የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች
6.74K subscribers
1.04K photos
78 videos
2 files
191 links
በግጥም የውስጥ ስሜትን እናጣጥም
Download Telegram
ስታጠፋ እያየች _ ዝም  ካለቺህ  ሴት
ፍፁም እንዳታየው _ ልክ እንደሞኝነት
ውስጧ  እየሞተ  ነው _ ላንተ ያላት ስሜት
ወይ እየሰራች ነው _ የሚያዋጣትን ቤት
እናም እልሀለሁ......
ደጋግመህ ስትዋሻት  _ በደል ስትሰራ 
ንዝንዟን ሳይሆን  _ ዝምታዋን ፍራ
#ሼን ✍️
እድሌ ነው መሰል
ዙሪያዬ ላለ ሰው _ ልክ ሁኜ አልታይም
የምደክምላቸው _ ልፋቴን አያውቁም
ለሳቃቸው ስጥር _ሰርክ ያስለቅሱሳኛል
ጥፋት አይቼ ባልፍ _ እንደ ሞኝ ያዩኛል  
መሳሳታቸውን _ ደግሞ ስነግራቸው
ተጨቃጫቂ ነህ _  ይሆናል ወሪያቸው
ባስፈለጉኝ ሰአት  _  ከኔ ይርቃሉ
ለብቻዬ ስሆን
ምን አገኜህ ብለው _ ሀሜት ያወጋሉ
      ሳቄን ሰርቀው ወስደው
አኩራፊ ይሉኛል _  እነሱው መልሰው
#ሼን ✍️
@seanlph
ወደ ሂወትሽ ውስጥ_ ገብተው እየወጡ
አስተማሩሽ መሰል _ ሂወትን በቅጡ
በደንብ ያስታውቃል _ የባህሪሽ ለውጡ
አሁን እንደፊቱ _ በትልቅ በትንሽ
መናደድ ትተሻል _ አይተክዝም ፊትሽ
ጊዜ እየሰጠሽ ነው _ ለገዛ እኔነትሽ
ሳቅና ደስታሺን _ ከሰው አጠብቂም
ሰዎች መጡ ቀሩ _ ብዙ አትደነቂም
የመጣን መቀበል _ የሄደን መሸኜት
ቆዬ ሰነበተ _ ጎንሽ ከቻለበት

ተ ለ ው ጠ ሻ ል

#ሼን
#ለምን_እስካሁን_እንዳላገባሽ_ልንገርሽ 🤔
አስቀያሚ ሁነሽ _ መልክሽ አስጠልቶ
አንቺን የሚፈልግ _ ዙሪያሽ ወንድ ጠፍቶ  
ወይ ከሌሎች ሴቶች _ አመልሽ ተለይቶ
ፍፁም እንዳይመስልሽ _ እድሜሽም ኮብልሎ
ባገር ጠፍቶም አይደል _  ባንቺ ልክ ቬሎ
ወዳጅ ተቸግረሽ _ አፍቃሪ ስላጣሽ
ከቶውን አይደለም...
መጥፎ ስለሆነ _ የአርባ ቀኑ እጣሽ

እየወልሽ እቱ ....🤔
ያላገባሽበት ዋነኛው ምክኒያቱ
ላንቺ ግድ የሌለው _ ስሜት የማይሰጠው
መጣሽም ቀረሺም _ ከቶ የማይገርመው
ሰው እየተከተልሽ _ የማይፈልግሺን
ማየት ተስኖሽ ነው 🤔
በዙሪያሽ ያለውን _ የእውነት ወዳጂሽን
========================
#ሼን ✍️
@seanlph
====== ተውት አትሰሩት =====
ተውት አትሰሩት _ ልቀቁት በነፃ
ዜናም አትዘግቡ  _ አትስጡ  ገለፃ 
አንደ ከዚህ ቀደም _  እንደለመዳችሁ
ዘጠኝ አስር አመት _ ፍርድን ወስናችሁ
በናቲቱ ሀዘን ከምታላግጡ  ከምትሳለቁ
ይሻላል ባንድ ፊት _ባታስሩት ብትለቁ
ህዝቡም ቁርጡን ይወቅ_ ህግ አለመኖሩን
ሌላውም ይቀጥል _ መግደሉን መድፈሩን
ከዛም የሆነ እለት _ ይሄ ያውሬ ምግባር
ከቤታችሁ  ገብቶ _ ስታዩት በተግባር
በደንብ ሲገባችሁ ....
ምን ያክል እንደሆን _  ቁስሉና ሀዘኑ 
            ያኔ  ታውቃላችሁ ....
መዝቀጥ መዛባቱን _  ፍርዳችሁ ሚዛኑ

