ሴት ልጅ ባሏ በሀሳብ ቢቃረናትም ሸሪዓን በሚጥስ ነገር እስካላዘዛት ድረስ ባሏን የመታዘዝ ግዴታ አለባት!!
—————
ይህ ነጥብ ብዙዎች ዘንድ የተዘነጋ ነጥብ ነው። ሚስት ባሏን መታዘዝ ግዴታ የሆነባት ባል የርሷን ሀሳብ በማይነቅፍ ነገር ሲያዛት ብቻ ሳይሆን በዋነኝነት የርሷን ሀሳብ በሚነቅፋት ነገር ሲያዛት ነው። የሀሳብ ልዩነት በሌለው ነገርማ ማንኛውም አካል በአንድ ነገር ላይ ተነጋግሮ የሀሳብ ልዩነት እስከሌለ ተስማምቶ ይጓዛል። አብሮ መጓዝ የማይቻለው የሀሳብ ልዩነት ሲፈጠር ነው። በባልና ሚስት መካከልም መለያየቱ የሚፈጠረው በዋነኝነት የባልን ትእዛዝ አለማክበር ሲከሰት ነው።
ሚስት የሀሳብ ልዩነት ሲፈጠር ባሏን የማትታዘዝ ከሆነ አላስፈላጊ ንትርኮችና ጭቅጭቆች ይፈጠራሉ!!። ይህ ማለት ደግሞ በመካከላቸው የነበረው ፍቅርና መተሳሰብ በአጭር ጊዜ ይሻክራል። ይህ ደግሞ በትዳራቸው ውስጥ ከባድ አደጋ ይሆናል።
እህቶች ሆይ! የሚከተለውን የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ንግግር ልብ ብላችሁ አንብቡት:-
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«إذا صلت المرأة خمسها وصامت شهرها وحفظت فرجها وأطاعت زوجها قيل لها ادخلي الجنة من أي أبواب الجنة شئت» . ورواه ابن حبان في صحيحه عن أبي هريرة رضي الله عنه، والحديث صححه الألباني في الجامع الصغير.
አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
“ሴት ልጅ አምስት ወቅቷን ከሰገደች፣ የረመዷን ወሯንም ከፆመች፣ ብልቷንም (ከዝሙት) ከጠበቀች፣ ባሏን ከታዘዘች በፈለግሽው የጀነት በር ግቢ ትባላለች።” [ኢብን ሂባን በሶሂሃቸው የዘገቡት ሲሆን አልባኒም በጃሚዑ ሰጊር ሶሂህ ነው ብለውታል]
እህቶቼ ሆይ! ይህ ቀላል ነገር አይደለምና ልዩ ትኩረት ስጡት!!። የባልን ትእዛዝ ላለማክበር የተቀመጠው መስፈርት አንድ ነገር ብቻ መሆኑን አስተውሉ እሱም "ሸሪዓን በሚጥስ ነገር ካዘዘ አለመታዘዝ ነው" በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ብዙ ጊዜ እህቶች ዘንድ የሚስተዋለው ነገር ባል (አላህ ይጠብቀንና) ሸሪዓን በሚጥስ ነገር ሲያዛቸው ይታዘዙትና ሀሳባቸውን በሚቃረን ነገር ሲያዛቸው ደግሞ አለመታዘዛቸው ነው። መልእክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሴት ልጅ ባሏን መታዘዟን በተመለከተ ከታላላቅ ዒባደዎች "ከሶላት፣ ብልቷን ከዝሙት ከመጠበቅ፣ የረመዷን ወርን ከመፆም" ጋር አያይዘው ነው ጀነት ለመግባቷ እንደ ሰበብ የጠቀሱት።
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ (ዐለይሂ ረህመቱላህ) ሴት ልጅ የባሏን ሀቅ አስመልክተው የአላህንና የመልእክተኛውን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሐቅ ከማክበርና ከመጠበቅ ጋር በማያያዝ እንዲህ አሉ:-
قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله تعالى:
"ليس علي المرأة بعد حق الله ورسوله أوجب من حق الزوج."
(مجموع الفتاوى: 32/260)
"በአንዲት ሴት ላይ ከአላህና ከመልክተኛው ሀቅ በመቀጠል ከባሉዋ ሀቅ በላይ ግዴታ የለባትም።" [መጅሙዕ አል-ፈታዋ 32/260]
قال الإمام ابن تيمية رحمه الله:- (المرأة المتزوجة طاعتها لزوجها أفضل من طاعتها لأبويها)
مجموع الفتوى 10-428
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ (ረሂመሁላህ) ባለ ትዳሯ ሴት ባሏን የመታዘዝ ደረጃው ምን ያህል እንደሆነም እንዲህ ሲሉ ይገልፃሉ:-
“ባለ ትዳሯ ሴት ለባለቤቷ መታዘዟ ወላጆቿን ከምትታዘዘው ይበልጥላታል።” [መጅሙዕ አል-ፈታዋ 10/428]
✍🏻ኢብን ሽፋ t.me/IbnShifa
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa

Telegram
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
Forwarded from [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
ሰዎችን በጭፍን አትከተል!!
—————
ሰዎች በሐቅ ይመዘናሉ እንጂ ሐቅ በሰዎች አይመዘንም!! የሀቅ እንጂ የሰዎች ጭፍን ተከታይ አትሁን!። ምክንያቱም የታዘዝከው ሐቅን እንጂ ሰዎችን እንድትከተል አይደለም!። በጭፍን ውዴታ ጥግ መድረስ አደጋ አለው። ጭፍን ተከታይ መሆን ሐቅ ከመቀበል ያውርሃልና ተጠንቀቅ!። በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም። አላህ ይጠብቀንና በጭፍን የተከተልከው ሰው ከተንሸራተተ አለያም ድንበር አላፊ ከሆነ አንተም አብረሀው ገደል ልትገባ ትችላለህና ጭፍን ተከታይ አትሁን!!።
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) “በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም” ብለዋል። በመሆኑም የሰዎች ጭፍን ተከታይ መሆንን ተጠንቀቅ። ወደ ቁል ቁል ሲወርዱ እንዳያወርዱህ፣ ድንበር ሲያልፉም በጭፍን ተከትለሃቸው እንዳታልፍ። የሰዎች ንግግር ትክክል ካልሆነ ተመላሽ ነው። ፍፁም የሆነውና ሊመለስ የማይችለው የመልእክተኛው ﷺ ንግግርና ተግባር ብቻና ብቻ ነው።
ኢማሙ ማሊክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ማለታቸውን አትዘንጋ:- "ሁላችንም ተመላሾችና የተናገርነውም የሚመለስ ነው የዚህ ቀብር ባለ ቤት ሲቀር።" አሉ። የቀብሩ ባለ ቤት በማለታቸው የፈለጉበት መልአክተኛውን ﷺ ነው።
ሐቅን እወቅ! ከዚያም ሰዎችን በሀቅ ትመዝናቸዋለህ። የሀቅ ሰዎችንም ታውቃለህ። ሰዎችን አውቀህ በጭፍን የምትከተላቸው ከሆነ ግን የሐቅ መመዘኛ መሰረትህ ትክክለኛ ማስረጃ ላይ የተገነባ ሳይሆን የሰዎች ጭፍን ውዴታና ጭፍን ተከታይነት ይሆንና ሲገለባበጡም አብሮ መገለባበጥ ይሆናል።
ቆም ብለህ አስተውል! ቡድንተኝነትና ጭፍን ውዴታ አያውርህ!። ነገ አላህ ፊት ወዳጅህ ጠላት ሊሆንብህ ይችላል። አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-
الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ
«ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡» አዝ-ዙኽሩፍ 67
ታዲያ ስትወድም ሆነ ስትጠላ በጭፍን አይሁን!። የወደድከው አቅጣጫ ከሳተና ለየት ያሉ ነገሮችን ካስተዋልክበት ቆም በል። በጭፍን መውደድም መጥላትም አደጋው የከፋ ነውና ተጠንቀቅ!!። ሳታስበው በሰለፊያ መንሀጅ ስም በተመሰረተ ልዩ በሆነ ቡድንተኝነትና ዘመናዊ ሙሪድነት አዘቅጥ ውስጥ እንዳትዘፈቅ!!። በጭፍን በውዴታው የከነፍከለት አካል መንገድ ከሳተ ተከትለሀው መሳትህ አይጠቅምህም! ከባድ አደጋ ነው። የሚጠቅምህ በየትኛውም ወቅት ሀቅን አጥብቀህ መያዝህ ነው!!።
በተለይ በፊትና ጊዜ ምንም ያህል በአንዳንድ መልካም ስራዎቹ የምትወደው በዳዒነት የገነነ ነገር ግን እውቀቱ እዚህ ግባ የማይባል የምትወደው ሰው ቢኖር እንኳ ጠንካራ ነጥቦች ሲነሱ፣ የሆነ ጊዜ "እኔ እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን አንስቼ ለመናገር እውቀቴ አይፈቅድልኝም" እያለ በሌላ ጊዜ ደግሞ የእውቀት ደረጃው በማይፈቅደው አጀንዳ ውስጥ ገብቶ ሲዘባርቅ እያየሀው ስለ ወደድከው ብቻ በጭፍን መከተል የለብህም!።
በየትኛውም ወቅት የጠንካራ እውቀት ባለ ቤቶችን እና በዳዒነት የገነኑ ያለ እውቀት ደረጃቸው ተከታይ ስላላቸው ብቻ በድፍረት የሚናገሩና ተከታዮቻቸውን ይዘው ወደፈለጉበት አቅጣጫ የሚዋዥቁ ያለ እውቀት ታዋቂ የሆኑ ሰዎችን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። ሐቅ በጋጋታና ከተለያየ አቅጣጫ በሚጮሁ በተደራጁ ቲፎዞዎች ጩሀት አይለካም!። እውነትን ቆም ብሎ በማስረጃ መለየት ነው እንጂ ጭፍን ተከታይ መሆን አደጋው የከፋ ነው!። ትላንት በጥሩ አቋምና በትክክለኛው መንሀጅ እያለ ጠላቶቹ የነበሩ ኢኽዋንን ጨምሮ "አይንህ ላፈር" የሚሉት ሰዎች ዛሬ እንዴት ወዳጆቹ ሊሆኑና እሱን ሊያደንቁ፣ ሊያሞግሱ እንደቻሉ? ቆም ብለህ ፈትሽ!!። እሱ ተለሳልሶ ከአቋሙ ሸርተት ብሎ ነው ወይስ እነሱ ወደ ትክክለኛው አቋምና መንሀጅ ተመልሰው ነው? ብለህ እራስህን ጠይቅ። ያለፉ ሂደቶችንና በወቅቱ ያሉ ሂደቶችንም በተረጋጋና በገለልተኝነት መንፈስ ቃኝ!። እውነት ጭፍን ተከታይነትና ቡድንተኝነት ሳያውረው ከልቡ ለፈለጋት ሰው ግልፅ ትሆናለች!።
ታላቁ ሸይኽ አሕመድ ኢብኑ የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ: -
“ወላሂ! በጌታዬ ይሁንብኝ አላህ ዘንድ እገሌና አገሌ አይጠቅሙህም!። የሚጠቅምህማ በሀቅ ላይ መቆምህና ለሀቅና ለተከታዮቹ ረዳት መሆንህ ነው።” ረዱል ጀዋብ 54
»» ሐቅን ተከተል!። ለሸይኽ አሕመድ ቢን የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) ድንቅ ንግግር ትኩረት ስጠው!። ወገንተኝነት አያጥቃህ፣ ለሀቅ ብቻ ወግን! ሀቁ በበቂና በትክክለኛ ማስረጃ ከተነገረህ አንተም ሆንክ የምትወደው ዳዒ አለያም ከጎንህ ያሉ ወዳጆችህ መንገድ ስህተት እስከሆነ ወደ ሀቁ ለመመለስ አታንገራግር!! የተነገረህ እውነት እሰከሆነ ለመቀበል ቆራጥ አቋም ይኑርህ!። ምክንያቱም ወገንተኛ የምትሆንለት አካል ከአላህና ከመልእክተኛው ﷺ በላይ የለምና ለአላህ እና ለመልእክተኛው ﷺ እና ለሐቅ ብቻ ወገንተኛ ሁን!!። ሐቅ ከየትም ይምጣ ከማንም ሐቅ እስከሆነ መቀበል ነው። ሀቁ ካልተገለጠልህ ደግሞ እስኪገለጥልህ ከቡድንተኝነትና ጭፍን ተከታይነት ገለልተኛ ሆነህ በአደብ ፈልገው፣ በንፁህ ኒያ እስከፈለግከው ኢንሻአላህ ቢዘገይ እንኳ ፍንትው ብሎ ይታይሃል!!።
ግን ግን አደራ ምን ጊዜም ለግለሰቦች ከወገንተኝነት፣ ከጭፍን ተከታይነትና ከቡድንተኝነት ራስህን አርቅ!!። ምን ጊዜም ወገንተኝነታችሁ ለሐቅ ከሆነ ሐቅን የሚከተልን ትወዱታላችሁ ታከብሩታላችሁ እንጂ ጭፍን ተከታይ አትሆኑለትም!!።
አላህ ሐቁ ለተደበቀበት ግልፅ ያድርግለት!! የሀቅ ተከታዮችና በሐቅ ላይ ከሚፀኑ ባሮቹም ያድርገን!!
✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#join ⤵️

ታላቁ ዓሊም ሱፍያን አስ-ሰውሪይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-
•
"የቢዳዓ ባልተቤት ጋር የተቀማመጠ ከሶስት ነገር ባንዱ ሰላም አይሆንም
•
1, ወይ ለሌሎች ሰዎች ፊትና ይሆናል! (ይህ በብዛት በዚህ ጊዜ የሚስተዋለው ከባድ አደጋ ነው)
2, ወይ በልቦናው ላይ የሆነ ነገር ሊከሰት (ይችላል) በርሱ ምክኒያት ይጠምና አላህ እሳት ያስገባዋል
3, አልያም (ሙብተዲዕዎች) በተናገሩት ንግግር በአላህ ይሁንብኝ ደንታ የለኝም፣ እኔ በነፍሴ እተማመናለሁ፣ ይላል። አላህን ደግሞ የዐይን እርግብታ ያክል በዲኑ ላይ (ምንም አያደርገኝም በራሴ እብቃቃለሁ በማለት) የተማመነ (አላህ) ዲኑን ይቀመዋል።"
•
【አል–ኢዕቲሷም 1/130】
•
አኚህ ታላቅ ዓሊም ከቢዳዓ ሰዎች ጋር የሚቀማመጥን ሰው በነዚህ ሶስት ከባባድ አደጋዎች አስጠንቅቀዋል!!።
ስለዚህ:-
ከቢደዓ ባለቤቶች ጋር ከመቀማመጥ እራስህን ቆጥብ!!
#join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል

ነሺዳ-Ibn Shifa.61page.pdf
871.4 KB
ነሺዳ የሱፊዮች እና የኢኽዋኖች ዘፈን እንጂ ኢስላማዊ አይደለም!! PDF
"""""""
በኢብን ሽፋ ከ 3አመት በፊት ነሺዳን በተመለከተ ከኢኽዋኖችና ሱፊዮች ዘንድ ለሚነሱ ብዥታዎች አንድ በአንድ በቁርኣንና በሀዲስ የተሰጠ መልስ
#share #ሼር_አድርጉት!
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
"""""""
በኢብን ሽፋ ከ 3አመት በፊት ነሺዳን በተመለከተ ከኢኽዋኖችና ሱፊዮች ዘንድ ለሚነሱ ብዥታዎች አንድ በአንድ በቁርኣንና በሀዲስ የተሰጠ መልስ
#share #ሼር_አድርጉት!
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
Forwarded from [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
ነሺዳ የሱፊዮች እና የኢኽዋኖች ዘፈን እንጂ ኢስላማዊ አይደለም!!
""""""""""""""የመፅሃፉ መቅድም""""""""""""""
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ በሆነው፣ በእርሱም እታገዛለሁ!።
ምስጋና በጠቅላላ ለዓለማቱ ብቸኛ ለሆነውና በሀይማኖቱ ደንጋጊ (ህግ አውጪ) ለሆነው፤ የሰው ልጆችን እውቀቱ በሌላቸው ነገር ላይ መከተልን የከለከለ ለሆነው፤ ብቸኛ ተመላኪ ለሆነው አምላካችን አላህ የተገባ ነው!!፡፡
የሰው ልጆችን እውቀቱ የሌላቸውን ነገር እንዳይከተሉ እንዲህ በማለት ከልክሏል፡-
﴿وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا ﴾ [الإسراء:٣٦]
“ለአንተ በርሱ እውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፡፡ መስሚያ፤ ማያም፤ ልብም እነዚህ ሁሉ ‹ባለቤታቸው› ከእነሱ ተጠያቂ ነውና፡፡” አል ኢስራእ 36
ከነፍሳችን ተንኮልና ከብልሹ ስራችን በአላህ እንጠበቃለን፤ አላህ የመራውን የሚያጠመው የለም፤ አላህ ያጠመመውንም የሚያቃናው የለም! ከአንድ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ (በልቤ ያመንኩ ስሆን) የምስክርነት ቃሌን እሰጣለሁ፤ እርሱም ብቸኛና ምንም ተጋሪ የለውም! ነቢዩ ሙሐመድምﷺ የእርሱ ባሪያና መልእክተኛው መሆናቸውን (በልቤ ያመንኩ ስሆን) የምስክርነት ቃሌን እሰጣለሁ፡፡
ከንግግር ሁሉ እውነተኛው ንግግር የአላህ ቃል የሆነው ቁርኣን ነው! ከመንገዶች ሁሉ ትክክለኛው መንገድ (እምነት) የመልዕክተኛው የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ መንገድ (እምነት) ነው፡፡
የነገሮች ሁሉ አደገኛ በሀይማኖት ላይ አዲስ ፈጠራ (ቢድዓ) ማምጣት ነው! በሀይማኖት ላይ ፈጠራ (ቢድዓ) ሁሉ “ከነቢዩ ﷺ ያልተለመደ” መጤ ነው፤ መጤ የተባለ በሙሉ ጥመት ነው፤ የጥመት ጎዳና በሙሉ የእሳት ነው።
ከዚህ በመቀጠል…
በዚህን ጊዜ እንደሚታወቀው በብዛት በተጨባጭ እንደሚታየውም በአላህና በመልክተኛው ክልክል የተደረገው እንደተፈቀደ ነገር፤ የተፈቀደው ደግሞ እንደተወገዘ ነገር የሚታይበት ተጨባጭ ነው የሚታውየው። ለዚህም ያለ በቂ እውቀት ዝና እና ተወዳጅነትን ፍለጋ ብይን (ፈትዋ) የሚሰጡ አላዋቂ መሀይማን (ጃሂሎች) ዘንድ ሙፍቲ ተደርገው የተቀመጡ በስሜትና በመሀይማን ጭፍን ድጋፍ ሀቅን ላለመቀበል በትቢት የተወጠሩ፤ ያለ ደረጃቸው በመሀይማን ሸይኽና ኡስታዝ ተብለው የተሰቀሉ ብልሽትን የሚያስፋፉ (የፈሳድ) ሙፍቲዎች አሉ፡፡
ታዲያ እንዲህ ያሉ የጥመት ብይን (ፈትዋ) የሚሰጡ ሰዎችን ሀቅ ፈላጊውን ሚስኪኑን ህዝብ፤ በእንዲህ ያለ ፈትዋቸው ሲያስቱ ዝም ብሎ ማየት የአላህን ሀቅን ግልፅ የማድረግ አማና በአግባቡ አለመወጣት ከመሆኑም ባሻገር፤ የተወገዘን ንግግር የሚናገሩና በተወገዘ ነገር ላይ ይፈቀዳል ብለው ያለ እውቀት በድፍረት ፈትዋ የሚሰጡ ሰዎችን ባለማውገዛችን ከአይሁዶች እንዳንመሳሰል ያሰጋል፡፡ አላህ እነዚያ ከበኒ ኢስራኢል ከሀዲ የሆኑት የተረገሙበትን ምክንያት እንዲህ በማለት ገልፆልናል፡-
﴿لُعِنَ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ بَنِي إِسْرَائِيلَ عَلَى لِسَانِ دَاوُودَ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ذَلِكَ بِمَا عَصَوْا وَكَانُوا يَعْتَدُونَ٧٨كَانُوا لَا يَتَنَاهَوْنَ عَنْ مُنْكَرٍ فَعَلُوهُ ﴾ [المائدة: 78-79]
“ከኢስራኢል ልጆች እነዚያ የካዱት በዳውድና በመርያም ልጅ በዒሳ ምላስ ተረገሙ፡፡ ይህ ትእዛዝን በመጣሳቸውና ወሰንን የሚያልፉ በመሆናቸው ነው፡፡ ከሰሩት መጥፎ ነገር አይከላከሉም ነበር፡፡” አልማኢዳ 78-79
ይህ በመሆኑም አንዱ ሲሳሳት ሌላኛው ተው! ማለት ግድ ይለዋል!፡፡ በመሆኑም ነሺዳን በተመለከተ የተሰጠውን የተሳሳተ ፈትዋ በቁርኣንና በሶሂህ ሀዲስ፤ በኢስላም ሊቃውንቶች የጋራ ስምምነት (ኢጅማዕ) ስህተት መሆኑን ለህዝበ ሙስሊሙ በተቻለ መጠን ግልፅ የተደረገ ሲሆን፤ ነሺዳን ሀላል ለማስመሰል የተነሱ ብዥታዎች ላይም አንድ በአንድ መልስ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ይህን ሶፍት ኮፒ/PDF አንብበው ለሌሎች በማሰራጨት ሌሎችንም ከነሺዳ ብዥታ ይታደጉ!!
ለአስተያየትና ለጥቆማ የሚከተለውን የኢሜይል አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡- Ibn.shifa11@gmail.com
PDFን በዚህ ሊንክም 👇👇 ያገኙታል
https://t.me/IbnShifa/1383

https://t…
"""""""
በኢብን ሽፋ ከ 3አመት በፊት ነሺዳን በተመለከተ ከኢኽዋኖችና ሱፊዮች ዘንድ ለሚነሱ ብዥታዎች አንድ በአንድ በቁርኣንና በሀዲስ የተሰጠ መልስ
#share #ሼር_አድርጉት!
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://t…
Forwarded from [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
በተራዊህ ሶላት ላይም ይሁን በሌላ ሶላት ላይ ኢማሙ እየቀራ፣ ተከታዩ (መእሙሙ) ቁርኣን ይዞ መከታተሉ እንዴት ይታያል?!
—————
ለታላቁ ፈቂህ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንደሚከተለው ጥያቄ ቀረበላቸው:-
ጥያቄ:- ኢማምን መከተል ነው በሚል ማስረጃ ቁርኣን ይዞ ከኢማሙ ኋላ በተራዊህ ሶላት ላይ መከታተል ብይኑ ምንድነው?!
