የማህበሩ የስራ አመራር ቦርድ እንዲሁም በዋና መ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅን ጨምሮ የተለያዩ የሥራ ክፍል ሥራ አስኪያጆች በተገኙበት የማህበሩን ልዩ ልዩ የሥራ ክፍል መመርያዎች አዲስ ለተቀላቀሉት የቦርድ ኃላፊዎች ገለጻና ማብራርያ በህዳር 03 2017 ዓ.ም በማህበሩ ዋና መ/ቤት ተደርጓል ፤
👍2🤝1
በህዳር 07 ቀን 2017 ዓ.ም ከተለያዩ ቅርንጫፎች ለተመረጡ የማህበሩ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የምክክር ጊዜ በማህበሩ ዋና ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተደርጓል፤
በዕለቱም የተገኙ አባላት ለማህበሩ መጠናከር እና መሻሻል የሚገባቸዉን አስተያየት እና ጥያቄ አቅርበዋል ፤ ከማህበሩም የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ እና ማብራርያ ተሰቷቸዋል፤
በተጨማሪም የዕጣ/አክሲዮን መጠናቸዉን፣ ቁጠባቸዉን ለመጨመርና ለሌሎች ሰዎች ወደ ማህበሩ እንዲቀላቀሉ ለመናገርና ለመጋበዝ ቃል በመግባት እንዲሁም በዕለቱም በገቡት መሰረት በመከፈል መልካም ጊዜ አሳልፈናል፡፡
ይህ ከአባላት ጋር የመገኛኘትና የመመካከር ሂደት በሌሎችም አባላቶች ተጠናክሮ ይቀጥላል ፡፡

🙏7👍4🤝1
ከማህበሩ ቀደምት አባል ከሆኑት መምህር አለማየሁ አጋ ጋር የተደረገ የምስክርነት ቆይታ ፤
• መምህር አለማየሁ አጋ ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ የጆሽዋ ቁጠባና ብድር አባል ናቸዉ፤ሲቆጥቡ ሰንብተዉ ለትምህርት ቤታቸዉ ኡርጂ በሪ ኬጂ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፍያ እንዲሆን ብድር ጠየቁ፤ የሚያስፈልጋቸዉን ብድር ጆሽዋ ቁ/ብ/ኃ/የተ/መ/የህ/ሥራ ማህበር አቀረበላቸ እሳቸዉም፤ በታማኝነት በወቅቱ መለሱ፤ ቀጥለዉም በተደጋጋሚ እየተበደሩ መልሰዉ አሁን ላይ አንድ ሚሊዮን ብር ተበድረዉ በአግባቡ በመመለስ ላይ የሚገኙ ታታሪ ፣ ጠንካራ የሥራ ሰዉ ናቸዉ ፡፡
• መምህር አለማየሁ ትምህርት ቤታቸዉን ሲጀምሩ 22 ህጻናት በመያዝ ነበር በአሁኑ ወቅት ግን ትምህርት ቤቱን አስፋፍተዉ የተማሪዎቻቸዉ ቁጥር 477 አድርሰዋል ፤ ለወደፊቱም ከዚህ ለመጨመር ከጆሽዋ ጋር አብሮ ለመስራት ብዙ እቅድ አላቸዉ ፡፡
• በአሁኑ ወቅትም በኡርጂ በሪ ትምህርት ቤት 30 ለሚሆኑ መምህራንና የአስተዳደር ስራ የሚሰሩ ሠራተኞችን የሥራ ዕድል ፈጥረዉ በማስተዳደር ላይ ይገኛሉ፡፡
• በተጨማሪም ትምህርት ቤቱ በአከባቢዉ ለሚገኙ ማህበረሰብ እጅግ ከፍተኛ የሆነ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ በቦታዉ ተገኝተን መመልከት ችለናል፡፡
• መምህር አለማየሁ ስለ ጆሽዋ ቁጠባና ብድር ሲያብራሩ እጅግ ባለዉለታቸዉ እንደሆነ ከትንሽ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እያገዛቸዉ እንደሚገኝ ትናንት በእግራቸዉ እንደሚንቀሳቀሱ ዛሬ ግን መንቀሳቀሻ መኪና እንዳላቸዉ አብራርተዋል ፤ ለወገኖችም መልእክትም ሲያስተላልፉ ወደ ጆሽዋ ቁጠባና ብድር እንዲመጡና አባል በመሆን ቆጥበዉ በመበደር እራሳቸዉን ጨምሮ ለሌሎች መትረፍ እንዲችሉ አበረታታለዉ ብለዋል ፡፡
በተጨማሪ ከመምህር አለማየዉ አጋ አንደበት እንከታተል ፡፡
ምስክርነቱ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የጠዋት ገበያ ፕሮግራም ላይ ጥር 07 ቀን 2017 ዓ.ም የተላለፈ ነዉ ፡፡

👍5❤1🤝1