Haile roots
240 subscribers
24 photos
1 video
1 file
21 links
Download Telegram
Up date awtar !
Forwarded from Bineyam Yohannes
4Killo
New Album on sell ! on Amazon!
Subscribe!
Back to my roots 1 and 2 :- በሚል ዓላማ ወደ አኽሱም / ትግራይ እና ጎንደር / አማራ ክልሎች ያደረግነውን ጉዞ በተመለከተ በዋናነት ቤተሰቦቻችንን ለማየት እና ባሣለፍናቸው ጊዜያቶች በወገኖቻችን መካከል የተፈጠረውን መቋሰል በዕርቅ ለማሻር ፣ እንዲሁም ሁላችንም "ከራሳችንና ከአምላካችን እንታረቅ " በሚል ልባዊ እሳቤ አቅማችን በፈቀደው ሁሉ የበኩላችንን ጥረት እያደረግን እንገኛለን ።
በተለይም በእዚህ የሰላምና የፍቅር ጉዟችን ላይ ዓላማችንን ተረድታችሁ ምንም ነገር እንዳይጎድልብን የበኩላችሁን እገዛ ከልባችሁ ላደረጋችሁልን ቤተሰቦቻችን እና ወዳጆቻችን በሙሉ የከበረ ምሥጋናችንን እናቀርባለን ።
ይኽንን የሕዝብ ለሕዝብ የማቀራረብ ዓላማችንን በተመለከለም የተለመደው ትብብራችሁ ወደ ፊትም ቢሆን እንደማይለየን በማመን ምን ጊዜም ከሰላም ፣ ከፍቅር ፣ እንዲሁም ከእውነተኛና ሃቀኛ ፍትሕ ፈላጊዎች ጎን እንደምንቆም እናረጋግጣለን ።
ምንም እንኳን የዓላማችን መነሻ አሁን ካለው የአገራችን ሁኔታ አንፃር ያደረግነው ነገር ይሁን እንጂ የዓላማችን መዳረሻ የአፍሪካ አንድነት መሆኑንም ጨምረን እየገለጥን በድጋሚ በሄድንባቸው ቦታዎች ሁሉ ለተደረገልን መስተንግዶ እግዚአብሔር ይስጥልን እንላለን ።
ኃይሌ ሩትሥ / 2016.