊሞች የኢስላም ነቢይ ሙሐመድ በተውራት ወይም ኦሪት እና ኢንጅል ወይም ወንጌል፥ ማለትም በአይሁድ እና በክርስቲያኖች መጽሐፍ በብሉይ እና አዲስ ኪዳን ተደጋግሞ እንደተጻፈና እንደተተነበየ ይናገራሉ። ይህን የሚሉት በሱራ 61፥6 ዒሳ ከእርሱ በኋላ አሕመድ የተባለ መልእክተኛ እንደሚመጣ ስለ ተናገረ ነው። ጥቅሱ እንዲህ ይላል፤

የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥና ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር ስኾን ወደእናንተ (የተላክሁ) የአላህ መልክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በግልጽ ተዓምራቶች በመጣቸውም ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡ ይላል።

ዒሳ ለሙስሊሞች እንደሚመስላቸው ኢየሱስ ነው። ነገር ግን ዒሳና ኢየሱስ ከቶም አንድ አይደሉም። ይህ ራሱን የቻለ ጉዳይ ነውና እንለፈው። በነገራችን ላይ እንደዚህ የሚሉት እንደ አሕመድ ዲዳት እና ዛኪር ናይክ የመሰሉት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እናውቃለን የሚሉ ናቸው እንጂ የቀደሙት ሙፈሲሮች ይህንን አላሉም። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሙሐመድ ተተንብዮአል የሚሉት ደግሞ የአይሁድም የክርስቲያኖችም መጽሐፎች የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል እያሉም ነው። ይህ የመበረዝ ጉዳይም ራሱን የቻለ ሌላ ርእስ ነውና እንለፈው። እና ይህ የተበረዘ የሚሉት መጽሐፍ ስለ ሙሐመድ ተነበየ የሚሉትን ወይም እንደተነበየ የሚመስላቸውን ምንባቦች መበረዙንና መበላሸቱን ሳይጠራጠሩ ይቀበሉታል።

እነዚህን ሙሐመድ ተጠቀሰባቸው የሚሏቸው ምንባቦች ብዙ አይደሉምና እንመለከታቸዋለን። በእውነት ስለ ሙሐመድ እንደሚናገሩም እንፈትሻቸዋለን። ባለፈው፥ ‘አጽናኙ ሙሐመድ’ በሚል በዮሐንስ ወንጌል ከ14-16 ባሉት ምዕራፎች ስለ አጽናኙ (ጰራቅሊጦስ ወይም መንፈስ ቅዱስ) የተነገረው ስለ ሙሐመድ የተተነበየ ትንቢት ነው ስለሚሉት ተመልክተናል። ቀጥሎ በዚህ ክፍል ደግሞ ከሙሴ በኋላ የሚመጣው ነቢይ የተባለው ሙሐመድ ነው የሚሉትን እንመለከታለን።

የተነገረው ትንቢት እንዲህ የሚል ነው፤ ዘዳ. 18፥18-19 ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ ቃሌንም በአፉ አደርጋለሁ፥ ያዘዝሁትንም ቃል ሁሉ ይነግራቸዋል፤ በስሜም የሚናገረውን ቃሌን የማይሰማውን ሰው እኔ እበቀልለታለሁ።

ይህ ክፍል ሙስሊሞች ስለ ሙሐመድ የተተነበየ ትንቢት ነው ብለው የሚያሸበርቁት ምንባብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል እያሉ ይህ ክፍል አልተበረዘም የሚሉ ከሆነ መጽሐፉን ወይም የጥቅሱን ዙሪያ ገባ (ዐውድ) ይቀበላሉ ማለት ነው። እዚያው 18፥16 ላይ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ታደምጣለህ። የሚል ቃል አለ። እነዚህ ጥቅሶች

ሙስሊሞች ሙሴና ሙሐመድ የሚገናኙባቸው መመሳሰሎች በማለት የሚዘረዝሯቸው ነገሮች አሉ፤ ሙሴ የሕዝቡ መሪ፥ ሙሐመድም የሕዝቡ መሪ፤ ሙሴ ሕግ የሰጠ፥ ሙሐመድም ሕግ የሰጠ፤ ሙሴና ሙሐመድ እናትና አባት አላቸው፤ ወዘተ፥ ይላሉ። ይህንን፥ ‘እናትና አባት አላቸው’ የሚሉት ያ ነቢይ ኢየሱስ እንዳልሆነ ከንጽጽሩ ውስጥ ለማውጣት ነው። በዚህ መልኩ ከዘረዘርን፥ ማለቂያም የለውም፤ ማንንም ከማንም ጋር ልናመሳስልም እንችላለን። ሙሴም ሙሐመድም በ’ሙ’ ይጀምራሉ፤ ሁለቱም አሥር ጣቶች አሏቸው፤ ወዘተ ማለትም እንችላለን። እንደዚያ የመሰሉ ዝርዝሮች የሚያቀርቡም አሉ።

እዚህ እግዚአብሔር የተናገረው ለእስራኤል የሚሰጣቸው፥ ‘እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ’ በእውነት የኢስላም ነቢይ ሙሐመድ ነው? ሙሐመድ በእውን የእስራኤል ልጆች ወንድም ነው? ‘ወንድም ሲባል ሰፊ ትርጉም አለውና የእስማኤል ልጅ ያው የአብርሃም ልጅ መሆኑ ነው።’ ይላሉ። ሲጀመር ሙሐመድ የእስማኤል ልጅ ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለም። ሙሐመድ ዓረባዊ ነው። ዓረባውያን የምድረ በዳ ሰዎች ማለት ነው እንጂ አንድ ወይም ሌላ ጎሳም አይደለም። ከእስማኤል 12 ነገዶች ውስጥ ደግሞ ዓረባውያን የሉም። ደህና፤ ከነዚያ አንዱ ናቸው ብለን እንውሰድ። ከሆነም እስማኤል ራሱ ግማሽ ዕብራዊ ግማሽ ግብፃዊ መሆኑን መርሳት የለብንም። ተጨባጭ ማረጋገጫ ባይኖርም፥ ‘ይሁን፤ እስማኤላዊ ነው።’ ብለን እንውሰድ።

እዚህ እግዚአብሔር እየተናገራቸው ያለው ግን ለእስማኤል ልጆች ሳይሆን ለይስሐቅ ልጆች ነው። ከይስሐቅ እና ከእስማኤልም ሌላ አብርሃም ብዙ ልጆች ነበሩትና እዚህ የተነገረው ይስሐቅ መሆኑ ይሰመርበት። ከይስሐቅም ደግሞ የዔሳው ሳይሆኑ የያዕቆብ ልጆች ናቸው እዚህ ይህ፥ ‘ከወንድሞቻችሁ መካከል’ የሚለው ቃል የተነገራቸው። ከእስማኤል ይልቅ ዔሳው ወይም ኤዶማውያን ለእስራኤል ይቀርባሉ። እንዲያውም የዔሳው ልጆች፥ ‘ወንድሞቻችሁ’ ተብለዋል፤ ዘዳ. 2፥4። እንዲያም ሆኖ ይህ እዚህ የምንመለከተው ቃል እነሱን እንኳ አይመለከትም።

ከወንድሞቻቸው መካከል የሚል ሌላ አሳብ ብንወስድ ይህንን አሳብ ይበልጥ ይከስትልናልና ያንን እንይ። በዘዳ. 17፥15 ላይ፥ አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን በላይህ ታነግሣለህ፤ ከወንድሞችህ መካከል የሆነውን በአንተ ላይ ንጉሥ ታነግሣለህ፤ ወንድምህ ያልሆነውን ከሌላ ወገን ሰው በላይህ ንጉሥ ታደርግ ዘንድ አይገባህም። የሚል ቃል ይገኛል። እስራኤል ወደፊት ንጉሥ እንደሚያነግሡ ተነገራቸው፤ ደግሞም አነገሡ። እና ያነገሡት ከማን ወገን ነው? ከእስማኤላውያን ወይም ከኤዶማውያን ሊያነግሡ ከቶስ ይታሰባልን? አይታሰብም። በእስራኤል ላይ የነገሡት የመጀመሪያዎቹ ንጉሦች ሳኦል፥ ዳዊት፥ እና ሰሎሞን ከየት ናቸው? ከእስራኤል። ከዳዊት በኋላ ሁሉም ከይሁዳ ነገድ ናቸው። ከዚያ በኋላ እሁለት ተከፍለው የሰሜኑ የተለያዩ ሰዎች ቢነግሡባቸውም በደቡቡ ሁሉም የሰሎሞን ዘር ልጆች ናቸው። በሰሜኑም የነገሡት ጥቂት ቅይጦች ቢኖሩም አይሁዳውያን ናቸው። ነገሥታቱም፥ ነቢያቱም እንደሚነሡ የተነገረባቸው ወንድሞች በእርግጥ ወንድሞቻቸው የሆኑ የእስራኤል (ያዕቆብ) ልጆች እንጂ ሌላ አይደሉም። በሕጋዊነት የነገሡት ነገሥታት ሁሉ አይሁዳውያን ብቻ ናቸው። ስለ ነቢዩ፥ ‘ወንድም’ የሚለው ቃልና ስለ ንጉሦቻቸው፥ ‘ወንድም’ የሚለው ቃል ተመሳሳይ ሆኖ፥ ቃሉ ብቻ ሳይሆን አሳቡም ተመሳሳይ ነው።