መልስ:- ለዚህ ጉዳይ ብሎ ቁርኣንን ይዞ ሶላት ላይ መቆም በሚከተሉት ምክያቶች ሱናን ይቃረናል:-
① አንድ ሰው ሶላቱ ላይ ከቆመ ቀኝ እጁን ግራው እጅ ላይ ማሳረፍ አለበትና ይህን ያስመልጠዋል። (ቁርኣን ይዞ ከሆነ ይህን ሊተገብር አይመቸውምና)
② አላስፈላጊና ከሶላቱ ውጪ ለሆኑ በርካታ እንቅስቃሴዎች ይጋብዘዋል፣ ለምሳሌ:- ቁርኣኑን ለመክፈትና ለመዝጋት፣ ለማስቀመጥ… መሰል ነገሮች ብሎ ከሶላቱ ውጪ የሆነን እንቅስቃሴ ያደርጋል።
③ ሰጋጁ በእነዚህ እንቅስቃሴዎች ይወጠርና (ሶላቱ ውስጥ የሚጠበቅበትን ኹሹዕና እርጋታ አይኖረውም።)
④ ሰጋጁን ወደ ሱጁድ ቦታ መመልከት ያመልጠዋል። አብዘሃኛው የኢስላም ሊቃውንቶች ሰጋጁ ወደ ሱጁድ ማድረጊያው ቦታ መመልከቱ ሱና እና በላጭ ነው ይላሉ።
⑤ ሰጋጁ ምናልባትም ሶላት ላይ መሆኑን የሚረሳበት ሁኔታ ሊኖርም ይችላል። ምክንያቱም:- ልቡ ሶላቱ ላይ አልተሰበሰበም፣ ሶላት ውስጥ ከመተናነስ በተቃራኒው ቀኝ እጁን ግራው ላይ አላሳረፈም፣ ጭንቅላቱን ወደ ሱጁድ ቦታ አቀርቅሮ እየተመለከተ ስላልሆነ… ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች ቢተገብር ልቡ ሶላቱ ላይ ሰብሰብ ይል ነበር፣ ይህም ሶላት ላይ ለመተናነስ ይረዳው ነበር። ከኢማም ኋላ ሆኖ እየሰገደ መሆኑንም ያውቅ ነበር…
[መጅሙዕ አል-ፈታዋ ኢብኑ ዑሰይሚን 14/232]
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ!
በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ!
ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ!
ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን
በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ!
ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ!
ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን
Forwarded from [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
አላህ ይጠብቀን!!
🔹ብዙ ጊዜ ለሀላል ትዳር ተጠይቀው ባልሆነና እዚህ ግባ በማይባል ምክንያት ጥያቄውን ውድቅ የሚያደርጉ ሴቶች መጨረሻቸው ላይ ደስ የሚል ዜና አይሰማም!!። ይህ ብዙ ጊዜ የምናስተውለው ነውና እህቶች ዲኑንና አኽላቁን የምትወዱት ከመጣ ሳታንገራግሩ ቶሎ በሀላል ተሰተሩ!!

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
የደላው መች ቀረ......?!
ሁሉም ይሞታታል አስጠላም አማረ
ሁሉም ይጓዛታል ያቺን የሩቅ ጉዞ
የሌለው ባዶውን ያለው ስንቁን ይዞ
ዛሬማ ምን አለ ባይሰግዱ ባይፆሙ
ይቸግራል እንጂ አላህ ፊት ሲቆሙ
ዛሬማ ምን አለ ቢጠጡ ቢሰክሩ
ይቸግራል እንጂ ሙተው ሲቀበሩ
ዛሬማ ማን አለ የሚያጋልጥሽ
ከቀብር ስትገቢ ይታያል ጉድሽ
◈ ሸይኽ ሙሀመድ ወሌ (ረሂመሁላህ)
ዓጀብ ነው!! አላህ ኻቲማችን ያሳምረው!!
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
ሁሉም ይሞታታል አስጠላም አማረ
ሁሉም ይጓዛታል ያቺን የሩቅ ጉዞ
የሌለው ባዶውን ያለው ስንቁን ይዞ
ዛሬማ ምን አለ ባይሰግዱ ባይፆሙ
ይቸግራል እንጂ አላህ ፊት ሲቆሙ
ዛሬማ ምን አለ ቢጠጡ ቢሰክሩ
ይቸግራል እንጂ ሙተው ሲቀበሩ
ዛሬማ ማን አለ የሚያጋልጥሽ
ከቀብር ስትገቢ ይታያል ጉድሽ
◈ ሸይኽ ሙሀመድ ወሌ (ረሂመሁላህ)
ዓጀብ ነው!! አላህ ኻቲማችን ያሳምረው!!
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
Forwarded from [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
ከአሉ ተባለ ወሬ ተከልክለናልና እንጠንቀቅ!!
———
አሎባልታ ወሬ ብዙዎችን በተለያየ መንገድ አክስሯል!! አሉ ተባለ ወሬ በማህበረሰቡ ላይ ጉዳቱና መዘዙ የከፋ ስለሆነ ሸሪዓችን አጥብቆ ከልክሏል።
ከወርራድ አስሰቀፊይ ተይዞ እንዲህ አለ:-
ሙዓዊየህ ወደ ሙጊረህ ቢን ሹዕበህ እንዲህ በማለት ፃፈ፣ ከአላህ መልክተኛ ﷺ ከሰማሀው ምክር የሆነ ነገር ወደኔ ፃፍልኝ አለው፣ ሹዕበህ ኢብኑ ሙጊረህም እኔ ከመልክተኛው ﷺ የሚከተለውን ሲሉ ሰምቻለሁ በማለት ፃፈለት:- “አላህ ሶስት ነገሮችን ጠልቶላችኋል፣ አሉ ተባለን፣ ገንዘብን ማባከንና ጥያቄ ማብዛትን።” [ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት ሶሂህ ሀዲስ ነው።]
በዚህ አሉ ተባለ ወሬ ስንቱ ሱሰኛ ሆነ?!
ስንቱ ከቂርኣት (ከደርስ) ርቆ በዚህ ተጠመደ?!
ያውም የበለጠ ከማበላሸት ውጭ ሊያስተካክለው በማይችለው ነገር ላይ ገብቶ ስንቱ ተጠመደ?!
ስንቱ ነው በእንዲህ ያሉ ወሬዎች ተጠምዶ እውቀት ፈላጊ ምስኪኖችን ከደርስ ያቋረጠው?!
ስንቱ ነው በዚህ መልኩ ለቢድዐህ ባለቤቶችና ለአስመሳዮች በር የከፈተው?!
ስንቱ ነው በዚህ ተግባር ተዘፍቆ ከድሮ ጀምሮ ወደ ቡድንተኝነት (ተሀዙብ) ያመራው?!
እንንቃ!! ጎበዝ ጊዜያችን አናባክን!! ወዳጅነትን አሻክረው በጀመዓ ላይ ክፍተት እንዲፈጠር ሰበብ ከሚሆኑ ተግባሮች እንራቅ!! አሉ ተባለ ወሬን አጥብቀን ተጠይፈን እንራቅ!!
ታላቁ ፈቂህ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “በአሉ ተባለ ወሬ፣ ጥያቄን በማብዛትና ጊዜን በማባከን መወጠር (ቢዚ busy) መሆን በሰዎች መካከል ከተንሰራፋ በእውነቱ በሽታ ነው!! አላህን ጤነኛነትን እንጠይቀዋለ!!። ይህ ተግባር እንደ ትልቅ አንገብጋቢ ጉዳይ ይሆንበታል፣ በል እንዲያውም አንዳንዴ (በዚህ ተግባር ያልገጠመውን) ጥላትነት ለማይገባው ሁሉ ጥላትነትን ይጠቀማል፣ አለያም ደግሞ (በዚህ ተግባር ስለ ገጠመው ብቻ) ወዳጅነት የማይገባውን ወዳጅ ሊያደርግ ይችላል። ወደዚህ ደረጃ የሚደርሰው፣ ለዚህ እውቀትን ከመፈለግ አርቆ ውጥረት ውስጥ ለከተተው (ለአሉ ባልታ ወሬ) ከሰጠው ትኩረት የተነሳ ነው። እንደ ማስረጃ የሚያቀርበው ደግሞ ሀቅን መርዳት ነው የሚል ነው። እውነታው ግን እንደዛ አይደለም!። ይልቅ እውነታው ነፍስንም ሆነ ሰዎችን በማይመለከታቸው ነገር ውጥረት ውስጥ መክተት ነው!!።
የሆነ ወሬ ሳትፈልገው መምጣቱ ግን ውጥረት ውስጥ ሊከትህ አይችልም፣ እንደ ወሬ ማንኛውም ሰው ዘንድ ሳይፈልገውና ለወሬው ቦታ ሰጥቶ ሳይዘጋጅለት ሊመጣው ይችላል ነገር ግን ቦታ አይሰጠውም፣ በሱ ውጥረት ውስጥ አይገባም!!። ትልቅ ትኩረት የሚሰጠውም ጉዳዩ አይሆንም!! ምክንያቱም እውቀት ከመፈለግ ያዘናገዋል፣ ነገሮችንም ያበላሽበታል፣ በማህበረሰቡም ውስጥ የቡድንተኝነትን በር ይከፍታል፣ በዚህ ሰበብም ኡመቱ ለመከፋፈል ይበቃል።” [መጅሙዕ አል-ፈታዋ 26/127]
ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) በድጋሚ ተፍሲሩ ጁዝእ ዐማ ገፅ 197 ላይ እንዲህ አሉ:- “በእኛ ላይ ግዴታ የሚሆነው ፊትናዎችን ግልፅ የወጡትንም ይሁን በድብቅ የሚሰራጩትን መጠንቀቅ ነው!!፣ ሰዎችንም ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ ከሚያነሳሱ ነገሮች ሁሉ መራቅ ይጠበቅብናል፣ ሁሌም መረጋጋትን መያዝ ይጠበቅብናል፣ ከአሉ ተባለ ወሬ እና ጥያቄን ከማብዛት መራቅ ግዴታ ይሆንብናል፣ ይህ ነቢዩ ﷺ ከከለከሉት ተግባርም ነው። ስንት (በአሉ ተባለ ወሬ የምትሰራጭ) አንዲት ቃል የሰላ ሰይፍ የማይሰራውን ሰርታለች?!፣ በእኛ ላይ ግዴታ የሚሆነው የሚግባባና የሚዋደድ ማህበረሰብ እንዲሆን ከፊትና እና ፊትናን ከሚቀሰቅስ ነገር መራቅ ነው!!።”
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

የጓደኝነት መስፈርቶች
———
አል ፈቂህ ኢብኑ ጁዚይ አል'ማሊኪይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
የጓደኝነት መስፈርቶችማ ሰባት ናቸው
1ኛ, በእምነቱ ሱኒይ ሊሆን ግድ ነው።
2ኛ, በዲኑ ላይ አላህን የሚፈራ ሊሆን ነው። እርሱ የቢድዐህ ሰው ከሆነ አለያም ፋሲቅ አመፀኛ ሰው ከሆነ ባልደረባውን ወዳለበት አካሄድ ሊጎትተው ይችላል፣ አለያም ሰዎች በዚህ ይጠረጥሩታል፣ አንድ ሰው በጓደኛው ዲን ላይ ነውና።
3ኛ, የጥሩ አዕምሮ ባለ ቤት ሊሆን ይገባል። የሞኛሞኝ ሰው ጓደኝነት በላእ ነው።
4ኛ, የጥሩ ስነ-ምግባር ባለ ቤት ሊሆን ይገባል። መጥፎ ስነ-ምግባር ያለው ሰው ጠላትነቱ አይታመንም፣ ይህንም በምታስቆጣው ጊዜ ትፈትነዋለህ፣ ከተቆጣ ጓደኝነቱን ተወው።
5ኛ, ከሀሜት፣ ከምቀኝነት፣ ከሸር ፈላጊነትና ከሁለት ፊትነት ልቡ ንፁህ መሆን አለበት።
6ኛ, በቃሉ የሚፀና የማይዋልልና የማይቀያየር መሆን አለበት።
7ኛ, ለእርሱ ሐቅ እንደምትቆመው ለአንተም ሀቅ የሚቆምልህ መሆን አለበት። በአንተ ላይ ሀቅ እንዳለው እየተመለከትከለት ለአንተም ሀቅ አለህ ብሎ የማይመለከትልህ (ለሀቁ እንደምትቆምለት ለሀቅህ የማይቆምልህ) ጓደኛ ኸይር የለውም።
[አል-ቀዋኒን አል-ፊቅሂየህ ገፅ 460]
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
➥ በዚህ ዘመን እነዚህን መስፈርቶች ያሟላ ጓደኛ ያለው ሰው ምንኛ ታድሏል!! ዋና ዋና መስፈርቶችንም ያሟላ ማግኘት ትልቅ ነገር ነው!!

የወንጀል ጠባሳ እና የሰው ልጆችን አዋራጅነቱ!!
———
ኢማም ኢብኑል ቀይም (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል:-
“በአንድ ሀገር ወንጀል አልሰፈነችም ያንን ሀገር ብታወድመው እንጂ።
» በሰዎች ልብም አትሰፍንም ልባቸውን እውር ብታደርገው እንጂ።
» በአንድ አካልም አትሰፍንም ያንን አካል ብታሰቃየው እንጂ።
» በህዝቦች ላይም አትሰፍንም ያንን ህዝብ ብታሳንሰው እንጂ።
» በነፍስ ላይም አትሰፍንም ያቺን ነፍስ ብታበላሻት እንጂ።
ወንጀል አትከሰትም አላህ ዘንድ ለባሪያው ውርደት ምክንያት ብትሆን እንጂ፣ ባሪያው አላህ ዘንድ ከተዋረደ ማንም አያከብረውም።
ልክ አላህ እንደተናገረው:-
{ وَمَنْ يُهِـنِ اللَّهُ فـَمـَا لَـهُ مِنْ مُكْـرِم ٍ} الحج ١٨
«አላህ የሚያዋርደውም ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለውም።» አል ሐጅ 18
በዚህች አለምና በመጨረሻይቱ አለም ተንኮል (ሸር)ና በሽታ አለን? ምክንያቱ (ሰበቡ) ወንጀልና አመፅ ቢሆን እንጂ።” [አዳኡ ወደዋእ ገፅ 42]
አላህ ከትልቁም ከትንሹም ወንጀል ይጠብቀን!!