የሰለፍያ ደዕዋ በቻግኒالدعوة السلفية فى مدينة الشاغنى
669 subscribers
634 photos
56 videos
163 files
1.86K links
ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot

ይፃፉልን። ይላኩልን።
Download Telegram
ሰዎችን በጭፍን አትከተል!!
—————
ሰዎች በሐቅ ይመዘናሉ እንጂ ሐቅ በሰዎች አይመዘንም!! የሀቅ እንጂ የሰዎች ጭፍን ተከታይ አትሁን!። ምክንያቱም የታዘዝከው ሐቅን እንጂ ሰዎችን እንድትከተል አይደለም!። በጭፍን ውዴታ ጥግ መድረስ አደጋ አለው። ጭፍን ተከታይ መሆን ሐቅ ከመቀበል ያውርሃልና ተጠንቀቅ!። በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም። አላህ ይጠብቀንና በጭፍን የተከተልከው ሰው ከተንሸራተተ አለያም ድንበር አላፊ ከሆነ አንተም አብረሀው ገደል ልትገባ ትችላለህና ጭፍን ተከታይ አትሁን!!።
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) “በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም” ብለዋል። በመሆኑም የሰዎች ጭፍን ተከታይ መሆንን ተጠንቀቅ። ወደ ቁል ቁል ሲወርዱ እንዳያወርዱህ፣ ድንበር ሲያልፉም በጭፍን ተከትለሃቸው እንዳታልፍ። የሰዎች ንግግር ትክክል ካልሆነ ተመላሽ ነው። ፍፁም የሆነውና ሊመለስ የማይችለው የመልእክተኛው ንግግርና ተግባር ብቻና ብቻ ነው።

ኢማሙ ማሊክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ማለታቸውን አትዘንጋ:- "ሁላችንም ተመላሾችና የተናገርነውም የሚመለስ ነው የዚህ ቀብር ባለ ቤት ሲቀር።" አሉ። የቀብሩ ባለ ቤት በማለታቸው የፈለጉበት መልአክተኛውን ነው።
ሐቅን እወቅ! ከዚያም ሰዎችን በሀቅ ትመዝናቸዋለህ። የሀቅ ሰዎችንም ታውቃለህ። ሰዎችን አውቀህ በጭፍን የምትከተላቸው ከሆነ ግን የሐቅ መመዘኛ መሰረትህ ትክክለኛ ማስረጃ ላይ የተገነባ ሳይሆን የሰዎች ጭፍን ውዴታና ጭፍን ተከታይነት ይሆንና ሲገለባበጡም አብሮ መገለባበጥ ይሆናል።

ቆም ብለህ አስተውል! ቡድንተኝነትና ጭፍን ውዴታ አያውርህ!። ነገ አላህ ፊት ወዳጅህ ጠላት ሊሆንብህ ይችላል። አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ

«ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡» አዝ-ዙኽሩፍ 67

ታዲያ ስትወድም ሆነ ስትጠላ በጭፍን አይሁን!። የወደድከው አቅጣጫ ከሳተና ለየት ያሉ ነገሮችን ካስተዋልክበት ቆም በል። በጭፍን መውደድም መጥላትም አደጋው የከፋ ነውና ተጠንቀቅ!!። ሳታስበው በሰለፊያ መንሀጅ ስም በተመሰረተ ልዩ በሆነ ቡድንተኝነትና ዘመናዊ ሙሪድነት አዘቅጥ ውስጥ እንዳትዘፈቅ!!። በጭፍን በውዴታው የከነፍከለት አካል መንገድ ከሳተ ተከትለሀው መሳትህ አይጠቅምህም! ከባድ አደጋ ነው። የሚጠቅምህ በየትኛውም ወቅት ሀቅን አጥብቀህ መያዝህ ነው!!።

በተለይ በፊትና ጊዜ ምንም ያህል በአንዳንድ መልካም ስራዎቹ የምትወደው በዳዒነት የገነነ ነገር ግን እውቀቱ እዚህ ግባ የማይባል የምትወደው ሰው ቢኖር እንኳ ጠንካራ ነጥቦች ሲነሱ፣ የሆነ ጊዜ "እኔ እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን አንስቼ ለመናገር እውቀቴ አይፈቅድልኝም" እያለ በሌላ ጊዜ ደግሞ የእውቀት ደረጃው በማይፈቅደው አጀንዳ ውስጥ ገብቶ ሲዘባርቅ እያየሀው ስለ ወደድከው ብቻ በጭፍን መከተል የለብህም!።

በየትኛውም ወቅት የጠንካራ እውቀት ባለ ቤቶችን እና በዳዒነት የገነኑ ያለ እውቀት ደረጃቸው ተከታይ ስላላቸው ብቻ በድፍረት የሚናገሩና ተከታዮቻቸውን ይዘው ወደፈለጉበት አቅጣጫ የሚዋዥቁ ያለ እውቀት ታዋቂ የሆኑ ሰዎችን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። ሐቅ በጋጋታና ከተለያየ አቅጣጫ በሚጮሁ በተደራጁ ቲፎዞዎች ጩሀት አይለካም!። እውነትን ቆም ብሎ በማስረጃ መለየት ነው እንጂ ጭፍን ተከታይ መሆን አደጋው የከፋ ነው!። ትላንት በጥሩ አቋምና በትክክለኛው መንሀጅ እያለ ጠላቶቹ የነበሩ ኢኽዋንን ጨምሮ "አይንህ ላፈር" የሚሉት ሰዎች ዛሬ እንዴት ወዳጆቹ ሊሆኑና እሱን ሊያደንቁ፣ ሊያሞግሱ እንደቻሉ? ቆም ብለህ ፈትሽ!!። እሱ ተለሳልሶ ከአቋሙ ሸርተት ብሎ ነው ወይስ እነሱ ወደ ትክክለኛው አቋምና መንሀጅ ተመልሰው ነው? ብለህ እራስህን ጠይቅ። ያለፉ ሂደቶችንና በወቅቱ ያሉ ሂደቶችንም በተረጋጋና በገለልተኝነት መንፈስ ቃኝ!። እውነት ጭፍን ተከታይነትና ቡድንተኝነት ሳያውረው ከልቡ ለፈለጋት ሰው ግልፅ ትሆናለች!።