ደግሞም ያ ነቢይ ለማም ነው የሚነሣው? ወይም እግዚአብሔር ለማን ነው የሚያስነሣላቸው? ለእስራኤላውያን። ሙሐመድ የአይሁድ ወይም የእስራኤላውያን ነቢይ አይደለም። ሙሐመድ የመካና አካባቢዋ አስፈራሪ ተደርጎ የተላከ እንጂ ለአይሁድ የተላከ አይደለም። ‘የለም፤ እርሱ ለዓለሙ ሁሉ የተላከ ነው’ ከተባለም አለመሆኑን የሚያረጋግጠው የተወረደለት በዐረብኛ ብቻ መሆኑ ነው። ቁርኣን 42፥7 እንደዚሁም የከተሞች እናት የሆነችውን (የመካን ሰዎች)፣ በአካባቢዋ ያሉትንም ልታስፈራራ፣ የመሰብሰቢያውንም ቀን፣ በርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ልታስጠነቅቅ ዐረብኛ የሆነን ቁርአን ወደአንተ አወረድን፤ (ከነሱም) ከፊሉ በገነት ውስጥ ከፊሉም በእሳት ውስጥ ነው። ይላል። በተጨማሪ፥ 16፥103፤ 20፥113፤ 41፥3፤ 43፥3፤ 46፥12፤ ወዘተ፥ ቁር ኣን የተወረደው በዐረብኛ መሆኑ ለዐረብኛ ተናጋሪዎች መሆኑን ያሳያል። አይሁድ ደግሞ ዐረብኛ ተናጋሪ አይደሉም። ሙሐመድ የተነሣውም ለአይሁድ እና በአይሁድ መካከል አይደለም።
ታዲያ ይህ ከወንድሞቻቸው መካከል የሚነሣ ነቢይ ማን ነው? በአዲስ ኪዳን ይህ ነቢይ ማን መሆኑ በእርግጥና በግልጽ ተጽፎአል። በሐዋርያት ሥራ ይህ የዘዳግም ጥቅስ ሁለቴ የተጠቀሰ ሲሆን (ሐዋ. 3፥22 እና 7፥37) ከሁለቱ በአንዱ በእርግጥ ያ ነቢይ ኢየሱስ መሆኑ በግልጽ ተጽፎአል። ቃሉ የራሱ ምስክር ነውና ቃሉ የሚለውን እናንብብ፤ ሐዋ. 3፥13-26 ይህን ይላል፤

የአብርሃምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ፥ የአባቶቻችን አምላክ፥ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ሊፈታው ቈርጦ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን ብላቴናውን ኢየሱስን አከበረው። እናንተ ግን ቅዱሱን ጻድቁንም ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩን ሰው ይሰጣችሁ ዘንድ ለመናችሁ፥ የሕይወትንም ራስ ገደላችሁት፤ እርሱን ግን እግዚአብሔር ከሙታን አስነሣው፥ ለዚህም ነገር እኛ ምስክሮች ነን። በስሙም በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፥ በእርሱም በኩል የሆነው እምነት በሁላችሁ ፊት ይህን ፍጹም ጤና ሰጠው። አሁንም፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ እንደ አለቆቻችሁ ደግሞ ባለማወቅ እንዳደረጋችሁት አውቄአለሁ፤ እግዚአብሔር ግን ክርስቶስ መከራ እንዲቀበል አስቀድሞ በነቢያት ሁሉ አፍ የተናገረውን እንዲሁ ፈጸመው።

እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም። እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገረው፥ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባልና። ሙሴም ለአባቶች፦ ጌታ አምላክ እኔን እንዳስነሣኝ ነቢይን ከወንድሞቻችሁ ያስነሣላችኋል፤ በሚነግራችሁ ሁሉ እርሱን ስሙት። ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች አለ። ሁለተኛም ከሳሙኤል ጀምሮ ከእርሱም በኋላ የተናገሩት ነቢያት ሁሉ ደግሞ ስለዚህ ወራት ተናገሩ። እናንተ የነቢያት ልጆችና እግዚአብሔር ለአብርሃም፦ በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ ብሎ፥ ከአባቶቻችን ጋር ያደረገው የኪዳን ልጆች ናችሁ። ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።

ያ ከወንድሞቻችሁ መካከል የተባለው ነቢይ ሌላ ማንም ሳይሆን ኢየሱስ ነው።

ዘላለም ነኝ።
"ነውነኛ ድርጊት የፈፀመው የ30 ዓመት ወጣት"🙈

(ስለወጣቱ የተነገሩ አንዳንድ አስተያየቶች)

* "ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የ30 አመት ወጣት በተገኘበት መገደል አለበት"
የ tiktok ሰባኪዎች🤳

* "የ30 አመቱ ወጣት እጅግ አሳፋሪ በሆነ መንገድ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አስነዋሪ ድርጊት ፈፀመ"
የ Facebook ቅዱሳን🤳

* " የሃይማኖት ተቋማት ተከባብረውና ተቻችለው በሚኖሩባት ሃገራችን ውስጥ የተፈፀመው ይህ ነውር ሃይማኖታችንን እንደማይወክል እንገልፃለን።"
የሃይማኖት ተቋማት

* " እንዲህ አይነት ግለሰቦች ላይ መንግስት እርምጃ ሊወስድ ይገባል።"
አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች😂

- ይህ "ነውር" በተፈፀመ ጊዜ Facebook , tiktok , YouTube 📱💻📹..... ያለመኖራቸው በጀው እንጂ ከላይ ያነበባችኋቸው ተቃውሞዎች የሚዘንቡበት የ30 አመት ወጣት ማን ይመስላችኋል?? ኢየሱስ ነው😭

- ጊዜው የዛሬ 2000 አመት ገደማ ነበር። ወጣቱ ኢየሱስ ለፀሎት ወደ ቤተመቅደስ ሲያቀና ያልጠበቀው ጉድ ገጠመው። ሽቀላው ጦፏል! እንስሳት ይቸበቸባሉ🐓🕊🐏 ! የገንዘብ ዝውውሩ ደርቷል!💰💵💶 ሸቀጣሸቀጥ የፀሎት ስፍራውን ሞልቶታል .....
ምእመናኑ የተበላሸውን የቤተ መቅደስ ስርአት ባላየ ያልፉታል! ታድያ በዚህ ድምፅ እንኳን ተቀንሶ በሚወራበት"ቅዱስ ስፍራ" ኢየሱስ ምን ቢያደርግ ጥሩ ነው?? ጅራፍ ሰርቶ የቤተመቅደሱን ነጋዴዎች ገረፋቸው፣ ገፈተራቸው😁 ፣ የሚሸጧቸውን እንስሳት ፈቶ ለቀቀባቸው፣ ቁሳቁሶቹን ገለባበጣቸው.... በቃ! መቅደሱን አተረማመሰው። አመሰቃቀለው።
ከአንድ ሃይማኖተኛ የማይጠበቅ "ነውረኛ ድርጊቶችን" ፈፀመ።

አስቡት እስቲ አሁን በኛ ዘመን ወደ እናንተ የሃይማኖት ስፍራ መጥቶ ንዋያተ ቅድሳትን ቢገለባብጥ🙄 ጭራሽ ነጋዴዎቹን ልግረፍ ቢል።
"የመቅደሱን ስርአት የማያከብር ዱርዬ ትውልድ መጣብን " መባሉ አይቀርም😂😂

