የሰለፍያ ደዕዋ በቻግኒالدعوة السلفية فى مدينة الشاغنى
681 subscribers
652 photos
56 videos
165 files
1.98K links
ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot

ይፃፉልን። ይላኩልን።
Download Telegram
#ወንድ___ከሆንክ____አግባ___!!

#ዱንያ_ላይ_የለችም__!!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ትዳርን ስትፈልግ አስበህ ተነሳ፡
አቧራህን አራግፍ ጉድፍህን አንሳ፡
አለምን ብትቃኝ ብትዞር ዳር እስከ ዳር፡
ከግንቦት-ነሀሴ ከመስከረም_ህዳር፡
ብትፈልግ ብትለፋ ሁሌ ቀንና አዳር፡
ብዙ ሴት በማየት አይገኝም ትዳር ፡
አይን መስፈርት አታርግ ልብህን አስውበው፡
በውስጥ ጥምረት ነው ፍቅር የሚደልበው፡
አብሮ በመኖር ነው ሁብ የሚከሰበው፡
ከዕለት ወደ እለት ነው ትዳር የሚያብበው፡
ከአመት ወደ አመት አብቦ ያፈራል፡
ስኬታማ ጥምረት በልጅ ይበሰራል፡
ሌላም ይደገማል እያደር ይገራል፡
ይህንን እውነታ ሁሉም ይናገራል፡
ስለዚህ ቶሎ አግባ ምኞት አታስረዝም፡
አንዷን ፅደቅባት አትበል ዝምዝም፡
ከዛውጭ አቃቂር በማውዛት መስፈርት ካበዛህ፡
ወጣትነት ያልፋል ሳትፈካ ጠነዛህ፡
ከጓሮ ሳትወጣ በታዛ ጠነዛህ፡
ዋጋህን አርክሰህ በነፃ ተገዛህ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ይህንንም ስልህ አትፍራ ፈፅሞ፡
ከልክህ አትነስ ስሜትህ ተዳክሞ፡
ሚዛንህ ሀቅ ይሁን አትውጣ ከመስመር፡
በሱና ተወዳጂ በመንሀጂ ተጣመር፡
በቃ ወንድ ከሆንክ ሴት ተፈጥሮልሀል፡
በሀላሉ ድፈር አግባ ተብለሀል፡
ከዚህ ውጭ ክብር ምን ያደርግልሀል፡
#የኔ_እህት___!!
አንችም ሸርጥ አታብዥ ሀላሉን ድፈሪው፡
እየተግደረደርሽ በተስፋ አታኑሪው፡
ሞቅ በረድ እያልሽ በቃ አታደናግሪው፡
በሀላሉ እሽ በይ ሱናውን ድፈሪው፡
ሰለፍይ ከሆነ ምን አለው አትበይ፡
አርኪ መልስ ስጭው አግቢ መርሀባ በይ፡
#ወንድሜ__!!
መስፈርት አትደርድር ላይሆን አትውተርተር፡
በል ደርሰሀል አግባ በሱናው ተሰተር፡
ውሸት አትቀምም በወሬ አትተርተር፡
እውነትን ተናገር ውሸት አትጨምር፡
የሀሰት ጂማሮ ፍፃሜው ላያምር፡
የተባረከች ሴት በምርጫ አትገኝም፡
ሱንይ ጀግና እንስት ፈፅሞ አትሞኝም፡
ስለዚህ ወዳጀ አንዷን ፅደቅባት፡
ሞክረው ትዳሩን አለው ግሩም ቅባት፡
ንፁህ እህትህን ተው ግራ አታጋባት፡
ቀጠሮን አታብዛ በል ወስነህ አግባት፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ዛሬ ከአንደኛዋ ነገ ካንደኛዋ ሁሌ ቃል አትግባ፡
አቋም የለሽ ዋላይ አትሁን የማትረባ፡
ምርጫ እሚያበዛ ሰው ፍፃሜው አያምርም፡
ደስታ ይርቀዋል ስኬቱም አይሰምርም፡
ብዙ ሴት በማየት ሙራድህ ላይሞላ፡
በል ወስንና አግባ አትበል ወደ ኋላ፡
አንዷ ላይ አተኩር አትይ ወደ ሌላ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አግባ አትጨናነቅ ወንድ ነህ ሴት ሞልቷል፡
ነው ወንድ አይደለህም ስብዕናህ ሞቷል!?
ጤና ይጎድልሀል አዕምሮህ ተነክቷል!?
በህመም ምክንያት ልብህ ቀልብህ ጓሽቷል!?
በወንጀልህ ብዛህ አዕምሮህ ታውኳል!?
ከጂስምህ ርቋል የወንድነት አስኳል!?
ምርጫህን አታብዛ ከዚችም ከዛችም፡
ይህች አለም ጠፊ ነች ዘውታሪ አይደለችም፡
ለተጣመረ እንጂ ለላጤ አትመችም፡
አቋምህን ግለፅ ወሬን አትቸምችም፡
የብቻ ኑሮህን ለምን አትሰለችም?
ምድራዊ ሴት አግባ በተስፋ አትገችም፡
ሁረልዒን ከሆነች ዱንያ ላይ የለችም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በኑረዲን አል አረቢ 19/01/1443
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