የሮም ነፍሰ ገዳይ ስብስብን ያሸነፉ
የአንበሳ ሰማዕታት
ክፍል አራት
"Gods Generals -The Martyrs -By Robert Liyardon"
ትርጉም: ቢቶ (@Bito45tesfu44)
$$$
ብላዲናና ከእርስዋ ጋር የታሰሩት 48ንቱም ክርስቲያን እስረኞች ከተገደሉ በኋላም ክርስቲያኖችን የማሳደድ እብደቱ አላቆመም ነበር፡፡ ይብሱኑ እየተፋፋመ መጣ እንጂ፤ በክርስቲያኖች ላይ የተቆጣው ህዝብም ሰማዕታት የሆኑት ክርስቲያኖች እንዳይቀበሩ አደረጉ፡፡ ሬሳዎችን ለዱር አውሬዎች በመተው ህዝቡ ያፌዝ ጀመር
‹‹አምላካቸው የት አለ? ሀይማኖቸውስ ምንድን ነው? ከሕይወት ይልቅ የመረጡት የት አለ? ምንስ ጠቀማቸው?›› ይሉ ነበር
በመጨረሻም ከዱር እንስሳቱ የተረፉትን ሬሳዎች በጅምላ አቃጠሉዋቸው፡፡ በአሸናፊነት መንፈስም ድላቸውን አከበሩ፡፡ ዱካቸው ለአንዴና ለመጨረሳ ጊዜ በምድር ላይ እንዳይኖር በማሰብ የሰማዕታቱን አመድ በመውሰድ በርሆኔ ወንዝ ላይ በተኑት፡፡
በሊዮን የሚገኘው ሕዝብ እብደቱ አታሎት ነበር ይህን ያህል ጭካኔ በክርስቲያኖቹ ላይ ለምን ማድረስ እንዳስፈለጋቸው እንኳን በቅጡ አልተረዱትም፡፡ አስክሬናቸውን ወደ አመድነት ቀይረው ከምድረገፅ ለማጥፋት በወንዙ ላይ በመበተናቸው ተስፋቸውንና የሙታን ትንሳኤ እንዳያገኙ ማድረግ የሚችሉ መስሏቸዋል፡፡ እንዴት ሰው በዚህ ልክ ሊሳሳትና ሊታለል ይችላል? ምክንያቱም የሰይጣን ተከታዮች ስለነበሩ ነው፡፡ የመጨረሻው ድል ግን የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
የሊዮን ክርስቲያን ሰማዕታት ሁሉም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመጣ በክብር ይነሳሉ አሳዳጆቻቸው ግን ይህን ለማስቀረት ይሞክራሉ፡፡
የጋውል/የሊዮን ሚሲዮናውያን
እ.አ.አ 117 ዓ.ም በጥንትዋ ጋውል በአሁንዋ ሊዮን የነበረው አስከፊው ስደት ለአስር ዓመታት ያህል ጋብ ብሎ ነበር፡፡ የክርስቲያኖች ሰማዕትነትና ለእግዚአብሔር የነበራቸው ፍቅ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አዲስ አማኞችን ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ ያስቻለ ነበር፡፡ በወጣትነቱ የፖሊካርፕን ትምህርት የሰማው የሰምርኔሱ ክርስቲያንና ይቅርታ ጠያቂው ኢራኒየስ የሊዮን ቀጣዩ ሊቀነ ጳጳስ ሆኖ ተሾመ።
ለሃያ አምስት አመታት ያህል የክርስቲያኖች ቆራጥ መሪ የነበረው ኢራኒየስ ለጋውል ማህበረሰብ ስለኢየሱስ ክርስቶስ በድፍረት መናገርና መስበክ ጀመረ፡፡ በዚህም አገልግሎቱ አያሌ ክርስቲያኖችን ለሚሽነሪ አገልግሎት አነሳሳ በዚህም ምክንያት የክርስቶስ ወንጌል ከሊዮን ከተማ ተነስቶ መላ የፈረንሳይን ግዛት አዳረሰ፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለሚገኘው ዘላለማዊ ድነት በመስበክ አዳዲስ የክርስቲያን ማህበሮችን አቋቋመ፡፡
በዚህ ብቻ ያልተገደበው ኢራኒየስ በቤተክርስቲያን ውስጥም እየታየ ስላለው የሀሰት ትምህርትም የአቅበት እምነት አገልግሎትም ያገለግል ነበር፡፡ በዚህም አገልግሎቱ የግኖስቲሲዝምን ትምህርት እርቃኑን ያስቀረ ሲሆን ሌሎች በመጀመሪያዎች ዓመታት ሲታዩ የነበሩ የሀሰት ትምህርቶችንም በሚገባ ተከላክሏል፡፡ ምንም እንኳን ግኖስቲኮች ራሳቸውን ክርስቲያን ነን ብለው ቢጠሩም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር በስጋ እንደመጣ ይክዳሉ ያም ብቻ ሳይሆን መከራን የተቀበለ፤ የተቀበረ እና የተነሳ ስጋ የለውም ብለው ያስተምራሉ፡፡ ኢየሱስ በምድር ሲመላለስ በፍፁም አምላክነቱ እንጂ በፍፁም ሰውነቱ አይደለም ይላሉ፡፡ ግኖስቲኮች መዳን የሚያገኙት ጥቂት የተመረጡት ብቻ እና ግኖሲስ ለሆነ ወይንም የመንፈሳዊው አለም ሚስጥር ለተገለጠላቸው ብቻ እንደሆነ ሲያስተምሩ ነበር ይህንትምህርታቸውን በመመከት ቅዱስ ኢራኒየስ ትልቅ ሚና ተወጥቷል፡፡
የክርስያኖች እንቅስቃሴ እየሰፋና እያደገ በመጣበት ወቅት ግን ሌላ አሳዛኝ ክስተት ተከሰተ፡፡ እ.አ.አ 202 ዓ.ም በንጉሠ ነገሥት ሴፕቲሚየስ ሴቭረስ ዘመን በሊዮን/ጋውል አምፊቲያትር ውስጥ ደፋሩና ለክርስቶስ ወንጌል ቀናተኛው ጳጳስ ቅዱስ ኢራኒየስ በሰማዕትነት አለፈ፡፡ …. ይቀጥላል
