የሰለፍያ ደዕዋ በቻግኒالدعوة السلفية فى مدينة الشاغنى
692 subscribers
643 photos
56 videos
164 files
1.9K links
ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot

ይፃፉልን። ይላኩልን።
Download Telegram
ከአላህ ውጪ ባለ ነገር መማል ሀራም ነው!!
(ከሺርክ አይነቶችም ይመደባል)
—————
ከዑመር ኢብኑል ኸጧብ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ተይዞ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል አለ:-
አላህ በወላጆቻችሁ መማልን ይከለክላችኋል።” ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። በሌላ ዘገባ ደግሞ እንዲህ ብለዋል:- “መማል የፈለገ ሰው በአላህ ይማል አልያ ዝም ይበል!።” ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

በሌላ ዘገባ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ - ረዲየላሁ ዐንሁ - እንዲህ አሉ:- "ወላሂ በጌታዬ ይሁንብኝ የአላህ መልእክተኛ ከከለከሉበት ጊዜ ጀምሮ በወላጆቼ (ከአላህ ውጪ በሆነ ነገር) ሆነ ብዬም ይሁን ስለ ሌላ ሰው ሳወራ ምዬ አላውቅም።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

አምላካችን አላህ ከእርሱ ውጪ ባለ ነገር ከመማል አጥብቆ ከልክሎናል። በወላጆቻችንም ይሁን በሌሎች በማንኛቸውም የክብር ባለ ቤት በሆኑ ፍጡሮች፣ በነቢያትም ይሁን በመላኢካ፣ በሸይኽም ይሁን በሌላ ከአላህ ውጪ በሆነ በየትኛውም ነገር መማልን ተከልክለናል። መሀላ ግድ ከሆነብን ሊማልበት የሚገባው ሀያልና የንግስና ባለቤት በሆነው ብቸኛ ፈጣሪና አምላክ በሆነው በአላህ ብቻ እንድንምልና ካልሆነም ደግሞ ዝም እንድንል ነው የታዘዝነው።

ከአላህ ውጭ ባለ ነገር መማል ሺርክ ነው!።
ከዐብደላህ ኢብኑ ዑመር - ረዲየላሁ ዐንሁ - ተይዞ፣ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አለ:- “ከአላህ ውጪ በሆነ ነገር የማለ ሰው በእርግጥም በአላህ ላይ አጋርቷል።” አቡዳውድ 3251፣ ቲርሚዚይ 1535 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ኢርዋእ አል-ገሊል 8/189 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።

ሺርክ እንደምናውቀው በሁለት አይነት ይካፈላል። እሱም:- ከእስልምና የሚያስወጣው ትልቁ ሺርክና ከእስልምና የማያስወጣው ትንሹ ሺርክ ነው። ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) ከአላህ ውጪ ባለ ነገር ላይ መማል ከየትኛው ይመደባል? የሚለውን በተመለከተ እንዲህ ብለዋል:-
በእርግጥ ትንሹ ሺርክም ወደ ትልቁ ሺርክ ከፍ የሚልበት ሁኔታ አለ። ከአላህ ውጪ የማለው ሰው ወይም አላህ እና እገሌ ከፈለጉ የሚለው ሰው፣ የማለበት አካልና ከአላህ ፍላጎት ጋር ያገናኘው አካል በዚህ አለም ከአላህ ውጪ ነገሮችን የማገላበጥ አቅም አለው ብሎ የሚያምን ከሆነ፣ አለያም ከአላህ ፍላጎት ውጪ የሆነ የማድረግ አቅምና ፍላጎት አለው ብሎ የሚያምን ከሆነ፣ ከአላህ ውጪ የመጥቀምም ሆነ የመጉዳት አቅምና ችሎታ አለው ብሎ የሚያምን ከሆነ፣ አለያም ከአላህ ውጪ ሊመለክ ይመቻል፣ ከእርሱም በጭንቅ ጊዜ እርዳታ መለመን ይፍቀዳል ብሎ የሚያምን ከሆነ በዚህ እምነቱ ሰበብ በዚህ አካል መማል ከትልቁ ሺርክ ይመደባል።

አለያ ግን እንዲሁ ያለ እነዚህ እምነት ዝንብሎ ከአላህ ውጪ ባለ ነገር በምላስ ብቻ መማል፣ ይህን አካል ነቢይ ስለሆነ ወይም መልካም ሰው ስለሆነ ወይም ወላጆቹ ስለሆኑ… በማላቅ ከሆነ የማለው ይህ ከትንሹ ሺርክ ነው ሚመደበው። ከእስልምና ከሚያስወጣው ከትልቁ ሺርክ አይደለም።
” [ኑሩን ዐለ-ደርብ ካሴት ቁ.1 ወይም መጅሙዕ አል-ፈታዋ 28/369]
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
መንሀጅ አስ-ሰለፍ.pdf
861.1 KB
👉 PDF
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ

ለዓለማቱ ጌታ አላህ የላቀ ምስጋና ይገባው!። በነቢያችን ላይ የአላህ ሰላምና ውዳሴ ይስፈን!!

ይህ እጅግ በጣም ጠቃሚና በአጭር ደቂቃዎች ውስጥ መንሀጀ ሰለፍን የሚያሥገነዝብ የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊህ ቢን ፈውዛን አል-ፈውን 36 ደቂቃ ገደማ የሚሆን “የደጋግ ቀደምቶች መንገድና ለሙስሊሞች አስፈላጊነቱ (ወሳኝነቱ)” በሚል ርእስ ያደረጉት ሙሃደራ ሲሆን፤ ሁሉም ሰው በቀላሉ እንዲገነዘበው በማሰብ ወደ አማርኛ ቋንቋ የተተረጎመ ነው፡፡ አንብቡት! ሌሎችም ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ አሰራጩት፡፡

የፅሁፉን PDF ለማግኘት የሚከተለውን ⤵️ ሊንክ ይጫኑ

https://t.me/IbnShifa/1149

ዐረቢኛ የሚቀለውና የሸይኹን ሙሃደራ በድምፅ ማግኘት የፈለገ ሰው የሚከተለውን ሊንክ ተጭኖ ማግኘት ይችላል፡፡

⤵️

https://t.me/IbnShifa/1148

መልካም ንባብ!

✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
ረመዷን ታላቅ የዱዓ ወር ነው!!
—————በዱዓ እንበርታ!!
ይህ የረመዷን ወር ታላቅ የዱዓ ወር ነው!። ዱዓ ላይ አንዘናጋ!! በዲናችንም በዱኒያችንም ጉዳይ አላህን ተናንሰን ዝቅ ብለን ከእርሱም ከጃይ ሆነን እንለምን። አላህ ሀገራችን ሰላም እንዲያደርጋት፣ በየ አቅጣጫው የሚሰማው የሙስሊሙን መከራ በቃችሁ እንዲለን ከወንጀላችን ተመልሰን ከልብ ዱዓ እናድርግ እንማፀነው!!፣ አላህ ወደ እርሱ ተመላሽ የሆነውን ባሪያውን ተማፅኖ እሺ የሚል ተቀባይ ጌታ ነው!!።

በየ አቅጣጫው ሙስሊሙ ላይ በደል በዝቷል!። ባለ ስልጣናት ቢሯቸውን ጆሯቸውን ዘግተው ሊያደምጡም ፈቃደኛ አይደሉም!። ባለ ሀብቱና የተሻለ አቅም ያለውም መተዛዘን የሚባል ነገር ከልቡ ጠፍቶ በሩን ዘግቶ ይበላል። የአላህ በር ግን ሁሌም ክፍት ነው!! ከአዛኞች ሁሉ በላይ ወደር የሌለው አዛኝ ነው!! በዚህ በተከበረው የረመዷን ወር በዚያ ላይ የተበዳይን ዱዓ ይቀበላልና ከወንጀልና እርሱን ከማመፅ ርቀን እንደሚቀበለንም እርግጠኛ ሆነን እንለምነው!! አላህ ግፈኞችና በዳዮች ከሚሰሩት በደልና ግፍ ዝንጉ የሆነ አምላክ አይደለም! በተቀደሰው ቃሉም እንዲህ ብሏል:-

وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ

«አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡» ኢብራሂም 42

ይህን በደልና ግፍ ተከትለው የአክፍሮት ሀይሎች ተስፋቸው የተሟጠጡ ሙስሊሞችን ለማክፈር ቋምጠዋል። እንዲህ ያለ ፈተና በሚከሰትበት ወቅት በሐቅ ላይ እንዲያፀናን እና ሌሎችም በዲናቸው ፀንተው ችግሮችን ተሻግረው አላህ እንዲፈርጃቸው አጥብቀን ዱዓ ማድረግ ይኖርብናል!!

