Renaissance School®
1.97K subscribers
451 photos
11 videos
193 files
34 links
Renaissance School
Download Telegram
Forwarded from Ministry Of Education
#National_ID

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላይ ለመቀመጥ ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ቅድመ ሁኔታ ተደረገ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት " ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ለፈተና ለመቀመጥ ቅድመ ሁኔታ ነው " ብሏል።

" ማንኛውም የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ከፈተና ምዝገባ ቀድሞ ማውጣትና በእጁ መያዝ ይገባዋል " ሲል አሳውቋል።

" ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) የሌለው ተማሪ ለፈተና መመዝገብ ሆነ በማንኛውም ሁኔታ መፈተን አይችልም " ሲል አስገንዝቧል።

ተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ይዘው እንዲገኙ ፦
- የተማሪ ቤተሰብ
- መምህራን
- የትምህርት አመራሮች
- የሚዲያ አካላት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#National_ID

ትምህርት ሚኒስቴር 💠

🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!

✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Ministry Of Education
#Update

የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ይዘቶች ይፋ ሆኑ፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ተማሪዎች፣ የተማሪ ቤተሰቦች፣ መምህራንና የትምህርት አመራር ለፈተና ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ፈተና የሚሸፍናቸው የይዘት አካባቢዎች ይፋ አድርጓል።

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ከፍል ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር የሚከተሉትን ያካትታል፡፡ 

1. የትምህርት ዓይነቶችን በተመለከተ

ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ፦
- እንግሊዘኛ፣
- ሒሳብ፣
- እስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣
- ኬሚስትሪ፣
- ፊዝክስና ባዮሎጂ

ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ፦
- እንግሊዘኛ፣
- ሒሳብ፣
- እስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣
- ታሪክ፣
- ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ናቸው።

2. ፈተናው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ደረጃዎችን እና በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች ይሸፍናል፡፡

3. ከ10ኛ – 12ኛ ክፍል ሁሉም የትምህርት ዓይነት ፈተና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት እየተዘጋጀ ያለ ሲሆን የ9ኛ ክፍል ደግሞ የሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ፈተናዎች ከቀድሞውና ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘቶችን ብቻ አካቶ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

4. ፈተናው ማንኛውም ተፈታኝ ተማሪ ከተማረው ሥርዓተ ትምህርትና ከተማሪው መጽሐፍ ላይ ብቻ ተመስርቶ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

5. የፈተናው አስተዳደር በበይነ መረብና በወረቀት ጎን ለጎን የሚሰጥ ሲሆን አብዛኛው ተፈታኝ በበይነ መረብ እንዲፈተን እየተሠራ ያለ በመሆኑ ተፈታኞች እራሳቸውን በበይነ መረብ ለመፈተን ሊያዘጋጁ ይገባል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር 💠

🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!

✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1
ሬነሳንስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡ የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ቶፕ-25 ተማሪዎችን ይመለከታል፤
የ አዲስ አበባ ት/ቢሮ በሰጠው መመሪያ መሰረት በት/ቤታችን የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ቶፕ-25 ተማሪዎች ቅዳሜ ጥቅምት 22/2018 ዓ/ም ጀምሮ በተመደቡበት ክላስተር ቀራኒዮ መድሐኒያለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በመገኘት ትምሕርታቸውን እንዲከታተሉ ወላጆች አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንድታደርጉ እናሳውቃለን።
ት/ቤቱ
ሬነሳንስ ት/ቤት
አዲስ አበባ

የ2ኛ ሩብ ዓመት የት/ት አገልግሎት ክፍያ የሚከፈለው ከሕዳር ዐ1/2018 - ሕዳር 13/2018 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ክፍያውን በመፈጸም የወላጅነት ግዴታዎን እንዲወጡ በአክብሮት እንገልፃለን።
ት/ቤቱ
ሬነሳንስ ት/ቤት
አዲስ አበባ

11ኛ ክፍል ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች physics ፈተና ከማክሰኞ ወደ ሐሙስ ስለተሸጋገረ ተማሪዎች በዚህ መሰረት እንዲዘጋጁ እናስታውቃለን።
ሐሙስ፤ Physics and IT
ት/ቤቱ
ሬነሳንስ ት/ቤት
አዲስ አበባ

ለውድ የተማሪ ወላጆች
የ2ኛ ሩብ ዓመት የት/ት አገልግሎት ክፍያ የሚጠናቀቀው ቅዳሜ ህዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም በመሆኑ ወላጆች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያውን እንድትፈፅሙ በአክብሮት እንገልፃለን።
ማሳሰቢያ፤
ከሰኞ ህዳር 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ በቅጣት የሚከፈል ይሆናል።
ት/ቤቱ
2
9👍8🕊4🎄1