ፀፀሎትህን አታቋርጥ!!
ፀሎት ማድረግ እግዚአብሔር ጋር የምንነጋገርበት ቋንቋ ነው ፣ የልቦናችን ብርሃን ፀሎት በምናደርግበት ሰዓት ይበራል ይህም የሚያመላክተው ከፈጠረን አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር በመለኮታዊ የብርሃን ንዝረት በቀጥታ የምንገናኝበት ስርዓት ነው። ዛሬ የምንኖርባት ዓለም በጣም ብዙ አስጨናቂ ነገሮችን በዙሪያችን አስቀምጣብናለች ይህም የጨለማው ሃይል ብርታት አግኝቶ የኛን የፍርሀት ንዝረት እሱ እንደሃይል እየተመገበው ፀሎታችን ወደፈጣሪያችን እንዳይደርስ ይታትራል። ይህ የማወራው ነገር ተራ ወሬ ሳይሆን በዘመነ ኦሪት በትንቢተ ዳንኤል ላይ ተጽፎ የምናገኘው እውነት ነው፣ “የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት።” ትንቢተ ዳንኤል 10፥13
ዳንኤል ለረጅም ቀናት እራሱን አዋርዶ በሀዘን ውስጥ ሆኖ በፀሎት ሆኖ እንጀራም አልበላም፥ ሥጋና ጠጅም በአፉ አልገባም፥ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባም፣ ለፀሎቱ መልስን ወዲያው አላገኘም ነበር ሆኖም ግን በሃያ አራተኛው ቀን ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦለት የፋርስ መንግስት ለ21 ቀን እንደተቋቋመው እና ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ወደ ቅዱስ ገብርኤል እንደመጣ ያሳየናል፣ በመከራችን ውስጥ ሆነን እግዚአብሄርን በፀሎት ስናገኘው የጨለማው ገዥ ሃይሉ ይዳከማል ምክንያቱም ፍርሃታችን እንጂ ጸሎታችን ለሱ ጉልበት አይሆነውም በዚህም የብርሃናዊው መለኮት ይገለጣል ቅዱሳን መላእክትም ይረዱናል ፣ በጠላታችን ላይ አብዝተን እንበረታለን ።
ስለዚህ ወንድሞቼ እና እህቶቼ አብዝተን እንጸልይ፣ በቅዱሳኑ ላይ ያደረ እግዚአብሄር በእኛም ላይ በረከቱን ያሳድርብን፣ ስለሃገራችን ሰላም፣ ስለምድራችን ሰላም አብዝተን እንፀልይ፣ በጊዜያዊ ተንጠልጣይ አጀንዳዎች ራሳችንን በከንቱ አናባክን።
እግዚአብሄር ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን ፣ የቅዱሳኑ በረከት በኛ ላይ ይደርብን፣ የቅዱሳን መላእክት የቅዱስ ሚካኤል፣ የቅዱስ ገብርኤል፣ የቅዱስ ሩፋኤል፣ የቅዱስ ፋኑኤል፣ የቅዱስ ዑራኤል፣ የቅዱስ ራጉኤል፣ የቅዱስ አፍኒን እና የቅዱስ ሳቁኤል አማላጅነታቸው ጥበቃቸው በረከታቸው ረዳኤታቸው አይለየን፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነቷ በረከቷ ረዳኤቷ በኛ ላይ ይደርብን፣ የፃድቃን የቅዱሳን ሰማእታት ልመናቸው በረከታቸው ረድኤታቸው በኛ ላይ ይደርብን።
ቸር ያቆየን።

❤1
እንዃን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሰን ❤❤❤❤❤
100 የቅዱስ ሚካኤል ስምና ክብር ፦
1) ሊቀ መላእክት
2) የሰማይ ሰራዊት አዛዥ
3) የጌታ ሰራዊት መሪ
4) የሰማይ ኃይላት ልዑል
5) ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት መካከል የመጀመርያው
6) የገነት ጠባቂ
7) ታማኝ ጠባቂ
8) የሰይጣን ያሸነፈ
9) የቤተክርስቲያን ተከላካይ
10) የሕዝብ ጠባቂ
11) የክብር አብሳሪ
12) የጽድቅ ተዋጊ
13) ሰማያዊ አማላጅ
14) የሥላሴ አገልጋይ
15) የፍትህ ሰይፍ የየዘ
16) የነበልባል ሰይፍ ተሸካሚ
17) የክፋት ሰራዊትን አጥፊ
18) የነፍሳት መሪ
19) የቅድስና ምስክር
20) አዋጅ ነጋሪ
21) የመላእክት ሠራዊት ብርሃን
22) የእስራኤል ጠባቂ
23) የመላእክት ጦርነት መሪ
24) ነበልባላዊ
25) የገዳማት ጠባቂ
26) የጥንካሬ ግንብ
27) የመለኮታዊ ኃይል ማኅተም
28) የአምላክ ነጎድጓድ
29) የእግዚአብሔር በቀል ሰይፍ ተሸካሚ
30) የፍርድ አስፈጻሚ
31) የመለኮት ዙፋን ጠባቂ
32) የሰልፉ መሪ
33) የባህራን ወደጅ
34) የጨለማ ውስጥ ብርሃን
35) የጻድቃን ወዳጅ
36) የሰማዕታት ድፍረት
37) የነብያት ረዳት
38) የመሠዊያ ላይ አገልጋይ
39) የጌታ ትእዛዝ ድምፅ
40) የትሁታን ጋሻ
41) የቤተክርስቲያን ጠባቂ
42) በገነት ውስጥ የመጀመሪያው
43) የሰራዊቶች አስታጣቂ
44) የሰማይ የድል መለከት
45) ዘንዶውን ያደቀቀ (ራእይ 12)
46) ንቁ ጠባቂ
47) የመለኮት እሳት ተሸካሚ
48) የገነት ደጃፍ ጠባቂ
49) አዛኝ መልአክ
50) ሩህሩህ መልአክ
51) የተሰደዱትን አዳኝ
52) የተጨቆኑ ረዳት
53) የደካሞች ብርታት
54) መብረቃዊ ልብስ
55) የታዛዥነት አርአያ
56) የመላእክት ዓለም ኮከብ
57) የሕያው አምላክ አገልጋይ
58) የቁጣ አብራጅ
59) ሐዋርያ መልአክ
60) የአጋንንት ፍርሃት
61) የጠዋት ኮከብ
62) የሰራዊተ መላእክት ክብር
63) የሚያቃጥል እሳት
64) የሰማይ ሰራዊት ዓይን
65) የዋህ መልአክ
66) ከዋነኞቹ መልአክ አንዱ
68) ጠላትን የሚያዋርድ
69) መስቀል ተሸካሚ
70) የጽዮን ክብር ጠበቃ
71) በልዑል የተመረጠ
72) የዳግም ምጽአት አርበኛ
73) የቃል ኪዳኑ መልአክ
74) የሰማይ ግዛት አበጋዝ
75) ተወዳጅ መልአክ
76) መንጦላእት ከፋች
77) ባለ መለከት መልአክ
78) የምህረት መልአክ
79) የፍቅር መልአክ
80) የመለኮት መልእክት የሚያስፈጽም
81) እይባን የሚያብስ
82) የእግዚአብሔር ቅጣት መሣሪያ
83) ዐይኑ የሚያበራ
84) ፍርድ ወንበር ፊት አማላጅ
85) የእግዚአብሔር ቅድስና ብርሃን
86) የሕይወት መጽሐፍ ተሸካሚ
87) በለ ራእይ መልአክ
88) በሞት ውስጥ ረዳት
89) ድል አድራጊ
90) የምስኪኖች ወዳጅ
91) ስምህ ድንቅ የሆነ
92) ታማኝ የሕያው ብርሃን
92) የሰማይ ንፅህና ክብር
93) የበረከት ድልድይ
94) የዳንኤል ወዳጅ
95) የመጨረሻውን መለከት አስተዋዋቂ
96) የጻድቃን በረከት አዳይ
97) የክፉዎች ሽብር
98) የኢየሩሳሌም ሰማያዊት ክብር
99) የክርስቶስ ታማኝ አገልጋይ
100) የነፍስ ወዳጅ እና ጠባቂ
ልመናው አማላጅነቱ አይለየን። ይጠብቀን ይጎብኘን ይምራን ይከተለን። አሜን 🙏🙏🙏

❤2
"#የእመቤታችን_120_መጠሪያ_ስሞች"
==========================
1.የቅዱሳን ጥበብ
2.ልዕልት
3.ውድስት
4.የአቤል መዓዛ
5.ማኅደረ ትፍስሕት
6.የሮቤል ተክል
7.የነቢያት ትንቢት
8.የአሴር በረከት
9.የይሳኮር ልደት
10.የሰማዕታት እናት
11.የዮዲት ጥበብ
12.የመላዕክት እኅት
13.የሔኖክ ደግነት
14.የኖኅ መርከብ
15.መዓረገ ሕይወት
16.ምስጢረ ስብሐት
17.የአሚናዳብ ሠረገላ
18.ርግብየ ሠናይት
19.ጽላተ ሕግ
20.ደብተራ ዘትዕይንት
21.የኢያሱ የምስክር ሐውልት
22.የኤልሣዕ ልሕኩት
23.የአሮን ጸናጽል
24.የብንያም የሰርክ መና
25.ሐመልማለ ገነት
26.የንፍታሌም ዘንባባ
27.የላሜህ ዕረፍት
28.የገብርኤል ብሥራት
29.የሣራ ድንኳን
30.የባሮክ በለስ
31.አቁራሪተ መዓት
32.የዮሐንስ አንደበቱ
33.የሄኖክ ራዕይ
34.ጽርሕ ንጽሕት
35.እናተ ብዙኀን
36.መቅደስ
37.ዕፀ ሕይወት
38.በአታ ኪዳነ
39.የአቤል የዋሕቱ
40.የሰሎሞን አክሊል
41.ዳግማዊት ሰማይ
42.የያፌት ርስት
43.ዕዝራ ያያት በሴትነት አምሳል
44.ምሥራቀ ምሥራቃት
45.በዳርቻ የምትቀመጥ የውሃ መንቀል
46.አክሊል
47.የወርቅ ግምጃ
48.የገነት ኩል
49.የናቡቴን ተክል
50.ነያ ሠናይት
51.እምነ ጽዮን ድንግል
52.የጦቢት የዓይኗ ብርሃን
53.ለአብርሃም ገራሕቱ
54.የዘካርያስ መቅረዝ
55.የአልዓዛር እኅቱ
56.የሕዝቅኤል በር
57.የሀጌ ቤት
58.የሴም ምርቃቱ
59.የኢዮብ አምባ መጠጊያ
60.የይስሐቅ ሽቱ
61.የሳሙኤል ሽቱ
62.ብሩሕ ቀስተ ደመና
63.ለዳዊት ወለቱ
65.የዘካርያስ ደስታ
66.ማኅደረ ሰላም
67.ርሕርሕተ ልብ
68.ወለተ ሐና ወኢያቄም
69.ምልዕተ ውዳሴ
70.ቤዛዊተ ዓለም
71.መድኃኒት ይእቲ
72.እግዝትነ ማርያም
73.ምልዕተ ጸጋ
74.የሲና እፀ ጰጦስ
75.ምልዕተ ፍሥሐ
76.የሐዋርያት ሞገስ
77.ምልዕተ ክብር
78.የሐይማኖት መቅደስ
79.የአዳም ተስፋ
80.ሀገረ ክርስቶስ
81.የሴም ዕድል ፈንታ
82. ሶልያና
83.የዮሴፍ አረጋጊ
84.ሙዳየ መና
85.ለሶስና የኀዘን ዕረፍት
86.እኅትነ ነያ
87. የአቤል ሕልውና
88.የደስታ መገኛ
89.ሐመልማለ ወርቅ
90.የኤፍሬም ባራኪ
91.የኤልያስ መሶበወርቅ
92.የሚያኪያስ ኤፍራታ
93.ሙጻአ ፀሐይ
94.ትቅዋመ ዘወርቅ
94.በትረ አሮን
95.ኆኅተ ምስራቅ
96.ወለተ ጽዮን
97.እሙ ለጸሐየ ጽድቅ
98.የሕዝቅኤል አዳራሽ
99.ንጽሕተ ፍቅር
100.አንቀጸ አድኅኖ
101.የእሴይ ሥር
102.ብርሃነ ሕይወት
103.ሀገረ እግዚአብሔር
104.ርግብ ጸአዳ
105.የጌዴዎን ጸምር
106.የሳሙኤል የቅብዐ መንግሥቱ
107.መንፈሳዊ ሀገር
108.የሲሳራን ሞት
109.የዲቦራ ምስጋና
110.ታቦተ ዘዶር
111.እመ ብዙሃን
112. ንጽሕተ ንጹሐን
113.ቅድስተ ቅዱሳን
114.እመ ብርሃን
115.እምነ ጽዮን
116.መዝገበ ቃል
117. ሐረገ ወይን
118.ናዛዚተ ኅዙናን
119.ጽላተ ኪዳን
120.አንቀጸ ብርሃን
የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን አሜን!
==========================
1.የቅዱሳን ጥበብ
2.ልዕልት
3.ውድስት
4.የአቤል መዓዛ
5.ማኅደረ ትፍስሕት
6.የሮቤል ተክል
7.የነቢያት ትንቢት
8.የአሴር በረከት
9.የይሳኮር ልደት
10.የሰማዕታት እናት
11.የዮዲት ጥበብ
12.የመላዕክት እኅት
13.የሔኖክ ደግነት
14.የኖኅ መርከብ
15.መዓረገ ሕይወት
16.ምስጢረ ስብሐት
17.የአሚናዳብ ሠረገላ
18.ርግብየ ሠናይት
19.ጽላተ ሕግ
20.ደብተራ ዘትዕይንት
21.የኢያሱ የምስክር ሐውልት
22.የኤልሣዕ ልሕኩት
23.የአሮን ጸናጽል
24.የብንያም የሰርክ መና
25.ሐመልማለ ገነት
26.የንፍታሌም ዘንባባ
27.የላሜህ ዕረፍት
28.የገብርኤል ብሥራት
29.የሣራ ድንኳን
30.የባሮክ በለስ
31.አቁራሪተ መዓት
32.የዮሐንስ አንደበቱ
33.የሄኖክ ራዕይ
34.ጽርሕ ንጽሕት
35.እናተ ብዙኀን
36.መቅደስ
37.ዕፀ ሕይወት
38.በአታ ኪዳነ
39.የአቤል የዋሕቱ
40.የሰሎሞን አክሊል
41.ዳግማዊት ሰማይ
42.የያፌት ርስት
43.ዕዝራ ያያት በሴትነት አምሳል
44.ምሥራቀ ምሥራቃት
45.በዳርቻ የምትቀመጥ የውሃ መንቀል
46.አክሊል
47.የወርቅ ግምጃ
48.የገነት ኩል
49.የናቡቴን ተክል
50.ነያ ሠናይት
51.እምነ ጽዮን ድንግል
52.የጦቢት የዓይኗ ብርሃን
53.ለአብርሃም ገራሕቱ
54.የዘካርያስ መቅረዝ
55.የአልዓዛር እኅቱ
56.የሕዝቅኤል በር
57.የሀጌ ቤት
58.የሴም ምርቃቱ
59.የኢዮብ አምባ መጠጊያ
60.የይስሐቅ ሽቱ
61.የሳሙኤል ሽቱ
62.ብሩሕ ቀስተ ደመና
63.ለዳዊት ወለቱ
65.የዘካርያስ ደስታ
66.ማኅደረ ሰላም
67.ርሕርሕተ ልብ
68.ወለተ ሐና ወኢያቄም
69.ምልዕተ ውዳሴ
70.ቤዛዊተ ዓለም
71.መድኃኒት ይእቲ
72.እግዝትነ ማርያም
73.ምልዕተ ጸጋ
74.የሲና እፀ ጰጦስ
75.ምልዕተ ፍሥሐ
76.የሐዋርያት ሞገስ
77.ምልዕተ ክብር
78.የሐይማኖት መቅደስ
79.የአዳም ተስፋ
80.ሀገረ ክርስቶስ
81.የሴም ዕድል ፈንታ
82. ሶልያና
83.የዮሴፍ አረጋጊ
84.ሙዳየ መና
85.ለሶስና የኀዘን ዕረፍት
86.እኅትነ ነያ
87. የአቤል ሕልውና
88.የደስታ መገኛ
89.ሐመልማለ ወርቅ
90.የኤፍሬም ባራኪ
91.የኤልያስ መሶበወርቅ
92.የሚያኪያስ ኤፍራታ
93.ሙጻአ ፀሐይ
94.ትቅዋመ ዘወርቅ
94.በትረ አሮን
95.ኆኅተ ምስራቅ
96.ወለተ ጽዮን
97.እሙ ለጸሐየ ጽድቅ
98.የሕዝቅኤል አዳራሽ
99.ንጽሕተ ፍቅር
100.አንቀጸ አድኅኖ
101.የእሴይ ሥር
102.ብርሃነ ሕይወት
103.ሀገረ እግዚአብሔር
104.ርግብ ጸአዳ
105.የጌዴዎን ጸምር
106.የሳሙኤል የቅብዐ መንግሥቱ
107.መንፈሳዊ ሀገር
108.የሲሳራን ሞት
109.የዲቦራ ምስጋና
110.ታቦተ ዘዶር
111.እመ ብዙሃን
112. ንጽሕተ ንጹሐን
113.ቅድስተ ቅዱሳን
114.እመ ብርሃን
115.እምነ ጽዮን
116.መዝገበ ቃል
117. ሐረገ ወይን
118.ናዛዚተ ኅዙናን
119.ጽላተ ኪዳን
120.አንቀጸ ብርሃን
የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን አሜን!
❗ #ሰኔ 21 #ሰኔ_ጐልጐታ ❗
🔷👉#ወሕንጸተ_ቤተክርስቲያን
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔷👉 ሰኔ 21 በሁለት ታላላቅ ምክንያቶች ይከበራል !
❗(1), ሰኔ ጎልጎታ❗
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህች ቀን ልጇን ወዳጇን ጐልጐታ በሚባል ቦታ ላይ እንባዋ እንደ ጅረት እስኪፈስ ድረስ ለኃጥአን ምሕረትን የለመነችበት ዕለት ነው ::
🔵👉 ጌታችንም ልመናዋን ተቀብሎ ‹‹ስምሽን የጠራውን፤ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ፡፡›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል፡፡ በዚህም ምክንያት ሰኔ ጎልጎታ እያልን እናከብራለን። በይበልጥ ለመረዳት የሰኔ ጐልጐታን ይመልከቱ !
❗(2), ሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን❗
ሰኔ 21 ከእመቤታችን #33ቱ በዓላት አንዱ ሲኾን፤ ሕንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል፡፡ ይኸውም በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በአምላክ እናት ስም ሰኔ 20 ቀን ታንጻ ሰኔ 21 ቀን ደግሞ ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበት ነው፡፡
🔴 👉 አናጺውም ደግሞ እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ ቦታው በፊልጵስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።
🔵👉 ጥንተ ነገሩስ (ታሪኩ) እንደምን ነው ቢሉ :-
🔷👉 ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን መደኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ‹‹ሑሩ ወመሐሩ ኵሎ አሕዛበ፤ አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ፡፡›› /ማቴ. 28፥19/ ባላቸው ቃል መሠረት ሐዋርያት በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል::
🔴👉 የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና (ዮሐ. 6፥ 56) አበው ሐዋርያት ቊርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር:: በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን፣ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲህ ይከናወን ነበር፡፡ ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኵራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቊጥር እጅጉን በመብዛቱ /በተለይ ቅዱስ ዻውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ::/ በዚህ ምክንያት መምህራን ሕዝቡን ‹‹ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?›› ቢሏቸው ‹‹እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት ቤት የለን››ሲሉ መለሱላቸው:: ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ዻውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች ቤት ‹‹ለምን አናንጽም?›› ብለው ነበር:: ቅዱስ ዻውሎስ ግን ‹‹ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም›› አለ:: (ለዚህ ነው ዛሬም ሊቀ ዻዻስ ካልፈቀደ ቤተክርስቲያን የማይታነጸው፡፡) ከዚያ ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ዼጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱ ቅዱስ #ዼጥሮስም ‹‹የጌታችን ፈቃዱመኾኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ›› ብሎ አዋጅ ነገረ::
🔴👉 በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔያቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መላአክትን አስከትሎ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ፤እመቤታችን በቀኙ ነበረች፡፡ ኹሉንም ሐዋርያት በሩቅም በቅርብም ያሉትን ደቀ መዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ በሚባል ሃገር ሰበሰባቸው፡፡ ከዚያም በስተምሥራቅ ከከተማ ወጣ ወዳለ ሥፍራ ወሰዳቸው፡፡
🔵👉 በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፡፡ 3ቱንም ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው፡፡ ድንጋዮቹም እንደሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ፡፡ ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፡፡
እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም በእጃቸው እየለመለሙ (እየሳቡ) ቁመቱን 24፥ ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ዕጽብት፥ ግርምት የምትኾን 3 ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን በ52 ዓ/ም ሰኔ 20 ቀን አነጹ፡፡
🔴👉 ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ፤ ጌታችንም በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት፤ ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ፡፡›› ብሏቸው ዐረገ፡፡
🔷👉 በማግስቱ ሰኔ 21 ዕለት ደግሞ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክትን፣ ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዞ ወረደ:: ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ፤ አስቀድሞ ቤተክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ ሥርዐተ ቤተክርስቲያንን አሳየ:: ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስን ከመካከል አቁሞ ‹‹አርሳይሮስ›› ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት (ፓትርያርክ) ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ‹ ‹‹አክስዮስ››(አክዮስ)እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: አክዮስ ማለት በግዕዙ ‹‹ይደልዎ›› በአማርኛው ደግሞ ‹‹ይገባዋል፤ ያስምርለት›› እንደ ማለት ነው::
🔴👉 ጌታችን ይህን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ:: አማናዊት ማኅደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ኾኖ፣ ሐዋርያት ድንግልን ከበው፣ መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቆመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ::
🔵👉 በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይችል ደስታ ተደረገ:: ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን አዘዛቸው:: ‹‹ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም አብያተ ክርስቲያናትን አንጹ፤ ይህችን እለት የሚያከብራትን አከብረዋለሁ::›› ብሏቸው ከድንግል እናቱና ከመላእክቱ ጋር ዐረገ::
ምንጭ :- ስንክሳር ሰኔ 20 _21 እንዲሁም የሰኔ ጎልጎታ የፀሎት መፅሐፍ
🔴⏩የእናታችን ልመናዋ ክብሯ አማላጅነቷ በሁላችን ላይ ይደርብን !!!
ሰኔ 21 / 2018 ዓ.ም

✨ ❖ 【 የጥበብና የምሕረት መልአክ ፦ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል 】 ❖ ✨
#መልአኩ_ቅዱስ_ዑራኤል በእግዚአብሔር ፊት ከሚቆሙት ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን፥ በቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት መሠረት እጅግ ታላቅና ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት ያለው የብርሃን መልአክ ነው።
📖 መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ትውፊታዊ መሠረቱ፦
ስለ ቅዱሳን መላእክት ተልእኮ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር፦
"ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገልገል የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?" 【ዕብ ፩፥፲፬】 በማለት እንደገለጸው፣ ቅዱስ ዑራኤልም የሰው ልጆችን ለማገልገልና ለመጠበቅ ከሚላኩት ታላላቅ መላእክት አንዱ ነው።
ክብሩንና አገልግሎቱን ስናስብ፦
🕊️ የስደት መንገድ መሪ፦ ቅድስት ድንግል ማርያምን ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ የመራ፣ በበረሃው ሐሩርና ድካም ያጸና ነው።
🩸 የድኅነት ጽዋን የያዘ፦ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በቀራንዮ አደባባይ በተሰቀለ ጊዜ፣ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ ታላቅ መልአክ ነው።
📜 የጥበብና የምሥጢር መልአክ፦ * ምሥጢረ ሰማይና እውቀትን ሁሉ ለነቢዩ ሄኖክ የገለጸለት፣ የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃን የሚመራ መሆኑን ያሳወቀው እርሱ ነው።
ኢትዮጵያዊውን ታላቅ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በርካታ ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዲደርሱ ያገዘ፣ የረዳና የዕውቀት ጽዋን ያጠጣ መልአክ ነው።
የቅዱስ ዑራኤል ምልጃና ጸሎት በረከት አይለየን! የጥበብና የማስተዋልን ጽዋ ያጠጣን! ሀገራችንንና ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን። አሜን!!! 🙏

ሰኔ 23/2018 እንኳን ኣደረሳችሁ ለ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮረጊስ።
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
#ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ ብሩህ ሐረገ ወይን ፀሐይ ማለት ነው ሊቀ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በጥር 20 ቀን በ 277ዓ/ም ተወለደ ሃገሩ ፍልስጤኤም ሲሆን ልዩ ስሟ ልዳ ይበላል አባቱ ዞሮንቶስ አንስጣስዮስ ይባላል ከልዳ መኳንንት ተሹሞ ይኖር ነበር እናቱ ቴዎብስታ አቅሌስያ ትባላለች ማርታና እስያ ተብለዉ የሚጠሩ እህቶች ነበሩት
👉10 አመት ሲሞላው አባቱ ስለ ሞተ ሌላ ደግ ክርስትያናዊ መስፍን ከቤቱ አሳደገው በጦር ሃይልም አሰለጠነው 20 ዓመት ሲሞላዉ የ15 ዓመት ልጅ ሊያጋቡት ሲሉ #እግዚአብሔር የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ #ቅዱስ_ጊዮርጊስም ወደ ቤሩት ሄደ
👉በቤሩት ደራጎን ያመልኩና ሴት ልጃቸውን ይገብሩለት ነበርና በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ህዝቡን ወደ አምልኮተ #እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል #እኔ_ክርስትያን_ነኝ_በኢየሱስ_ክርስቶስ አምናለሁ አለው
👉እርሱንም ማንነቱ ከተረዳ በኋላ አንተ እማ የእኛ ነህ በ10 አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የእኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ አለው #ቅዱስ_ጊዮርጊስም ሹመት ሽልማትክ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬን #ኢየሱስ_ክርስቶስን አልክድም አለ በዚህ ጊዜ እጅግ ተናዶ መከራን አጸናበት
👉እርሱ ግን ይህን ከሀዲ እስካስፈራው ድረስ ነፍሴን አትውሰድ በማለት #እግዚአብሔርን ለመነና እንደ ጸሎቱ ተደረገለት በእምነቱ ጽናት ሰው ሊሸከመዉ የማይቻለውን መከራ የተቀበለ ቅዱስ #ሰማእት ነው
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሰማእቱ ረድኤት በረከት ያሣትፈን የኢትዮጵያ ጠባቂ ሰማዕቱ ቅዱስ #ጊዮርጊስ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅ ዘንድ በምልጃህ በፀሎትህ አስበን።"አሜን" ✝️ 💒