@senpareAdisketemaFGC

ክፍል አምስት

*-*-*-*-*-*-*-*-*
የክርስያኖች እንቅስቃሴ እየሰፋና እያደገ በመጣበት ወቅት ግን ሌላ አሳዛኝ ክስተት ተከሰተ፡፡ እ.አ.አ 202 ዓ.ም በንጉሠ ነገሥት ሴፕቲሚየስ ሴቭረስ ዘመን በሊዮን/ጋውል አምፊቲያትር ውስጥ ደፋሩና ለክርስቶስ ወንጌል ቀናተኛው ጳጳስ ቅዱስ ኢራኒየስ በሰማዕትነት አለፈ፡፡
ከበርካታ አስርት አመታት በኋላ የሮም ቢሾፕ ፋቢያን የሰማዕቱን ቅዱስ ኢራኒየስን ስራ እንዲያስቀጥሉ ወደ ሰባት የሚደርሱ ሐዋርያትን ሚሲዮናዊ አድርገው ወደ ጋውል ላኩ፡፡ እነዚህም ሚሲዩኒያውን በዛሬያይቱ ፈረንሳይ በመላው በሚባል ደረጃ የክርስቲያን ማህበረሰቦችን አቋቋሙ፡፡
እ.ኤ.አ በ240 ዓ.ም ንጉስ ዴሲየስ ንጉሰ ነገስት ሆኖ ዘውድን ጫነ፡፡ ከርሱ ቀድመው እንደነበሩት ሌሎች የሮማ ንጉስ ነገስታት ዴሲየስም የክርስቲያኖችን በመላው ግዛት መስፋፋት ለማስቆም የራሱን መንገድ ከመፈለግ ወደ ኋላ አላለም፡፡
ንጉስ ዴሲየስ ከላይ ጀምሮ ያሉ ሁሉም የክርስቲያን መሪዎች ሮማውያን አማልክት እንዲያጥኑና እንዲያመልኩት በዚህም ለስርዓቱ ያላቸውን ታማኝነት ማረጋገጥ እንዲችሉ አስገዳጅ ትዕዛዝ አወጣ፡፡
የሮም ኤጲስ ቆጶስ የሆኑት ቅዱስ ፋቢያን ግን ለዚህ ትዕዛዝ ለመገዛት ፍቃደኛ አለመሆናቸውን አረጋገጡ፡፡ ለሮማውያን አማልክት እንደማይሰግዱ አረጋገጡ፡፡ በዚህም የተነሳ ንጉስ ዴሲየስ ፋቢያንን በመግደል ለሌሎች ክርስቲያኖች ምሳሌ ሊያደርጋቸው በውሳኔው ፀና፡፡ እ.ኤ.አ ጥር 20/250 ዓ.ም ላይ ፋቢያንን አስገደለ፡፡ ቅዱስ ፋቢያንም በካታኮምቡ ተቀበረ፡፡ በመቃብሩ ላይ በግሪክ ቋንቋ የተፃፈው እስከዛሬ ድረስ በጉልህ ይታያል ‹‹ሰማዕቱ ጳጳስ ፋቢያን›› ይላል፡፡ በእርግጥ ቅዱስ ፋቢያን ሽልማቱ በሰማይ ተዘጋጅቶለታል፡
ብዙ የክርስቲያን መሪዎች የዴሲየስን ትዕዛዝ ለመታዘዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እና የራሳቸውን የሞት ማዘዣ በመፈረም የቅዱስ ፋቢያንን ፈለግ ተከተሉ። የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን እያደገች ከመምጣት ማንም ሊከለክላት አልቻለም - የገሃነም ደጆችም ሊቋቋሟትም አልቻሉም፡፡
ፔርፑታና ፌልሲቲ ከአውሬዎቹ ጋር ፊት ለፊት
በቀደመችው ቤተክርስቲያን ውስጥ ከነበሩት እጅግ አስደናቂ የሰማዕታት ታሪኮች አንዱ በሰሜን አፍሪካ የተከሰተው ነው።
ይህም ታሪክ በካርቴጅ የምትኖር ሮማዊት ወጣት ሴት ማስታወሻ ደብተር ውስጥ የተገኘ ታሪክ ነው። በአሬና ውስጥ ከመገደሏ በፊት ባሉት ሳምንታት ውስጥ ከእስር ቤት ሆና የጻፈችው ታሪክ ነው።
ስሟም ቪቢያ ፔርፑታ ይባላል። ከአንድሺህ ስምንት መቶ አመታት በፊት መዝግባ ያስቀመጠቻቸው ፅሁፎችዋ በአለም አቀፍ ደረጃ በብዙ ክርስቲያኖች ዘንድ ተነበውላታል።
በ3ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ ወቅት ካርትሬጅ በሮም ኢምፓየር ዘመን ከሮም በመቀጠል ታዋቂዋና እጅግ የበለፀገች ሁለተኛዋ ከተማ ነበረች።
ካርቴጅ በሰሜን አፍሪቃ በአሁንዋ ቱኒዚያ የምትገኝ ከተማ ናት። ሮማውያን በቀላሉ ወደአፍሪካ ለመግባት ያመቻቸው ዘንድ እጅግ ያማረ ወደብ ሰርተውባት ነበር።
እ.ኤ.አ. በ203 ዓ.ም የሮማው ገዥ ሂላሪያኖስ ፖለቲካዊ ሽግግር እያደረገ ነበር የሮማ ንጉሰ ነገስት ሆኖ ይሾማል። በዚህም ጊዜ ጌታ የተሰኘውን ታናሽ ልጁን ልደት በካርቴጅ ለማክበር አቅዷል።
በዚሁ ጊዜ በካርቴጅ የምትገኘው የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በማደግ ላይ ነበረች። ከታላላቅ የቤተክርስቲያን የሃይማኖት ሊቃውንት አንዱ የሆነው ተርቱሊያን (160-220 ዓ.ም.) በካርቴጅ ውስጥ ይኖር ነበር። ተርቱሊያን ጎልቶ መውጣት የቻለ ክርስቲያን አስተማሪ ነበር።
ተርቱሊያን ስለ መንፈስቅዱስ ኃይልም በሰፊው ጽፏል እንዲሁም (ትሪኒቲ) "Trinity" የተሰኘውን የላቲን ቃል የእግዚአብሔር አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድነት ለማሳየት የተጠቀመ የመጀመሪያው ክርስቲያን ጸሐፊ ነበር። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ( #ሥላሴ )።