#ሼን ✍️
@seanlph
======= 🤔
ለባሌ ስጦታ _ ምን ልስጠው ውድ እቃ
ብላ ጠየቀቺኝ _  አንዷ ሴት ተጨንቃ
ባል ሚስቱ  _  ብትሰጠው
ከሁሉ  _ ሚያበልጠው 
አብዝቶ ሚወደው _ እጅግ ውዱ ነገር
አንድ ሰላሙን ነው _ ሌላኛው መከበር 
እኒህን ሁለቱን _ ስጪው ሳትሰስቺ 
ያኔ በሱ ልብ ውስጥ_ ትነግሻለሽ አንቺ
#ሼን ✍️
በ 0939006488 ቴሌግራም ላይ ይዘዙ 🙏🙏🙏
አላስኬድ ካለኮ _ እግርም ይቆረጣል 
ያንቺ ልብ አሁንም _ ሰው ይለማመጣል
ተይ ይከብዳል አትበይ _ እድሜኮ ያመልጣል
በሾህ ንግግሩ _  አድምቶ  እየወጋ
ደጋግሞ ነግሮሻል _ ስላንቺ ያለውን ስሜትና ዋጋ

ሴትነትሽን ንቆ _ በመግፈፍ እንደጨርቅ
መሄጃ ቢስ አርጎሽ _ እንደዛ  ሲሳለቅ
እልፍ አስተውለሻል ...

ይወደኛል እያልሽ _  እራስሺን አትካጅ
በግድ ያቆየሺው _ አይሆንሽም ወዳጅ
 
ሂወት ስለማይቆም _ ባንድ ሀዘን ተሰብሮ
የሰው ልጅ ይኖራል _ እናቱንም ቀብሮ
ያለፈው በቃ አልፏል
ዋጋሽን አክብረሽ _  ጀምሪ አዲስ ኑሮ
  ያልተወደድሺበት _ ያልተከበርሺበት ያልተፈለግሺበት _   ጥንቅር ይበል ጎጆ 
በምንም ሁኔታ _ ከዚህ የተሻለ ይገባሻል ቆንጆ
#ሼን
@seanlph
ኑሮኝ ባደርግልሽ
ላንገትሽ ወርቅ ሀብል _ ለጣትሽ ደግሞ እንቁ 
ቤትም ብሰራልሽ _ ቪላ በትልቁ  
በእግርሽ እንዳቴጂም _ ብገዛ ራቫፎር
ልብሶችሽን ከቱርክ _ ሜካፕ ከሲንጋፖር
ሽቶሽን ከፍራንስ
ደስ ባለሽ ብራንድ _ በፈለግሺው ግላስ
ኑሮኝ ብገዛልሽ _  እንዳሻሽ ባሰልፍ 
ደስታው ለኔ ነበር _ ካንቺ በላይ በጥፍ
አቅም አንሶኝ እንጂ  _ ገንዘብ ቢኖር ከጄ 
በመንደሩ ሰው ልክ _ ሙክት ሰንጋ አርጄ
ደግሼ ባገባሽ _ ጉድ በሚያሰኝ ሰርግ
ደስታው ለኔ ነበር  _  ላንቺ ምንም ባረግ

ግን የለኝም በቃ  _ በዚህ መጠን ወረት
አሁን ባለሁበት _ ሁኔታ ማንነት 
የምትወጂኝ ከሆን _ ከልብሽ የእውነት

አብረን እንድንኖር ...
ግዴታኮ አይደለም _ ወርቅና ጌጣጌጥ
ግዴታኮ አይደለም_  ድግስን መለጠጥ 
ግዴታኮ አይደለም _ መኪናና ቪላ
ግዴታኮ አይደለም _  መኖር እንደሌላ

ስላንቺ ያለኝን መውደድና _ ክብር በውል እያወቅሺኝ
ነገዬን ልቀይር በምችለው  መጠን ስለፋ እያየሺኝ
ለጊዚያዊ  ምቾት _  አስበልጠሽ ገንዘብ
የኔን የእውነት ፍቅር _ ካቃተሽ መገንዘብ 
ግድ ቆዪ ብዬ _ አላስረፍድሺም
ሂጂ ዛሬውኑ _  ክፍት ነው መንገዱ 
ባንቺ አልተጀመረም _ እንዲህ ነው አንዳንዱ
ልቡን እያስራበ _  ኗሪ ነው ለሆዱ
#ሼን
@seanlph