🔹ሌላው ደግሞ ብዙ ሰዎች (አላህ ይጠብቀንና) ዲናቸው (መንሃጃቸው) ላይ መገለባበጥን ያበዙበት ወቅት ላይ ስለሆንን አላህ በሀቅ ላይ ፅናት እንዲሰጠን አጥብቀን እንለምነው!!
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዱዓ በሚያደርጉበት ጊዜ የሚከተለውን ዱዓ ያበዙ ነበር:-

اللهم مقلب القلوب ثبّت قلبي على دينك، اللهم مصرف القلوب صرّف قلبي على طاعتك“ رواه مسلم.

አልላሁመ ሙቀሊበል ቁሉብ ሰብቢት ቀልቢ ዐላ ዲኒከ፣ አልላሁመ ሙሶሪፈል ቁሉብ ሶሪፍ ቀልቢ ዐላ ጣዐቲከ

ትርጉም:- ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው አላህ ሆይ! በዲንህ ላይ ልቤን አፅናው። ልቦችን የምትቀያይር የሆንከው አላህ ሆይ! ልቤን አንተን በመታዘዝ ላይ አፅናው፣ (ከአንዱ ዒባዳ ወደ ሌላው ዒባዳም) ቀያይረው።” [ሙስሊም ዘግበውታል።]

ኢማሙ'ል ኣጁሪይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
አላህ መልካም የፈለገበትን ሰው የዱዓ በሮችን ይከፍትለታል። ቸር ወደ ሆነው አምላኩ አላህ ይጠጋል። በዲኑ ጉዳይም ይፈራል (ይጠነቀቃል)። ጊዜውንም ያውቃል፣ ምላሱንም ይጠብቃል። ፍንትው ያለችውን እውነተኛዋን (ነጭዋን) ሜዳና ሰዋዱል አዕዞምንም አጥብቆ ይዛል። በዲኑ ላይ አይቀያየርም!!።” [አሽ-ሸሪዐህ ሊል ኣጁሪይ 1/393]
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን 👇👇 #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
ታገስ! አላህ ታጋሾችን ያለ ገደብ ይመነዳል!!
————
ትግስት (ሶብር) እጅግ በጣም ታላቅ ስጦታ ነው!። ትግስት በእርግጥ ጅምሩ መራራና ከባድ ቢሆንም መጨረሻው ደግሞ ከማር የበለጠ ጣፋጭ ነው!።

አንድም ሰው ከትግስት የተሻለ ስጦታ የተሰጠው የለም!። ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
የሚታገስ ሰው አላህ ያስታግሰዋል፣ አንድም ሰው ከትግስት የተሻለ ስጦታ አልተሰጠውም!።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

የትግስት ምንዳ አላህ ዘንድ እጅግ በጣም የላቀ ከመሆኑ አንፃር ታጋሾችን የሚመነዳው ያለ ገደብ ነው። አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል:-

قُلْ يَا عِبَادِ الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا رَبَّكُمْ ۚ لِلَّذِينَ أَحْسَنُوا فِي هَٰذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةٌ ۗ وَأَرْضُ اللَّهِ وَاسِعَةٌ ۗ إِنَّمَا يُوَفَّى الصَّابِرُونَ أَجْرَهُم بِغَيْرِ حِسَابٍ

«ጌታችሁ፣ እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ!፡፡ ለነዚያ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ለሠሩት መልካም ምንዳ አላቸው፡፡ የአላህ ምድርም ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ ተሰደዱ)፡፡ ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው፣ (ይላል) በላቸው፡፡» አዝ-ዙመር 10

ስለ ትግስት እጅግ በጣም በርካታ የቁርኣን አንቀፆችና ሶሂህ ሀዲሶች አሉ። በግል ጉዳይም ይሁን በጀመዓ ጉዳይ፣ በአኼራ ጉዳይም ይሁን በዱኒያ ጉዳይ በተለያየ መንገድ በሚደርሱ ችግሮችና ፈተናዎች ምንም ያህል ቢበረቱ ዋጥ አድርጎ ታጋሽ ሆኖ በጥንቃቄ ማሳለፍ መጨረሻው ያማረና ገደብ የለሽ ለሆነ ምንዳ ያደርሳል!!።

ብዙ ጊዜ ለእኛ ክፉ መስለው የሚታዩን ስለደረሱብን ወይም ስላመለጡን፣ አለያም ሀብት ንብረት ስለወደመ፣ ደክመን ጥረን ሰበብ አድርሰን ከሰራነው ቤት ስለተፈናቀልን… የምንቆጭባቸውና ትግስት የምናጣባቸው ነገሮች በትግስት ዱዓ እያደረግን አላህ እስልምናን እና ጤናን ጨምሮ ሌሎች ተቆጥረው የማያልቁ ፀጋዎችን እንዳጎናፀፈን እያስተዋልን በማመስገን በጥንቃቄ ስናልፋቸው መጨረሻቸው መልካም ሆነው እናገኛቸዋለን!።

ታዳ አንተ ምን ጨነቀህ?! ታገሽ ብቻ ሁን!፣ አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና። አላህ እንዲህ ብሏል:-

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ

«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ተረዱ፡፡ አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡» አል-በቀረህ 153

ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“ትክክለኛው ወርቅ በእሳት ካልተፈተነ አይታወቅም፣ የእንጨቱ (ዌራ) ሽታ አይታወቅም በእሳት ሲቃጠል ቢሆን እንጂ። እንዲሁም አማኝ የሆነ ሰው አይታወቅም በመፈተን ቢሆን እንጂ። ወንድሜ ሆይ! አደራ በትግስት!፣ እርግጥ ነው በዲንህ ትፈተናለህ፣ በእርግጥም ያፌዙብህ ይሆናል…፣ ታገስ እውነተኛ ሁን! መልእክተኞች ኡሉል ዐዝሞች ላይ የደረሰውን ተመልከት (አስታውስ)።

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መስጂደል ሀረም (መካ) አካባቢ ለአላህ ሱጁድ ላይ ሆነው እያለ፣ ከሰዎች ሁሉ ጠማማ የሆኑት ይመጡና የግመል ፈርስና እንግዴ ልጅ ይጥሉባቸው ነበር፣ ሱጁድ ላይ ሆነው ነው ይህን የሚያደርጉባቸው የነበረው፣ ይህ እጅግ በጣም ከባድና ከመልእክተኞችና ኡሉል ዐዝሞች ያልሆነ ሰው የማይታገስበት ተግባር ነው!። በህፃንና በጨቅላ እድሜዋ የነበረችው ልጃቸው ፋጢማ (ረዲየላሁ ዐንሃ) መጥታ እስክታነሳላቸው ድረስ ሁሉ ይቆይ ነበር፣ እንደዛም ሆኖ ሙሽሪኮች ይስቁ ያላግጡ ነበር።

ታገስ! አላህ ዘንድም ምንዳ አገኝበታለሁ ብለህ አስብ፣ እወቅ! የስቃይህና የችግርህ ማብቂያ ሞት ከሆነና ለአላህ ብለህ ታጋሽ ሆነህ ከሞትክ፣ ከአንድ ሀገር ወደተሻለና መልካም ወደሆነ ሀገር ተሸጋግረሃል።” [ተፍሲር ኢብኑ ዑሰይሚን 3/41]
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
ጊዜያችን በአጋጉል ነገር አናቃጥል።
———
በጊዜም ጉዳይ መጠየቅ አለና ጊዜያችን በአግባቡ እንጠቀምበት!። እናንብብ፣ ራሳችንን በእውቀት እንገንባ፣ በዒልም እንታጠቅ።

ይህቺን የሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) ምክር አጥብቀን እንያዛት በጣም ጠቃሚ ስለሆነች በአግባቡ እንጠቀምባት፣ እንዲህ ይላሉ:-

«ጊዜህ በማይረባ ነገር እየባከነብህ (እየጠፋብህ) መሆኑን ካገኘሀው፣ ልብህን መቆጣጠር ግድ ይልሃል። ምክንያቱም ይህ አላህን ከማውሳት በመዘንጋት የሚከሰት ነው።
ያለፉ ታሪኮችን ብትመለከት፣ የኢስላም ሊቃውንቶች እንዴት ውጤታማ ሆነው መፅሃፎችን እንዳዘጋጁ፣ በነርሱ ምክንያት ለውጤት የበቁ ዓሊሞችን ብትመለከት በእርግጥም አንት ከኖርካት እድሜ በታች ሆነ (ትገኛለች)።

ይህ የሆነውም አላህ ልባቸውን በሞላው ዚክር (አላህን ማስታወስ) ሰበብ ነው። በእድሜያቸው አንድ አፍታ እንኳን ያለ አግባብ የምትጠፋ ወቅት እስከማትኖር ደርሰዋል።

አደራህን!! ለዚህ የልብ በሽታ ትኩተረት ስጥ። መድኃኒቱን በመፈለግ ላይ በርታ። ምክንያቱም በሽታው በልብህ ከተሰራጨ (አላህን ጤናማነትን እንጠይቀዋልን) ይሞታል። በርሱ ላይም የታተመ/የታሸገ ይሆናል። ሀቅን ሀቅነቱን አይገነዘብም፣ ባጢልንም ባጢልነቱን አይገነዘብም።» [ተፍሲሩ ሱረት አል_አህዛብ]
✍🏻ኢብን ሽፋ: (t.me/ibnshifa)

#join ⤵️

https://telegram.me/IbnShifa
ትንሹ ዒድ ባህላዊ በዓል ወይስ እንደ አምልኮ ዘርፍ የተያዘ ቢድዐ?!
—————
ከዒደል ፊጥር ማግስት ጀምሮ የሚፆመውን 6ቀን የሸዋል ፆምን ተከትሎ ዒደል ፊጥር በወጣ በሳምንቱ የተወሰኑ ሙስሊሞች ዘንድ የሚከበር የሸዋል ፍቺ ወይም ትንሹ ዒድ በመባል የሚታወቅ በዓል አለ። ይህ በዓል እንደ ሸሪዓ ምንም አይነት ማስረጃ የሌለው በዋናነት ወደ ደቡብ ያሉ የተወሰኑ ብሔረሰቦች ዘንድ የሚከበር መሰረተ ቢስ የሆነ በዓል ነው። በተለይ አላህ ምንም አይነት ማስረጃን ያላወረደበት ይህ በዓል ስልጤና ጉራጌ ብሔረሰብ ዘንድ በልዩ ሁኔታ የሚከበር በዓል ነው። ዲናችን ሙሉ ነው። ከሁለቱ ዒድና ከሳምንታዊ ጁምዓ ውጪ ምንም ይሁን ምን አዲስ ፈጠራ (ቢድዐ) ነው። በዲናችን ላይ አዲስ ፈጠራ ሁሉ ደግሞ ጥመት ነው። የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በየ ሳምንት ጁምዓ ኹጥባቸው ላይ እንዲህ ይሉ ነበር:-
«…የነገሮች ሁሉ ሸር ማለት (በዲን ላይ) አዲስ ፈጠራ ነው፣ አዲስ ፈጠራ (ቢድዐ) ሁሉ ጥመት ነው» ሙስሊምና ነሳኢይ የዘገቡት ሲሆን፣ ነሳኢይ «ጥመት ሁሉ የእሳት ነው» የሚል ዘገባ ጨምሯል፣ ሰነዱም ሶሂህ ነው።

ይህ በዓል ከላይ የጠቀስኩላችሁ ብሔረሰቦች ዘንድ የሚከበር መሰረቱ ገጠር የነበረ ቢሆንም ከጊዜ ወዲህ ግን በየ ከተማውም በተለየ መልኩ ሌሎች ብሔረሰቦችም ተሳትፈውበት መከበር ጀምሯል። ለበዓሉም ልክ እንደሌሎች በሸሪዓ እንደተጠቀሱ በዓሎች (እንዲያውም በበለጠ መልኩ) የተለያዩ ዝግጅቶች ሲደረጉ ይስተዋላል። ታዲያ ማስረጃ የሌለው በዓል እስከሆነ ድረስ ምንም ይሁን ምን፣ መውሊድን ጨምሮ መላው የአለማችን ህዝብ ቢያከብረው እንኳን ቢድዐ ከመሆን አይወገድም!!። ቢድዐ ደግሞ ጥመት ነው፣ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው።

በትንሹ ዒድ ላይ አንዳንድ ስለ ዲናቸው ግንዛቤ አላቸው የሚባሉ፣ ሸሪዓው ከሚያግራራው ውጭ እያግራሩ ህዝብ ዘንድ ተደማጭነት ለማግኘት የሚዳክሩ ሰዎች የሚያነሱት ብዥታ አለ። እሱም "ምን ችግር አለው? ቢከበር ባህል ነው እንጂ ሃይማኖታዊ ይዘት የለውም" ይላሉ።

መልስ:-
1ኛ, ባህላዊ በዓል ቢሆንስ በዚህ መልኩ በየ አመቱ እየጠበቁ በድምቀጥ ማክበሩን ማን ፈቀደው?

የሙስሊሞች ሸይኽ በመባል የሚታወቁት ታላቁ ሊቅ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ (ረሂመሁላህ) የሸዋልን ስምንተኛውን ቀን እንደ በዓል አድርገው የሚይዙና (የደጋጎች ዒድ) ብለው የሰየሙ ሰዎችን አስመልክተው እንዲህ ይላሉ:-

(وأما ثامن شوال : فليس عيداً لا للأبرار ولا للفجار , ولا يجوز لأحد أن يعتقده عيداً, ولا يحدث فيه شيئاً من شعائر الأعياد ) ا. هـ. الاختيارات الفقهية ص/199

የሸዋል ስምንተኛው ቀንማ ለደጋጎችም ሆነ ለጠማሞች ዒድ አይደለም!። ለአንድም ሰው እለቱን ልዩ የመደሰቻ ዒድ ቀን አድርጎና አምኖ መያዝ አይፈቀድለትም!። በእለቱም ምንም አይነት ለዒድ ከሚንፀባረቁ ነገሮች ማንፀባረቅ አይፈቀድለትም!።” [አል-ኢኽትያራት አል-ፊቅሂየህ 199]

ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢምሙ ዐብዲልዐዚዝ ቢን ባዝ (ረሂመሁላህ) በውስጣቸው ሸሪዓን የሚፃረር ነገር ባይኖርባቸው እንኳን እንደ ባህል (ልማድ) ተደርገው የሚከበሩ በዓላትን በተመለከተ ተጠይቀው ሲመልሱ እንዲህ ይላሉ:- “ከሁለቱ ዒዶች ውጪ ማንኛውንም ዒድ አድርጎ መያዝ አይፈቀድም!። የእርዱ ቀን ዒድ (ዒደል አድሃ) እና ዒደል ፊጥር፣ እነዚህ ናቸው የሙስሊሞች ዒድ ማለት። እንዲሁም በየ ሳምንቱ የሚመጣው የሚሰገድበት እለተ ጁም ነው። በተረፈ በየ አመቱ የሚሽከረከር የሚሰባሰቡበት የሆነን ዒድ መያዝ መሰረት የሌለው ተግባር ነው። ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በኋላ ሶሃቦችም ይሁኑ ታቢዒዮች 3ቱ ክፍለ ዘመናት ውስጥ የነበሩ ትውልዶችም እንዲህ ያሉ በዓላትን አላከበሩም!። በኛ ላይ ግዴታው እነሱ የተጓዙበትን መከተልና በመንገዳቸው መጓዝ ብቻ ነው… ሰዎች መልካም ነው ብለው የሚያስቡት የሚደጋገም ባህል ካላቸው ሀቁን ካወቁና ከተረዱ በኋላ ያንን ባህል መተው ግዴታ ይሆንባቸዋል…” [የሸይኹ ዌብሳይት ላይ በድምፅም በፅሁፍም አለ።]

2ኛ, እንደ አምልኮ ዘርፍ ነው የሚይዙት።
2.1, ለዒደል ፊጥ ከሚያደርጉት ዝግጅት የበለጥ ለዚህ ቀን ነው የሚዘጋጁት።
2.2, በዋናናት አባቶችና እናቶች የሸዋልን 6ቀን አከታትለው የሚፆሙት የዚህን ቀን ፍቺ ለማክበር ነው።
2.3, በተጋነነ መልኩ ለዒደል ፊጥር ሀይላቸውን ቆጠብ አድርገው ለዚህ ቀን ግን ሀይላቸውን አሟጠው ይጨርሱና ከፊታችን ለሚመጣው ዒደል አድሃ እንኳን በቂ ዝግጅት አያደርጉም። ለዚህም ነው ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንቶች "አንድ ቢድዐ በተተካ ቁጥር ሌላ አንድ ሱንና ይሰርዛል" የሚሉት።
2.4, ዝግጅቱን በዋናነት የሚያከብሩ ሰዎች ሲጠየቁ የሸዋል 6ቀን ፆም ፍቺ (ዒድ) ነው ብለው ነው የሚናገሩት እንጂ ባህል ነው የሚል አመለካከት የላቸውም። ይህ (ባህል ነው) የሚለው አመለካከት ጠንካራ አቋም ያላቸው የሱና ሰዎች "ትንሹ ዒድ ቢድዐ ነው" ብለው ሲያስጠነቅቁ እነ ሸህ ገራገር ህዝቡ ዘንድ ተወዳጅነት ለማግኘት ሲጠየቁ የፈበረኩት አመለካከት ነው። ይህን አመለካከት ሲፈበርኩ ግን ይህን ሁሉ እውነታ ያውቁታል። እያወቁ ሀቁን ይደብቁታል፣ ያምታቱታል። ይህ ደግሞ አላህ እንዲህ በማለት አይሁዶችን የወቀሰበት አደገኛ ተግባር ነው:-

وَلَا تَلْبِسُوا الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُوا الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

«እውነቱንም በውሸት አትቀላቅሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ፡፡» አል-በቀረህ 42

3ኛ, እንዲህ ያሉ በዓላት ላይ ሌላው ከባድ አደጋ!! የተለያዩ የኢስላምና የሙስሊሙ ጠላቶች እንዲህ ያሉ አዳዲስ በዓላትን ቀንና መስለው በተለየ መልኩ በየ ሚዲያዎቻቸው እያስተዋወቁ ሙስሊሙ በሀይማኖቱ ከተደነገጉ ብርቅዬ በዓላት እንዲዘናጋና ከሀይማኖቱ ተቃራኒ መንገድ እንዲጓዝ ይሰራሉ።
ወላሁ አዕለም!!
✍🏻 ኢብን ሽፋ: (t.me/ibnshifa)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም 👇👇 ቻናላችን #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
የተረዳችዋ መንገድ ነጃ የምትወጣዋ የነቢያት መንገድ ናት። እሷን አጥብቀህ ያዝ!!
———
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዶ/ር ሙሀመድ ቢን ሰዒድ ረስላን (አላህ ይጠብቃቸውና) እንዲህ ብለዋል:-
«የነቢያት መንገድ ነጃ የምትወጣዋና የተረዳችዋ አንጃ መንገድ ናት፣ እሷም በሚከተሉት ምሶሶዎች የቆመች ናት:-
1⃣ በቀደምቶች ግንዛቤ፣ በሶሃቦችና እነሱንም በመልካም በተከተሏቸው ቀደምቶች ግንዛቤ ወደ ቁርኣንና ሀዲስ መመለስ ነው።
2⃣ አላህን በአምልኮ አንድ ወደማድረግ (ተውሒድ) ጥሪ ማድረግና ስራንም ብቸኛና ተጋሪ ለሌለው አላህ ብቻ ጥርት ማድረግ ነው።
3⃣ ሰዎችን በአላህ ላይ ከማጋራት (ሺርክ) ከተለያየ ቅርፁና እሱንም ከሚያጠናክሩ ነገሮች ማስጠንቀቅ ነው!።
4⃣ ከስህተት ፍፁም የሆኑትን ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መከተል ጥሪ ማድረግ ነው።
5⃣ ሰዎችን መከተልን እና ስሜትን መከተልን አርቆ መወርወር ነው።
6⃣ በሀይማኖት ላይ አዲስ ፈጠራን (ቢድዓን) መጠንቀቅ!፣ በግልፅም በውስጥም ከቢድዓ መጥራት።
7⃣ የቢድዓ ሰዎችን መጠንቀቅ! ከነሱ በማስጠንቀቅም በተመቻቸ መንገድ ሁሉ መቆም ነው።
8⃣ ጠቃሚ (ኢስላማዊ) እውቀትን ከቦታው መፈለግ ነው።
9⃣ ቀጥተኛውን መንገድ የሚከተሉና ስሜትን የሚጠነቀቁ ዑለማዎችን ደረጃቸውን ማወቅ ነው።
1⃣0⃣ ቁርኣንና ሀዲስን በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ ይገነዘባሉ።
1⃣1⃣ በኢማንና በኩፍር እንዲሁም በኢማን ጥብቅ በሆኑ ደሞች ጉዳይ ግንዛቤን ከሶሃቦች መያዝ ነው።
1⃣2⃣ በመልካም ማዘዝ ከተወገዘ ነገር መከልከል ነው።
1⃣3⃣ ከራስ ለመከላከልም ሆነ ፈልጎ በአላህ መንገድ ላይ መታገል ነው።
1⃣4⃣ ሙስሊም የዲን መሪነትና ለእርሱም ቃል መግባት ነው።
1⃣5⃣ (ሱንና ላይ ያሉ) የሙስሊሞችን ጀማዓ መያዝ።
1⃣6⃣ ከመሪዎች ጋር በመልካም ግንኙነት መፍጠርና ለአላህ ብሎ መውደድ ለአላህ ብሎ መጥላት።
1⃣7⃣ ወገንተኝነትን እና ጉሩፕተኝነትን አርቆ መወርወር።
1⃣8⃣ መልካም በሆነ ስነ–ምግባርና ስራን በማሳመር መጣበቅ ነው።
[ምንጭ:- ደዓኢሙ ሚንሃጅ አን-ኑቡወህ 25]
ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድርግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
👉 በሶስት_ነገሮች_ጊዜ_አታጥፋ__!!

‏ثلاث أمور لا تضيع بها وقتك ..

التحسر على ما فاتك لأنه لن يعود.

❶ባለፈ ነገር አትቆጭ አይመለስም
مقارنة نفسك بغيرك لأنه لن يفيد ,

❷ ነፍሰህን ከሌሎች ጋር አታነፃፅር አይጠቅምህም።

محاولة إرضاء كل الناس لأنه لن يكون

❸ ሁሉም ሰው እንድወድህ አትሞክር አይሳካም።

📌 የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️
#join ያድርጉና ይቀላቀሉ
⤵️
Join us ↪️ share
⤵️ join
🌐 https://t.me/YusufAsselafy
https://t.me/YusufAsselafy
https://t.me/YusufAsselafy
ሴት ልጅ ባሏ በሀሳብ ቢቃረናትም ሸሪዓን በሚጥስ ነገር እስካላዘዛት ድረስ ባሏን የመታዘዝ ግዴታ አለባት!!
—————
ይህ ነጥብ ብዙዎች ዘንድ የተዘነጋ ነጥብ ነው። ሚስት ባሏን መታዘዝ ግዴታ የሆነባት ባል የርሷን ሀሳብ በማይነቅፍ ነገር ሲያዛት ብቻ ሳይሆን በዋነኝነት የርሷን ሀሳብ በሚነቅፋት ነገር ሲያዛት ነው። የሀሳብ ልዩነት በሌለው ነገርማ ማንኛውም አካል በአንድ ነገር ላይ ተነጋግሮ የሀሳብ ልዩነት እስከሌለ ተስማምቶ ይጓዛል። አብሮ መጓዝ የማይቻለው የሀሳብ ልዩነት ሲፈጠር ነው። በባልና ሚስት መካከልም መለያየቱ የሚፈጠረው በዋነኝነት የባልን ትእዛዝ አለማክበር ሲከሰት ነው።

ሚስት የሀሳብ ልዩነት ሲፈጠር ባሏን የማትታዘዝ ከሆነ አላስፈላጊ ንትርኮችና ጭቅጭቆች ይፈጠራሉ!!። ይህ ማለት ደግሞ በመካከላቸው የነበረው ፍቅርና መተሳሰብ በአጭር ጊዜ ይሻክራል። ይህ ደግሞ በትዳራቸው ውስጥ ከባድ አደጋ ይሆናል።

እህቶች ሆይ! የሚከተለውን የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ንግግር ልብ ብላችሁ አንብቡት:-

قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«إذا صلت المرأة خمسها وصامت شهرها وحفظت فرجها وأطاعت زوجها قيل لها ادخلي الجنة من أي أبواب الجنة شئت» . ورواه ابن حبان في صحيحه عن أبي هريرة رضي الله عنه، والحديث صححه الألباني في الجامع الصغير.

አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
ሴት ልጅ አምስት ወቅቷን ከሰገደች፣ የረመዷን ወሯንም ከፆመች፣ ብልቷንም (ከዝሙት) ከጠበቀች፣ ባሏን ከታዘዘች በፈለግሽው የጀነት በር ግቢ ትባላለች።” [ኢብን ሂባን በሶሂሃቸው የዘገቡት ሲሆን አልባኒም በጃሚዑ ሰጊር ሶሂህ ነው ብለውታል]

እህቶቼ ሆይ! ይህ ቀላል ነገር አይደለምና ልዩ ትኩረት ስጡት!!። የባልን ትእዛዝ ላለማክበር የተቀመጠው መስፈርት አንድ ነገር ብቻ መሆኑን አስተውሉ እሱም "ሸሪዓን በሚጥስ ነገር ካዘዘ አለመታዘዝ ነው" በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ብዙ ጊዜ እህቶች ዘንድ የሚስተዋለው ነገር ባል (አላህ ይጠብቀንና) ሸሪዓን በሚጥስ ነገር ሲያዛቸው ይታዘዙትና ሀሳባቸውን በሚቃረን ነገር ሲያዛቸው ደግሞ አለመታዘዛቸው ነው። መልእክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሴት ልጅ ባሏን መታዘዟን በተመለከተ ከታላላቅ ዒባደዎች "ከሶላት፣ ብልቷን ከዝሙት ከመጠበቅ፣ የረመዷን ወርን ከመፆም" ጋር አያይዘው ነው ጀነት ለመግባቷ እንደ ሰበብ የጠቀሱት።

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ (ዐለይሂ ረህመቱላህ) ሴት ልጅ የባሏን ሀቅ አስመልክተው የአላህንና የመልእክተኛውን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሐቅ ከማክበርና ከመጠበቅ ጋር በማያያዝ እንዲህ አሉ:-

قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله تعالى:
"ليس علي المرأة بعد حق الله ورسوله أوجب من حق الزوج."
(مجموع الفتاوى: 32/260)

"በአንዲት ሴት ላይ ከአላህና ከመልክተኛው ሀቅ በመቀጠል ከባሉዋ ሀቅ በላይ ግዴታ የለባትም።" [መጅሙዕ አል-ፈታዋ 32/260]

قال الإمام ابن تيمية رحمه الله:- (المرأة المتزوجة طاعتها لزوجها أفضل من طاعتها لأبويها)
مجموع الفتوى 10-428

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ (ረሂመሁላህ) ባለ ትዳሯ ሴት ባሏን የመታዘዝ ደረጃው ምን ያህል እንደሆነም እንዲህ ሲሉ ይገልፃሉ:-

ባለ ትዳሯ ሴት ለባለቤቷ መታዘዟ ወላጆቿን ከምትታዘዘው ይበልጥላታል።” [መጅሙዕ አል-ፈታዋ 10/428]
✍🏻ኢብን ሽፋ t.me/IbnShifa

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
ሰዎችን በጭፍን አትከተል!!
—————
ሰዎች በሐቅ ይመዘናሉ እንጂ ሐቅ በሰዎች አይመዘንም!! የሀቅ እንጂ የሰዎች ጭፍን ተከታይ አትሁን!። ምክንያቱም የታዘዝከው ሐቅን እንጂ ሰዎችን እንድትከተል አይደለም!። በጭፍን ውዴታ ጥግ መድረስ አደጋ አለው። ጭፍን ተከታይ መሆን ሐቅ ከመቀበል ያውርሃልና ተጠንቀቅ!። በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም። አላህ ይጠብቀንና በጭፍን የተከተልከው ሰው ከተንሸራተተ አለያም ድንበር አላፊ ከሆነ አንተም አብረሀው ገደል ልትገባ ትችላለህና ጭፍን ተከታይ አትሁን!!።
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) “በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም” ብለዋል። በመሆኑም የሰዎች ጭፍን ተከታይ መሆንን ተጠንቀቅ። ወደ ቁል ቁል ሲወርዱ እንዳያወርዱህ፣ ድንበር ሲያልፉም በጭፍን ተከትለሃቸው እንዳታልፍ። የሰዎች ንግግር ትክክል ካልሆነ ተመላሽ ነው። ፍፁም የሆነውና ሊመለስ የማይችለው የመልእክተኛው ንግግርና ተግባር ብቻና ብቻ ነው።

ኢማሙ ማሊክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ማለታቸውን አትዘንጋ:- "ሁላችንም ተመላሾችና የተናገርነውም የሚመለስ ነው የዚህ ቀብር ባለ ቤት ሲቀር።" አሉ። የቀብሩ ባለ ቤት በማለታቸው የፈለጉበት መልአክተኛውን ነው።
ሐቅን እወቅ! ከዚያም ሰዎችን በሀቅ ትመዝናቸዋለህ። የሀቅ ሰዎችንም ታውቃለህ። ሰዎችን አውቀህ በጭፍን የምትከተላቸው ከሆነ ግን የሐቅ መመዘኛ መሰረትህ ትክክለኛ ማስረጃ ላይ የተገነባ ሳይሆን የሰዎች ጭፍን ውዴታና ጭፍን ተከታይነት ይሆንና ሲገለባበጡም አብሮ መገለባበጥ ይሆናል።

ቆም ብለህ አስተውል! ቡድንተኝነትና ጭፍን ውዴታ አያውርህ!። ነገ አላህ ፊት ወዳጅህ ጠላት ሊሆንብህ ይችላል። አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ

«ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡» አዝ-ዙኽሩፍ 67

ታዲያ ስትወድም ሆነ ስትጠላ በጭፍን አይሁን!። የወደድከው አቅጣጫ ከሳተና ለየት ያሉ ነገሮችን ካስተዋልክበት ቆም በል። በጭፍን መውደድም መጥላትም አደጋው የከፋ ነውና ተጠንቀቅ!!። ሳታስበው በሰለፊያ መንሀጅ ስም በተመሰረተ ልዩ በሆነ ቡድንተኝነትና ዘመናዊ ሙሪድነት አዘቅጥ ውስጥ እንዳትዘፈቅ!!። በጭፍን በውዴታው የከነፍከለት አካል መንገድ ከሳተ ተከትለሀው መሳትህ አይጠቅምህም! ከባድ አደጋ ነው። የሚጠቅምህ በየትኛውም ወቅት ሀቅን አጥብቀህ መያዝህ ነው!!።

በተለይ በፊትና ጊዜ ምንም ያህል በአንዳንድ መልካም ስራዎቹ የምትወደው በዳዒነት የገነነ ነገር ግን እውቀቱ እዚህ ግባ የማይባል የምትወደው ሰው ቢኖር እንኳ ጠንካራ ነጥቦች ሲነሱ፣ የሆነ ጊዜ "እኔ እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን አንስቼ ለመናገር እውቀቴ አይፈቅድልኝም" እያለ በሌላ ጊዜ ደግሞ የእውቀት ደረጃው በማይፈቅደው አጀንዳ ውስጥ ገብቶ ሲዘባርቅ እያየሀው ስለ ወደድከው ብቻ በጭፍን መከተል የለብህም!።

በየትኛውም ወቅት የጠንካራ እውቀት ባለ ቤቶችን እና በዳዒነት የገነኑ ያለ እውቀት ደረጃቸው ተከታይ ስላላቸው ብቻ በድፍረት የሚናገሩና ተከታዮቻቸውን ይዘው ወደፈለጉበት አቅጣጫ የሚዋዥቁ ያለ እውቀት ታዋቂ የሆኑ ሰዎችን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። ሐቅ በጋጋታና ከተለያየ አቅጣጫ በሚጮሁ በተደራጁ ቲፎዞዎች ጩሀት አይለካም!። እውነትን ቆም ብሎ በማስረጃ መለየት ነው እንጂ ጭፍን ተከታይ መሆን አደጋው የከፋ ነው!። ትላንት በጥሩ አቋምና በትክክለኛው መንሀጅ እያለ ጠላቶቹ የነበሩ ኢኽዋንን ጨምሮ "አይንህ ላፈር" የሚሉት ሰዎች ዛሬ እንዴት ወዳጆቹ ሊሆኑና እሱን ሊያደንቁ፣ ሊያሞግሱ እንደቻሉ? ቆም ብለህ ፈትሽ!!። እሱ ተለሳልሶ ከአቋሙ ሸርተት ብሎ ነው ወይስ እነሱ ወደ ትክክለኛው አቋምና መንሀጅ ተመልሰው ነው? ብለህ እራስህን ጠይቅ። ያለፉ ሂደቶችንና በወቅቱ ያሉ ሂደቶችንም በተረጋጋና በገለልተኝነት መንፈስ ቃኝ!። እውነት ጭፍን ተከታይነትና ቡድንተኝነት ሳያውረው ከልቡ ለፈለጋት ሰው ግልፅ ትሆናለች!።

ታላቁ ሸይኽ አሕመድ ኢብኑ የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ: -
ወላሂ! በጌታዬ ይሁንብኝ አላህ ዘንድ እገሌና አገሌ አይጠቅሙህም!። የሚጠቅምህማ በሀቅ ላይ መቆምህና ለሀቅና ለተከታዮቹ ረዳት መሆንህ ነው።” ረዱል ጀዋብ 54

»» ሐቅን ተከተል!። ለሸይኽ አሕመድ ቢን የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) ድንቅ ንግግር ትኩረት ስጠው!። ወገንተኝነት አያጥቃህ፣ ለሀቅ ብቻ ወግን! ሀቁ በበቂና በትክክለኛ ማስረጃ ከተነገረህ አንተም ሆንክ የምትወደው ዳዒ አለያም ከጎንህ ያሉ ወዳጆችህ መንገድ ስህተት እስከሆነ ወደ ሀቁ ለመመለስ አታንገራግር!! የተነገረህ እውነት እሰከሆነ ለመቀበል ቆራጥ አቋም ይኑርህ!። ምክንያቱም ወገንተኛ የምትሆንለት አካል ከአላህና ከመልእክተኛው በላይ የለምና ለአላህ እና ለመልእክተኛው እና ለሐቅ ብቻ ወገንተኛ ሁን!!። ሐቅ ከየትም ይምጣ ከማንም ሐቅ እስከሆነ መቀበል ነው። ሀቁ ካልተገለጠልህ ደግሞ እስኪገለጥልህ ከቡድንተኝነትና ጭፍን ተከታይነት ገለልተኛ ሆነህ በአደብ ፈልገው፣ በንፁህ ኒያ እስከፈለግከው ኢንሻአላህ ቢዘገይ እንኳ ፍንትው ብሎ ይታይሃል!!።
ግን ግን አደራ ምን ጊዜም ለግለሰቦች ከወገንተኝነት፣ ከጭፍን ተከታይነትና ከቡድንተኝነት ራስህን አርቅ!!። ምን ጊዜም ወገንተኝነታችሁ ለሐቅ ከሆነ ሐቅን የሚከተልን ትወዱታላችሁ ታከብሩታላችሁ እንጂ ጭፍን ተከታይ አትሆኑለትም!!።
አላህ ሐቁ ለተደበቀበት ግልፅ ያድርግለት!! የሀቅ ተከታዮችና በሐቅ ላይ ከሚፀኑ ባሮቹም ያድርገን!!

✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

#join ⤵️
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
ታላቁ ዓሊም ሱፍያን አስ-ሰውሪይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-

"የቢዳዓ ባልተቤት ጋር የተቀማመጠ ከሶስት ነገር ባንዱ ሰላም አይሆንም

1, ወይ ለሌሎች ሰዎች ፊትና ይሆናል! (ይህ በብዛት በዚህ ጊዜ የሚስተዋለው ከባድ አደጋ ነው)

2, ወይ በልቦናው ላይ የሆነ ነገር ሊከሰት (ይችላል) በርሱ ምክኒያት ይጠምና አላህ እሳት ያስገባዋል

3, አልያም (ሙብተዲዕዎች) በተናገሩት ንግግር በአላህ ይሁንብኝ ደንታ የለኝም፣ እኔ በነፍሴ እተማመናለሁ፣ ይላል። አላህን ደግሞ የዐይን እርግብታ ያክል በዲኑ ላይ (ምንም አያደርገኝም በራሴ እብቃቃለሁ በማለት) የተማመነ (አላህ) ዲኑን ይቀመዋል።"

【አል–ኢዕቲሷም 1/130】

አኚህ ታላቅ ዓሊም ከቢዳዓ ሰዎች ጋር የሚቀማመጥን ሰው በነዚህ ሶስት ከባባድ አደጋዎች አስጠንቅቀዋል!!።

ስለዚህ:-
ከቢደዓ ባለቤቶች ጋር ከመቀማመጥ እራስህን ቆጥብ!!

#join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
ነሺዳ-Ibn Shifa.61page.pdf
871.4 KB
ነሺዳ የሱፊዮች እና የኢኽዋኖች ዘፈን እንጂ ኢስላማዊ አይደለም!! PDF
"""""""
በኢብን ሽፋ ከ 3አመት በፊት ነሺዳን በተመለከተ ከኢኽዋኖችና ሱፊዮች ዘንድ ለሚነሱ ብዥታዎች አንድ በአንድ በቁርኣንና በሀዲስ የተሰጠ መልስ
#share #ሼር_አድርጉት!

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
ነሺዳ የሱፊዮች እና የኢኽዋኖች ዘፈን እንጂ ኢስላማዊ አይደለም!!

""""""""""""""የመፅሃፉ መቅድም""""""""""""""
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ በሆነው፣ በእርሱም እታገዛለሁ!።
ምስጋና በጠቅላላ ለዓለማቱ ብቸኛ ለሆነውና በሀይማኖቱ ደንጋጊ (ህግ አውጪ) ለሆነው፤ የሰው ልጆችን እውቀቱ በሌላቸው ነገር ላይ መከተልን የከለከለ ለሆነው፤ ብቸኛ ተመላኪ ለሆነው አምላካችን አላህ የተገባ ነው!!፡፡

የሰው ልጆችን እውቀቱ የሌላቸውን ነገር እንዳይከተሉ እንዲህ በማለት ከልክሏል፡-

﴿وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ  إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا ﴾ [الإسراء:٣٦]

ለአንተ በርሱ እውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፡፡ መስሚያ፤ ማያም፤ ልብም እነዚህ ሁሉ ‹ባለቤታቸው› ከእነሱ ተጠያቂ ነውና፡፡” አል ኢስራእ 36

ከነፍሳችን ተንኮልና ከብልሹ ስራችን በአላህ እንጠበቃለን፤ አላህ የመራውን የሚያጠመው የለም፤ አላህ ያጠመመውንም የሚያቃናው የለም! ከአንድ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ (በልቤ ያመንኩ ስሆን) የምስክርነት ቃሌን እሰጣለሁ፤ እርሱም ብቸኛና ምንም ተጋሪ የለውም! ነቢዩ ሙሐመድምﷺ የእርሱ ባሪያና መልእክተኛው መሆናቸውን (በልቤ ያመንኩ ስሆን) የምስክርነት ቃሌን እሰጣለሁ፡፡
ከንግግር ሁሉ እውነተኛው ንግግር የአላህ ቃል የሆነው ቁርኣን ነው! ከመንገዶች ሁሉ ትክክለኛው መንገድ (እምነት) የመልዕክተኛው የነቢዩ ሙሐመድ መንገድ (እምነት) ነው፡፡
የነገሮች ሁሉ አደገኛ በሀይማኖት ላይ አዲስ ፈጠራ (ቢድዓ) ማምጣት ነው! በሀይማኖት ላይ ፈጠራ (ቢድዓ) ሁሉ “ከነቢዩ ያልተለመደ” መጤ ነው፤ መጤ የተባለ በሙሉ ጥመት ነው፤ የጥመት ጎዳና በሙሉ የእሳት ነው።

ከዚህ በመቀጠል
በዚህን ጊዜ እንደሚታወቀው በብዛት በተጨባጭ እንደሚታየውም በአላህና በመልክተኛው ክልክል የተደረገው እንደተፈቀደ ነገር፤ የተፈቀደው ደግሞ እንደተወገዘ ነገር የሚታይበት ተጨባጭ ነው የሚታውየው። ለዚህም ያለ በቂ እውቀት ዝና እና ተወዳጅነትን ፍለጋ ብይን (ፈትዋ) የሚሰጡ አላዋቂ መሀይማን (ጃሂሎች) ዘንድ ሙፍቲ ተደርገው የተቀመጡ በስሜትና በመሀይማን ጭፍን ድጋፍ ሀቅን ላለመቀበል በትቢት የተወጠሩ፤ ያለ ደረጃቸው በመሀይማን ሸይኽና ኡስታዝ ተብለው የተሰቀሉ ብልሽትን የሚያስፋፉ (የፈሳድ) ሙፍቲዎች አሉ፡፡