ታላቁ ሸይኽ አሕመድ ኢብኑ የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ: -
ወላሂ! በጌታዬ ይሁንብኝ አላህ ዘንድ እገሌና አገሌ አይጠቅሙህም!። የሚጠቅምህማ በሀቅ ላይ መቆምህና ለሀቅና ለተከታዮቹ ረዳት መሆንህ ነው።” ረዱል ጀዋብ 54

»» ሐቅን ተከተል!። ለሸይኽ አሕመድ ቢን የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) ድንቅ ንግግር ትኩረት ስጠው!። ወገንተኝነት አያጥቃህ፣ ለሀቅ ብቻ ወግን! ሀቁ በበቂና በትክክለኛ ማስረጃ ከተነገረህ አንተም ሆንክ የምትወደው ዳዒ አለያም ከጎንህ ያሉ ወዳጆችህ መንገድ ስህተት እስከሆነ ወደ ሀቁ ለመመለስ አታንገራግር!! የተነገረህ እውነት እሰከሆነ ለመቀበል ቆራጥ አቋም ይኑርህ!። ምክንያቱም ወገንተኛ የምትሆንለት አካል ከአላህና ከመልእክተኛው በላይ የለምና ለአላህ እና ለመልእክተኛው እና ለሐቅ ብቻ ወገንተኛ ሁን!!። ሐቅ ከየትም ይምጣ ከማንም ሐቅ እስከሆነ መቀበል ነው። ሀቁ ካልተገለጠልህ ደግሞ እስኪገለጥልህ ከቡድንተኝነትና ጭፍን ተከታይነት ገለልተኛ ሆነህ በአደብ ፈልገው፣ በንፁህ ኒያ እስከፈለግከው ኢንሻአላህ ቢዘገይ እንኳ ፍንትው ብሎ ይታይሃል!!።
ግን ግን አደራ ምን ጊዜም ለግለሰቦች ከወገንተኝነት፣ ከጭፍን ተከታይነትና ከቡድንተኝነት ራስህን አርቅ!!። ምን ጊዜም ወገንተኝነታችሁ ለሐቅ ከሆነ ሐቅን የሚከተልን ትወዱታላችሁ ታከብሩታላችሁ እንጂ ጭፍን ተከታይ አትሆኑለትም!!።
አላህ ሐቁ ለተደበቀበት ግልፅ ያድርግለት!! የሀቅ ተከታዮችና በሐቅ ላይ ከሚፀኑ ባሮቹም ያድርገን!!

✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

#join ⤵️
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
የምን ፕራንክ ነው!? እንዴ!!!
መሰልጠን እና መሰይጠን ለዩ

       ❪„„„„„„„„„„„„„„„„„❫

ባለንበት የተደበላለቀ ዘመን የጠራ እውቀት ላይ ሆኖ ዲኑን እና ክብሩን የጠበቀ ታድሏል።

♻️ በአሁኑ ሰዓት አብዛኛውን ሰው busy ካደረጉት የምዕራባውያን ኮተቶች መካከል “ፕራንክ” ❮prank❯ የሚሉት ነው።
➲ Prank ማለት ራሳቸው ምዕራባውያን እንደሚከተለው ይተረጉሙታል፦
«Prank is a mischievous trick or practical joke.»
ፕራንክ ማለት የተሳሳተ ተንኮል ወይም ተግባራዊ ቀልድ ነው።


ይህ የተሳሳተ ተንኮል ሰዎች ባለወቁበት መልኩ የሚያስደነግጥ ነገር ይተገበርባቸዋል። ከደነገጡ ብሎም ካለቀሱ በኋላ prank ይባላሉ። በዚህ ተግባር በርካታ አላስፈላጊ ኮተቶች አሉ።

↪️ ሙስሊሞች በዚህ ተግባር መሳተፍ የለባቸውም በፍፁም አንዳንድ ሙስሊሞች ተሳትፈውበታል። የድሮ ፍቅረኛዬ ምናምን እያሉ ወንጀላቸውን በሚዲያ የበተኑ ሙስሊም ሴቶችን  አስተውያለሁ። ካፊር ሴት እያቀፈ የሚጃጃል ወንድም ተመልክቻለሁ። ሌሎችም

ስለዚህ ከዚህ እና መሰል ኮተቶች መራቅ አስፈላጊ ነው። የዚህን መሰል ፈሳድ ካፊሮች ሲያመጡ መከተል እነሱን ከመወዳጀት  ነው። ይህ ደግሞ አደጋ መሆኑ ግለሰፅ ነው።

«وَمَنْ يَتَوَلَّهُمْ مِنْكُمْ فَإِنَّهُ مِنْهُمْ»
[المائدة: 51]
ከእናንተ የተወደጃቸው ሁሉ እርሱ ከእነርሱ ነው❞

♻️ ነብዩ ﷺ ይህን አይነት መመሳሰል በግልጽ ማውገዛቸው ከማናችንም የሚሰወር አይመስለኝም።

عَنِ ابْنِ عُمَرَ قَالَ:- قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:- "مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ".
(صحيح أبي داود)
حسنه الألباني (3401)


