satenaw
4.67K subscribers
3.48K photos
177 videos
5 files
1.31K links
🔖

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
Download Telegram
ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በአደጋ በሞቱ ምዕመናንን የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽ በአ/ምንጭ ከተማ በሚገኙ ሁሉም አድባራትና ገዳም ጸሎተ ፍትኃት እንዲደረግ አባታዊ መመርያ ሰጥተዋል።
***

ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በአርባምንጭ ዝጊቲ አቡነ ግብር መንፈስ ቅዱስ የመጋቢት አቦ የንግስ በዓል አክብረው በመመለስ ላይ ሳሉ በተከሰተ የመኪና አደጋ ህይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ላስተናገዱት ከሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተጉዘው በመጡ ምዕመናንን የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽ

የእግዚአብሔር ፍቃድ ሆኖ በአደጋው ምክንያት ከሥጋ ድካም ላረፉ ወንድም እና እህቶች በአርባምንጭ ከተማ በሚገኙ ሁሉም አድባራት እና አንድ ገዳም ጸሎተ ፍትኃት እንዲደረግ አባታዊ መመርያ ሰጥተዋል።

አምላካቸውን ብለው ታምነው ከቤት ለወጡ ነፍሳት ልዑል እግዚአብሔር ዕረፍት ይስጣቸው!!!

ጻድቁ በምልጃ ይቁምላቸው
#Earthquake

ዛሬ ምሽት 3:55 ገደማ ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ አካባቢ ተከስቷል።

በአዲስ አበባ ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ጠንከር ያለ ንዝረትም ተሰምቷል።
satenaw
Photo
አፈትላኪ መረጃ!

ታንክ እና ድሮን ታጥቀን ክላሽ ብቻ በያዘ ፋኖ ከባድ ጉዳት ደርሶብናል፡ ሰራዊታችንም የመዋጋት ሞራሉና አቅሙ ተዳክሟል ሲሉ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል መሐመድ ተሰማ ተናገሩ!

ከብር ሸለቆ፣ ከገርባሣ እና ከሐረር ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያዎች የተወጣጡ የምስራቅ ዕዝ ወታደራዊ አዛዦችና መስመራዊ የጦር መኮነኖች እንዲሁም የእስታፍ አባላት የዕዙ ጦር ስላለበት ወቅታዊ ሁኔታ ከሰሞኑ በፕላዝማ የግምገማ መድረክ ማካሄዳቸውን ወታደራዊ ምንጮች ተናግረዋል።

በፕላዝማ በተካሄደው በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ የሆኑት ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ክፉኛ ተበሳጭተው የበታች አመራሮቻቸውን መዝለፋቸውን ጭምር ምንጮቻን ጠቅሰዋል።

ሌተናል ጄኔራሉ" ዘመናዊ የሆኑ ታንክና መድፎችን እንዲሁም ድሮን እና ሌሎች ሜካናይዝ መሣሪያዎችን ታጥቅን እንዴት ከድሽቃና ብሬን የዘለለ የቡድን መሣሪያ ያልያዘ ኃይል በዚህ ልክ ሊያፍረከርከን ይችላል በሚል ለመስመራዊ የጦር መኮነኖችና ለክ/ጦር ዘመቻ መሪዎች ቁጣ አዘል ጥያቄ ማንሳታቸው ነው የታወቀው።

በግምገማ መድረኩ ላይ፡ በዕዙ ስር ከነበሩ የአማራ ተወላጅ ወታደሮች መካከል 85% በላይ የሚሆኑ ወታደሮች ስርዓቱን በመክዳት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸውን የሚያመለክት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፡ ይሄ ሪፖርትም ሌተናል ጄነራሉን ክፉኛ አስቆጥቷቸዋል ነው የተባለው።

ሌተናል ጄነራሉ በተለይ የዕዙ የሰው ሀብት ክፍል እና አስተዳደር ክፍል አመራሮችን በስም ሁሉ እየጠቀሱ "ይህ ሁሉ ወታደር እስከሚከዳ ምን እየሰራችሁ ነበር?" የሚል ቁጣ አዘል ጥያቄ ማንሳታቸውን ወታደራዊ ምንጮች ገልፀዋል።