ታዲያ እንዲህ ያሉ የጥመት ብይን (ፈትዋ) የሚሰጡ ሰዎችን ሀቅ ፈላጊውን ሚስኪኑን ህዝብ፤ በእንዲህ ያለ ፈትዋቸው ሲያስቱ ዝም ብሎ ማየት የአላህን ሀቅን ግልፅ የማድረግ አማና በአግባቡ አለመወጣት ከመሆኑም ባሻገር፤ የተወገዘን ንግግር የሚናገሩና በተወገዘ ነገር ላይ ይፈቀዳል ብለው ያለ እውቀት በድፍረት ፈትዋ የሚሰጡ ሰዎችን ባለማውገዛችን ከአይሁዶች እንዳንመሳሰል ያሰጋል፡፡ አላህ እነዚያ ከበኒ ኢስራኢል ከሀዲ የሆኑት የተረገሙበትን ምክንያት እንዲህ በማለት ገልፆልናል፡-

﴿لُعِنَ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ بَنِي إِسْرَائِيلَ عَلَى لِسَانِ دَاوُودَ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ  ذَلِكَ بِمَا عَصَوْا وَكَانُوا يَعْتَدُونَ٧٨كَانُوا لَا يَتَنَاهَوْنَ عَنْ مُنْكَرٍ فَعَلُوهُ ﴾ [المائدة: 78-79]

ከኢስራኢል ልጆች እነዚያ የካዱት በዳውድና በመርያም ልጅ በዒሳ ምላስ ተረገሙ፡፡ ይህ ትእዛዝን በመጣሳቸውና ወሰንን የሚያልፉ በመሆናቸው ነው፡፡ ከሰሩት መጥፎ ነገር አይከላከሉም ነበር፡፡” አልማኢዳ 78-79

ይህ በመሆኑም አንዱ ሲሳሳት ሌላኛው ተው! ማለት ግድ ይለዋል!፡፡ በመሆኑም ነሺዳን በተመለከተ የተሰጠውን የተሳሳተ ፈትዋ በቁርኣንና በሶሂህ ሀዲስ፤ በኢስላም ሊቃውንቶች የጋራ ስምምነት (ኢጅማዕ) ስህተት መሆኑን ለህዝበ ሙስሊሙ በተቻለ መጠን ግልፅ የተደረገ ሲሆን፤ ነሺዳን ሀላል ለማስመሰል የተነሱ ብዥታዎች ላይም አንድ በአንድ መልስ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ይህን ሶፍት ኮፒ/PDF አንብበው ለሌሎች በማሰራጨት ሌሎችንም ከነሺዳ ብዥታ ይታደጉ!!
ለአስተያየትና ለጥቆማ የሚከተለውን የኢሜይል አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡- Ibn.shifa11@gmail.com
PDFን በዚህ ሊንክም 👇👇 ያገኙታል
https://t.me/IbnShifa/1383

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
በተራዊህ ሶላት ላይም ይሁን በሌላ ሶላት ላይ ኢማሙ እየቀራ፣ ተከታዩ (መእሙሙ) ቁርኣን ይዞ መከታተሉ እንዴት ይታያል?!
—————
ለታላቁ ፈቂህ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንደሚከተለው ጥያቄ ቀረበላቸው:-
ጥያቄ:- ኢማምን መከተል ነው በሚል ማስረጃ ቁርኣን ይዞ ከኢማሙ ኋላ በተራዊህ ሶላት ላይ መከታተል ብይኑ ምንድነው?!

መልስ:- ለዚህ ጉዳይ ብሎ ቁርኣንን ይዞ ሶላት ላይ መቆም በሚከተሉት ምክያቶች ሱናን ይቃረናል:-
① አንድ ሰው ሶላቱ ላይ ከቆመ ቀኝ እጁን ግራው እጅ ላይ ማሳረፍ አለበትና ይህን ያስመልጠዋል። (ቁርኣን ይዞ ከሆነ ይህን ሊተገብር አይመቸውምና)
② አላስፈላጊና ከሶላቱ ውጪ ለሆኑ በርካታ እንቅስቃሴዎች ይጋብዘዋል፣ ለምሳሌ:- ቁርኣኑን ለመክፈትና ለመዝጋት፣ ለማስቀመጥ… መሰል ነገሮች ብሎ ከሶላቱ ውጪ የሆነን እንቅስቃሴ ያደርጋል።
③ ሰጋጁ በእነዚህ እንቅስቃሴዎች ይወጠርና (ሶላቱ ውስጥ የሚጠበቅበትን ኹሹዕና እርጋታ አይኖረውም።)
④ ሰጋጁን ወደ ሱጁድ ቦታ መመልከት ያመልጠዋል። አብዘሃኛው የኢስላም ሊቃውንቶች ሰጋጁ ወደ ሱጁድ ማድረጊያው ቦታ መመልከቱ ሱና እና በላጭ ነው ይላሉ።
⑤ ሰጋጁ ምናልባትም ሶላት ላይ መሆኑን የሚረሳበት ሁኔታ ሊኖርም ይችላል። ምክንያቱም:- ልቡ ሶላቱ ላይ አልተሰበሰበም፣ ሶላት ውስጥ ከመተናነስ በተቃራኒው ቀኝ እጁን ግራው ላይ አላሳረፈም፣ ጭንቅላቱን ወደ ሱጁድ ቦታ አቀርቅሮ እየተመለከተ ስላልሆነ… ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች ቢተገብር ልቡ ሶላቱ ላይ ሰብሰብ ይል ነበር፣ ይህም ሶላት ላይ ለመተናነስ ይረዳው ነበር። ከኢማም ኋላ ሆኖ እየሰገደ መሆኑንም ያውቅ ነበር…
[መጅሙዕ አል-ፈታዋ ኢብኑ ዑሰይሚን 14/232]
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
አላህ ይጠብቀን!!
🔹ብዙ ጊዜ ለሀላል ትዳር ተጠይቀው ባልሆነና እዚህ ግባ በማይባል ምክንያት ጥያቄውን ውድቅ የሚያደርጉ ሴቶች መጨረሻቸው ላይ ደስ የሚል ዜና አይሰማም!!። ይህ ብዙ ጊዜ የምናስተውለው ነውና እህቶች ዲኑንና አኽላቁን የምትወዱት ከመጣ ሳታንገራግሩ ቶሎ በሀላል ተሰተሩ!!

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የደላው  መች  ቀረ......?!
    
     ሁሉም ይሞታታል አስጠላም አማረ

   ሁሉም  ይጓዛታል ያቺን  የሩቅ ጉዞ

  የሌለው ባዶውን ያለው ስንቁን ይዞ

ዛሬማ ምን አለ ባይሰግዱ ባይፆሙ

ይቸግራል  እንጂ  አላህ  ፊት ሲቆሙ

ዛሬማ  ምን  አለ  ቢጠጡ  ቢሰክሩ

ይቸግራል  እንጂ  ሙተው  ሲቀበሩ

ዛሬማ  ማን  አለ   የሚያጋልጥሽ

ከቀብር  ስትገቢ  ይታያል  ጉድሽ


    ◈ ሸይኽ ሙሀመድ ወሌ (ረሂመሁላህ)

ዓጀብ ነው!! አላህ ኻቲማችን ያሳምረው!!

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
ከአሉ ተባለ ወሬ ተከልክለናልና እንጠንቀቅ!!
———
አሎባልታ ወሬ ብዙዎችን በተለያየ መንገድ አክስሯል!! አሉ ተባለ ወሬ በማህበረሰቡ ላይ ጉዳቱና መዘዙ የከፋ ስለሆነ ሸሪዓችን አጥብቆ ከልክሏል።
ከወርራድ አስሰቀፊይ ተይዞ እንዲህ አለ:-
ሙዓዊየህ ወደ ሙጊረህ ቢን ሹዕበህ እንዲህ በማለት ፃፈ፣ ከአላህ መልክተኛ ﷺ ከሰማሀው ምክር የሆነ ነገር ወደኔ ፃፍልኝ አለው፣ ሹዕበህ ኢብኑ ሙጊረህም እኔ ከመልክተኛው ﷺ የሚከተለውን ሲሉ ሰምቻለሁ በማለት ፃፈለት:- “አላህ ሶስት ነገሮችን ጠልቶላችኋል፣ አሉ ተባለን፣ ገንዘብን ማባከንና ጥያቄ ማብዛትን።” [ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት ሶሂህ ሀዲስ ነው።]

በዚህ አሉ ተባለ ወሬ ስንቱ ሱሰኛ ሆነ?!
ስንቱ ከቂርኣት (ከደርስ) ርቆ በዚህ ተጠመደ?!
ያውም የበለጠ ከማበላሸት ውጭ ሊያስተካክለው በማይችለው ነገር ላይ ገብቶ ስንቱ ተጠመደ?!
ስንቱ ነው በእንዲህ ያሉ ወሬዎች ተጠምዶ እውቀት ፈላጊ ምስኪኖችን ከደርስ ያቋረጠው?!
ስንቱ ነው በዚህ መልኩ ለቢድዐህ ባለቤቶችና ለአስመሳዮች በር የከፈተው?!
ስንቱ ነው በዚህ ተግባር ተዘፍቆ ከድሮ ጀምሮ ወደ ቡድንተኝነት (ተሀዙብ) ያመራው?!
እንንቃ!! ጎበዝ ጊዜያችን አናባክን!! ወዳጅነትን አሻክረው በጀመዓ ላይ ክፍተት እንዲፈጠር ሰበብ ከሚሆኑ ተግባሮች እንራቅ!! አሉ ተባለ ወሬን አጥብቀን ተጠይፈን እንራቅ!!

ታላቁ ፈቂህ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “በአሉ ተባለ ወሬ፣ ጥያቄን በማብዛትና ጊዜን በማባከን መወጠር (ቢዚ busy) መሆን በሰዎች መካከል ከተንሰራፋ በእውነቱ በሽታ ነው!! አላህን ጤነኛነትን እንጠይቀዋለ!!። ይህ ተግባር እንደ ትልቅ አንገብጋቢ ጉዳይ ይሆንበታል፣ በል እንዲያውም አንዳንዴ (በዚህ ተግባር ያልገጠመውን) ጥላትነት ለማይገባው ሁሉ ጥላትነትን ይጠቀማል፣ አለያም ደግሞ (በዚህ ተግባር ስለ ገጠመው ብቻ) ወዳጅነት የማይገባውን ወዳጅ ሊያደርግ ይችላል። ወደዚህ ደረጃ የሚደርሰው፣ ለዚህ እውቀትን ከመፈለግ አርቆ ውጥረት ውስጥ ለከተተው (ለአሉ ባልታ ወሬ) ከሰጠው ትኩረት የተነሳ ነው። እንደ ማስረጃ የሚያቀርበው ደግሞ ሀቅን መርዳት ነው የሚል ነው። እውነታው ግን እንደዛ አይደለም!። ይልቅ እውነታው ነፍስንም ሆነ ሰዎችን በማይመለከታቸው ነገር ውጥረት ውስጥ መክተት ነው!!።
የሆነ ወሬ ሳትፈልገው መምጣቱ ግን ውጥረት ውስጥ ሊከትህ አይችልም፣ እንደ ወሬ ማንኛውም ሰው ዘንድ ሳይፈልገውና ለወሬው ቦታ ሰጥቶ ሳይዘጋጅለት ሊመጣው ይችላል ነገር ግን ቦታ አይሰጠውም፣ በሱ ውጥረት ውስጥ አይገባም!!። ትልቅ ትኩረት የሚሰጠውም ጉዳዩ አይሆንም!! ምክንያቱም እውቀት ከመፈለግ ያዘናገዋል፣ ነገሮችንም ያበላሽበታል፣ በማህበረሰቡም ውስጥ የቡድንተኝነትን በር ይከፍታል፣ በዚህ ሰበብም ኡመቱ ለመከፋፈል ይበቃል።” [መጅሙዕ አል-ፈታዋ 26/127]

ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) በድጋሚ ተፍሲሩ ጁዝእ ዐማ ገፅ 197 ላይ እንዲህ አሉ:- “በእኛ ላይ ግዴታ የሚሆነው ፊትናዎችን ግልፅ የወጡትንም ይሁን በድብቅ የሚሰራጩትን መጠንቀቅ ነው!!፣ ሰዎችንም ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ ከሚያነሳሱ ነገሮች ሁሉ መራቅ ይጠበቅብናል፣ ሁሌም መረጋጋትን መያዝ ይጠበቅብናል፣ ከአሉ ተባለ ወሬ እና ጥያቄን ከማብዛት መራቅ ግዴታ ይሆንብናል፣ ይህ ነቢዩ ﷺ ከከለከሉት ተግባርም ነው። ስንት (በአሉ ተባለ ወሬ የምትሰራጭ) አንዲት ቃል የሰላ ሰይፍ የማይሰራውን ሰርታለች?!፣ በእኛ ላይ ግዴታ የሚሆነው የሚግባባና የሚዋደድ ማህበረሰብ እንዲሆን ከፊትና እና ፊትናን ከሚቀሰቅስ ነገር መራቅ ነው!!።”
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
የጓደኝነት መስፈርቶች
———
አል ፈቂህ ኢብኑ ጁዚይ አል'ማሊኪይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
የጓደኝነት መስፈርቶችማ ሰባት ናቸው

1ኛ, በእምነቱ ሱኒይ ሊሆን ግድ ነው።

2ኛ, በዲኑ ላይ አላህን የሚፈራ ሊሆን ነው። እርሱ የቢድዐህ ሰው ከሆነ አለያም ፋሲቅ አመፀኛ ሰው ከሆነ ባልደረባውን ወዳለበት አካሄድ ሊጎትተው ይችላል፣ አለያም ሰዎች በዚህ ይጠረጥሩታል፣ አንድ ሰው በጓደኛው ዲን ላይ ነውና።

3ኛ, የጥሩ አዕምሮ ባለ ቤት ሊሆን ይገባል። የሞኛሞኝ ሰው ጓደኝነት በላእ ነው።

4ኛ, የጥሩ ስነ-ምግባር ባለ ቤት ሊሆን ይገባል። መጥፎ ስነ-ምግባር ያለው ሰው ጠላትነቱ አይታመንም፣ ይህንም በምታስቆጣው ጊዜ ትፈትነዋለህ፣ ከተቆጣ ጓደኝነቱን ተወው።

5ኛ, ከሀሜት፣ ከምቀኝነት፣ ከሸር ፈላጊነትና ከሁለት ፊትነት ልቡ ንፁህ መሆን አለበት።

6ኛ, በቃሉ የሚፀና የማይዋልልና የማይቀያየር መሆን አለበት።

7ኛ, ለእርሱ ሐቅ እንደምትቆመው ለአንተም ሀቅ የሚቆምልህ መሆን አለበት። በአንተ ላይ ሀቅ እንዳለው እየተመለከትከለት ለአንተም ሀቅ አለህ ብሎ የማይመለከትልህ (ለሀቁ እንደምትቆምለት ለሀቅህ የማይቆምልህ) ጓደኛ ኸይር የለውም።
[አል-ቀዋኒን አል-ፊቅሂየህ ገፅ 460]
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

በዚህ ዘመን እነዚህን መስፈርቶች ያሟላ ጓደኛ ያለው ሰው ምንኛ ታድሏል!! ዋና ዋና መስፈርቶችንም ያሟላ ማግኘት ትልቅ ነገር ነው!!

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
የወንጀል ጠባሳ እና የሰው ልጆችን አዋራጅነቱ!!
———
ኢማም ኢብኑል ቀይም (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል:-

“በአንድ ሀገር ወንጀል አልሰፈነችም ያንን ሀገር ብታወድመው እንጂ።

» በሰዎች ልብም አትሰፍንም ልባቸውን እውር ብታደርገው እንጂ።

» በአንድ አካልም አትሰፍንም ያንን አካል ብታሰቃየው እንጂ።

» በህዝቦች ላይም አትሰፍንም ያንን ህዝብ ብታሳንሰው እንጂ።

» በነፍስ ላይም አትሰፍንም ያቺን ነፍስ ብታበላሻት እንጂ።
ወንጀል አትከሰትም አላህ ዘንድ ለባሪያው ውርደት ምክንያት ብትሆን እንጂ፣ ባሪያው አላህ ዘንድ ከተዋረደ ማንም አያከብረውም።
ልክ አላህ እንደተናገረው:-

{ وَمَنْ يُهِـنِ اللَّهُ فـَمـَا لَـهُ مِنْ مُكْـرِم ٍ} الحج ١٨

«አላህ የሚያዋርደውም ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለውም።» አል ሐጅ 18

በዚህች አለምና በመጨረሻይቱ አለም ተንኮል (ሸር)ና በሽታ አለን? ምክንያቱ (ሰበቡ) ወንጀልና አመፅ ቢሆን እንጂ።” [አዳኡ ወደዋእ ገፅ 42]
አላህ ከትልቁም ከትንሹም ወንጀል ይጠብቀን!!
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa