ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
27.4K subscribers
346 photos
9 videos
91 files
89 links
Join @Rovibook
😎
<|>
/\
👢👢

መካሪ ከተገኘ ህይወት ቀላል ነው!!
ለማንኛውም ማስታወቂያ ነክ ጉዳዮች @RASNAMRUD ያናግሩን
Download Telegram
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

" #አትድገሙ

ክፉ ነገር በማሰብ ይጀምራል፡፡ በማድረግ ይደመደማል፡፡ ማሰብ ለክፋት ፅንሰቱ ማድረግ ልደቱ ነው፡፡ ክፉ ነገር በማድረግ እየተገለጠ ይመጣል፡፡ ክፉ ነገርን የጦር ኀይል የፍርድ ጽናት የቅጣት ብዛት አያስቆመውም፡፡ክፉ ማሰብ ባለቤቱን ይበክላል ክፉ መናገር የጎረቤትን ሰላም ያናጋል አዕምሮን ያቆሽሻል ክፉ ማድረግ ማድረግ ማህበረሰብን ይጎዳል ያፈናቅላል፡፡ ክፉን መድገም ያደነድናል፡፡

#ያለመውደቅን_ያህል_ወድቆ_መነሳት_ክብር_ነው፡፡

የማይወድቅ የለም መልዐክ ካልሆነ የማፀፀት የለም ሰይጣን ካልሆነ፡፡

መድገም ማስተጋባት ነው፡፡ የሌሎችን ክፋት ማወደስ ለክፋት በነፃ ማስታወቂያ መስራት ነው፡፡ ሳይከፍሉን በቅዱስ አደባባይ ርኩስ ማስታወቂያ መስራት ነው፡፡ አንድ ጊዜ ክፉ ነገርን ከሚፈፅሙለት ይልቅ ደግመው በሚያወሩለት ሰይጣን ይደሰታል፡፡ ኃጢያት በተግባር ከሚፈፅሙ በምኞትና በትዝታ የሚጨልጡ ይበዙለታል፡፡

ሰው ነንና ክፉ ነገር እናስብ ይሆናል አለመናገር መልካም ነው፡፡ ሰው ነንና ተናግረን ይሆናል አለማድረግ ግን የተሻለ ነው ሰው ነንና አድርገን ይሆናል አለመድገም ግን መልካም ነው፡፡ መድገም መስራት ብቻ ሳይሆን ማስተዋወቅም ነው፡፡ ነገሩን ደግሞ ማውራት አይገባም፡፡

አዝረከርካለው ያልነውን ጉዳይ አንሰራፍተነው ሊሆን ይችላል፡፡ መድገም ብዙ ደቀመዝሙርትን ያፈራል፡፡ "ክፉ ነገርን አትናገሩ ደግማችሁም አታውሩ" ለምን ስንል፡- ያደረገ ካለ ይደፍራል ያሰበ ካለይፈፅማል የጀመረ ካለ ብቻዬን አይደለሁም ይላል የፈራ ካለ ልብ ያገኛል አደራረጉ የጠፋው ካለ ስልቱን ያገኛል፡፡

ክፋ ነገርን እግዚአብሔር ይገስፅህ በማለት መቅበር ያስፈልጋል፡፡
ዝርዝር ማውራት ለሴጣን ስፖንሰር መሆን ነው፡፡ ይህን ለመገንዘብ መንፈሳዊ ሰው ብቻ ሳይሆን ጨዋ አስተዳደግም በቂ ነው፡፡

#እጅግ_ግልፅነት_እብደት_ነው፡፡

ሰይጣን ዋንኛ ስራ ጆሮን ማስለመድ ነው፡፡ ጆሮን ማስለመድ የፖለቲካ ትልቅ ስልት ነው፡፡ የክፉዎች ትልቅ መንገድ ነው፡፡ ጆሮ ከለመደው አፈፃፀሙ ቀላል ነው፡፡ የምንናገረውን ሰዎች ይለማመዱታል ማስደንበርን ነው የምንፈራው ከዛም የተለየ ነገር አለ፡፡

ብዙ ክፉ ድርጊቶች ሲወሩ ይብሳሉ፡፡
ዝርዝር የሚወራው የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ ዛሬ ግን አጋንትን እያስለፈለፉ ትምህርት እንሰጣለን እየተባለ ነው፡፡ የሐሰት አባት ከተባለው የእውነት መረጃ እየተፈለገ ነው፡፡ ስብከት ሲያልቅብን ወደዚህ መግባታችን ያሳዝናል፡፡"

"መጥፎን ነገር እንደምንጠላ የሚያረጋግጥልን ስራችን ብቻ ነው" እና ከክፉ እንራቅ መልካምነትን እንዝራ እላለሁ

@jahABP ነኘ አሰተያየታችሁን አድርሱኘ መልካም ጊዜ ተመኘሁ፡፡
😍😁👍🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD