ኢትዮጵያ የአየር ኃይሏን ለማጠናከር የፓኪስታንን ተሞክሮ የመውሰድ ፍላጎት እንዳላት ተጠቆመ
(ሰሞንኛ )
ባለፈው ወር ነሐሴ 2015 የኢትዮጵያው አየር ኃይል አዘዥ ሌፍተነናንት ጀነራል ይልማ መርዳሳ ወደእስላማባድ ተጉዘው ከፓኪስታኑ አቻቸው ማርሻል ዛሂር አህመድ ሲድሁ ጋር መምከራቸውን ያስታወሰው የሆርን ሪቪው ዘገባ፤ ይህም ኢትዮጵያ ጦሯን ለማዘመን በተለይም የአየር ኃይሏን ለማጠናከር ከፓኪስታን ጋር ትርጉም ያለው ወታደራዊ ትብብር ማድረግ እንደምትፈልግ የሚያመላክት መሆኑን ገልጿል።
ፓኪስታን የአየር ኃይል የደህንነቴ ዋነኛ ምሰሶ ነው ብላ የምታምንና ለኃይሏ ልዩ ትኩረት በመስጠት የምትታወቅ ሀገር ናት። በመሆኑም “ዒላማን የመምታት የላቀ ብቃት፣ ጠላት ጥቃት መፈጸም እንዳያስብ የሚያደርግ አስፈሪ የማጥቃት ብቃት መገንባትና ቴክኖሎጂን አሻሽሎ የመጠቀም ጥበብ” በሚል መርሕ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የአየር ኃይል መገንባት የቻለች ሀገር መሆኗዓ ይነገርላታል።
ኢትዮጵያም ከሀገሪቱ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ በማሸጋገር ይህንኑ የፓኪስታን አየር ኃይል መርህ በመከተልና ተሞክሮውን ወደራሷ በመውሰድ ብሎም የዕውቀትና የቴክኒክ ድጋፍ እንድታገኝ የሚያስችሉ ትብብሮችን በመፈረም የአየር ኃይሏን አቅም ለማሳደግና በዓለም ላይ ስም ካላቸው አየር ኃይሎች ተርታ የማሰለፍ ፍላጎት አላት ።

❤9👍3