መከላከያ ሰራዊቱ ፋኖን ለማጥፋት የሚወስደውን እርምጃ ፋኖ ደግሞ በፀረ ማጥቃት ስልት እየመከተና አፀፋዊ ምላሽ እየሰጠ ስላለበት ሁኔታ እና የፋኖ ኃይል ወቅታዊ ወታደራዊ አቋም እንዲሁም የምስራቅ ዕዝ አባላት የደረሰባቸውን የሰብአዊና የቁሳዊ ኪሳራን በሚመለክት በሰፊው በተዳሰሰበት በፕላዝማ በተካሄደ በዚህ የግምገማ መድረክ፡ እንደ ዕዝ መፍትሔ ይሆናሉ የተባሉ የተለያዩ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ተሞክሯል ነው የተባለው።

በቀጣይ በሚደረጉ ወታደራዊ ዘመቻዎች፡ የፋኖ ሎጅስቲክ ማከማቻ አከባቢዎችና የቡድን መሣሪያዎቻቸው በልዩ ሁኔታ ዋና ኢላማ መደረግ እንዳለባቸው ሌተናል ጄነራል መሐመድ ተሰማ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የፋኖ አዛዦች የሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች በልዩ ሁኔታ ተጠንተው በድሮንና በሌሎች ከባባድ መሣሪያዎች የታገዘ የተሳካ የማጥቃት ዘመቻ መክፈት፣ ከከተማ እስከ ገጠር ያለውን የፋኖን ሴል ለመበጣጠስ ከፋኖ ከድተው የሚወጡ ታጣቂዎች ካሉ እነሱን መጠቀም፣ እንዲሁም አሁን በፋኖ አደረጃጀት ውስጥ የሚታዩ ልዩነቶችን በሚዲያ ሰራዊቱ በኩል አጉልቶ ማውጣት የሚል አቅጣጫም መቀመጡን ወታደራዊ ምንጮች ገልፀዋል።

በተጨማሪም በውጊያ ጊዜ የኃይል ማዛባትና(ትንሽ ኃይል ከፊት ለፊት በመላክ በሌላ አቅጣጫ የከበባ ስራ መስራት)፣ ስቦ የመደምሰስ እና ኔትዎርክ አጥፍቶ ጨለማን ተገን በማድረግ ፋኖ ካለበት ተስቦ ደርሶ ማፈን፡ እንዲሁም የሽምቅ ውጊያ ስልትን መጠቀም በሚል የተሰጠው የመፍትሔ ሃሳብ በአስቸኳይ እንዲተገበር አቅጣጫ ተቀምጧል ተብሏል።

በቀጣይ ዕዙ በሚያካሂደው ዘመቻ የሽምቅ(ደፈጣ) ጥቃትን በሰፊው ለመተግበር ከቲም ምክትል አዛዥ እስከ ክ/ ጦር ዘመቻ መሪ ድረስ ወደ ብርሸለቆ እና ገርባሣ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች ገብተው የተሃዲሶ ስልጠና እንዲወስዱ መመሪያ ተላልፎ ወደ ስራ ተገብቷል ሲሉ ስለ ግምገማ መድረኩ መረጃ ያጋሩን ወታደራዊ ምንጮች ጨምረው ገልፀዋል።

ዘገባው የመረብ ሚዲያ ነው!

ተጨማሪ መረጃ

https://youtu.be/JZtHnflqrJI?si=dExxtzd3wVebnfiG
ፍርድ ቤቱ በእነ ዮሐንስ ቧያለው የክስ መዝገብ ተከሳሾች ላይ አቃቢ ህግ ያቀረባቸው ምስክሮችን ማድመጥ ጀመረ!

በዛሬው ዕለት በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛና 2ተኛ ህገ-መንግስታዊ ና ፀረ -ሽብር ችሎት አቃቤ ህግ በእነ ዮሐንስ ቧ ያለው የክስ መዝገብ  በሚገኙ ተጠርጣሪዎች ላያ ያቀረባቸውን ምስክሮች ፍርድ ቤቱ ማድመጡን ከተከሳሾቹ ጠበቆች መካከል ሰለሞን ገዛኽኝ ተናግረዋል፡፡

በመዝገቡ ከተዘረዘሩት 52  ተከሳሾች  መካከል 16ቱ ብቻ ክሳቸውን በችሎት ቀርበው እየተከታተሉ እንደሚገገኙ ያስታወሱት ጠበቃው፤ አቃቢ ህግ አሉኝ ካላቸው 21 ምስክሮች መካከል 4ቱን በችሎቱ  የዛሬ ውሎ ማቅረቡን ገልጸዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ  የአቃቢ ህግ ምስክሮችን  የማድመጥ ሂደቱን እስከ መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም  እንደሚቀጥል ከተከሳሾቹ ጠበቃ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
via asham tv
የዶናልድ ትራምፕን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮን ከስርጭት አስወጣ
የዶናልድ ትራምፕን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ተከትሎ የአሜሪካ ድምጽ ሰራተኞች አስገዳጅ አስተዳደራዊ እረፍት እንዲወስዱ በመደረጋቸውና፣ የኮንትራት ሰራተኞች ደግሞ ከስራ በመሰናበታቸውን ሳብያ ስርጭቱ መገታቱ ተገልጿል።
በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 6 ሰዓት በኋላ የጣለው ዝናብ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የመንገድ መዘጋጋት ማስከተሉን አሐዱ በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውሮ መታዘብ ችሏል፡፡

ዝናቡ በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች የትራፊክ መጨናነቅን ያስከተለ ሲሆን፤ አሽከርካሪዎች የተከለከሉ የኮሪደር የእግረኛ መንገዶችን ጨምሮ አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ላይ እንደሚገኙም ለመመልከት ችሏል፡፡

እናንተስ በየት የት አካባቢዎች በዝናቡ ምክንያት የተከሰቱ የመንገድ መዘጋጋቶች አጋጠሟችሁ?  አአስተያየት መስጫ ሳጥኑ ላይ ሃሳባችሁን አካፍሉን!
satenaw
Photo
"የዘመቻ አንድነት'' ድሎች በጎንደር ግንባር

        መጋቢት 10/2017 ዓ.ም

ለነፃነትና ለአንድነት ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በጎንደር ሁሉም ማዕዘናት በፋሽስቱ ዓብይ አህመድ ሰራዊት ላይ የተጀመረው ወታደራዊ ማጥቃት በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።

የዘመቻው አካል የሆነው የጎንደር ሰ/ምዕራብ ቀጠና በተለይም በጅንግር እና መሬና በጠላት ላይ በተወሰደ ወታደራዊ ማጥቃት 06 ብሬን፣ 01 ስናይፐርና ከ112 በላይ ነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ፣ ከ4000 በላይ ተተኳሽ ጥይት፣ 81 ፈንጅዎች፣ ከጠላት የተማረከ ሲሆን ከ116 በላይ ጠላት ተደምስሷል።

35 ጠላት በህይወት ተማርኳል።

   የጎቤ ክ/ጦር፣ የተከዜ ክ/ጦር፣ የዘራይ ክ/ጦር፣ የሰ/አምባራስ ክ/ጦሮ የድሎ ባለቤቶች ናቸው።

    ከጠዋቱ 11:00 ሰዓት የጎንደር ዙሪያ ወረዳ መቀመጫ ማክሰኝት ከተማ የመሸገው የጠላት ሀይል ላይ ማጥቃት የከፈተው የጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር አካል ብርጌድና ሻለቆች፣ ዞዝ አምባ ንጉሥ እና የጥቁር አንበሳ ብርጌድ ከጎንደር ባህ/ዳር ዋና መንገድ በመቁረጥ ከተማዋን የተቆጣጠረ ሲሆን የጠላትን ማጎሪያ እስር ቤት በመስበር እስረኞችን ነፃ አድርጓል።

በተጨማሪ ከ30 በላይ ሙት እና ከ20 በላይ ቁስለኛ ሁኗል።

በደበቡባዊ የጎንደር ቀጠና ሰፊ ቀጠና የሸፈነ አውደ ውጊያ እየተደረገ ሲሆን የሜ/ጀ/ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ኢንጂነር ስመኘው ተዋርዋሪ ክፍለጦር፣ እና መብረቁ ክፍለጦር፣  በአምበሳሜ፣ ወረታ፣ ጋሳይ፣ ዓለም በር ፣ ጎላሀ እና አዲዘመን የሰፈረው የጠላት ሀይል ሙሉ በሙሉና በከፊል የተደመሰሰ ሲሆን የወረደ መቀመጫ የሆነችውን አምበሳሜ ከተማ ሰፍሮ የነበረው ጠላት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል። በወገን ቁጥጥርም ትገኛለች።

በዚህ አውደ ውጊያ ግንባር ከ160 በላይ የተደመሰሰ ከ95 በላይ ቁስለኛ ሁኗል።
ምርኮኛ፦ ከጠላት ከ100 በላይ የጦር መሳሪያ ተማርኳል። በቀጠናው የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር አካል ክ/ጦሮች
1-ጉና ክ/ጦር
2-ሜ/ጀ/ውባን አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር
3-ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር
4-ፋሲል ክ/ጦርና
5-ኢ/ስመኘው ክ/ጦሮች የድሉ ባለቤቶች ናቸው።

በቋራ እና መተማ ግንባር፦ በዘመቻ አንድነት በተሰራ ልዩ ኦፕሬሽን በምዕራብ ጎንደር መተማ ወረዳ ሽንፋ ከተማ ገበያ ማዕከል አካባቢ ስብሰባ ባደረገበት ብሶት የወለዳቸው የአማራ ተወላጆች በቀረበላቸው አጀንዳ ዙሪያ ማለትም "የአማራ ሕዝብን እናጥፋ" በማለታቸው በዚህ የተናደዱ ወታደሮች በቦንብ 39 ሲገድሉ፤ 50 አቁስለዋል። በተጨማሪ በቋራ ወረዳ በሙር እርስበእርሳቸው ከፍተኛ እልቂት ላይ ናቸው።

ጠቅላላ በጎንደር ግንባር በዘመቻ አንድነት የተገኙ ድሎች

የተደመሰሰ 345
የቆሰለ 155
ክላሽ፦ 212
ብሬን፦ 6
ስናይፐር፦ 1
ፈንጂ፦ 81

አሁንም በቀጠናው ዘመቻ አንድነት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

         አንድነት ኃይል ነው!
ድል ለአማራ
  ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር
      ጎንደር /አማራ/ ኢትዮጵያ
satenaw
Photo
A luta continua....!

*

አመሠግናለሁ የተከበሩ አፈ-ጉባዔ፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩንም ለጊዜዎት አመሠግናለሁ!

ጥያቄየንም እንደሚከተለው በንባብ አቀርባለሁ፦

ሀገራችን ዛሬ ያጋጠሟት ውስብስብ ችግሮች፣ ተግዳሮቶች እና ስጋቶች ፖለቲካ ወለድ ሲሆኑ፣ መፍትሔያቸውም ፖለቲካዊ እንጂ የጠመንጃ አፈሙዝ ሊሆን አይችልም። በድህነት አዙሪት (Vicious Circle of Poverity) ውስጥ የኖረች ሀገር ባለፉት 7 የብልጽግና አገዛዝ አመታት ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የከፋ የጸጥታ እና የደህንነት ቀውስ አዙሪት (Cycle of Security Crisis)፣ እንዲሁም ማባሪያ የሌላቸው አውዳሚ የርስ በርስ ጦርነቶች ውስጥ አስገብቷታል። ኢሕአዴግ አንባገነናዊ ልማታዊ አገዛዝ ነበር። ወደ ብልጽግና ያደረገው መለወጥ (metamorphosis) ደግሞ የሙሉ ጊዜ ጦረኛና እልቂት ጠማቂ አገዛዝ እንዲሆን አድርጎታል።

በመደማመጥ እና በሰጥቶ መቀበል መርሕ ላይ ተመስርተን አገራዊ ልዩነቶቻችን በማጥበብ ሁሉን አካታች ወደሆነ ማሕበረሰባዊ መግባባት እና ፓለቲካዊ ስምምነት (political settlement) ከማምራት ይልቅ ብልጽግና ፓርቲ በሚከተለው ጠቅላይ አገዛዝ (totalitarian leadership) ምክንያት ሠላም ከራቀን ከራረምን።