ኢብኑ ዑመር  ነብዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፏል፦
“ከሆኑ ሰዎች ጋር የተመሳሰለ ከነሱው ነው”
[ሶሂህ አቡ ዳውድ]

ፕራንክ የምዕራባውያን ፍብርክ መሆኑ ግልፅ ነው። በዚህ ተግባር መሰለፍ ከእነሱ መመሳሰል ነው። ሲጀመር በውስጡ ያሉ ፈሳዶች ❪ጥፋቶች❫ ፕራንክ መራቅ ካሉብን ተግባራት መሆኑን ይጠቁሙናል።

ሌላ አንድ ሀዲስ እንጨምር፦
«عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:- ((لَتَتْبَعُنَّ سَنَنَ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ شِبْرًا شِبْرًا وَذِرَاعًا بِذِرَاعٍ، حَتَّى لَوْ دَخَلُوا جُحْرَ ضَبٍّ تَبِعْتُمُوهُمْ)). قُلْنَا يَا رَسُولَ اللَّهِ الْيَهُودُ وَالنَّصَارَى قَالَ:- ((فَمَنْ)).»
رواه البخار ٧٣٢٠

↪️ አብደላህ ብን ኹድሪይ እንዳስተላለፈው ነብዩ ﷺ የሚከተለውንብለዋል፦
“ከናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ፈለጎች ስንዝር በስንዝር ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ። የአርጃኖ ጉድጓድ ቢገቡ እንኳን በርግጥም ትገቡታላችሁ!” ሲሉ “አይሁድና ክርስቲያኖችን ነው (ትከተላላችሁ) የምትለን?” ብለው ቦጠይቁ “ታዲያ ማንን ነው?!”
  [ቡኻሪ፡ 7320]

ከዚህ ሀዲስ አንፃር የት ነን!? በፕራንክ ጉዳይ busy የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ሀዲስ ልትገሰፁ ይገባል። እስከመቼ ይሁዳ እና ነሷራ ተከትለን እንጓዛለን!? ደግሞ ሙሉዕ የሆነ ዲን እያለን!!! እስልምና ያጓደለው ምንም የለም።  እስልምና ያላስተማረው ካለና ከሰራነው በትክክል ጥመት ነው። በጥመት ተግባር መሳተፋችንንም ማወቅ አለብን። ነገሮችን ቀለል ማድረግ ትተን ከፕራንክ እና መሰል ኮተቶች መራቅ አለብን።

↪️ በነገራችን ላይ በዚህ ፕራንክ በሚሉት ኮተት ብዙ ጊዜ የሚከሰቱበት ሁለት ተግባሮች አሉ እነሱም፦
❶ኛ ሰዎችን ማሸበር ወይም ማስደንገጥ እና
❷ኛ በውሸት ቅንብር ማሳቅ ነው።


☑️ እነዚህ ሁለት ተግባራት ደግሞ በእስልምና የተከለከሉ ናቸው። ማስረጃዎችን እንመልከት፦

የመጀመሪያውን በተመለከተ ሙስሊም ሌላ ሙስሊምን ማስጨነቅ ወይም ማሸበር አይፈቅድም፦

عن عبدالرحمن بن أبي ليلى قال:-  قال رسول الله ﷺ "لا يحلُّ لمسلمٍ أن يروِّعَ مسلمًا"
       صححه الإمام  الألباني 
         سنن أبي داود


አብዱረህማን ኢብኑ አቢ ሌይላ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
"አንድ ሙስሊም ሙስሊምን ማሸበር አይፈቀድለትም"
ሱነን አቢ ዳውድ
ኢማም አልባኒ ሶሂህ ብለውታል


ሁለተኛው ደግሞ ሰዎችን ለማሳቅ በሚል ውሸት እየፈጠሩ መናገር በኢስላም አይፈቀድም። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-

وَيْلٌ لِلَّذِي يُحَدِّثُ بِالْحَدِيثِ لِيُضْحِكَ بِهِ الْقَوْمَ فَيَكْذِبُ وَيْلٌ لَهُ وَيْلٌ لَهُ»

"ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ እየዋሸ ወሬን የሚያወራ ሰው ወዮለት! ወዮለት! ወዮለት!"

አቡነ ዳውድ፣ ነሳኢይ፣ ቲርሚዚይ
ሸይኹል አልባኒይ “ሐሰን” ብለውታል፡፡


በሌላ በኩል ደግሞ የሚከተለውን ሀዲስ እናገኛለን፦
عن أبي أمامة رضي الله عنه قال:- قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم:-
"أنا زعيم ببيت في ربض الجنة لمن ترك المراء وإن كان محقا، وببيت في وسط الجنة لمن ترك الكذب وإن كان مازحا، وببيت في أعلى الجنة لمن حسن خلقه".
 سنن أبي داود
وحسنه الألباني.


♻️ አቡ ኡማማህ ረዲየሏሁ ዐንሁም እንዲህ ብለዋል፡- የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፡-
"እኔ እውነተኛ ቢሆን እንኳን ክርክርን ለተወ ሰው በጀነት ዙሪያ ወይም ዳርቻ ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ። ቀላጅ እንኳን ቢሆን ደግሞ ውሸትን ለተወ ሰው በጀነት መሀል ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ። ስነ ምግባሩ ላማረለት ደግሞ በጀነት የላይኛው ክፍል ውስጥ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ።"
ሱነን አቢ ዳውድ
አል-አልባኒ ሀሰን ብለውታል።


➲ በዚህ ሀዲስ ❸ ነጥቦች ጎልተው ተጠቅሰዋል።
❶ኛ ክርክር
❷ኛ ውሸት
❸ኛ ስነ-ምግባር


ውዱ ነብይ ﷺቀላጅ እንኳን ቢሆን ደግሞ ውሸትን ለተወ ሰው በጀነት መሀል ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ።❞ በማለት በቀልዳችን መዋሸት እንደሌለብን አስረድተዋል። ስለዚህ ውድ እህት ወንድሞች በፕራንክ ቀልድ የሚደረጉ ውሸቶች ትክክል አይደሉም። እኛም ተጠንቅቀን ሌሎችንም ልናስጠነቅቅ ይገባል።

📝 አቡ ዒምራን ሙሐመድ መኮንን

https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
#የወንድ ሀያዕ!
~  ~
     #ወንድ ልጅ  በተፈጥሮው ሀያዕ ያላትን ሴት ይፈራል! ያፍራልም! ሰተር ያልሽና ቁጥብ ከሆንሽ ሊላከፍሽ ይቅርና ቀና ብሎ አንቺን ለማየት አይደፍርም ።

    #ራስሽን ካከበርሽ ወንድ ልጅ ያከብርሻል ለራስሽ ክብር ከሌለሽ ደግሞ ወንድ ልጅ ሊያከብርሽ አይችልም ።

      #ክብርሽን ስትጠብቂ ከነ_ክብረሽ ሊወስድሽ ወላጆችሽን ይማፀናል!

      #ራስሽን ስታረክሺ ግን ጊዜ ለማሳለፊያ እንጂ ለቁም ነገር አይፈልግሽም ።

    #ሴት ልጅ ራሷን ሰብሰብ አድርጋ ስትኖር ወንድ ሊያት ያፍራል በጎኑ እንኳን ብታልፍ ቀና ብሎ አያይም ።

    #የወንድ ልጅ ሀያዕው ሴት በጎኑ ስታልፍ አይኑን ሰበር ማድርግ ነው አንቺ ሰተር ብለሽ ስትመጪ ደሞ ማየትን አይሻም ።

     #ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ
ራስሽን ሰትር አድርጊ እንቁ ትሆኛለሽ ውዷዬ !

https://t.me/umusaymen
Forwarded from «ሰለፎችን እንከተል» channel (abdurahman(አቡ ፉዶይል))
ወንድም እህቶቼ

🔶መስጅድ ስንገባ ጫማችንን በፔስታል ይዘን እንገባለን ወይም የሚጠብቅ ካለ እንሰጣለን፣......... ይሄ ሁሉ ጥንቃቄ ጫማችን በሌባ እንዳይሰረቅ ነው!!! ጡሩ።
አቂዳችንና መንሃጃችንስ እንዳይሰረቅ ምን እያደረግን ነው
እኔ ከታዘብኩት ላካፍላችሁ፦
⛔️ምኑንም የማያውቁትን ሰው ፣ በሚድያ ብቻ ድምፁን ሰምተው ወደውት አቂዳና መንሃጃቸውን አሳልፈው የሰጡ ብዙ ሰወች አሉ‼️ በቃ ዓሊም ይሁን መሃይም ይሁን ምኑንም ሳያውቁ ሚድያ ላይ የዘለለንና የጮኸን እንደጅራት የሚከተሉ በጣም ብዙ ናቸው‼️ በተለይ በተለይ ውጭ ሃገሩ ያሉ እህቶቻችን (ሁሉም)አይደሉም ግን አብዛኞቹን በሚባል ደረጃ ምንም አያውቁም 👉 ኪታብ አይደለም ቁርአን ያልጀመሩ ግን በአፈቅቤ ወንዶች ተሸውደው የሱን ጀልባ ተሳፍረው እየነጎዱ ነው።

ዓላመቱ ሷሊህ አል'ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንድህ ይላሉ፦

#አንተ

አንተ ሸቀጣሸቀጥ ለመግዛት ስትፈልግ ፤ መኪና ለመግዛት ስትፈልግ ወይም ሌላ ትንሽ ነገር ለመግዛት ፈልገህ ሰለዛ እቃ ምንም እውቀት ከሌለህ #ተሳስተህ_የማይሆን ነገር እንዳትገዛ #ፈርተህ ስለዛ እቃ #ወደሚያወቅ_ሰው_ሄደህ_ትጠይቃለህ!!!👈ይሄ በዱኒያዊ ጉዳይ ነው። 👉 #በድንህ_ጉዳይ #ለምንድነው አዋቂወችን፣ አላህን የሚፈሩትን ፣የእውቀት ባለቤቶችን #የማትጠይቀው

#ለዱኒያህ_እየመረመርክ_ለድንህ_ለምድነው_የማትመረምረው»

ምንጭ፦ሚን አዳቢ አል'ሙፍቲ
ወአል'ሙስተፍቲ

⛔️ በቃ የወደዱትን ሰው ሌላ ሰው በመረጃ ጥፋቱን ቢናገርም በቃ ተናጋሪው ማንም ይሁን‼️ ለምን ዓሊም፣ ሸይኽ አይሆንም አውርደው ከመፈጥፈጥ ወደሗላ አይሉም‼️ ምን ያክል ተዓሱብ እንዳሰከራቸው በግልጽ እያየነው ያለ ጉዳይ ነው። ደግሞ ወደሰለፊያ (የውሸት)መጠጋታቸው ነገሩን ይበልጥ አስጠሊታ ያደርገዋል። ለምን ካላችሁ ሙሪድነት ሰለፊያ ላይ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ስለሆነ ነው።

⛔️ ከወንዶች ደግሞ እዚህ ሚድያ ላይ የታዘብኩት👉 ፉላን የነቃ ነው ፣ እሱ ትንሽ እውቀት አለው ፣ አስተዋይና በሳል ነው፣........ ብለን የምናስባቸው የተመዩዕ ፊትና ስትመጣ ብጥስጥሳቸው ወጥቶ ፣ ሹቡሃ ጠራርጎ ወሰዳቸው። በዚህም አልበቃቸውም ሰለፊያን ከጠላቶቿ ጎን ቆመው መዋጋት ጀመሩ‼️
ለካ ተሳስተን ነበር ብለናል።


وَتَحْسَبُهُمْ أَيْقَاظًا وَهُمْ رُقُودٌ ۚ

እነሱም የተኙ ሆነው ሳሉ (ዓይኖቻቸው በመከፈታቸው) ንቁዎች ናቸው ብለህ ታስባቸዋለህ፡፡

ሱራ አል'ካህፍ:18

↪️ ይሄን ያክል ርቀት የተጓዛችሁለት ሰው የሰለፊያን የማይቀማ ሰርቲፊኬት ማነው የሰጠው አወ በፊት ሰለፊይ ሊሆን ይችላል!!! ታድያስ በህይወት ያለ ሰውኮ ፊትና አይታመንለትም!!! ሊጠም ይችላል በል እንዳውም ከሃድም ሊሆን ይችላል‼️ ታድያስ ማነው ግለሰብ ላይ ተጣበቁ ያላችሁ

🔰ዓበደላህ ኢብኑ መስዑድ ረድየላሁ ዓንሁ እንድህ ብለዋል፦

«ሰዎችን መከተል የፈለገ የሞቱትን ይከተል፡፡ በህይወት ያለው ፈተና ላይ ላለመውደቁ ዋስትና የለም፡፡ እነዚያ የሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰሐቦች ከዚህ ኡማ በላጭ ህዝብ ነበሩ፡፡ ቅን ልቦና ያላቸው፣ እውቀታቸው የጠለቀ፣ መፈላፈል የማያበዙ ነበሩ፡፡ አላህ የሱን ነብይ እንዲጎዳኙ፣ ዲኑን እንዲያቃኑ የመረጣቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ደረጃቸውን እወቁላቸው፡፡ ትውፊቶቻቸውን ተከተሉ፡፡ በተቻላችሁ ስነ-ምግባራቸውንና ዲናቸውን አጥብቃችሁ ያዙ፡፡ ምክኒያቱም እነሱ ቀጥ ያለው ጎዳና ላይ ነበሩና፡፡»

📚 [(ጃሚዑል በያን፡ 2/97) ሊ ኢብኒ ዐብዱልበር]

ሸይኸል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሂመሁላህ እንድህ ብለዋል፦

« ሸይኽን ወይም ዓሊምን እሱ የሚለውንና የሚሰራውን በሙሉ በመከተል የያዘ ሁሉ ከረሡል ዓለይሂ ሶላት ወሰላም ውጭ ከእሱ(ከሸይኹ ወይም ዓሊሙ) #ጋር_የተስማማን_የሚወዳጅ_ከሆነ‼️‼️‼️#ከሱ_ጋር_የማይስማማን_ጠላት_የሚያደር_ከሆነ‼️‼️‼️#እሱ_ሙብተድዕ_ጠማማ_ነው👉ከኪታብና(ከቁርአን) ከሱና ያፈነገጠ ነው»

📚ጃሚዑ አልመሳኢል:7/464

#በህይወት_ያለ_ሰው_ፈተና_አይታመንለትም

ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁላህ እንድህ ብለዋል፦
↪️ « #በፊት_በትክክለኛው_አቂዳ ቀጥ ብለው #በሗላ_ግን_የሚፈተን ስንትና ስንት ሰው አለ?
#ይሄን ጊዜ #ቀጥ_ብሎ_በነበረበት ሁኔታ #ተከትለኸው ፣ እሱ በሄደበት ሄደህ፣ #መሪ_አድርገህ_ይዘኸው!!! #አንተ_በእሱ ላይ #እምነት_አሳድረህ #አንተ_ሳታውቅ_ሊያፈነግጥ_ይችላል‼️ይሄን ጊዜ #አብረኸው_ትከስራለህ‼️በህይወት ያለ ሰው ፊትና አይታመንለትም»

📖ሸርሁ አል'ዓቂደቱ አል'ተድሙሪያ:20


https://t.me/nu_selefochin_enketel
ዝምድና የመቀጠል ጥቅሞች!
=======>


❶ኛ ዝምድናን መቀጠል ወንጀል ለማስማር ምክንያት ይሆናል፡፡
🍥 عن ابن عمر رضي الله عنه قال:أتى النبي صلى الله عليه وسلم رجل فقال : إني أذنبت ذنبا عظيما ، فهل لي من توبة ؟ فقال : النبي صلى الله عليه وسلم " : هل لك من أم؟"قال:لا . قال " فهل لك من خالة ؟ " قال : نعم . قال " : فبرها"

🍥
ኢብን ዑመር የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡- አንድ ሰው ወደ ነብዩ ﷺ በመምጣት “ታላቅ ወንጀል ፈጽሜያለሁ ፤ ጸጸት (ተውበት) ይኖረኝ ይሆን? አላቸው፡፡ “እናት አለችህ?” አሉት፡፡ “የለኝም” አለ፤ “አክስት አለችህ?” አሉት፤ “አዎ” አለ፡፡ “ለእርሷ በጎ ስራ” አሉት፡፡
📚ቲርሚዚይ

❷ኛ ዝምድና መቀጠል ሲሳይ ለመስፋት፤ እድሜ ለመርዘም ምክንያት ይሆናል፡፡
👈 عن علي بن أبي طالب رضي الله عنه ، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال" :من سره أن يمد له في عمره ، ويوسع له في رزقه ، ويدفع عنه ميتة السوء ، فليتق الله ، وليصل رحمه "
📚 رواه الحاكم والبزار بسند جيد.

👉 ዓልይ ብን አቢ ጧሊብ 4 የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡- “የእድሜው መጨመር፤ የሲሳዩ መስፋት፤ ከእርሱ ላይ መጥፎ ፍጻሜ መወገዱ የሚያስደስተው ሰው አላህን ይፍራ፤ ዝምድናን ይቀጥል፡፡”

وعن أنس رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال" :من أحب أن يبسط له في رزقه ، وينسأ له في أثره ، فليصل رحمه"
📚 رواه البخاري ومسلم.
አነስ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-
“ሲሳዩ እንዲሰፋለት፤ እድሜው እንዲረዝምለት የሚፈልግ ሰው ዝምድናን ይቀጥል፡፡”
📚ቡኻሪና ሙስሊም

ዝምድናን መቀጠል ከአላህ ዘንድ ተወዳጅ ከሆኑ ተግባራት አንዱ ነው፡፡ ረሡል ﷺ ከሶሃቦች ጋር እያሉ ከኸይሰም ጎሳዎች አንድ ሰው መጣ፡፡ “ረሡል ነኝ የምትለው አንተ ነህ እንዴ?” አልኳቸው ይላል፡፡ እርሳቸውም “አዎ” አሉ፡፡ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ወደአላህ ተወዳጅ የሆነው ስራ የቱ ነው?” አልኳቸው፡፡ “በአላህ ማመን” አሉኝ ፡፡ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከዚያስ” አልኳቸው፤ “ዝምድናን መቀጠል ነው” አሉኝ፡፡ “የአላህ መልክተኛ ሆይ!ከአላህ ዘንድ የሚያስቆጣ ተግባር ምንድን ነው?” አልኳቸው ፤ “በአላህ ማጋራት” አሉኝ፡፡ ከዚየም “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከዚያስ?” አልኳቸው፡፡ “ዝምድናን መቁረጥ ነው” አሉኝ፡፡ አቡ የዕላ ፊሙስነዲሂ፡ ጀይድ ጥሩ በሆነ ሰነድ አውርቶታል፡፡ዝምድናን መቀጠል ጀነት ለመግባት ከእሳት ለመዳን ምክንያት ይሆናል፡፡

☑️ አቡ አዩብ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል፡- “አንድ የገጠር ሰው በሰፈር ድንገት ከረሡል ﷺ ጋር ተገናኘና የግመላቸውን ልጓም በመያዝ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! - ሙሀመድ ሆይ!- ወደ ጀነት የሚያቀርበኝ፤ ከእሳት የሚያርቀኝን ስራ ንገሩኝ” አላቸው፤ ረሡል ﷺ መልስ ከመስጠት ተቆጠቡና ሶሃቦችን መመልከት ጀመሩ፤ ከዚያም “በእርግጥ ተገጠመ ወይም በርግጥ ተመራ” አሉ፡፡ “ምን አልክ?” በማለት ረሡል ﷺ በድጋሜ ግለሰቡን ጠየቁት፤ እርሱም በድጋሜ ነገራቸው፤ ከዚያም ነብዩ ﷺ የሚከተለውን ተናገሩ፡- “አንድንም በእርሱ ሳታጋራ አላህን ልትገዛ ነው፤ ሶላትን ደንቡን ጠብቀህ ልትስግድ፤ ዘካ ልታወጣ፤ ዝምድናን ልትቀጥል፤ ግመሏን ተዋት (ልቀቃት)፡፡” በሌላ ዘገባ “የዝምድናን ባለቤት ልትቀጥል” ነው፡፡ ሰውየው ጠይቆ ከሄደ በኋላ “ይህ ሰው ባዘዝኩት መሰረት አጥብቆ ከያዘ ጀነት ገባ” በማለት የአላህ መልክተኛ ተናገሩ፡፡
📚ቡኻሪና ሙስሊም

↪️ ዝምድና መቀጠል ውለታን በመመለስ አይደለም ዝምድና ከተቀጠለ ብቻ የሚቀጥል፤ ከቆረጡ ደግሞ የሚቆርጥ ሰው አለ፡፡ እንደዚህ አይነቱ ሰው ውለታን መላሽ እንጅ ዝምድናን ቀጣይ አይባልም፡፡

እንዲህ አይነቱ ተግባር ለቅርብም ይሁን ለሩቁ ሊሆን የሚችል ነው፡፡ ውለታን መመለስ በቅርብ ዘመድ ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ ትክክለኛው ዝምድናን ቀጣይ ቆረጡም ቀጠሉም ዘመዶችን ለአላህ ብሎ የሚቀጥል ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ረሡል ﷺ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
"ليس الواصل بالمكافئ ، ولكن الواصل الذي إذا قطعت رحمه وصلها"
📚رواه البخاري ومسلم
“ውለታ መላሽ ዝምድናን ቀጣይ አይባልም፤ ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ዝምድናው በተቆረጠ ጊዜ የሚቀጥል ነው፡፡”
📚 (ቡኻሪ፡ 5991)

https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
Audio
«ﺍﻟﺪﻳﻦ ﺍﻟﻨﺼﻴﺤﺔ»
«ዲን ምክክር ነው»
ክፍል አንድ:—①

ቦታ :— ቻግኒ

መጠን :– 2.2MB

እርዝመት :—9:15

በአቡ ጁበይር.

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni
قال يحيى بن يحيى شيخ البخاري ومسلم رحمه الله :

الذب عن السنة أفضل من الجهاد .

📚 نقض المنطق : (12)
قال العلامة الفوزان:

(فهذا الإمام - أحمد - يجب أن نعرف موقفه من أجل أن نقتدي به، وأن نعرف- أيضا- موقفنا من الفرق الضالة والفرق المخالفة لأهل السنة والجماعة حتى لا نتساهل معها، ونعمل عملية تجميع، ونقول: نحن نجمع ولا نفرق كما تقوله بعض الجماعات!. بل يجب أن نفرق بين أهل الحق وأهل الباطل، نحن مع أهل الحق وإن قلوا، ولسنا مع أهل الباطل وإن كثروا، هذا هو الموقف الصحيح. فالإمام أحمد وحده وقف في وجه أمة، ونصره الله عليهم، ولا بد أن الإنسان يناله أذى في مقابل موقفه وصبره وثباته، لكن ما دام على الحق لا يهمه ذلك، وهذا في موازينه وفي حسناته عند الله)

إعانة المستفيد
Audio
የአቡ በከር አሕመድ ጅህልና

በአቡ በከር አሕመድ ላይ ረድ
ክፍል ሁለት
➶➶➶➶
ክፍል አንድን ለማግኘት ⬇️
https://t.me/bahruteka/3734

አቡ በከር አሕመድ ከሚቀጥፋቸው ቅጥፈቶች ውስጥ
– የሳውዲ ስርኣት የመደንይ ስርኣት ነው
መደንይ የሚለውን በንጉሳዊ አገዛዝ መተርጎሙ ቀጥሎ
የመደንይ ስርኣት ማለት ሰው በሰውመቱ፣ በእምነቱ፣ በአስተሳሰቡ የማይወገዝበት ሁሉን አካታች ስርኣት ነው ይላል። (ይህ ነው ትክክለኛ ትርጉሙ)
– የመደንይ ስርኣት ሸሪዓ የሚያዝበት ነው
ኢትዮዽያ ውስጥ ኢስላማዊ ሸሪዓ አይታሰብም ማሰቡም ወንጀል ነው
– ኢትዮዽያ ውስጥ ኢስላማዊ ስርኣት እንዲመጣ የሚያስብ ካለ ወንጀለኛ ነው ብለን እናምናለን
– የመደንይ ስርኣት (ሰው በሰውነቱ፣ በእምነቱ፣ በአስተሳሰቡ፣ የማይወገዝበት ስርኣት) ከመጣ እምነቴን (እስልምናን) ይወክላል

https://t.me/bahruteka
# السلام عليكم ورحمة الله وبركاته.
* እኔ የሚገርመኝ fb ላይ ያለው ሁሉ በእውቀት ደረጃ ተመሳሳይ የሚመስለው ሰው ነው ።
ስለ አህለል ቢድአ የሆነ አካል በመረጃ ሲናገር /ሲፖስት/
" የእኔ እና አንተ ቤጤ/አምሳያ/አርፈን ብንቀመጥ ይሻላል ይልህል።"
እኔ ማንኝ ?
አንተ ማነህ ?
ራስህን ስለ ዲንህ ባለህ የእውቀት ደረጃ ፈትሽ።
እፈትሻለሁ።
* ትኩረታችን ከጉዳዮ ነው ሀቅ ከገጠመ ትቀበላለህ ካልገጠመ ጣለው።
* ይህን ለመመዘን ግን በመጠኑም ቢሆን ስለ ዲንህ ማወቅ ይጠበቅብሀል።
* ከዚያ ውጭ ግን ሀቅ ሲነገር እኔና አንተ እያሉ ማዘናጋት የሀቅ ሰዎችን ወደ ሗላ እንደማይላቸው እወቅ።
እንዲያውም ያጠነክራቸዋል።
* ስለዚህ fb ላይ በዲናቸው ከእኛ የታሻሉ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ መገንዘብም አስፈላጊ ነው።
* የበዲን ላይ ያለ እወቅት ከመናገር አሏህ ይጠብቀን።
* ምክንያቱም ከተላላቅ ወንጀሎች የሚመደብና ከሺርክ ጋር ተቆራኝቶ የተገለፀ ገባድ ወንጀል ነው።

قال سبحانه وتعالى:–
[قُلْ إِنَّمَا حَرَّمَ رَبِّيَ الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ وَالْإِثْمَ وَالْبَغْيَ بِغَيْرِ الْحَقِّ وَأَن تُشْرِكُوا بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا وَأَن تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ]
{«ጌታዬ እርም ያደረገው መጥፎ ሥራዎችን፣ ከርሷ የተገለጸውንና የተደበቀውን ኃጢኣትንም፣ ያላግባብ መበደልንም፣ በርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን (ጣዖት) በአላህ ማጋራታችሁን፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው» በላቸው፡፡}
* ያለ እውቀት መናገር ከሸይጧን የሚመጣ ትዛዝ ነው።
قال سبحانه وتعالى:–
[إِنَّمَا يَأْمُرُكُم بِالسُّوءِ وَالْفَحْشَاءِ وَأَن تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ]
{(እርሱ) የሚያዛችሁ በኃጢኣትና በጸያፍ ነገር በአላህም ላይ የማታውቁትን እንድትናገሩ ብቻ ነው፡፡}
* ስለዚህ ሸይጧንን በየትኛውም ጉዳይ ልንታዘዘው እንደማይችል ለሁሉም ሙስሊም ግልፅ ነው።
ሆኖም ግን አብዛኛው ሰው በተለይ በዚህ ጉዳይ
(በዲን ላይ ያለ እውቀት በመናገር)
አብዛኛው ሰው በተግባር ሲታዘዘው ይታያል።
* ይህ ደግሞ አደጋው በእኛ ብቻ የማይገደብና ወደ ሌሎች የሚሸጋገር መሆኑ ይበልጥ የከፋ ያደርገዋል።

اللهم ارزقنا علما نافعا وعملا صالحا خالصا لوجهك الكريم.
ونعوذ بك من علم لاينفع ومن قلب لاتخشع.
📝 አቡ ጃቢር ሙሐመድ

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot

ይፃፉልን። ይላኩልን
Audio
«ﺍﻟﺪﻳﻦ ﺍﻟﻨﺼﻴﺤﺔ»
«ዲን ምክክር ነው»
ክፍል ሁለት:—②

ቦታ :— ቻግኒ

መጠን :– 2.8MB

እርዝመት :—12:08 ደቂቃ

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot
Audio
«ﺍﻟﺪﻳﻦ ﺍﻟﻨﺼﻴﺤﺔ»
«ዲን ምክክር ነው»
ክፍል ሶስት:—③
أبو جبير
ቦታ :— ቻግኒ

መጠን :– 2.7MB

እርዝመት :—11:42 ደቂቃ

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot
Audio
خطبة الجمعة:-
«ﺍﻟﺒﺪﻉ ﻭﺍﻟﻤﺒﺘﺪﻋﺔ ﻣﻦ ﺃﻋﻈﻢ ﺃﺳﺒﺎﺏ ﺍﻟﺘﻔﺮﻕ للأمة.»
የጁመአ ኹጥባ:—
ርዕስ :– " በደአዎችና ቢደአ አራማጆች ለኡማው መበታተን ትልቅ ምክንያት ናቸው።"

ቦታ :— ቻግኒ

መጠን :– 7.7MB

እርዝመት :—32:59ደቂቃ

በወንድም አቡ ጁበይር ሙሀመድ

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot.
Audio
«ﺍﻟﺪﻳﻦ ﺍﻟﻨﺼﻴﺤﺔ»
«ዲን ምክክር ነው»
ክፍል አራት:—④

ቦታ :— ቻግኒ

መጠን :– 2.6MB

እርዝመት :—11:00 ደቂቃ

በአቡ ጁበይር

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot
Audio
صفر(٢) ٠٤/١٤٤٥
«ﺍﻟﺪﻳﻦ ﺍﻟﻨﺼﻴﺤﺔ»
«ዲን ምክክር ነው»
ክፍል አምስት:—⑤

ቦታ :— ቻግኒ

መጠን :– 2.9MB

እርዝመት :—12:20 ደቂቃ

በአቡ ጁበይር

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot
Audio
23/12/2015
صفر (٢) ١٤٤٥/١٢
«ﺍﻟﺪﻳﻦ ﺍﻟﻨﺼﻴﺤﺔ»
«ዲን ምክክር ነው»
ክፍል ስድስት:—⑥
أبو جبير
ቦታ :— ቻግኒ

መጠን :– 2.9MB

እርዝመት :—12:20 ደቂቃ

በአቡ ጁበይር

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot
Audio
صفر(٢) ١٤٤٥/١٦.
27/12/2015
«ﺍﻟﺪﻳﻦ ﺍﻟﻨﺼﻴﺤﺔ»
«ዲን ምክክር ነው»
ክፍል ሰባት:—⑦
የመጨረሻው ክፍል
أبو جبير
ቦታ :— ቻግኒ

መጠን :– 3.2MB

እርዝመት :—13:46 ደቂቃ

በአቡ ጁበይር

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni
Audio
# ﻟﻤﺎﺫﺍ ﺗﻘﺴﻮ ﻗﻠﻮﺑﻨﺎ.؟_ # ልቦቻችን ለምን ይደርቃሉ_ _ ክፍል አን...اهر قسوة القلب._ የልብ ድርቅና መገለጫዎች።_ በወንድም አቡ ጁበይር ሙሀመድ.m4a
ربيع الثاني. ١٤٤٥/٢٥.
# ﻟﻤﺎﺫﺍ ﺗﻘﺴﻮ ﻗﻠﻮﺑﻨﺎ.؟
# ልቦቻችን ለምን ይደርቃሉ?
ክፍል አንድ ①
* مظاهر قسوة القلب.
የልብ ድርቅና መገለጫዎች።

ቦታ :— ቻግኒ

መጠን :–5.1 MB

እርዝመት :—22:02ደቂቃ

በወንድም አቡ ጁበይር.

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot
Audio
# ﻟﻤﺎﺫﺍ ﺗﻘﺴﻮ ﻗﻠﻮﺑﻨﺎ.؟_ # ልቦቻችን ለምን ይደርቃሉ_ _ ክፍል ሁ...ለب قسوة القلب._ የልብ ድርቅና ምክኔያቶቸች።_ በወንድም አቡ ጁበይር ሙሀመድ..m4a
# ﻟﻤﺎﺫﺍ ﺗﻘﺴﻮ ﻗﻠﻮﺑﻨﺎ.؟
# ልቦቻችን ለምን ይደርቃሉ?
ክፍል ሁለት ②
** أسباب قسوة القلب.
የልብ ድርቅና ምክኔያቶቸች:—

ቦታ :— ቻግኒ

መጠን :–4.4MB

እርዝመት :—18:58ደቂቃ

በወንድም አቡ ጁበይር ሙሀመድ.

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot
Audio
جمادى الأول.١٤٤٥_١١._14_03_16.خطبة الجمعة_– عنوان_–_ _في... ኹጥባ_ ርዕስ_—የአሏህን እና መልዕክተኛውን ጥሪ መቀበልበወንድም አቡ ጁበይር ሙሀመድ..m4a
جمادى الأول.١٤٤٥/١١.
14/03/16.
خطبة الجمعة:– عنوان:–
"في الاستجابة لله ولرسوله."
የጁመአ ኹጥባ: ርዕስ:—
"የአሏህን እና መልዕክተኛውን ጥሪ መቀበል"

ቦታ :— ቻግኒ

መጠን :–7.6MB

እርዝመት :—32:40ደቂቃ

በወንድም አቡ ጁበይር ሙሀመድ.

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته