Sebah Media official
228 subscribers
680 photos
18 videos
2 files
217 links
ማነኛውም ሀሳብና አስተያየት ካላችሁ በ @fp3138 ማድረስ ትችላላችሁ
Download Telegram
በአክሱም የተላለፈው ውሳኔ ፀረ-እስልምናና ሕገ-መንግሥታዊ ጥሰት ነው”-

ዛሬ በመቐለ ከተማ ከሚገኙ ከ15 በላይ መስጊዶች የተወከሉ የከተማዋ ሙስሊም ነዋሪዎች በአክሱም ሙስሊም ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ላይ እየደረሰ ያለውን በደል አስመልክቶ ሰፊ የውይይት መድረክ አካሂደዋል። በውይይቱ ላይ በአክሱም ከተማ አስተዳደርና በሃይማኖት መሪዎች የተላለፉት ውሳኔዎች በኢትዮጵያና በትግራይ ክልል ሕገ-መንግሥታት የፀደቂ መሰረታዊ መብቶችን የሚጥሱ መሆናቸው በዝርዝር ተገምግሟል። ማ/ሰቡም በአክሱም ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እጅግ እንዳሳዘነውና ድርጊቱንም በጽኑ እንደሚኮንን በቁጣ ገልጿል።

በመድረኩ ላይ በዋናነት የተነሳው ነጥብ በአክሱም ሙስሊም ተወካዮች ተፈርሟል የተባለው ሰነድ በከፍተኛ ማስፈራሪያና ጫና የተፈረመ በመሆኑ ፍጹም ተቀባይነት እንደሌለው ገልፀዋል። ተሳታፊዎቹ እንደገለጹት፣ የአክሱም ሙስሊሞች ኢስላማዊ ማንነታቸውን እንዲጥሉ በግዳጅ እየተሰራ ነው። በመሆኑም በክልሉ ሚዲያዎች "የመቻቻል ስምምነት" ተብሎ የቀረበው ባለ 4 ነጥብ ሰነድ የእስልምናን መሰረታዊ መርሆችን የሚፃረር በመሆኑ በመቐለ ሙስሊሞች ሙሉ ድምፅ ውድቅ ተደርጓል። "የአክሱም ሙስሊም ኮሚቴዎች በፈረሙት ፊርማ የፈጣሪ ቃል አይቀየርም" ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

በመጨረሻም የመቐለ ሙስሊም ማህበረሰብ ለአክሱም ወንድሞቻቸው "አይዞአችሁ፤ መላው ህዝብና ከሁሉ በላይ ፈጣሪ ከእናንተ ጋር ነው" የሚል ሙስሊሞች በተወለዱባትና ባደጉባት የአክሱም ከተማ መሰረታዊ መብታቸው ሊገፈፍ እንደማይገባና የሃይማኖት እኩልነት ሊከበር እንደሚገባ አሳስበዋል። በትግራይ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተጀመረው ይህ የተቃውሞና የውይይት መድረክ በሁሉም የትግራይ ዞኖችና አካባቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቅጣጫ ተቀምጧል።
@Sebahofficial
👍31
መብት በትግል እንጂ በልመና አይገኝም!

  የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ከ20 ወራት ቡሃላ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ ከፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ተሰባስበዋል።

  ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !

@sebahofficial
👍2🔥1
Forwarded from Abuja Media
የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ተማሪወች መልእክት

ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 2:40 ሰዓት ድረስ፣ ተማሪዎች በብርዱና በጨለማው ውስጥ ቁጭ ብለው ለጥያቄዎቻቸው ምላሽ እየጠበቁ ይገኛሉ። መብትንና ክብርን ለማስከበር የሚደረግ ጉዞ መራራና ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም፣ የእነዚህ ወጣቶች ጽናት ግን የፍትሃዊነታቸው ትልቁ ማረጋገጫ ነው።

📌 ለተማሪዎቻችን፦ በዚህ ብርድ በበዛበት ምሽት እያሳያችሁት ያለው ተስፋ አለመቁረጥና ቁርጠኝነት ታሪክ የማይረሳው ታላቅ የጽናት መዝገብ ነው። ቅስማችሁ አይሰበር፣ ሞራላችሁ አይውረድ። በዚህ አስቸጋሪ ሰዓት የምታሳዩት ትዕግስት ና አንድነት ለነገው ድላችሁ መሰረት ነው። አላህ እውነተኞችንና መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ የሚጠይቁትን መቼም ቢሆን አይጥልም።

📌 ለሚዲያ አካላት፦ እነዚህ ወጣቶች የነገዋ ሀገር ተስፋዎች እንጂ የሁከት አራማጆች አይደሉም። ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ ህጋዊና ሰብአዊ መብቶቻቸውን ይዘው መልስ ፍለጋ በብርድ ላይ ተቀምጠዋል። ለነዚህ ተማሪዎች ድምጽ በመሆን ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን።

📌 ለዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት፦ ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ ላነሷቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ፣ ግልጽና ፍትሃዊ ምላሽ መስጠት የሀላፊነት ሁሉ መጀመሪያ ነው። ጉዳዩን በቸልተኝነት መመልከት ወይንም ማዘግየት መፍትሄ አይሆንም። አሁንም ጥያቄያችን ግልጽ ነው! ከምላሹ መሸሽ አይቻልም!

📌 ለመጅሊስ፦ የናንተ የመጀመሪያ ኃላፊነት የሙስሊሙን መብት ማስጠበቅ ነው። ሰላማዊው ጥያቄያችን በፍትሐዊ መንገድ ይመለስ ዘንድ ስሩ። ሴት ልጅ ብርድ ላይ አትደር፤ ተማሪዎች እንቅልፍ አጥተው ሜዳ ላይ አይደሩ። ስለፍትሕ ቁሙ! ታሪክ እየተፃፈ ነው!!

📌 ለሙስሊም ማህበረሰብ፦ እነዚህን በብርድና በጨለማ ውስጥ ያሉ ልጆቻችሁን በዱዓና በሞራል ከጎናቸው ቁሙ

@abujamedia
2👍1
Forwarded from Abuja Media
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እና የአዲስ አበባ መጅሊስ ዋና ፀሀፊ ኡስታዝ ሸሀቡዲን ሸህ ኑራ ከሌሎችም አመራሮች ጋር በመሆን ወደ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አየሄዱ ነው!!

አዲስ ነገር ካለ እናሳውቃለን

@abujamedia
3👍1
Forwarded from Abuja Media
ተማሪውን ለማረጋጋት እየተሞከረ ቢሆንም ግን ተማሪው አቋሙን አለቅም በሚል ቀጥሏል። ለጥያቄዬም መልስ ሳይሰጠኝ የትም አልሄድም በሚል አቋሙ ጸንቶ ነው ያለው።

አሚሮች ከመጅሊስ አካላት ጋር ንግግር እያደረጉ ይገኛሉ!

@abujamedia
👍2🔥1
Forwarded from Abuja Media
Update!

ከመጅሊስ በኩል ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ፣ ኡስታዝ አዩብ ደርባቸው፣ ኡስታዝ ሸሃቡዲን ሸኑራን ጨምሮ 5 ልዑካን አባላት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተገኝተው ከጀማዓው ተወካዮች እንዲሁም ከአጠቃላይ ተማሪዎች ጋር ውይይት ካደረጉ በኃላ በነገው ዕለት ከዩኒቨርሲቲው ጋር ውይይት እንደሚደረግ፤ ይህንንም ጉዳይ በኃላፊነት እንደሚይዙት በመናገር ተማሪዎች እንዲበተኑ ሆኗል።

አሁንም የመጅሊስ አመራሮች ለተማሪዎች የገባችሁትን ቃል አክብሩ! ተማሪው እናንተን አምኖ ጥያቄየን ታሳካላችሁ ብሎ አማና ሰጥቷችኃል። ይህን አማና መብላት አላህ ፊት፤ ተማሪው ፊት፤ ህዝብ ፊት እንዲሁም ታሪክ ፊት ተጠያቂ ያደርጋችኃልና አማናችሁ ተወጡ!

ተጨማሪ በቅርቡ የምንመለስ ይሆናል።

©️ aaumsu

@abujamedia
👍2👏1
Forwarded from Abuja Media
ትምህርት ሚኒስቴር ከኢድ ዋዜማ እና ማግስት ሊሰጥ የነበረውን የሪሜድያል ፈተና ወደ ግንቦት 27 መራዘሙን ገልጿል።

  ቢዘገዩም ማስተካከላቸው ኸይር ነው። ይህንን ስህተት ግን በየአመቱ ባይደግሙት ኸይር ነው። ቋሚ የሆነ አሰራር እና መፍትሔም ሊቀመጥለት ይገባል።

@abujamedia
👍5
Forwarded from Abuja Media
እሺ ነገ ፀሀይ ከወጣችበት ቀናት ሁሉ ምርጡ ቀን ነው፣ ነገ አላህ የ 2 አመት ወንጀል የሚምርበት ቀን ነው፣ ነገ አላህ ብዙ ባሮቹን ከ እሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን ነው፣ ነገ የ ዱዓዎች ሁሉ በላጭ ዱዓ የሚደረግበት ቀን ነው፣ ነገ አላህ መላዒኮቹ ፊት በኛ የ ሚመፃደቅበት ቀን ነው፣ ነገ ልዩ ቀን ነው፣ ነገ የ አመቱ ምርጥ ቀን ጌታችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ለኛ ቅርብ የሚሆንበት ቀን ነው ያ ጀማዓ የነገው ቀን normal ቀን አይደለም እና አደራ በ normal ውሎ እንዳያልፍ።

እና ከ ፈጅር በፊት 30 ደቂቃ ቀደም ብለን እንነሳና 2 ረከዓ በ ጥሞና ልክ ከዚህ በፊት እንዳልሰገድነው፣ ልክ አላህ ፊት ቆመን ጀነት በ ቀኛችን በግራችን ጀሀነም እንዳለ እያሰብን 1 ረከዓ ደግሞ ዱዓችንን የተዘበራረቀ ስሜታችንን ርግፍ አድርገን ለ አላህዬ እንነግረዋለን። ግን እኮ ለይል ሰግጄ አላውቅም? ኢሄ ቀን ኖርማል አይደለም እያልኩህ🥰 ከዛም ሱሁራችንን ቀመስ ቀመስ አድርገን ወደ ፈጅራችን🖤

ከዛም ፈጅራችንን ሰግደን ጸሀይ እስክትወጣ በመስገጃችን ላይ ቁርዓን እየቀራን ቁጭ ብለን የ ንጋቱን ውበት እያስተነተንን ሀሳባችንን ሰብስበን ሀጃዎቻችንን በ ፎልደር ሰብስበን የምንፈልገውን ነገር በደንብ አውቀን ወደ ስራችን / ክላሳችን / ጉዳያችን🖤

የ ከሰዓቱ ክፍለ ጊዜ is the treasure ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርገህ ትተህ ወደ መስገጃህ እዬዬ ብለህ ማረኝ በለው፣ ጭቅጭቅ እያደረከው ከ ጀሀነም ነፃ አውጣኝ በለው፣ ጠዋት ላይ በ ፋይል ያስቀመጥከውን ሀጃዎችክን ዘርግፋቸው አላህን እኮ ነው የምትጠይቀው አታመንታ ሁሉንም ዘርግፍ... አላህ አይሆንም አይሳካም በ ጭራሽ! ያልከውን ሁሉ በ አንድ ጀንበር ሁን ሊለው አይችልምን? ይችላል በደንብ ይችላል በደንብብብብ!

ከደከምክ እስከ አስር የ 30 ደቂቃ nap ውሰድ እና ለ አስር ተነስ ከ አስር በኋላ ግን እንድች ብለህ እንዳትዘናጋ፤ እነዚህ የምትሮጥላቸው ሀጃዎች ሁሉ በ አላህ እጅ ናቸው ሙጥኝ ብለህ ለምነው ልብህ እስኪረጋጋ እና ጌታህ እሺ ያለህ እስኪመስልህ ድረስ እጅህን አታውርድ። ታዲያ ይህን ስታደርጉ በ መሀል ስሜን ማስገባትን አትርሱ🖤

ይህን ማድረግ ያልቻለ የ ስራው በሀሪ ያልፈቀደለት ግን ከ ቀኑ የ ከሰዓቱን ክፍል 30 ደቂቃን ወሰዶ ጌታውን ይለምን፣ ቀኑን በዚክር ያሳልፍ፣ ቁርዓኑን ይቅራ🖤

ሀይድ ላይ ያለሽ እህት አንቺ ደግሞ ያልፆመ እንዳይጠይቀኝ አልተባለም ሲደክምሽ እየበላሽ እየጠጣሽ ዘክሪ፣ ፆመኞችን ነይተሽ አስፈጥሪ በያንዳንዷ ልፋትሽ ውስጥ ኢህቲሳብ አድርጊ🖤

አላህ ያግራልን አላህ ይቀበለን🥰
@abujamedia
👍3
ኢዱኩም ሙባረክ!

በበዓሉ፦
በሁሉም የአለም ክፍል የተበደሉ ሰዎችን ፍትሕ ያሳየን። የፍልስጤም እህት ወንድሞቻችንን ድል ያሰማን። በአክሱም የተጨቆኑ ሙስሊሞችን ፍትሕ ያቅርብ። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጀምሮ በትምህርት ተቋማት መብታቸው እየተጣሱ ያሉ ሙስሊም ተማሪዎች መብት ተከብሮ ያሳየን። ፍትሕ መስፈኑ ግድ ነው። ይህንን በዓል ለዚያ ሰበብ ያድርግልን።

ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሃል አዕማል!

@sebahofficial
4
በሚና ቤተ- መንግስት በተካሄደ የሐጅ የክብር እንግዶች አቀባበል ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና የዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ሙሐመድ ሷሊህ ከሳዑዲው አሚር ሙሐመድ ቢን ሰልማን ጋር እንደተገናኙ ተገልጿል።

ማሻአላህ 😍👏

@sebahofficial
3
Forwarded from Abuja Media
የሀላባ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በነገው ዕለት የዝናብ ሶላት መርሐግብር እንደሚከናወን አስታወቀ።

ሰኔ 5/2018 ሀላባ ቲቪ
------------------------------

ምክር ቤቱ በህዝብ ግንኙነት ክፍሉ በኩል እንዳስታወቀው በዞናችን በነገው ዕለት ቅዳሜ ጠዋት ከ1:00 ጀምሮ በሚከናወነው የዝናብ ልመና ሶላት (ሶላተል እስቲስቃዕ) መርሐግብር የሀላባና አካባቢው ሙስሊም ማሕበረሰብ በሀላባ አለም አቀፍ ስታዲየም ተገኝቶ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርቧል።

በተያያዘም በሀላባና አካባቢው ዝናብ ከወትሮም በበለጠ ሁኔታ የሚያስፈለግበት ወቅት መሆኑን በመጠቆም አሁን ግን ዝናብ ባለመዝነቡና በጥቂቱ የዘነበውም ቢሆን ሁሉንም ቦታ ያላዳረሰ ከመሆኑ የተነሳ የተዘራ እህል መብቀል አለመቻሉንና የበቀለውና እያደገ ያለውም በዝናብ ዕጥረት ምክንያት እየደረቀ በመሆኑ የዝናብ ሶላትን መስገድ ግድ እንዲሆነ አብራርቷል።

በዚህም ምክንያት ምክር ቤቱ ከዞኑ ኡለማዕ ምክር ቤት ጋር በመነጋገር በነገው ዕለተ ቅዳሜ ሰኔ 06/2018 ከጧቱ 1:00 ሰዓት ላይ በሀላባ አለም አቀፍ ስታዲየም ለዝናብ ልመና ሰላተል ኢስቲስቃዕ እንዲሰገድ መወሰኑን አስታውቋል።

በመሆኑም በዞናችን የሚትገኙ ሙስሊም ማህበረሰብ ክፍሎች ወንድ፣ ሴት፤ ትልቅ፥ ትንሽ ሳይል ሁሉም በነቂስና በሠዓቱ ወጥቶ ሠላተል እስትስቃዕ ላይ እንዲሳተፍ ሲል ይፋዊ ጥሪውን አቅርቧል።

በመጨረሻም ከሀላባ ቁሊቶ ከተማ ርቀው በሚገኙ ከተሞች ማለትም በጉባ፣ በሸኖ፣ ሚቶ ዲጆ፤ አቦክቾ ወ.ዘ.ተ ከተሞች ጭምር ሠላተል እስትስቃዕ እንድሠገድ ጭምር ምክር ቤቱ መልዕክቱን አስተላልፏል።

©️Halaba tv
@abujamedia
👍5
Forwarded from Abuja Media
ከነገው ጀምሮ የኢንትራንስ ፈተናን ለምትወስዱ እህት ወንድሞቼ መልካም ፈተና። አላህ ያግዛችሁ! ተጨናንቃችሁ የምትጨምሩት ውጤት አይኖርምና ተረጋግታችሁ ለመስራት ሞክሩ። ዱዓ እና ዚክር ላይም ጠንክሩ። መልካም ፈተና!!

@abujamedia
5
Forwarded from Abuja Media
ተመልከቱ፦ 12 አመት ሙሉ ተምራ ወደ ዩኒቨርስቲ ትገባ ዘንድ የሚወሰድን ፈተና ለመውሰድ አመቱን ሙሉ ተዘጋጅታለች፤ ይህንን ሁሉ ስታደርግ እስልምናዋ የሚያዛትን ኒቃብ ለብሳ ነው። ሆኖም ግን ፈተናውን ለመውሰድ ከመፈተኛ ጣቢያ ስትደርስ ኒቃብሽን ካላወለቅሽ አትገቢም ተብላ ከበር ቆማለች። ይህ ሁሉ ሲሆን ሀገር ዝም ብላለች። ይህ ሁሉ ሲሆን ሙስሊሙን የሚወክለው ተቋም ዝም ብሏል። ይህ ሁሉ ሲሆን መፍትሔ ለማምጣት መሬት የያዘ ስራ እየሰራ ያለ አካል የለም። በዚህ ምክንያት ፈተና ለሚያመልጣት ተማሪ ተጠያቂው ማን ነው? በዚህ ምክንያት ከፈተና ለምትስተጓጎል ተማሪ ተጠያቂው ማን ነው? ደግሞኮ ይህ እንደሚፈጠር ከዛሬ ቀደም ደጋግመን ስንናገር ነበር። ለምንድን ነው ከቁምነገር ያልተወሰደው? ወይንስ ዋጋዋ አንሶባቸው ነው? ለእነርሱ የአንድ ሙስሊም ተማሪ ዋጋ ስንት ነው?

@abujamedia
😢3
Forwarded from Abuja Media
ኒቃቢስት እህቶች እንግልት ከደረሰባቸው ቡሃላ እንዲገቡ ሆኗል። ይህንን ስኬት ብለን የምንቆጥር ከሆነ ግን ውርደት ነው። መንግስት ግልፅ ማብራሪያ መስጠት አለበት። መንግስት ይህንን ውንብድና የፈፀሙ አካላትን ተጠያቂ ማድረግ አለበት።
👍4
Forwarded from Abuja Media
ለሀላባ ሙስሊም ማህበረሰብ የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ

ሙሃረም 23/1448 ሂጅራ
ሀምሌ 1/2018 ዓ/ል
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
የሀላባ ዞን እስልምና ጉዳዮች ም/ቤትና የሀላባ ዞን ኡለማ ም/ቤት በጋራ ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት ነገ ሀሙስ ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ በሀላባ አለም አቀፍ ስቴድየም በሰላተል ኢስቲስቃዕ የሚሰገድ ይሆናል።
በመሆኑም በሀላባ ቁሊቶ ከተማና አጎራባች ቀበሌያት የሚገኝ ሙስሊም ማህበረሰብ ሴት፣ ወንድ፣ ትልቅ፣ ትንሽ፣ ወጣት፣ ሽማግሌ ሳይል በነቂስ በመውጣት አላህ እንዲማፀን ጥሪ ቀርቧል።
መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ በተቻለን ልክ ብር እናድርገው

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

የሀላባ ዞን እ/ጉ/ም/ቤት ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ክፍል

@abujamedia
👍5
ሼይኽ መከተ ሙሄ የፌደራል ጠቅላይ ሸሪያ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን ተሾሙ

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ሃምሌ 22 ቀን 2018 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን በዚህም መሰረት በራሳቸዉ ፈቃድ መልቀቂያ ባቀረቡ የፌደራል ጠቅላይ ሸሪያ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶች ምትክ በኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ተመልምለው የቀረቡ እጩዎችን በተመለከተ ጉባኤው ተገቢውን ማጣራት ካደረገ በኋላ ሼህ መከተ ሙሄ መኮንን የፌደራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍ/ቤት ፕሬዚደንት እንዲሁም ሼህ አብዱልመናን መሃመድ አህመድን የፌ/ጠ/ሸ/ፍ/ቤት ም/ፕሬዚደንት ሆነው እንዲሰሩ ሹመት ሰጥቷል፡፡

አዲሶቹ የፌደራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንቶች ህዝበ ሙስሊሙ ከተቋሙ ሊያገኝ የሚገባውን ቀልጣፋ እና ተቋሙን የሚመጥን አገልግሎት እንዲሰጥ ታላቅ ኃላፊነት ይኖርባቸዋል::

ለሼይኽ መከተ እና ለሼይኽ አብዱልመናን መልካም የሰራ ዘመን ይሆን ዘንድ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ

@sebahofficial
👍31
የመካ ስምምነት

ቱርክዬ፣ ሳዑዲ አረብያ እና ፓኪስታን "በአንድኛችን ላይ የሚደርስ ጥቃት በሶስታችንም ይመከታል!" - በሚል መሪ ቃል ወታደራዊ ስምምነት አድርገዋል። መቀራረብ፣ መወያየት፣ መተጋገዝ፣ ኢስላማዊ ወዳጅነትን ማጎልበት ደስ የሚል ነገር ነው። አላህ ያዝልቅላቸው፤ ያግዛቸው፤ ለመልካም ለውጥ ሰበብም ያድርግላቸው።

@sebahofficial
👍5