የመንፈስ ቅዱስ መገኘት አሁንም በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል በምልክትና በድንቅ፣ በትንቢት እና በራእይ እንደሚንቀሳቀስ አጥብቆ ያምን ነበር። ተርቱሊያን የአንበሳን ድፍረት የታደለ ስለነበር የክርስትናን እምነት ተከላክሏል። ለአገረ ገዥው ሒላሪያኖስ በApologeticus ላይ የተመዘገበውን ድፍረት የተሞላውን ደብዳቤ ፅፏል። በዚህም ፅሁፉ እያደገ ስለመጣው የክርስቲያኖች ህብረት እና ስላላቸው ጠቀሜታ በተጨማሪም በሮም አገዛዝ ውስጥ ሰለሚያበረክቱት አስተዋዕፆ ጠቅሷል። እንደዚሁም የክርስትና እምነት ከመቶ አመት በፊት እንደ ተመሠረተና ሁሉንም ስፍራዎች መሙላታቸውን አስፍሯል።
"እኛ በመካከላችሁ የሌለንበት ስፍራ የለም በከተሞች፣ በደሴቶች፣ በምሽጎች፣ በገበያ ቦታዎች፣ በጦር ካምፕ፣ በኩባንያዎች፣ በቤተ መንግስት፣ በሴኔት በሁሉም ስፍራዎች አለን ከጣዖቶቻችሁ ቤተመቅደስ ውጪ" ይላል የደፋሩ ተርቱሊያን ፅሁፍ።
በዚህ ጊዜ የሮም አገዛዝ 'ክርስትናን ለማጥፋት' አዲስ ሙከራ ለመተግበር ተነሳ።
ይቀጥላል

ክፍል ስድስት

ክርስቲያኖች እያበረከቱ ስለነበረው አስተዋዕፆ የሮም መንግስት ግድ አልነበረውም። የክርስትና ሀይማኖት መስፋፋትና የክርስቲየያኖች ትጋት በሮማውያን ዜጎች ዘንድ መወደዱ ስጋትን ፈጠረባቸው በዚህም ምክንያት ንጉሰ ነገስት ሰርቨረስ እንደቀደሞቹ ሁሉ ሊያጠፋቸው እቅድን አወጣ።
የንጉስ ሰርቨረስ እቅድ ከሌሎቹ የተለየ ነበር ክርስቲያኖችን ከማሳደድ ይልቅ አዲስ ህግ አወጣ «ማንኛውም ሮማዊ ዜግነት ያለው ሁሉ አዲስ የተለወጠ ክርስቲያን መሆን አይችልም» ይላል። ማንም ወደ ክርስትና እምነት ሀይማኖቱን መቀየር እንደማይችል ደነገገ።
በቀደመችው ቤተ ክርስቲያን አዳዲስ ደቀ መዛሙርት - ክርስቲያን ለመሆን ከፈለጉ በውሃ ከመጠመቃቸው እና ወደ ቤተ ክርስቲያን ከመጨመራቸው በፊት ቅዱሳት መጻሕፍትን መማር እና በኢየሱስ ማመን ነበረባቸው።
በንጉስ ሰርቨረስ በአዲሱ የሮማውያን ሕግ መሠረት ክርስቲያን ሆኖ የተጠመቀ ማንኛውም ሰው ተይዞ ይገደላል። በዚህ ጊዜ ነበር ሁለቱ ወጣት የእምነት አርበኛ ሴት ክርስቲያኖች የተገኙት ፔርፑታና ፌልሺቲ ይባላሉ።
የፔርፑታ የሕይወት ምስክርነት የሚነግረን ምንም ዋጋ ቢያስከፍል ክርስቶስን ለመከተል ስለወሰነችና ወደ ክርስትና ስለተለወጠች አንዲት ወጣት ሴት ነው። የሚያነቃቃ ታሪክ ባለቤት ናት ፔርፑታ።
ከሮማዊ መኳንንትና ከጤና ባለሙያ እናትዋ የተወለደችው ቪቢያ ፔርፑታ የሃያሁለት አመት ወጣት ሴት ናት። በሮማውያን ባሕል አባቶች ሴት ልጆቻቸውን (ያገቡትንም እንኳ) በእርጅና ዘመናቸው እንዲንከባከቧቸው ይጠበቃል፤ እንዲሁም ሴት ልጆች አባቶቻቸውን እንዲያከብሩ እና ቤተሰቡ በጋብቻ ውስጥ ያለውን ማህበራዊ ተሳትፎ እንዲያሻሽሉ ይጠበቅባቸው ነበር። በፔርፑታ ማስታወሻ ውስጥ ስለአባትዋ እንጂ ስለባልዋ የሰፈረ ነገር አልተገኘም።
በአንድ ሀብታም ሮማውያን ቤተሰብ ውስጥ እንደሚስትና እንደ እናት ሆና ለአባትዋ በመታዘዝ በምቾት ውስጥ በሕይወት በመቆየት ልጇን የምታሳድግበት እድል የነበራት ቢሆንም ጥልቅ ከነበረው ቤተሰባዊ ግንኙነት ይልቅ ፔርፑታ አንድ አስደንጋጭ ውሳኔ ወሰነች በጀግንነት ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል መረጠች።
ፔርፑታ ክርስቶስ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ በተናገረው የእውነት ቃል ላይ ፀንታ ቆማለች «ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል። ማቴ 19፡29»
የፔርፑታ ምስክርነት የባሪያዋ የፌሊሺቲ ታሪክም ነበር። አንዳቸው ለሌላው እና ለኢየሱስ ያላቸው ክርስቲያናዊ ፍቅር በካርቴጅ ውስጥ ጠንካራ መገለጫ ሆኗል። መኳንንትና ባሪያዎቻቸውን በሚመለከት የክርስቲያን ማህበረሰብ የነበራቸው ትስስር ከሮማውያን ሕግጋት የበለጠ ጠንካራ ነበር። በእስር ላይ በነበረችበት ጊዜ የስምንት ወር ነፍሰ ጡር የነበረችው ፔርፑታ እና ፌሊሺቲ በሰማዕትነት እኩል ቀርበዋል።
እነዚህ ሁለት ወጣት እናቶች የእናትነት ስሜታቸውን ብቻ ሳይሆን ኃይለኛውን የሮማውያን ማህበራዊ መዋቅርንም በክርስቶስ በመሆን አልፈዋል። ልክ ጳውሎስ ለገላትያ ቤተ ክርስቲያን፡- “አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።” (ገላትያ 3፡28) በማለት ተናግሯል። ይህች ደፋር ሴት በእውነትም “በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት” ሆናለች።
ምንም እንኳን በሮማውያን እጅ ጭካኔ የተሞላበት ስደት ቢኖርም፤ መንፈስ ቅዱስ በካርቴጅ አማኞች መካከል በሙላት ይንቀሳቀስ ነበር። ፔርፑታና ፌሊሺቲን ጨምሮ በመጀመሪያ የተያዙት የሰማዕታት ቡድን በቁም እስር ላይ እንዲሆኑ የተፈለገበት ምክንያት ካቴቹመን እና ገና ያልተጠመቁ ስለነበረ ነው። በውኃ ላለመጠመቅ ከወሰኑና ይልቁንም ለንጉሠ ነገሥቱ ክብር ከሰጡ ከቁም እስረኝነት ነፃ መውጣት ይችሉ ነበር።
ፔርፑታ ከመሞትዋ በፊት በእስር እያለች ትፅፋቸው የነበሩ ፅሁፎችዋን ለአንድ ለማይታወቅ አርታኢ በድብቅ ከእስር ቤት ትልክ ነበር። (ብዙ ስኮላሮች ይህ አርታኢ ተርቱሊያን እንደሆነ ያምናሉ) ስለፅሁፎችዋና ስለአማሟትዋ የአይን እማኞች የነበሩ ክርስቲያኖች ያሰፈሩት ዘገባ ዛሬ ላለነው ከርስቲያኖች ተሰንዶ ተቀምጧል።
በእርግጥም “The Passion of Perpetua and Felicity” የተሰኘው ፅሁፍ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በሴት የተፃፈ ጥንታዊ ታሪክ ነው።
ፔርፔታ ፅሁፍዋን ገና በእስር ቤት እያለች ከአባቷ ጋር ባደረገችው ውይይት ትጀምራለች
«አባቴ ከእኔ ፍቅር የተነሳ ሊያባብለኝ እና ውሳኔዬን ሊያስለውጠኝ ይሞክር ነበር። . . .» ይቀጥላል

ክፍል፡ ሰባት

ፔርፑታ በቤትዋ በቁም እስረኝነት ባለች ጊዜ ከአባትዋ ጋር ያደረገችውን ምልልስ ነው በማስታወሻ ደብተርዋ በመጀመሪያ ገፅ ላይ ያሰፈረችው
«አባቴ ለኔ ከነበረው ፍቅር የተነሳ ይንከባከኝና ሀሳቤን ለማስቀየር ይጥር ነበር . . . አንድ ቀንም
“አባቴ” አልኩት መልሼም
“ይታዩሃል እነዛ እቃዎች ለምሳሌ ያ የውሃ ማጠጫ ብቻ እዛጋ ያሉ እቃዎች ይታዩሃል?” አልኩት በጥያቄ
“አዎ ይታዩኛል” አለኝ
እኔም እንዲህ ብዬ ጠየቅሁት
“እነዛን እቃዎች ከሚጠሩበት ስያሜ ውጪ ልንጠራባቸው የምንችላቸው የተሻለ ስያሜ እናገኝላቸዋለን?”
“በፍፁም። “ አለኝ
“በጣም ጥሩ! የእኔም ነገር ተመሳሳይ ነው፥ አኹን ከምጠራበት የተሻለ ስያሜ አይገኝልኝም። ክርስቲያን ነኘ!” አልኹት። «ክርስቲያን» የሚለውን ቃል የሰማው አባቴ በጣም ተቆጣ ወደ እኔም በመጠጋት አይኖቼን ጎልጉሎ ለማውጣት ተቃርቦ ነበር ቢሆንም ትቶኝ ሄደ ይኹን እንጂ ከዚያን ጊዜ በኋላ ዲያብሎሳዊ በሆነው ክርክሩ ሊረታኝ ይሞክር ጀመር።» ይላል ማስታወሻ ደብተርዋ ላይ ያሰፈረችው።
ከጥቂት ቀናት በኋላ በቁም እስረኝነት በቤትዋ ውስጥ የነበረቸው ፔርፑታና ሌሎች አያሌ ክርስቲያኖች በውሃ ጥምቀት ተጠመቁ። ይህም ድርጊታቸው ክርስቲያኖች መሆናቸውን ያረጋገጡበት ብቸኛው መንገዳቸው ነበር። ባለስልጣናቱም እነፔርፑታ እንዲታሰሩ ትዕዛዝ አወጡ።
«ተሸብሬ ነበር፥ ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ጨለማ ክፍል ውስጥ ተገኝቼ አላውቅም። ለኔ በጣም ከባድ ጊዜ ነበር። ከመተፋፈናችን የተነሳ ሙቀቱ በጣም ያስጨንቀን ነበር። በዚያ ላይ እኛን ለማሳመን ወታደሮቹ ያሰቃዩን ነበር። ከምንም በላይ ግን ቤት ትቼ የመጣሁት የህፃን ልጄ ሁኔታ ያሳስበኝ ነበር።
ቴርቲየስ እና ፖምፖኒየስ የተባሉ ሁለት ዲያቆናት የእኛን ጉዳይ ይከታተሉ ነበር። ወታደሮቹ ለጥቂት ሰዓታትም ቢሆን በእስርቤቱ በተሻለው ስፍራ ላይ መቆየት እንድንችል እንዲፈቅዱ ጉቦ እስከመስጠት ደርሰው ነበር። ወታደሮቹ ይፈራረቃሉ ሁሉም ግን በዚያ ጨለማ ክፍል ውስጥ ይተውናል። የልጄ ሁኔታ ግን ያስጨንቀኛል በርሃብ ምክንያት ራሱን በሳተበት ወቅት የመጀመሪያ እርዳታ የሰጠሁበት ቅፅበት ትውስ ብሎኛል። እናቴን ስለልጄ ሁኔታ ላወራት ሞክሬአለሁ፤ ወንድሜ እያደረገ ባለው ነገር ተፅናንቼአለሁ፤ ልጄን እንዲንከባከቡት ለወላጆቼ ሰጥቼ ነበር ቢሆንም ግን በኔ ምክንያት ትንሽም ቢሆን ቤተሰቤ ላይ እየደረሰባቸው ባለው ነገር ተጨንቄ ነበር። እያሳለፍኩት የነበረው ጊዜ ለኔ እንደሙከራ ነበር ቀጣይ ለሚመጣው ነገር ራሴን እንዳጠክርበት። ከህመሜ ማገገም ጀመርኩ፤ በመጨረሻም ስፈራና ስጨነቅበት ከነበረው ሁኔታ የተወሰነ እረፍት አገኘኹ ምክንያቱም ልጄ ከእኔ ጋር በእስር ቤት እንዲሆን ፍቃድ ተሰጠኝ። ነገሮች በድንገት ተለወጡ እስርቤቱ ቤተመንግስት ሆነልኝ፤ ከየትም ስፍራ ይልቅ በእስር ቤቱ መቆየትን መረጥኹኝ።» ትላለች ፔርፑታ በማስታወሻዋ
በዚያ በጨለማ ክፍል ውስጥ እያለች ፔርፑታ እግዚአብሔር ራዕይን እንዲያሳያት ትጠይቅ ነበር ጥያቄዋን እግዚአብሔር እንደመለሰላት በማስታወሻ ደብተርዋ ላይ እንዲህ በማለት አስፍራለች
«የሚደንቅ ቁመት ያለው ወርቃማ መሰላል አየሁ። ሰማይ የሚደርስ ቁመትና በጣም ጠባብ ነበር። ከመሰላሉ ስር ትልቅ መጠን ያለው ዘንዶ አድፍጧል። በመሰላሉ የወጡት ይደቃሉ ሊወጡ ያሰቡትም መውጣቱ አስፈርቷቸው በፍርሃት ርደዋል። እኔ ግን እንዲህ ብዬ ጮህኩኝ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ሰም ይህ ዘንዶ ሊጎዳኝ አይቸልም” በዚህ ጊዜ መሰላሉ ስር የነበረው ዘንዶ ሲፈራኝ አየሁ፤ በቀስታም ጭንቅላቱን ወደ ውስጥ አሰገሰገ እኔ ግን ጭንቅላቱን ረግጬ መውጣት ጀመርኩ።»
ከዚህ በኋላ በራዕይዋ አንድ ነጭ የለበሰ ሰው በሚያምር ስፍራ እንኳን ደህና መጣሽ ሲላት ተመለከተች ቦታውም መንግስተ ሰማይ ነበር
የድላቸው ቀን መድመቅ
የድላቸው ቀን ብሩህ ነበር ነግቷል። ከእስር ቤቱ ወደ አምፊቲያትሩ ሲወጡ በሰልፍና በታላቅ ደስታ ውስጥ ሆነው ነበር። ወደ መንግስተ ሰማይ አንደሚሄዱ ቀድሞውኑ አውቀዋል። ከፊታቸው ላይ መረጋጋት ይነበባል። ሁሉም ላይ ከፍርሃት ይልቅ ደስታ ሞልቶባቸው ይታያል።
ፔርፑታ ፊትዋ እያበራ በእግዚአብሔር ፍቅር ተሞልታ በተረጋጋ እርምጃ ትራመዳለች ልክ እንደ ክርስቶስ ሙሽራ። ሌላ አለም ውስጥ ስለነበረቸው በአምፊቲያትር ውስጥ የነበረው ነገር አልተመለከተችውም። አብራት አንዲት ሴት ነበረች ፌሊሺቲ።
ፌሊሺቲ ልጇን በሰላም መገላገልዋ ደስ የሚል ነገር ነበር አኹን ግን ከአውሬዎቹ ጋር ፊት ለፊት ትፋለማለች። ለልጅ ስትል ደምን ከማፍሰስ በሌላ ጉዳይ ደሟን ወደ ማፍሰስ ትሸጋገራለች። አዎን ከአዋላጅ ነርስ ወደ ግላዲያተሮች ተሸጋግራለች።
ፔርፑታና ፌሊሺቲን ጨምሮ ሌሎች በአንድነት በዚያ በአንፊቲያትር ውስጥ ተሰዉ። ከእነርሱ መስዋዕትነት በኋላ ግን በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ምን ተፈጠረ? . . . . ይቀጥላል

ክፍል፡ ስምንት (የመጨረሻ ክፍል)

ፌሊሺቲ ልጇን በሰላም መገላገልዋ ደስ የሚል ነገር ነበር አኹን ግን ከአውሬዎቹ ጋር ፊት ለፊት ትፋለማለች። ለልጇ ስትል ደምን ከማፍሰስ በሌላ ጉዳይ ደሟን ወደ ማፍሰስ ትሸጋገራለች። አዎን ከአዋላጅ ነርስ ወደ ግላዲያተሮች ተሸጋግራለች።
ዘቦቹ ሮማውያንን ቀሳውስት (ጣዖት አምላኪዎቹ) የሚያደርጉትን ልብሶችና ቀሚሶች እንዲለብሱ ይጫኗቸው ጀመር ፔርፑታ ግን ይህን ሀሳብ በፅኑ ተቃወመችው። የወታደሮቹ ስብስብም ዘቦቹ ሀሳቡን እንዲተው አደረጉ
“እኛ እዚህ የመጣነው [ወደ ሞት ፍርድ] በራሳችን ነፃ ፈቃድ ነው። ይህ የእኛ ነፃነት ነው ህግ ሊጣስብን አይገባም። ” አለች መልሳም
“ምንም አይነት ጥፋት አልሰራንም [ጣዖት አላመለክንም] ቢሆንም ጥፋተኛ ናችሁ ተብለን በተከሰስነው ጉዳይ ህይወታችንን ጭምር ልንሰጥ ተስማምተናል።” አለች በዕለቱም ፔርፑታ ያሰማችው ሙግት አሸነፈ።
በሁለቱ ሴቶች በፔርፑታና በፌሊሺቲ መሪነት ወደ አሬናው ወጡ። ሁለቱም ሴቶች በተቆጡ ሴት ላሞች ተወግተዋል። ላሞቹ ቀንዳቸውን አሹለው መጥተው ወደ ላይ ወረወሩዋቸው ከደረሰባቸው ውጊያ የተነሳ ሁለቱም ራሳቸውን ስተው ደንዝዘው ነበር።
አቧራ ከከደነው ስፍራ ፔርፑታ ቀድማ ነቃች እጆቿንም ንፁህ የእህትነት ፍቅር በሚታይበት ሁኔታ አብራት መከራን እየተቀበለች ወደ ነበረችው ፌሊሺቲ ዘረጋች።
ወግታ የጣለቻቸው ላም ከአጠገባቸው ዘወር አለች። የዚህን ጊዜ በአሬናው በስተምዕራብ በኩል ወደ ሚገኘው «የሕይወት በር» እያሉ ወደ ሚጠሩት ስፍራ ሴቶቹ መጓዝ ጀመሩ። ወደ ዚያ በር በሚያመሩበት ጊዜ ፔርፑታ በቅርብ ርቀት ላይ ወደ ነበሩ ክርስቲያኖች ተመለከተች እነርሱም
“በዕምነት ፀንታችሁ ልትቆሙ ይገባል፤ እርስበርሳችሁ ተዋደዱ እየሆነባችሁ ባለው ነገር በፍፁም ተስፋ አትቁረጡ አትድከሙ። ” እያሉ ያበረታቱዋቸው ነበር።
በአሬናው/በሜዳ ውስጥ የነበሩት እንስሳቶች ክርስቲያኖቹን ለማጥቃት ተጨማሪ ፍላጎት ስላልነበራቸውና የግላዲያተሮች ፊልሚያ ሰዓትም ደርሶ ስለነበር ሂላሪየስ በሕይወት የተረፉት ክርስቲያኖች በሰይፍ እንዲገደሉ አዘዘ።
በእንስሳቶቹ ውጊያ ያልሞቱት ሁሉ አንገታቸው በሰይፍ እንዲቀላ ተጠሩ ነገር ግን ለሞት ከመሄዳቸው በፊት እርስ በእርሳቸው በቅዱስ አሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ። ሰማዕትነታቸውን በቅዱስ ሰላምታ አጀቡት።
ፔርፑታ ወደሞት የሚወስዳትን ደረጃ ስትወጣ ለመጨረሻ ጊዜ የዘንዶውን ጭንቅላት እንደረገጠች ተሰማት እናም ራሷን ቀና አድርጋ በፀጋና በሰላም ተሞልታ ደረጃዎቹን ትወጣ ጀመር። ልምድ የነበረው ግላዲያተር መጀመሪያ ላይ በደረሰባት ድብደባ ሊገድላት ስላልቻለ እጁን ወደ አንገትዋ አስጠጋች በዚያች ቅፅበት ሞትዋ ፈጠነ።
ፔርፑታና ፌሊሺቲን ጨምሮ ሌሎች በአንድነት በዚያ በአንፊቲያትር ውስጥ ተሰዉ። ከእነርሱ መስዋዕትነት በኋላ ግን በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ምን ተፈጠረ? አስደናቂ የታሪክ ክስተት።
ከይሁዳ ጥግ የተነሳ ትንሽና የተናቀ እንቅስቃሴ ባባህላዊ ሃይማኖቶችና በጣዖት አምልኮ ለታጠረው ለኃያሉ የሮማ ኢምፓየር ዋና እምነት ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ የማይታሰብ ነበር።
በመጀመሪያዎቹ መቶ ዓመታት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መስፋፋት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከተከሰቱ አስደናቂ ክስተቶች አንዱ ነው።
የመፅሃፍ ቅዱስ ሊቃውንት ከሚደነቁበት ነገር አንዱ አስቸጋሪ የመገናኛ ዘዴዎች በነበሩበትና ከሮም ነገስታት ጭካኔ የተነሳ ስደት ባየለበት በመጀመሪያዎቹ ሶስት መቶ ዓመታት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፈጣን ዕድገት ነበር።
እኛ ግን በዚህ ውስጥ የኢየሱስን ቅዱስ ተስፋ እናያለን “. . . በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። ማቴ 16የተነሳ
የክርስትና እምነት በኢየሩሳሌም ከተማ ተወለደ በሜዲትራንያን ባህር ተስፋፋ። ከጣሊያን በስተምዕራብ ወደታላቅዋ ብርታኒያ በምስራቅ ወደ ግሪክ፣ ሶሪያ እና እስከህንድ፤ በደቡብ ካርቴጅና አሌክሳንድሪያን ይዞ በአፍሪካ እና በሰሜን ወዳሉ ናልካን ግዛቶች እንዲሁም አንዳንድ የሩሲያ ግዛቶች ተስፋፋ።
የእምነት መልዕክተኞቹ ሚሲዮናውያን፣ ሐዋሪያት፣ የተሰደዱ ደቀመዛሙርት፣ ወደ ክርስትና የተለወጡ ነጋዴዎች እና በየግዛቱ የሚኖሩ ክርስትናን የተቀበሉ ተራ ዜጎች በክርስትና መስፋፋት ውስይ ጉልህ ድርሻ ነበራቸው። ሁሉንም ግን የሚያመሳስላቸው ሁለት ነገሮች አሉ፥
የመጀመሪያው ለክርስቶስ ኢየሱስ የነበራቸው ጥልቅ ፍቅር ሲሆን ሁለተኛው በዕምነታቸው ምክያንት ስደትንና ሰማዕትነትን መቀበላቸው ነው።
ተፈፀመ
በቀጣይ በሌላ ታሪክ እንገናኛለን
ተባረኩ🙏

የክርስቶስ ልደትን በማስመልከት ድንቅ ዝማሬ ወንድማችን ዘማሪ አንተነህ አባይነህ አበርክቶልናል እየሰማን
https://m.youtube.com/watch?si=tXzxym-PZ3pHGfZ4&fbclid=IwAR1HDnQlLLPV9yLxJTiyE8ZbJ_5vEHeW_qaCnXx0auuBROVZIRnZUNl4nkM&v=6caDmWR13eU&feature=youtu.be

YouTube
Anteneh Abayneh||ተወለደልን| የገና መዝሙር || አንተነህ አባይነህl | Christmas Song||New protestant song | Marcil tv
Anteneh Abayneh||ተወለደልን| የገና መዝሙር || አንተነህ አባይነህl | Christmas Song||New protestant song|Marcil tv song
presence,presence tv channel,prophet suraphel demissie,presence tv,suraphel demissie,prophet suraphel demissie 2020,prophet suraaphel demissie 2020,presence…

Am I the tree? Am I the river?
፟ዛፍን ነው ወይ የኔ ህይወት? ግንዱን ነች ወይ እቺ ነፍሴ? አዲስ ፍሬ አዲስ ቅጠል ይበቅላል ብስል ጥሬው በገላዬ። በጋ ክረምት ደግሞ ይረግፋል ቀን ጠብቆ ። ሰው ይመጣል ሰው ይሄዳል በእድሜዬ።
ዛፉን ነሽ ካልከኝ አደራ፦ ከጎኔ የበቀለ ሁሉ ሳያብብ አይክሰም ። እስኪረግፍ ፀደይ መጥቶ ይፍካ ይመርበት አብሮኝ ሲኖር። ላካፍለው ካለኝ ሁሉ። እሱ እንጂ የኔ እንግዳ እኔ መሄዱን አውቃለሁና። ሲረግፍም ቀን ጠብቆ ‘ሂድ መጣሁ’ ልበለው ። እኔስ ብሆን ከመሬት ጎን የበቀልኩ ቅርንጫፍ አይደለሁ?
ምን ቢራራቅ ፍጠረተ አለሙ ሁሉ መርገፍ በሚሉት የጋራ ሃቅ የቆመ አይደለ?
፟ወንዙን ነው ወይ ይሄ ልቤ? የጠለቀኝ የጠለቅኩት ይሰራኛል ያለድካም ።የነካሁት የታከከኝ መልኬ ይሆናል ።
ወንዝ ነሽም ካልከኝ አደራ ፦ የሰው ልጅ ንፅህና እንደውሃ ብዙ ባለመፍሰስ አይለካምና በወንዝነት ትርምስ ውስጥ ስፈስ በመንገዴ ከምገጨው ተራራ ስር የምንጭነትን ንፅህና አቅምሰኝ። የወደደኝ ሁሉ ሊጠጣኝ አይጠየፈኝ። ከመቀመስ ኋላ የምጠላ የምተፋ አታድርገኝ።
ዛፍን ነው ወይ የኔ ህይወት? ወንዙን ነው ወይ ይሄ ልቤ?
إن معي ربي سيهدين
©Newal Abubeker

****
ከአዳም ጀምሮ - የተከማቸው ኃጢአት
የእርግማኗ ቀንበር - ለዘመናት ተጭኗት
ቀና ማለት ተስኗት
ስትናወጥ ነበር ምድር - የአምላክ ቁጣ ነዶባት
የተነሱት ካህናት
የመጡላት ነቢያት
የነገሡባት ነገሥታት
ለጥቂት ጊዜያት - የሰጧት ቢመስልም እፎይታ
ዘላቂ መፍትሄ
ከቶ አላገኘችም - ለሐጢአትዋ ይቅርታ
ቢሆንም ቢሆንም
ከዘመናት በኋላ - ሰቆቃዋ እንዲያበቃ
እድፋምነትዋን ሊሽር - የሠላሙ አለቃ
ከቤተልሔም ከተማ - ከከብቶች በረት
ድንገት ተገኘ - ሊሆናት ብስራት
***
በጨለማው ላይ - ብርሃን የሚያበራ
ድንቅ መካር አምላክ - ለፍጥረቱ የሚራራ
አቅም የሌለው - ምስኪኖችን መስሎ
ከበረት ተገኘ - ክብሩን ኹሉ ጥሎ
*****-
የተከማቸውን ሐጢአት - የእርግማኑን ቀንበር
በደሙ ሊያስወግድ - በደሙ ሊስብር
የእግዚአብሔርን ቁጣ - በሞቱ ሊያበርድ
ደዌን ሊቀበል - በመስቀል ሊታረድ
እነሆ የእግዚአብሔር በግ - በረት ተወለደ
ምድር ሆይ ደስ ይበልሽ - ፍቅር ከላይ ወረደ
ኦ ሃሌሉያ!
ዕድፋሟ ፕላኔት - በአምላክ ምሕረት ተጎበኘች
ፍቅር በመወለዱ - እጅግ ደስ ተሰኘች፡፡
© ቢቶ
ከአዳም ጀምሮ - የተከማቸው ኃጢአት
የእርግማኗ ቀንበር - ለዘመናት ተጭኗት
ቀና ማለት ተስኗት
ስትናወጥ ነበር ምድር - የአምላክ ቁጣ ነዶባት
የተነሱት ካህናት
የመጡላት ነቢያት
የነገሡባት ነገሥታት
ለጥቂት ጊዜያት - የሰጧት ቢመስልም እፎይታ
ዘላቂ መፍትሄ
ከቶ አላገኘችም - ለሐጢአትዋ ይቅርታ
ቢሆንም ቢሆንም
ከዘመናት በኋላ - ሰቆቃዋ እንዲያበቃ
እድፋምነትዋን ሊሽር - የሠላሙ አለቃ
ከቤተልሔም ከተማ - ከከብቶች በረት
ድንገት ተገኘ - ሊሆናት ብስራት
***
በጨለማው ላይ - ብርሃን የሚያበራ
ድንቅ መካር አምላክ - ለፍጥረቱ የሚራራ
አቅም የሌለው - ምስኪኖችን መስሎ
ከበረት ተገኘ - ክብሩን ኹሉ ጥሎ
*****-
የተከማቸውን ሐጢአት - የእርግማኑን ቀንበር
በደሙ ሊያስወግድ - በደሙ ሊስብር
የእግዚአብሔርን ቁጣ - በሞቱ ሊያበርድ
ደዌን ሊቀበል - በመስቀል ሊታረድ
እነሆ የእግዚአብሔር በግ - በረት ተወለደ
ምድር ሆይ ደስ ይበልሽ - ፍቅር ከላይ ወረደ
ኦ ሃሌሉያ!
ዕድፋሟ ፕላኔት - በአምላክ ምሕረት ተጎበኘች
ፍቅር በመወለዱ - እጅግ ደስ ተሰኘች፡፡
© ቢቶ
"ሀጢአት ምክንያት ሆኖ ከእጁ የወደቀውን ፍጥረተ አለም ለማዳን መለኮት ሟች ስጋ ተላብሶ ከግርግም ተገኘ" መልካም በዓል!!! 🙏😍
አጽናኙ ሙሐመድ
ከዮሐ. 14-16 የተጻፈውን #አጽናኝ ሙስሊሞች ሙሐመድ ነው እንደሚሉ እናውቃለን?
በሱራ 61፥6 እንዲህ የሚል ጥቅስ አለ፤ የመርየም ልጅ ዒሳም፥ የእስራኤል ልጆች ሆይ እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥና ከኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በሆነው የማበስር ስሆን ወደናንተ (የተላክሁ) የአላህ መልክተኛ ነኝ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ በግልጽ ታምራቶች በመጣቸውም ጊዜ ይህ ግልጽ ድግምት ነው አሉ።
ስሙ አሕመድ የሆነውን አብሳሪው የመርየም ልጅ ዒሳ ነው። ዒሳና ኢየሱስ የተለያዩ መሆናቸውን ወይም የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አለመሆኑን ደጋግሜ ጽፌአለሁ። መጽሐፍም ሳይቀር ጽፌበታለሁ። ለጊዜው ግን ለእነርሱ እንደመሰላቸው ወይም እንደነሱ እናስብና ዒሳ ኢየሱስ ነው እንበል።
ችግሩ የሚፈጠረው ዒሳ ስለ አሕመድ የተናገረው መቼ ነው? ቢባል ያንን የሚመስል ነገር የለም። ከየት ይምጣ? ከየትም። አሕመድ ዲዳት ቢቸግረው ከእርሱ በፊት ከጻፈ አንድ ሰው ወስዶ፥ አጽናኝ (ጰራቅሊጦስ) የሚለውን በግሪክ παράκλητος (ፓራክሌቶስ) የሚባለውን፥ እርሱ ግን περικλυτος ፔሪክሉቶስ ነው፤ ትርጉሙም ከአሕመድ ይመሳሰላል ብሎ ተናገረም፤ ጻፈም።
ይህንን የዮሐንስ ወንጌል ክፍል ፔሪክሉቶስ በሚል ቃል የጻፈ አንድም ሰነድ፥ አንድም ትርጉም ግን ኖሮ አያውቅም። ያው ሙስሊሞች መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል፥ ተደልዟል፥ ተከልሷል ስለሚሉና፥ (በነገራችን ላይ ይህንን ቃል የኢስላም ነቢይ ሙሐመድም እንኳ አላለም።) ይህንን የተደለዘውንና የተበረዘውን እንድናስተያይ ያልተበረዘውን አምጡ ሲባል ሊያመጡ ስለማይችሉ እንደተበረዘ እንቁጠርና ይህ አጽናኝ ሙሐመድ ነው እንበል።
እንግዲህ አጽናኙ ሙሐመድ ከሆነ፥ ይህንን የሚሉ ሙስሊሞች ሊወጡ የማይችሉት ገደል ውስጥ ራሳቸውን ይከትታሉ። ጥቅሶቹን እንመልከታቸው፤
1ኛ) ዮሐ. 14፥15-16 እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ #አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውስጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።
ይህንን ጥቅስ ለሙሐመድ የሚጠቅሱ ከሆኑ፥ ሀ) ወልድ አብን እንደሚለምን፥ ለ) ከእነርሱ ከሐዋርያቱ ጀምሮ ከደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ጋር የሚኖር አጽናኝ እንደሚሰጣቸው፥ ሐ) ዓለም እንደማያውቀውና እንደማይቀበለው፥ መ) መንፈስ እንደሆነ፥ ሠ) በእነርሱ ዘንድ ብቻ ሳይሆን በውስጣቸውም እንደሚኖር ተነግሮአል። ሙሐመድ እነዚህን ሁሉ ያሟላል? ልብ እንበል በሐዋርያቱ ውስጥ ነው የሚኖረው። ሐዋርያቱ ሙሐመድ ተወልዶ በውስጣቸው እስኪገባ ኖረዋል ወይም ሙሐመድ ከመወለዱ በ500 በላይ ዓመታት በፊትም ነበረ ማለት ነው።
2ኛ) ዮሐ. 4፥26 አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው #አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።
ይህንን ጥቅስ ለሙሐመድ የሚጠቅሱ ከሆኑ፥ ሀ) የሚልከው አብ መሆኑን፥ ለ) የሚላከው በኢየሱስ ስም መሆኑን፥ ሐ) ሁሉን እንደሚያስተምር፥ መ) ኢየሱስ የነገራቸውን እንደሚያሳስብ፥ ሠ) አጽናኙ በግልጽ መንፈስ ቅዱስ እንደተባለ ይቀበላሉ ማለት ነው?
3ኛ) ዮሐ. 15፥26 ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ #አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤
ይህንን ጥቅስ ለሙሐመድ የሚጠቅሱ ከሆኑ፥ ሀ) አጽናኙን ከአብ ዘንድ የሚልከው ኢየሱስ መሆኑን፥ ለ) ከአብ የሚወጣ መሆኑን፥ ሐ) ስለ ኢየሱስ እንደሚመሰክር ይቀበላሉ ማለት ነው? ሙሐመድን የላከው ኢየሱስ መሆኑን ይቀበላሉ ማለት ነው?
4ኛ) እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ #አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።
ይህንን ጥቅስ ለሙሐመድ የሚጠቅሱ ከሆኑ፥ ሀ) ኢየሱስ ሲሄድ ብቻ አጽናኙ እንደሚመጣ፥ ለ) ኢየሱስ እርሱን እንደሚልከው ይናገራል። ኢየሱስ አጽናኙን ሙሐመድን እንደላከው ይቀበላሉ ማለት ነው?
የነ አሕመድ ዲዳት ፔሪክሉቶስ ገደል ገባ!!
ዘላለም ነኝ።