- ከዛ ኢየሱስን እዩትማ ፥ መቅደሱን ገለባብጦ ሲያበቃ ምን ቢል ጥሩ ነው? " እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝ'ና እኔን ምሰሉ"🙄🙄🙄

አየህ በኢየሱስ ቋንቋ ትህትና ማለት ድምፅ ቀንሶ ማውራት፣ ያሸከሙህን ሁሉ በፀጋ መሸከምና ስህተቶችን በዝምታ ማለፍ ... አይደለም። ትህትና መገልበጥ ያለበትን መገልበጥ ነው።💪መገረፍ ያለበትን መግረፍ ነው።💪 መገፍተር ያለበትን መገፍተር ነው።🤼‍♂️

© በቃሉ ግርማ
ዛሬ ይጀምራል 🙏
ዛሬም ይቀጥላል
The Renewal We Expect - Hawassa_240214_103442.pdf
289.5 KB
@ኮንፍረንስ ሪቫይቫል፦ የሚናፈቀው ተሃድሶ

(Revival:- The Renewal We Need or Expect)
ዛሬም ይቀጥላል
ይምጡና ይካፈሉ
“ትልልቆችን” በመያዝ ትልቅ የሚኾን ክርስትና የለንም!

ዘመኑ የውድድር ዘመን ስለመሆኑ በብዙ መልኩ ይነገራል፡፡ “ቀድሞ መገኘት ነው!” የሚል አስቀዳዳሚ ማስታወቂያ የትም የሚሰማ ነው፡፡ በዚህ ዘመን ሁሉም ነገር ውድድር መስሏል፤ ሁሉም ነገር ስል ሃይማኖትንም ይጨምራል፡፡ እንደውም ሃይማኖታዊ እሽድምድም ከብዙው ነገር ይልቅ ከፍተኛውን ቦታ ሳይዝ አይቀርም፡፡

የእኔ ሃይማኖት በላጭ ነው የሚለውን ለማስረገጥም ይሁን የእኔ አገልግሎት የተሻለ ነው ለማለት የሃይማኖት ሰዎች በእነርሱ ዙሪያ ያሉትን ታዋቂ ሰዎች እንደ ሰንደቅ ዓላማ ከፊት ከፍ አድርገው ያሰልፋሉ፡፡ ኦ#ርቶዶክሱ ተመለስኩ የሚለውን “መጋቢውን” ይዞ የእምነቱን ትልቅነት ሊለፍፍ ይሞክራል፤ ጴንጤው ሼሁን እና ቄሱን ይዞ ግዳይ እንደጣለ ሊፎክር ይዳዳዋል፤ እ#ስላሙ ቄሱን ወይ መጋቢውን ይይዝና ወደ እውነተኛይቱ ኑ የሚል ጥሪውን ያስተጋባል፡፡ ያው እነ ታዋቂ እና ተደናቂ እገሌዎች የሃይማኖቱ እውነተኝነት መለኪያ ማስረጃ መሆናቸው ነው፡፡ አሳዛኙ ነገር በዚህ መልኩ ታላቅ የሚሆን ሃይማኖት አለመኖሩ ነው፡፡

በሌላ ጎኑ ደግሞ ከዓለም አካባቢ ወደ ሃይማኖት ቤት የሚመጡ ታዋቂ ሰዎች ወይ ዘፋኞች አልያም ከአርትጋ ተያይዞ በየሚዲያው የገነኑ ሰዎች ናቸው፡፡ መቸም እንዲህ ያሉ ሰዎች ወደየእምነታችን ሲመጡ ደስ ማሰኘቱ አይቀሬ ነው፤ በአንድም በሌላም በዓለም ሳሉ የሚያደንቋቸው ሰዎችም የእነሱን መንገድ ለመከተል ይወሰወሱ ይሆናል (ይህንን እንደ በጎ አጋጣሚ መቁጠር ይቻልም ይሆናል)፡፡ ሆኖም ግን የእነዚህ ሰዎች ወደ ሆነ የእምነት ክፍል መምጣት የአንድን ሃይማኖት ትልቅነት አስረጋጭ ሊሆን አይችልም፤ ብዙዎቹ ታዋቂነታቸውን እንጂ ዐዋቂነታቸውን እርግጠኛ መሆን አይቻልምና፡፡ በተለይ የክርስትና እምነት በተከታዮቹ ሳቢያ ትልቅ ሊሆን የሚችል እምነት አይደለም፡፡

ክርስትና ከመሠረቱ እግዚአብሔር አምላክ የዓለምን የሆነውን ነገር ለማሳፈር ያልሆነው ነገር የተመረጠበት እምነት ነው፡፡ የክርስትና ጀማሪ እና ሐዋሪያ የሆነው ጌታችን የክርስትና እምነት አስቀጣይ የሆኑት ሐዋርያቱን ሲጠራ የሄደበት መንደር፣ ሄዶም የጠራቸው ሰዎች በእውነት የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ በቃ አንዳች ትምክህት ሊኖር አይችልም! ነገር ሁሉም ከጠሪው እንጂ ከተጠሪዎች አይደለም፡፡

በክርስትና እምነት ውስጥ ለታላቅነቱ ፍጻሜ የሌለው አንድ ትልቅ ብቻ አለ፤ ክርስትናችንም ከእርሱው የተነሳ ትልቅ ነው፡፡ እምነታችንን በእርሱው እንጂ በእነእከሌ ለማስተዋወቅ መሞከር መኮሰስ ነው፡፡ ሸንበቆ የሆነ ስጋ ለባሽ ማንም ቢኾን ተሰባሪ ነው፡፡ ማንም ከእዚህ ወደ እዚያ እየተመመ የእውነት አምድ መሆን አይችልም፡፡ እገሌ መጣ፤ እገሊት ሄደች የሚለው ሃይማኖታዊ ብሽሽቅ ራስ ከሆነው ከማራቅ በስተቀር ሌላ ፋይዳ የለውም፡፡

ክርስትና በደም የጸና እምነት ነው፡፡ በሞተው እና በተነሳው፤ እራሱ በቀጠረው ቀንም በሚመጣው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተመሥርቷል፡፡ ማንንም ወደ ክርስትና ለመጥራት ክርስቶስ በቂና ከበቂ በላይ ነው፡፡ በእምነታችን ያለን ትምክህት ሁሉ ከእርሱ እንጂ ከሌላ ሊመነጭ አይገባም፡፡ እንደ ውሃ ከሚዋልሉ ሰዎች ላይ እምነታችንን እናንሳ፤ በጸናው በእርሱ ላይ ልባችንን እናጽና!!!

Sintayehu Bekele 🙏🙏🙏
He knew what we were before conversion...wicked, guilty, and defiled; yet He loved us. He knows what we will be after conversion...weak, erring, and frail; yet He loves us.

-J.C. Ryle
ከእምነታችሁ ጋር ስትታገሉ፣ ነፍሳችሁ በአስጨናቂ ጨለማ ስትዋጥ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ባላችሁ ግንኙነት ግራ ስትጋቡ፣ ወደ ቅዱሳት መጽሐፍ ሽሹ! እግዚአብሔር መንፈሰ ቅዱስ የሚናገራችሁ፣ ነፍሳችሁን የሚያገለግለውና አስቀድሞ የሰጣችሁን እምነት የሚያጠናክረው በእነዚህ ገጾች አማካኝነት ነው።

RC Sproul
ወርሃዊው መንፈሳዊ የስነፅሁፍ ምሽታችን ቅዳሜ ይደረጋል። መጥተው ይካፈሉ።
“ክርስቲያን፥ የሆነውን ሁሉ ከመሆኑ በላይ ክርስቲያን ነው። ባለ እምነት ፣ ባለ መፅሐፍ እና ባለ ተልዕኮ ነው። ብልህ ክርስቲያን ይህን የወቅት “ልታይ ልታይ” ባይነት አባብሎና ገስፆ ፥ ወቅቱን በዘላለሙ ዋና ውቅር ላይ ያስቀምጣል። ተገቢው ቦታውንና ቅርፁን ይሰጠዋል። ይህን የሚያደርገው ለወቅትም ለዘላለምም ሲል  ነው።
ክርስቲያንነት ወቅታዊነትን በዘላለም አንፃር ዛሬን ማየት ነው። ዛሬን መተርጎም መቻል ነው። ለዛሬ ጥያቄ የሚደመጥ ዘላለማዊ መልስ መስጠት ነው።” 


ንጉሴ ቡልቻ፤ ወቅታዊ_ዘላለማዊ ገፅ ፬