ባለፉት 6 ዓመታት በኦሮምያ፣ በትግራይ፣ አማራና አፋር፤ ዛሬም ድረስ ደግሞ በአማራና በኦሮምያ ክልሎች በቀጠለው ጦርነት የድሃ አርሶአደር እና ከተሜው ልጆች በሁሉም በኩል እንደቅጠል እየረገፉ ነው። ማቆሚያ በታጣላቸው የእርስ በርስ ጦርነቶች በትሪሊየን የሚቆጠር የአገር ሀብት ንብረት እየወደመ እንደሆነ «የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ አማካሪ ቡድን» በሰራው ‶Economy Wide Estimation of the Northern Ethiopian War Damage″ የሚል ጥናት በአንድ ዓለም አቀፍ ኮንፈርረንስ ላይ ቀርቦ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ያደረሰው ጉዳት ግምቱ 32 ቢሊየን ዶላር እንደሚጠጋ ተተምኗል፡፡

እንዲሁም የዓለም ባንክ December 2022 ″Ethiopia Damage and Needs Assessment (DaNA)" ብሎ ባወጣው ሪፓርትም በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የደረሰው ጉዳት ግምት 28 ቢሊየን ዶላር ያደርሰዋል፡፡ አማካይ ግምቱ 30 ቢሊየን ዶላር ነው፡፡ ባለፉት 6 አመታት እስከ ዛሬ ድረስ በአማራ፣ በኦሮምያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በደቡብ፣ በጋምቤላ፣ በአፋርና በሶማሊ ክልሎች እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች እና የእርስ በርስ ግጭቶች የጉዳት ግምት ከሰሜኑ ጦርነት ጋር እኩል አድርገን 30 ቢሊየን ዶላር ምሁራዊ ግምት ብንወስድ ጠቅላላ ግምቱ ወደ 60 ቢሊየን ዶላር ወይም በሰሞኑ የባንክ ምንዛሬ በ130 ብር ሲሰላ 7 ነጥብ 8 ትሪሊን ብር ገደማ ነው፡፡ በዘንድሮው በጀት ልክ ቢሰላ ደግሞ የቀጣይ 8 ዓመት የአገራችን በጀት የሚሆን ሃብትና ንብረት በጦርነቶችና ግጭቶች አውድመን እንዲሁም በሚሊየን የሚቆጠሩ ወጣቶችን ጭዳ አድርገን ዛሬም የጦርነት ነጋሪት እየጎሰምን ቀጥለናል፡፡

የዚህ የርስ በርስ መጠፋፋት ጉዞ ውጤትም የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ባወጣው የ2024 Global Multidimensional Poverity Index (Poverity Amid Conflict) ሪፓርት እንዳመላከተው 72 በመቶ ወይም 86 ሚሊዮን ኢትዮጵዊያን በድህነት እንደሚኖሩ ይፋ አድርጓል፡፡ የውጭ ምንዛሬ ለውጡንና የኮሪደር ስራ ተያይዞ መኖሪያና እና የንግድ ቤታቸው የፈረሰባቸው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ችግር ላይ የወደቁ ዜጎችም አሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እንኳን ከኑሮ መሰረታቸው የተነቀሉት ይቅርና ስራ ሰርተው በላባቸው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጭምር የኑሮ ውድነቱን መቋቋም እና ልጆቻቸውን ማሳደግ ተስኗቸዋል፡፡ በዚህ የድህነት ምጣኔ እና የኑሮ ውድነት ላይ የተጨመረው የጦርነት አዙሪት ለሀገራችን ከፍተኛ ብሔራዊ የደህንነት አደጋ አዝሏል የሚል ስጋት አለኝ።

በሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ረገድም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ ላይ በቅርቡ ባወጣው "Update on the Human Rights Situation in Ethiopia, June 2024" ሪፖርት በሀገራችን ላይ እየደረሰ ያለውን ከፍተኛ ሰብአዊ መብት ጥሰት በዝርዝር አቅርቧል። ሪፖርቱ እንደ ሀገር የማያወላዳ ትኩረት እና አፋጣኝ እርምጃ እንድንወስድ የሚሹትን የተንሰራፉ እና ስልታዊ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች የደረሱበትን አሳሳቢ ሁኔታ ያሳያል። በሪፖርቱ የተካተቱ ጉዳዮች ልብን የሚሰብሩ እና በጣም አሳሳቢ ናቸው። ለምሳሌ በፈረንጆቹ 2023 ብቻ በተፈጸሙ 594 የመብት ጥሰቶች በትንሹ 8253 ተጎጂዎች ተመዝግበዋል። ከነዚህ ውስጥ 1106 ሲቪሊያኖች በአማራ ክልል፣ 366 ሲቪሊያኖች በኦሮምያ ክልል ተገድለዋል። በ5 ወራት ብቻ ከ250 በላይ ሰላማዊ ሰዎች በድሮን ተገድለዋል። ከላይ ለማሳያ በሪፖርቱ የተካተተው የተጎጂ ሲቪሎች ቁጥር ሲሆን፣ actual የተጎጂዎቹ ቁጥር ከዚህም የሚበልጥ ነው። እነዚህ የተንሰራፉ የመብት ረገጣዎች እና ከህግ ውጪ ግድያዎች በፈረንጆቹ 2024/25 ዓመትም ተባብሰው ቀጥለዋል። የድሮን ጥቃት ዛሬም በአማራ ክልል ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ህጻናትን ጨምሮ ሲቪሊያኖች እየተገደሉበትና የሲቪሊያን ተቋማት እየፈረሱ እንደሆነ ቢቢሲን ጨምሮ በአለማቀፍ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡

በተጨማሪም ሪፖርቱ የዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ አስፈላጊ ምሰሶዎች በሆኑት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመሰብሰብ እና የመደራጀት መብት ላይ ከፍተኛ ገደቦች መደረጋቸውን በአጽንኦት አመላክቷል። ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች እና ሰላማዊ ዜጎች እውነትን የመናገር መብታቸውን በመጠቀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን በመጠየቃቸው ብቻ ማስፈራራት፣ እንግልት፣ ስደት፣ እስራትና አለፍ ሲልም እገታና አስገድዶ ስወራ ይደርስባቸዋል ይላል። ለምሳሌም፡- ያለመከሰስ መብት ያላቸው አማራ የሆኑ የፌደራል እና የክልል የሕዝብ እንደራሴዎች የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና ዶ/ር ካሳ ተሻገር ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ተይዘው ለ20 ወራት ታስረው ይገኛሉ። የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የሆኑት የአብን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማሪያም፣ የኢዜማው ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደ ከታሰሩ ሁለት ዓመት ሊሞላቸው ነው፡፡

በተመሳሳይ በርካታ አማራ ጋዜጠኞች (ጋዜጠኛ መስከረም አበራ፣ ገነት አስማማው፣ ጎበዜ ሲሳይ፣ አባይ ዘውዱ፣ ዳዊት በጋሻው፣ ቴዎድሮስ ንብረት)፣ ምሁራን (ዶ/ር ወንዶሰን አሰፋ፣ ረ/ፕ ሲሳይ አውግቸው፣ ፕ/ር ማዕረጉ ቢበይን፣ ዶ/ር ዘሪሁን ባህሪው፣ ዶ/ር መሰረት ቀለመወርቅ፣ ዶ/ር ገብረአብ አለሙ፣ ረ/ፕ ዳኜ አበበ)፣ የህግ ጠበቃዎች (ጠበቃ አለልኝ ምህረቱ፣ ጠበቃ ኤርምያስ መኩሪያ)፣ የመንግስት ሰራተኞች እና ወጣቶች በአጠቃላይ 182 የሚደርሱ አማራዎች በ25 መዝገቦች በሽብር እና በህገ መንግስታዊ ወንጀሎች ተከሰው ያለ ፍትሕ ለ 20 ወራት ፍርድ ቤት ይመላለሳሉ። «የዘገየ ፍትህ እንደተነፈገ ይቆጠራል» እንዲሉ የፍትህ ስርዓቱ ዛሬም ቀልጣፋ እና ፍትሃዊ ውጤት ማምጣት እንዳልቻለ አመላካች ነው፡፡ በኢህአዴግ ጊዜ ይደረግ እንደነበረው ሁሉ ፍርድ ቤት በተደጋገሚ ይመላለሳሉ፡፡ ፍትህ ግን እንደሰማይ ርቋቸዋል፡፡ በጦር ሜዳ እያዋጉ ተይዘው የታሰሩ የሕወሓት አመራሮችን በአጭር ጊዜ የፈታ መንግስት በገዢው ፓርቲ አሰራሮች ላይ የሰላ ትችት የሚሰነዝሩ አማራዎችን ይሄን ያህል ጊዜ
satenaw
Photo
ያለፍርድ ማሰር የገዢውን ፓርቲ አማራ ጠል ፖሊሲ በግላጭ የሚያሳይ ነው። የአማራ ክልሉን ጦርነት ተከትሎ ለአስር ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት ባለፉት 20 ወራት ውስጥም በሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች መታወቂያቸው እየታየና በብሔር እየተለዩ (ethnic profiling) ታስረዋል፣ ኢ-ሰብአዊ ለሆኑ አያያዞች መጋለጣቸውንም መንግስታዊ የመብቶች ተቋም ኢሰመኮ እና አለማቀፍ ድርጅቶች ጭምር ገልጸውታል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተጠናቀቀ በኋላም ባለፈው ወር በመዲናችን እስከተካሄደው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ድረስ የአማራ ልጆች ጅምላ እስር አልቆመም፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት ውስጥ የተካተቱት አብዛኛዎቹ የመብት ጥሰቶች መንግስታዊ ተቋም በሆነው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በ2016 ዓ/ም ባወጣቸው በርካታ የምርመራ ሪፖርቶቹ ጭምር የተረጋገጡ ናቸው። በተጨማሪም ኢሰመጉ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ ሲፒጄ፣ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት፣ የአውሮፖ ሕብረት እና በአዲስ አበባ የሚገኙ የምዕራባውያን ኢምባሲዎች ባወጧቸው ሪፖርታቸው እና መግለጫዎቻቸው አሳሳቢነታቸውን ገልጸዋል። መንግስታዊው ኢሰመኮ ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርትም በአዲስ አበባ፣ በአማራ እና በኦሮምያ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ዜጎች የአስገድዶ መሰወር (Forced Disappearance) ሁኔታን ሊያቋቁም በሚችሉና ያሉበት ሳይገለጽ በተራዘመ እስር ውስጥ እንደሚገኙ አመላክቷል፡፡

የፓለቲካ ምህዳሩ ተዘግቶ ምንም አይነት የተቃውሞ ድምጾች እንዳይሰሙ ከፍተኛ የመብቶች እመቃ እየተፈጸመ ሲሆን፤ በብልጽግና የምግብ ዋስትና ፓኬጅ ውስጥ ያልተካተቱ ጥቂት የተቃውሞ ድምጾችም suffocate ተደርገው በደመነፍስ ለመተንፈስ እየተፍጨረጨሩ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ዓለም አቀፍ እና አገር አቀፍ ተቋማት የአገራችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ አሳስቧቸው ሪፖርታቸውን የሚያወጡት የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ትኩረት አድርገው ችግሮች እንዲፈቱ እንዲያደርጉ እና መንግስትዎ አፋጣኝ ርምጃ ወስዶ እንዲስተካከሉ እንዲሁም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ነው፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም አንድም ቀን እንኳ ሁኔታውን በተመለከተ በምክር ቤቱ ስብሰባዎቹ አጀንዳ አድርጎ አለመወያየቱ፣ሁኔታውን በተመለከተም በአስፈጻሚው ላይ በቂ ክትትል እና ቁጥጥር አለማድረጉና በሕገ መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሠረት አንድም የእርምት ርምጃ አለመውሰዱ በታሪክ እና በትውልድ ፊት ተጠያቂ የሚያደርገው ነው።

የተከበሩ አፈ ጉባዔ፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ከላይ ያለውን የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ የተመለከተ ረጅም ትችት ያቀረብኩት ለጥያቄየ መቅድም እንዲሆን እንጂ መቼም ብልጽግና ስለአገራዊ ችግሮቻችን "አላይም፣ አልሰማም፣ አልናገርም" ካለ ውሎ ማደሩ ጠፍቶኝ አይደለም። ብልጽግና የሚታየው ጦርነት፣ የሚሰማው የቄስ ሞገሴዎችን ከንቱ ውዳሴ፣ ከተናገረም ወይ ደረቅ ፕሮፓጋንዳ ወይም ደግሞ ነጭ ውሸት ነው። በመካከል የከሱ እና የመነመኑ እውነቶች የሉም ማለት ግን አይቻልም።

ወደ ጥያቄየ ስገባ ባለፉት 7 ዓመታት እና ከዚያም በፊት ባሉ አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በአማራ፣ በኦሮምያ፣ በአፋር፣ በትግራይ፣ በደቡብ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ እና ሌሎችም አካባቢዎች ለተፈጸሙ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች (Gross Human Rights violations)፣ በሰብዓዊነት ላይ ለተፈጸሙ ወንጀሎች (Crimes against Humanity)፣ የጦር ወንጀሎች (War Crimes) እንዲሁም የዘር ማሳሳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች (Ethnic Cleansing and Genocide) መፈጸማቸውን መንግስትዎ እውቅና የማይሰጠውና ሃላፊነት የማይወስደው እንዲሁም ገለልተኛ አለምአቀፍ ምርመራዎች እንዲካሄድ የሚደረጉ ጥሪዎችን የሚያጣጥለው ለምንድን ነው? የሽግግር ፍትህ ከመጀመሩ በፊት እነዚህ ወንጀሎች በገለልተኛ ዓለምአቀፍ ተቋማት ተመርምረው የተፈጸሙ ወንጀሎች እንዲለዩ (atrocity determination) እና በስማቸው እንዲጠሩ መደረግ አለበት፡፡ ከዚያ ጥፋት ፈጻሚዎችን ለፍርድ ማቅረብ እና ተጎጅዎችን መካስ ወዘተ… የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ አካል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

እንደ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አይነት ሂደቶች የሀገራችንን ችግሮች እንዲፈቱ ከልብ የምንፈልግ ከሆነ ደግሞ በአማራ እና በኦሮምያ ክልል እየተካሄዱ ያሉት ደም አፋሳሽ እና አውዳሚ የወንድማማቾች ጦርነቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ (Silencing the guns) መደረግ አለበት። የሠሜኑን ጦርነት እንዲቆም ያደረገው ዋነኛው አካል የፌደራል መንግስቱ ሲሆን አሁንም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ጦርነቶችን የማስቆም ተቀዳሚ ሀላፊነቱ፣ የሞራል እና የታሪክ ተጠየቅም የሚወድቀው በፌደራል መንግስቱ ላይ ነው። መንግስታዊ ያልሆኑ ተፋላሚዎች ኃላፊነታቸው በሁለተኛ ደረጃ የሚታይ ነው።

ዘመናዊ የሀገራችን ታሪክ ብናይ እንኳን ለመቶ ዓመታት የፓለቲካ ችግሮችን በጠመንጃ አፈሙዝ ለመፍታት የሄድንበት እና ዛሬም የቀጠልንበት መንገድ የአለም ጭራ፣ የሌሎች ሀገራት መሳቂያ መሳለቂያ ያደረገን ችግር ሲሆን ከዚህ የግጭትና የጦርነት አዙሪት በአስቸኳይ ካልወጣን እንደ ሀገር ለመቀጠል የምንችልበት ምንም ማስተማመኛ የለንም። በዚህ ረገድ መንግስት ዋነኛ ኃላፊነት ይኑርበት እንጂ የአማራ ፋኖ ኃይሎች እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትም ጦርነቶችን ለማስቆምና የሚታገሉላቸው ዓላማዎች በሠላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ማድረግ የሚቻልባቸውን ዕድሎች ሁሉ አሟጠው እንዲመለከቱ፤ ለሰላም ለሚደረጉ አገራዊም ሆነ አለማቀፋዊ ጥሪዎች እና ጥረቶች መሳካትም የድርሻቸውን እንዲወጡ በወከለኝ የባሕር ዳር ከተማ ሕዝብ፣ በመላ ኢትዮጵያዊያን እና በራሴ ስም ጥሪ ማቅረብ እፈልጋለሁ።

አመሰግናለሁ!