ከ989 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ከ989 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ተችሏል አለ፡፡
ከዚህም ውስጥ 969 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የገቢ እንዲሁም 20 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች መሆናቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
የኮንትሮባንድ እቃዎቹ የተያዙት ኮሚሽኑ ከፌደራልና ከክልል የፖሊስ ተቋማት እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ክትትል መሆኑን ገልጿል፡፡
ከኮንትሮባንድ ቁሳቁሶች በተጨማሪ የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 16 ተጠርጣሪዎችና 21 ተሽከርካሪዎች መያዛቸው ነው የተገለጸው፡፡
በዚህም አዳዲስና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ እቃዎች፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት፣ የቁም እንስሳትና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
ኮንትሮባንድ በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመከላከል ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ኮሚሽኑ ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመልክቷል፡፡

❤9👍1👏1
ዘምዘም ባንክ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ የተመዘገበ የመጀመሪያው ከወለድ ነጻ ባንክ ሆነ
ዘምዘም ባንክ አክሲዮን ማህበር በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በይፋ በመመዝገብ፣ በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ውስጥ ተሳታፊ የሆነ የመጀመሪያው ከወለድ ነጻ ባንክ መሆኑን አስታውቋል። ምዝገባው ባንኩ አክሲዮኖቹን ለህዝብ አቅርቦ እንዲገበያይ ህጋዊ ፈቃድ የሚሰጥ መሆኑ ተጠቁሟል።
የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መሊካ በድሪ እንደገለጹት፣ ምዝገባው የተከናወነው “ለህዝብ የሚቀርቡ የዋስትና ሰነዶች እና ግብይት መመሪያ ቁጥር 1030/2024”ን መሰረት በማድረግ ነው።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም፣ “ይህ ምዝገባ በካፒታል ገበያ ውስጥ ለመሳተፍ እና የ15 ቢሊዮን ብር የካፒታል ግባችንን ለማሳካት የሚያስችለን ወሳኝ እርምጃ ነው” ብለዋል። ባንኩ ከወጋገን ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር በመተባበር የግብይት ሂደቱን የሚያከናውን ይሆናል።
ባንኩ ይፋ ባደረገው የባለፈው በጀት ዓመት የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት መሰረት በሁሉም መለኪያዎች ላይ ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል።
በዚህም የደንበኞች ተቀማጭ ገንዘብ ከ11.6 ቢሊዮን ብር ወደ 21 ቢሊዮን ብር በማደግ የ81 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
በተመሳሳይ ጠቅላላ ሀብቱ በ75 በመቶ በማደግ 29.1 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ የተከፈለ ካፒታሉም በ123 በመቶ ዕድገት ወደ 5.64 ቢሊዮን ብር ከፍ ማለቱን የባንኩ ሪፖርት ያመለክታል።
ከዚህ በተጨማሪም የባንኩ ጠቅላላ ገቢ በ36 በመቶ በማደግ 3 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣
“አንሳር ዲጂታል” በተሰኘው የቴክኖሎጂ አማራጭ ከ9,800 በላይ ለሚሆኑ ደንበኞች ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ፋይናንስ ማቅረቡን የገለፀው ዘምዘም ባንክ በአሁኑ ወቅት በ130 ቅርንጫፎቹ አማካኝነት ከ973 ሺህ በላይ ደንበኞችን እያገለገለ እንደሚገኝ አስታውቋል።

❤13🎉3
#Pakistan International Airlines selects former #Ethiopian Airlines CEO Tewolde Gebremariam to lead post-privatization turnaround
Pakistan International Airlines (#PIA) has selected former Ethiopian Airlines Group Chief Executive Officer Tewolde Gebremariam as its new CEO following the airline’s privatization and transfer of management control to a consortium led by Arif Habib Group. The appointment is expected to spearhead efforts to revive the loss-making national carrier through fleet modernization, network expansion, and operational reforms backed by fresh investment.
Bloomberg previously reported that Tewolde had been shortlisted for the role, citing a person familiar with the matter, with a formal announcement expected after the completion of required procedures. Arab News reported that the airline is withholding an official announcement until security clearances are finalized.
Quoting unnamed sources, Arab News said a senior PIA official confirmed that the airline “would not announce his name until all the security clearances are completed,” while a major shareholder described Tewolde as “a very capable person” who “has done a lot of turnarounds.”
Tewolde served as Group CEO of Ethiopian Airlines from 2011 until his early retirement in March 2022. During his tenure, he oversaw the carrier’s transformation into Africa’s largest airline through major fleet expansion, route growth, and the development of Addis Abeba as a continental aviation hub. He stepped down citing health concerns, stating that he had been dealing with medical issues for nearly a year and had undergone treatment in the United States for several months, making it difficult to provide the level of on-site leadership required for the position.
His expected appointment is widely viewed as a strategic move to restore PIA’s financial and operational performance following its privatization.

👍7❤2
NBE gives green light to Sudanese expert as Amana Insurance President
By Eyasu Zekarias
Amana Insurance Share Company, Ethiopia’s first fully interest-free insurance firm, has reached the final stage before launching its official operations. Capital has confirmed from the company’s forming board that the pioneering institution is expected to receive its final operational license from the National Bank of Ethiopia (NBE) within the next two to four weeks, enabling it to become fully operational in the first quarter of 2026.
https://capitalethiopia.com/2026/07/12/nbe-gives-green-light-to-sudanese-expert-as-amana-insurance-president/

❤4👍2
የ2019 ዓ.ም የሬሜዲያል መርሐ ግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም የሬሜዲያል መርሐ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸውን የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል።
ሚኒስቴሩ የመቁረጫ ነጥቡ የተማሪዎች ውጤት፣ የዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም እና የሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህን መሰረት በማድረግ መወሰኑን ገልጿል።

❤5
ኢትዮጵያ አዲስ የባቡር ነዳጅ ማጓጓዣ አማራጭ ልታገኝ ነው፤ በጅቡቲ እየተገነባ ያለው ግዙፉ ፕሮጀክት
በጅቡቲ የዶራሌህ ሁለገብ ወደብ አዲስ የነዳጅ ማከማቻ ታንኮች ግንባታ በስፋት እየተካሄደ ነው። አፍሪካን ተርሚናል ኤንድሎጂስቲክስ ሰርቪስ እውን እያደረገው ያለው ይህ ፕሮጀክት፣ ነዳጅን በቀጥታ ከማከማቻው ወደ ባቡር በመጫን ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ የሚያስችል ታሪካዊ ዕቅድ ይዟል።
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በየብስ ትራንስፖርት ላይ ብቻ ጥገኛ የሆነውን የነዳጅ ኮሪደር ከጫና ነፃ ያወጣዋል ተብሎ ይጠበቃል። አሁን ላይ በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ የነዳጅ ቦቴ መኪኖች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚመላለሱ ሲሆን፣ አዲሱ የባቡር ማጓጓዣ ሥርዓት ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማድረስ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

❤3
የተሰረዘውን የተርን ኦቨር ታክስ የሚተካ አዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማሻሻያ ደንብ ጸደቀ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በፌዴራል ተጨማሪ እሴት ታክስ ማሻሻያ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አጸደቀ። ማሻሻያው የተዘጋጀው ቀደም ሲል የሙያ አገልግሎት እና ሌሎች አቅርቦቶችን በመስጠት የተርን ኦቨር ታክስ ይሰበስቡ የነበሩ ግብር ከፋዮች፣ የታክስ ሥርዓቱ በመሻሩ ምክንያት በቀጥታ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝግበው ታክሱን እንዲሰበስቡ ለማስቻል መሆኑ ተጠቁሟል።
በአንዳንድ አቅርቦቶች ላይ ተጥሎ የነበረው ታክስ በህብረተሰቡ መሰረታዊ ፍጆታዎች እና በአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪነት ላይ ጫና ማሳደሩ በመረጋገጡ፣ እነዚህ አቅርቦቶች ከታክስ ነፃ እንዲሆኑ መደረጉም ተገልጿል።
ምክር ቤቱ በረቂቅ ደንቡ ላይ በሰፊው ከመከረ በኋላ አስፈላጊዎቹን ግብአቶች አክሎበት፣ ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ የሚለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ተገለጸ
የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ኢትዮ ቴሌኮምን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ ተሹመዋል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የቆየው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀና ሀሰተኛ መሆኑን ኩባንያው ለካፒታል ጋዜጣ አስታወቀ።
በአሁኑ ወቅት ኩባንያውን በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት (Acting CEO) እየመሩ የሚገኙት በኢትዮ ቴሌኮም የዳይሬክተሮች ቦርድ ኃላፊነት የተሰጣቸው አቶ ታሪኩ ደምሴ መሆናቸው ተረጋግጧል።

❤4
ስለ ስራ! ፌስቡክ ግሩፕ 278ሺ በላይ አባላት ደርሷል።
ሁላችሁንም እናሰመግናለን፣ ቀሪ የስለ ስራ! የተረጋገጡ ማህበራዊ ድረ-ገፆችን እንድትቀላቀሉ እንጋብዛለን።
👉 FB - Group https://www.facebook.com/groups/1153093882014917/?ref=share&mibextid=NSMWBT
👉 FB - Page
https://www.facebook.com/profile.php?id=61552032783167&mibextid=ZbWKwL
👉 Youtube - https://www.youtube.com/@SilSira-zs5rw
👉 Tiktok - tiktok.com/@sile.sira
👉 WhatsApp
https://whatsapp.com/channel/0029Va5Ch0O9WtBw5eGcdZ3H
👉 Telegram
https://t.me/selesera
ስለ ስራ! የሁላችን ከሁላችን

Facebook
ስለ ስራ! | Facebook
አጠቃላይ ስራና ከስራ ጋር ግንኙነት ያላቸው መረጃዎች መለዋወጫ.
❤2👍2