ቤተ ክርስቲያን አልባ ክርስትና በመጽሐፍ ቅዱስም ኾነ በታሪክ አናገኝም። እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ አምነው የዳኑ አማኞች በትምህርት፣ በምክርና በተግሣጽ እያደጉ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር መኾን ይችሉ ዘንድ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው ያኖራቸው። ሐዋርያው ጳውሎስ፣ "እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚኾን ሰውን ኹሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ኹሉ እየገሠጽን፣ ሰውንም ኹሉ በጥበብ ኹሉ እያስተማርን የምንሰብከው ርሱ ነው" ይላል (ቆላ. 1፥2)። ለዚህም ነው አባቶች፣ "ቤተ ክርስቲያን እናትኽ ካልኾነች፣ እግዚአብሔር አባትኽ ሊኾን አይችልም" ያሉት።
የተለያየ ዐይነት መንፈሳዊ ትምህርት የተማሩ እና የተለያየ ዐይነት ጸጋ የተቀበሉ አማኞች በትምህርታቸውና በጸጋቸው የሚያገለግሉበት ቀዳማዩ ስፍራ ቤተ ክርስቲያን ነው። ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ትእዛዛት አንዳችን ለሌላችን እየፈጸምን የምንኖርበት የክርስቶስ አካል ናት። የአንድ አማኝ መንፈሳዊ ጤናማ ዕድገት የሚረጋገጠው በአካሉ ላይ ካሉ ብልቶች ጋራ በሚያደርገው ኅብረት አማካይነት ነው። ስለዚህ ለአማኝ ጤናማ መንፈሳዊ ዕድገት እግዚአብሔር ያዘጋጀው ስፍራ ቤተ ክርስቲያን ነው።
በሌላ መልኩ ደግሞ አንድ አማኝ በዐመፅና በኀጢአት ጸንቶ በመኖር እንደ አላማኝ ቢመላለስ ይህን ሰው በመገሠጽ የማቅናት ኀላፊነት የቤተ ክርስቲያን ነው። ይህ ሰው ቤተ ክርስቲያንን አልሰማ ብሎ በኀጢአቱ ከጸና ቤተ ክርስቲያን የተሰጣትን ሥልጣን በመጠቀም ከአካሉ ላይ ታስወግደዋለች (ይህም፣ "Excommunication" ይባላል። በነገራችን ላይ አንድን ሰው በክርስቶስ ሲያምን አጥምቀው፣ "ድኗል" የሚል ምስክርነት የምትሰጥም ኾነ፣ በዐመፅ ጸንቶ ሲገኝ፣ "እንዳልዳነ ሰው እየኖረ ስለኾነ ድነቱን ተጠራጥሬዋለኹ" የሚል ምስክርነተ ሰጥታ የምታሰነብተውም ቤተ ክርስቲያን ናት)። ሐዋርያው ጳውሎስ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የነበረውንና መገሠጽ የተገባውን ሰው በተመለከተ፣ "መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው" ይላል (1ቆሮ. 5፥5)። ይህ ሰው በአካሉ ላይ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር በጽድቅና በቅድስና ባለመኖሩ ምክንያት ከቤተ ክርስቲያን እንዲወገድ ኾኗል። ይሁን እንጂ ደግሞ ይህ ሰው ተገቢው ቅጣት ተቀብሎ፣ በንስሓና በጸጸት ተመልሶ ሲገኝ፣ ወደ ክርስቶስ አካል ይመለሳል። ከቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን እንዲወገድ ስለፈረደበት ሰው ጳውሎስ መልሶ፣ "እንደዚህ ላለ ሰው ይኽ ከእናንተ የምትበዙት የቀጣችኹት ቅጣት ይበቃዋልና እንደዚህ ያለው ከልክ በሚበዛ ኀዘን እንዳይዋጥ ይልቅ ተመልሳችኹ ይቅር ማለትና ማጽናናት ይገባችዃል" ይላቸዋል (2ቆሮ. 1፥5_6)።
በርካታ አማኞች በአኹኑ ዘመን ያለች ቤተ ክርስቲያን ለእነርሱ እንደማትመጥን በማውሳት ቤተ ክርስቲያን የለሽ ሕይወት ይመራሉ። ፊልፕ ያንሲ፣ "Church: Why Bother?" የሚል መጽሐፍ አለው። ያንሲ ነጮች በጥቁሮች ላይ እያሳደሩ የነበረውን መግለልና ክፋት እያየ በማደጒ ምክንያት በከፍተኛ ቅይማት ተመልቶ ቤተ ክርስቲያን ትቶ ዘዋሪ ኾኖ ነበር። ይህንም እውነት፣ "ቤተ ክርስቲያን ለኀጢአን የምትኾን ስፍራ አይደለችም። ብዙ ጸጋ አይታይባትም። በመኾኑም ጸጋ ፍለጋ ከቤተ ክርስቲያን ወጥቼ በዓለም ዞርኹኝ። ነገር ግን ምንም ዐይነት ጸጋ በሌላ ስፍራ ባለማግኘቴ ትንሹ ጸጋ ይሻለኛል ብዬ ወደ ቤተ ክርስቲያን ተመለስኹኝ" በማለት ይገልጻል።
ቤተ ክርስቲያን የለሽ አማኝ መኾን ለምኞቶቻችን ታልፈን እንድንሰጥ ከማድረጒም ባሻገር ለሰይጣን ጥቃት በቀላሉ ዒላማ እንድንኾን ያደርገናል። ለአማኝ በቤተ ክርስቲያን ጥላ መጠለል ምርጫ ሳይኾን ብቸኛ ግዴታው ነው። የአካል ብልቶች ርስ በርሱ ተገጣጥሞ እውነተኛውን ዕድገት በማደግ ፍሬ የሚያፈራው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው። የእግዚአብሔር በረከቶች በሙሉ የሚፈስሱት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው (እግዚአብሔር ቅዱሳት ምስጢራትን ለቤተ ክርስቲያን የሰጠው ለዚኹ ዓላማ ነው)!
ስለዚህም፣ "እኔ የትኛውም ዐይነት ተቋማዊ ክርስትና አይመቸኝም፤ የየትኛውም ዐይነት ቤተ ክርስቲያን አባል መኾን አልፈልግም" ማለት የጥፋት መንገድን መምረጥ ነው። እንደ ፈለጒ በዐመፅ ለመኖር ማመቻመች ነው። አንድ ጥፋት ውስጥ ያለን አማኝ መክራ፣ ገሥጻ ማቅናትና ለክርስቶስ ሕይወት ማብቃት የቤተ ክርስቲያን ሥራ ነው። አንድ አማኝ ግለ ሰብ ራሱን ገሥጾና መክሮ ከዐመፁና ከኀጢአቱ በማቅናት ትክክለኛ መንገድ ላይ ማምጣት እንደሚችል መጽሐፍ ቅዱስም ኾነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ አይነግረንም።
ፍጹም የኾነች ቤተ ክርስቲያን ምድር ላይ የለችም። ቤተ ክርስቲያን የደካማና ኀጢአተኛ ሰዎች ስብስብ እንጂ የጻድቃን ሙዚየም አይደለችም። በቅርቡ አንድ የቤተ ክርስቲያን መሪ የኾኑ አገልጋይ ጋራ ስለ ቤተ ክርስቲያን ሳወራ፣ "ጥንቅቅ ያለች ፍጹም ቤተ ክርስቲያን እየፈለግኽ ነው? አታገኛትም። ብታገኛትም አንተ ስትገባባት ትበላሻለች" ብለውኝ ነበር።
በተለይም ማኅበራዊ ድረ ገጾች በርካታ ተከታዮችና አድማጮችን እንደገፍ በሚያቀርብበት በዚህ አደገኛ ዘመን፣ ራስን ከጥፋት ማዳኛ ብቸኛው መንገድ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኾኖ የማኅበራዊ ድረ ገጽን በተገቢው መልኩ ለአካሉ ጥቅምና ለቅዱሳን መታነጽ መጠቀም ነው።
ወደ ቤተ ክርስቲያን እንመለስ!
ጸጋው ይብዛልን!
-አሌክስ ዘ ፀአት

ይህ ጸሎት የሰባኪዎች ሁሉ በኩር የሆነው የቻርልስ እስፐርጀን ጸሎት ነው። የእስፐርጀን ጸሎት በብዛት እንደ ስብከቶቹ ተጽፎ አናገኝም። ለምን ቢሉ ሰዎች የሱን ውብ የሆኑ ጸሎትን እየጻፉ በግላቸው እንዳይለማመዱና የግል ጸሎታቸውን እንዳያደክም፣ ከዚያም አልፎ የርሱ የጸሎቱ ባሪያ እንዳይሆኑ ከመፈለግ እንደሆነ ይታመናል። በእውነቱ ከሆነ የቻርልስ እስፐርጀንን ስብከት ለሚያቅ ሰው ጸሎቱ በጽሁፍ ተዘጋጅቶ ቢሆን እኔን ጨምሮ ጸሎቱን ከሚያነባንቡ መሃል እንሆን ነበር lol ይህ ጸሎት በ 1856 በምሽት የጸለየው ጸሎት ነው። እኛም በዚህ ምሽት ብንጸልይስ? ብዬ ወዲህ አመጣሁት….
"ጌታ ሆይ እባክህን ሕዝብህን አድን። ሕዝብህን አድን። ጸሎቴ በፊትህ መሆን እንደሚገባው እንዳልሆነ አምናለሁ፤ በጸጋህ እርዳኝ። በሰጠኸኝ ዕድሜና ጸጋ እንደሚገባ እንዳልሰበክሁ የተሰወረ አይደለም። ጌታ ሆይ በኔ በደል ሌሎችን ቸል አትበል። ሕዝብህን አድን፤ በእረኛው ጥፋት መንጋውን አትምታ። ይቅር በላቸው አባት ሆይ፣ ምሕረትህ ከነርሱ ጋር ትሁን። ይቅርታን ያላገኙ ብዙዎች በዚህ አሉ። ይድኑ ዘንድ ምን ያህል እንደደከምን አንተ ታውቃለህና። የሰው ልብ በእውነት ጠንካራ ነው አባት ሆይ፣ ነፍሱም እንደብረት የጠነከረች ነች።
ደምና ሥጋ ሰውን ለመለወጥ አይችሉም፤ መጋቢው ተስፋ ያደርጋል፣ አገልጋይህም ያምናል፡፡ ግን ሁለቱም ማዳን አይሆንላቸውም። ጌታ ሆይ አንተ ግን በኃይልህ ትችላለህ። አንተ ካልሳብካቸው ሊከተሉህ አይችሉም። የእሥራኤል አምላክ ሆይ በዚህ ዓመት ደግሞ ይህችን ቤተ-ክርስቲያን እርዳ። ሕዝብህን በጸሎት ባርክ፣ የሥጋን ነገር በመንፈስ ይገድሉ ዘንድ አበርታቸው፣ በዚህ ብቻ ሳይሆን በሁሉ ሥፍራ ኢየሩሳሌምን ለምስጋና እስክታደርጋት ድረስ እንዳያርፉ እርዳቸው፣ የጸሎትን ሃይል ጨምርላቸው ጌታ ሆይ።
የምንጮኸውና የምናነባው ስለቤተክርስቲያንህ ብቻ አይደለም፡፡ ስለ ዓለም ሁሉ እንጂ። በከንቱ እንደማልደክም አልተናገርኸኝምን? ለባሪያዎችህስ ይህንኑ አላልክምን? እንግዲያውስ በሰዎች መዳን አጥግበን፡፡ ‹ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ ምድርን እንደሚያረካ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ እንደሚያደርጋት ዘርንም ለሚዘራ እንጀራንም ለሚበላ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል› ተብሎ እንደተጻፈ ቤተ-ክርስቲያንህን አስፋ። አስፋልን ጌታ ሆይ። ዛሬም በዚህ ምሽት ቃልህ በከንቱ አይመለስ። ባሪያህ በቅን ልብ በርህራኄና በፍቅር የክብሩን ወንጌል እንዲሰብክ እርዳው። መንፈስ ቅዱስ ሆይ ና! ያላንተ ምንም ማድረግ አንችልምና በትሕትና እንጋብዝሃለን፡፡ በአብርሃም ይስሐቅና ያዕቆብ ላይ የነበርክ የከበሩ ሕልሞችን ለሰዎች ትንቢትን ለነቢያት የሰጠህ በሐዋርያትና በቀደመችው ቤተ-ክርስቲያን ላይ ያደርህ ታላቁ የእግዚአብሔር መንፈስ ሆይ በዚህ ምሽት ከኛ ጋር ሁን። በአንተ መገኘት ይህች ምድር ትናወጥ፣ ነፍሳትም ልባቸውን ከፍተው የከበረውን ቃልህን ይስሙ፣ ሥጋ ለባሽ ሁሉ አንተን በማወደስ ሐሤት ያድርግ። ለዘላለም ለሚኖረውና ከፍ ላለው ለአብ፣ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ይሁን።”
አሜን

በፍቅርህ ፍላጻ ልባችንን ሰንጥቀህ ገብተኻል። ቃልህም ከአንጀታችን እንደተጣበቀ ሁሉ ታትሞብን ይዘነው እንጓዛለን። ቃልህ ጽልመት የመሰልነውን ጸዳል ያለብሳል፤ ሙታን የነበርነውን ሕያው ያደርጋል፤ የአገልጋይህ አብነቶችም፥ በሐሳቦቻችን ደረት ሰፍረዋል። ተልፈስፍሶ እንደሬሳ የከበደው እኛነታችንንም፥ የከበደው ሬሳችንን አንድዶና ቀስቅሶ፥ ከነክብደታችን ወደ ምሽቁርቁር መልሰን መውደቅ እንዳይችል ያደርገናል። ይበልጥና ይበልጥም ያቀጣጥለናል፥ እያንዳንዱም የአሽሟጣቻችን አንደበት ቢራገብ ይበልጥ ይነዳል እንጂ አያጠፋንም።
ቅዱስ አውግስጢኖስ
ክፍል ፱፥ ምዕራፍ ፪፥ ቁጥር ፫
ቅዱስ አውግስጢኖስ
ክፍል ፱፥ ምዕራፍ ፪፥ ቁጥር ፫
በእርግማን ሞትህ በረከት ሆነኸኝ
ከጽዮን መጥተህ ከሲዖል ነጥቀኸኝ
በአብ ቀኝ ተገኘሁ ሞትን ዳግም ላላይ
የደምህ ጅረቱ ፈሶ ወደ ሰማይ።
Hallelujah🙌
@poemsforchrist11🙋♀
ከጽዮን መጥተህ ከሲዖል ነጥቀኸኝ
በአብ ቀኝ ተገኘሁ ሞትን ዳግም ላላይ
የደምህ ጅረቱ ፈሶ ወደ ሰማይ።
Hallelujah🙌
@poemsforchrist11🙋♀
እግዚአብሔር ደክሟል አረጀ ያለ ማነው
እኔስ እስከሚገባኝ ዛሬም ኤልሻዳይ ነው
የእኔ እምነት ቢፈተን ቢለዋወጥበት
እግዚአብሔር ግን ታምኖ አለ እዚያው ባለበት
© Tamirat Haile
እኔስ እስከሚገባኝ ዛሬም ኤልሻዳይ ነው
የእኔ እምነት ቢፈተን ቢለዋወጥበት
እግዚአብሔር ግን ታምኖ አለ እዚያው ባለበት
© Tamirat Haile
ቤዛ ሊሆነን የአምላካችን ደም ፈሰሰልን። በቀራኒዮ የፈሰሰው የአምላካችን ደም ልጁ አደረገን። ለስርየት የፈሰሰው የአምላካችን ደም ከአባቱ ጋር አስታረቀን። ቅዱሱ የአምላካችን ደሙ ከሃጢአታችን/ከበደላችን አጥቦን በክብር ሸላልሞን የመንግስቱ ወራሽ አደረገን። ከዘላለም ዘመናት በፊት ለበጎቹ የታሰበው ንጹህ ደሙ በዘመን መጨረሻ ለኛ በመቆረስ ከበጎቹ መሃል እንድንሆን አደረገን። የዘላለም እረኛችን ደም ለኛ ለምርጦቹ ሁሉ የሚሆን ማስተሰሪያ ሆነልን። ይህ ቅዱሱ የአምላካችን ደም ውጤት ላያመጣ አንዲት ነጠብጣቡ ከቶውንም በዘፈቀደ አልፈሰሰም። ለታቀደላቸው ለምርጦቹ ሁሉ የልቡን ምክር አንዲት ሳያስቀር በደሙ ፈጸመልን። ለፈሰሰልን ለኛ ለበጎቹ ሁሉ የዘላለም ዋስትና በከበረው ደሙ ሆነልን።
በደሙ የዘላለም ፍቅሩን ገለጠልን። በደሙ የሃይላትን ስልጣን ሻረልን። በደሙ ጽድቃችንን አረጋገጠልን። በደሙ አዲሱን ኪዳን መርቆ ከፈተልን። በደሙ ለመንግስቱ አገልጋይ እንድንሆን አደረገን። በደሙ መካከለኛችን ሆነልን። በከበረው ደሙ አካሉ የሆነችውን ቤተክርስቲያንን ከአመጻ መቤዠትን አደረገላት። ለዘላለም ላትቆረጥ በደሙ ራስና አለት ሆነላት። ምርጦቹን ከቁጣ ያስመለጠ፣ የረከሰውን የህዝቡን ህሊና ያነጻ፣ ለምህረት ሁሌ የሚጮህ፣ ለሃጢአት ይቅርታ ሁሌ ትኩስ የሆነ፣ ለኪዳኑ ማህበረሰብ ሁሌ የሚቆረስ የአምላካችንና የጌታችን የኢየሱስ ደም!
#ውጤታማ_መቤዠት _መቤዠት

ከተወሰኑ ጊዜያት ወዲህ የመዝሙር ሰንደቆችን ስሰማ፣ በወንጌላውያን እና በኦንሊ ጀሰሶች መካከል ያለው ልዩነት ምን ያህል ይታወቅ እንደ ሆነ ማሰብ ጀምሬያለሁ። አንድ ሰው ዐሥራ ምናምን መዝሙር ዘምሮ ሲያበቃ ሁሉም ነገር ኢየሱስ የሚል ብቻ እንዴት ይሆናል? በርግጥ አንድ ሁለት ቦታ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ልጅህን ልከህ” የሚል አገላለጥ መኖሩ አይቀርም። “አባት ሆንከኝ” የሚል ቢኖርም፣ አብዛኞቹ ዘማሪዎች ይህን የሚሉት ራሱን ኢየሱስን እንደ አባት እያሰቡ እንደሆን እገምታለሁ። ከዚያ ውጭ ግን መንፈስ ቅዱስ የሚል ቃል አንዴም እንኳን ያልተጠቀሰባቸው የመዝሙር አልበሞች አሉን። እኛን ኦንሊ ጂሰሶች በምን ይሆን የምንለያየው?
ስለዚህ የመዝሙር ሰንዱቃችን ኦንሊ ጂሰሶችጋ ቢወሰድ ምንም ሳይጎረብጣቸው ሙሉ በሙሉ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። የእነርሱም ዐልበም እኛጋ ቢመጣ ተመሳሳይ አቀባበል ያገኛል። ከዚህ በፊት አንዲት ዘማሪ እዚያው እያለች ያወጣችው አልበም በእኛ መካከል እጅግ ተቀባይነት ስላገኘ፣ አገልግሎትም እየሰጠናት ቀስ በቀስ እዚሁ ቀረች። ሌላኛው ደግሞ የመዝሙር አልበሙን ሙሉ በሙሉ እየሰማንለት፣ የእኛም ዘማሪዎች አምልኮ ሲመሩ መዝሙሮቹን እየዘመሯቸው ዘማሪውን ግን በአጋጣሚ ቦታ ሳንሰጠው ቀረን። ይህን ሁሉ ሳስበው ያስገርመኛል፤ ሥላሴያውያን አማኞችና ሥላሴያውያን ያልሆኑቱ እንዴት የመዝሙር አልበማቸው እንዴት ልዩነት የሌለው ይሆናል? ከሥላሴያዊነት ቀስ በቀስ ወደ ኢየሱሳዊነት-ብቻ እየተንሸራተትን ይሆን?
The Forgotten Trinity (የተረሳው ሥላሴ)፣ The Forgotten Father (የተረሳው አብ) የሚሉ መጻሕፍትን አንብቤያለሁ። እስካሁን ባላነብባቸውም The Holy Spirit: The Forgotten Person of the Trinity እንዲሁም በፍራንሲስ ቻን የተጻፈ The Forgotten God: Reversing Our Tragic Neglect of the Holy Spirit የሚሉ መጻሕፍት መኖራቸውን አውቃለሁ። እናም ችግሩ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ብቻ ሳይሆን፣ የሌሎቹም ይመስለኛል። በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኞች ላይ የጰንጠቆስጤአውያን ጫና መግዘፉ ተደጋግሞ ሲነገር እየሰማን መንፈስ ቅዱስን ችላ ማለታችን ዘይገርም ነው። ዋናው ችግር ስብከታችን ይሆን?
ዶክትሪን የሚዘምሩ ዘማሪዎችን ጌታ እንዲያስነሣልን እናፍቃለሁ።
© ጳውሎስ ፈቃዱ
https://youtu.be/ZvZ__czMIh0?si=xQ5_JOBuBFdNJcjJ

YouTube
ክብር ለስላሴ "KEBER LE SELASE" Glory to Trinity by Ruth Tesfaye 2022
Ruth Tesfaye New Ethiopian Gospel Song 2022.
Thanks for watching. LIKE, SHARE & SUBSCRIBE For More Videos!
Subscribe Now.
https://www.youtube.com/channel/UCJvQLWSVNdRvDSiAHEzwivQ
2ኛ ተሰሎንቄ 2 (አዲሱ መ.ት)
¹³ እግዚአብሔር እናንተን ከመጀመሪያ አንሥቶ በመንፈስ ተቀድሳችሁና በእውነትም አምናችሁ…

በተለያዩ ዘመናት ክርስቲያኖች የክርስቶስን መስቀል ገሸሽ ከማድረግ ይልቅ በሞቱ ሊመስሉት ምርጫቸው አድርገው የፅዮኑን ጉዞ መጓዛቸው እሙን ነው። በዚህ ዘመን ያለን የክርስቶስ ተከታይ የሆንን ክርስቲያኖች ‹‹ይህችን ፅዋ›› ለመሸሽና "መስቀል አልባ ክርስትና" ለመለማመድ የምንጠር ቆም ብለን ማሰብ ይጠበቅብናል፡፡ መስቀሉ ወደ ክብር የሚወስድ መንገድ ነው። ቃሉስ “መስቀሉን ተሸክሞ የማይከተለኝ ለኔ ሊሆን አይገባውም ”
ማቴ10፡ 38 (ዓ.መ.ት) አይደል የሚለው፡፡
"ይህች ፅዋ" የተሰኘው የመድረክ ስራም ይሄንን እውነት ለማውሳት የሚጥር ነው። ልዝብ የሆነውን የክርስቶስ መስቀል ተሸክሞ የሚጓዝ አማኝ ያለ ጥርጥር ከጽዮን መድረሱ አይቀርም።
የምትችሉ ነገ ማክሰኞ በሀዋሳ አዲስ ከተማ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ከ11:00 ጀምሮ እንገናኝ ።